ጨለማው በብርሃን አለቀ
ይህ ውብ የቤተክርስቲያን ግቢ በሲኦል ተከብቧል ብል አላጋነንኩም። ዙሪያውን ቀፋፊ በሆኑ የገባያ ቦታዎች፣ በመስጊዶች እና ቆሻሻ አውድማ የተከበበ ነው። ከመስጊዱ አዛን ጩኸት ጋር ውሾችም አብረው ሲጮሁና ሲያላዝኑ ይሰማሉ። የአካባቢው አቧራ ዓይን ያሳውራል፣ የቆሻሻው ሽታ አያድርስ ነው። በዚያ ላይ የአካባቢው ሰው ቀዥቃዣነትና ስነምግባር አልባነት፣ ለጣዖት የሚደፉት ሙስሊሞች እና ጥቁር ድንኳን ለብሰው ለገባያ የሚንጎራደዱት ሴቶቻቸው ሁኔታ፣ በእውነት ከአካባቢው ቶሎ ውጡ ውጡ የሚያሰኝ ነው። ሁሉም ነገር ጭልምልም ያለ ነው! ሌላ የሚያሳዝነው ነገር በአካባቢው ያሉት ክርስቲያኖችም ሆኑ ሙስሊሞች ይህን ነገር መላመዳቸውና ልዩነቱን ለመገንዘብ አለመቻላቸው ነው። እንግዲህ እነሱ ‘ኑሮ ካሉት፣ መቃብር ይሞቃል’ ይላሉ፡፡ እኔ ግን ‘ኑረው ካዩት፣ መቃብር ይሞቃል’ እላለሁ፡፡
አሁንም እያጋነንኩ አይደልም፤ ልክ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ ስገባ ያ ሁሉ መንፈስን የሚያውክ ነገር እልም ብሎ ጠፋ፤ ብርሃኑ የአካባቢውን ድቅድቅ ጨለማ በመግፋት አካባቢውን አፍክቶት ይታያል፡ የሚገርም ነው! በአንድ ሰዓት ውስጥ የሲዖልን እና የመንግሥተ ሰማያትን የተለያዩ ገጽታዎች በድጋሚ ለመገንዘብ በቅቼ ነበር።