Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2019
  M T W T F S S
   123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  25262728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for February 10th, 2019

በሐረርጌ ከሰማይ እንደዘነበው ዓይነት እሳት በቬኔዙዌላም ታየ | በ ሲ.አይ.ኤ መፈንቅለ-መንግሥት ማግስት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 10, 2019

የቆቅ ለማዳ የለውም፤ እባብንም ቆዳው ለሰለሰ ብለህ ቀበቶ አርገህ አትታጠቀውም

የሉሲፈራውያኑ የስለላ ድርጅት፡ ሲ.አይ.ኤ ብጥብጥ በፈጠረባት ቬኔዙዌላ ከሰማይ እሳት ዘነበ (‘ሜቲዎሪትነው አሉ!) ግን ዘመናዊ የጠፈር ቴክኖሎጂ እየተሞከረ ይሆን? የእግዚአብሔር እሳት ከመውረዱ በፊት ሉሲፈራውያኑ ቀድመው ማውረዳቸው ይሆን?

ፍጻሜ ዘመን ላይ እንገኛለን፤ የሉሲፈር ሠራዊት ተደናግጧል፤ ጌዜው በጣም አጥሮበታል፤ እርኩስ ድርጊቱን በየአገሩ ለመፈጸም በመጣደፍ ላይ ይገኛል። አሁን ሰብዓዊ ወታደሮች ወይም ታንኮች እምብዛም አያስፈልጉትም፤ በጠፈር መሣሪዎች የታጀቡ ሙከራዎችን ማካሄድ የሚችልበት ዘመን ነውና።

አሁን ክርስቲያኖችን እና አፍሪቃውያንን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት እንችላለን ብለው ያስባሉ/ይመኛሉ፤ አላማቸውም ይህ ነው፤ የዘገዩት እግዚአብሔር ስለከለከላቸው ነው። እርኩስ ሥራዎቻቸውን እንድንቀበል የእኛን ፈቃደኝነት ይሻሉ፤ ለዚህም እንደ እነ ዶ/ር አህመድ ያሉትን መሪዎች ስልጣን ላይ ያስቀምጣሉ፤ ከዚያም እሳቱን ባወረዱ ቁጥር፡ ለማይፈልጓቸው ፖለቲከኞች፡ “ዋ! ቴክኖሎጂው አለን፤ ከመላው ሕዝባችሁ ጋር ሙልጭ አድርገን እናጠፋችኋለን።” በማለት ያስፈራሯቸዋል። ለእኛ ለበጎቹ ደግሞ፡ “ኦ!! ከሰማይ የወረደ ሜቲዎሪት ነው” ይሉናል፤ ለእግዚአብሔር ደግሞ፡ “ያው በራሳቸው ፈቃድ ነው ይህን ያደረግነው” ይሉታል፤ “አመንዝራ የአፍሪቃ ትውልድ በሃጢአታቸው ነው በኤይድስ የተለከፉት…” እንደሚሉት። ከእነርሱ የባሰ ጣዖት አምላኪና አመንዛሪ እንደሌለ፤ ዲያብሎስ ስራው እንዲህ ነው።

በጂጂጋ ክርስቲያኖች ላይ የተካሄደው ጂሃዳዊ ጭፍጨፋ በሉሲፈራውያኑ በደንብ የተቀነባበረ ነበር። በማግስቱ የወረደው እሳትስ የእግዚአብሔር ቁጣ ወይስ ሉሲፈራውያኑ በኢትዮጵያ ላካሄዱት የመንግስትግልበጣ ሊያስጠንቀቁት ለፈለጉት ወገን የተላከ እሳት?

አዎ! በአሁኑ ዘመን ይህችን ምድር በመምራት ላይ ያለው ዲያብሎስ ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ አገር በመሪነት ቦታ ላይ መቀመጥ ያለባቸው የእርሱን ተልዕኮ ለማሟላት ፈቃደኞች የሆኑት ሰዎች ብቻ ናቸው። በኢትዮጵያ ያየነው ዓይነት መፈንቅለመንግስት ለቬኔዙዌላም ታስቧል፤ ልዩነቱ በኢትዮጵያ አገልግሎታቸውን የጨረሱት ፖለቲከኞች ወደውም ይሁን ተገድደው ከስልጣን ሲሰናበቱ፤ የቬኔዙዌላው ሌላ ወስላታ ማዱሮ ግን ፈቃደኛ አይደለም። ስለዚህ፡ እራሳቸው ያስቀመጡትን ይህን ሶሻሊስት አሁን ጠምደውታል፤ በሌላ አገር ጉዳይ የማዘዝ መብት እንዳላቸው፡ “ከስልጣን ውረድ፣ ጊዜህ አብቅቷል ይሉታል።!” በዚህም እንደ ሩሲያ፣ ቻይና፣ ኢራን እና ቱርክ የመሳሰሉ የድራማው ተካፋዮች በቁጥጥር ሥር እንዳሉ ተቃዋሚዎች ተቃራኒውን ሚና ለመጫዋት ይገደዳሉ። የወስላታው ፈላስፋ ጆርጅ ሄገል ዲያሌክቲክስ (Thesis + Antithesis = Synthesis)

በአገራችንም እየሠሩ ያሉት ሥራ ይህን ይመስላል፤ የራሳቸው የሆነውን ዶ/ር አብይን ስላጣን ላይ አወጡት፤ ከሩቅ የሚቆጣጠሩትን ተቃዋሚ ዶ/ር ደብረጽዮንን በተቃራኒው በኩል አስቀመጡት፤ ሁለቱ ሲፋጩ ለተፈለገው የሕዝብ ቁጥር ቅነሳ ጦርነት ይካሄዳል ሰው ያልቃል ማለት ነው። አቶ መለሰ ዜናዊ እና ኢሳያስ አፈወርቂ በባዳሜው ጦርነት ለአንድ ሚሊየን ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ሕይወት መቀጠፍ መሣሪያ ለመሆን እንደበቁት።

ልብ ብለን ካየን፤ በየአገሩ 666ቱ አውሬ የሚመረጡት ሁሉ ከየት እንደመጡ የማይታወቁ፣ ልምድ የሌላቸው ወጣት ፖለቲከኞች ናቸው ልክ እንደ ፈረንሳዩ ፕሬዚደንት ማክሮን (በጊዜው 39)እና የቬኔዙዌላው ተቃዋሚ መሪ ሁዋን ጋይዶ(35ቱ ነው)፤ ዶ/ር አህመድም ከአመት በፊት በፍጹም የማይታወቅ ሰው ነበር። እነ መንግስቱ ኃይለማርያምም በጣም ተመሳሳይ የሆነ አመጣጥ ነበር የነበራቸው። በአንድ ነገር ግን እርግጠኞች መሆን አለብን፡ እርሱም፤ እነዚህ ቅጥረኞች ሁሉም በአንድ ወቅት በአሜሪካ የስለላ ድርጅት(CIA) ትምህርት ተቀብለዋል፤ ተመልመለዋል።

_________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: