Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2019
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February 20th, 2019

ግብፃዊው የ YouTube ኮከብ “ኢስላም ዘረኛና ጨካኝ ነው” በማለት ከእስልምና ወጣ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 20, 2019

ግብዝ ሙስሊሞች እራሱን ወደ ማጥፋት ድረስ እንደገፋፉትም በተጨማሪ ተናግሯል።

ግብጻዊው ተወዳጅ የ YouTube ዜና አቅራቢ፡ „ሼዲ ስሩር“ ዘረኝነትን እና ጭካኔንእንደ ርዕሰጉዳይ” በመጥቀስ ከእስልምና መውጣቱን አስታውቋል።

በአሁኑ ጊዜ ከ 4 ሚሊዮን በላይ የዩቲዩብ ደንበኞች ያሉት ይህ የ 24 አመት ሰው ከ 102,000 በላይ አስተያየቶችን በተቀበለበት የፌስቡክ ደብዳቤ ከእስልምና መውቱን አስታውቆ ነበር።

በአምላክ እናምናለን የሚሉ ሰዎች ልብ ውስጥ ዘረኝነትን፣ ጥላቻንና ጭካኔን በማያቴ እስልምናን ትቸዋለሁ፤ በእርግጥ እነሱ ጨካኝና ግብዞች ናቸውበማለት በአረብኛ ቋንቋ ፊስቡክ ላይ ዘግቧል።

ሼዲ ስሩር በተጨማሪም ባለፈው አመት ብዙ ሙስሊሞች በኢንተርኔት ይሰድቡትና ያስጨንቁት እንደነበር፤ እንዲያውም ጉዳዩ በአንድ ወቅት እንደ አንድ ሰብአዊ ፍጡር ከፍተኛ የስነልቦና ቀውስ ውስጥ እንደከተተውና እራሱንም ወደ ማጥፋት ሊገፋፋው እንደሞከረ ገልጧል።

የግብጽን ጉዳይ በጥሞና እንከታተል፤ ብዙው ነገር ከኢትዮጵያ ጋር የተያያዘ ነው – እግዚአብሔር አምላክ ድንቅ ሥራውን እየሠራ ነው።

የእስልምናን አስቀያሚነት ብዙዎች እየመሰከሩ ነው። በሙስሊሙ ዓለም፡ ብዙ ሙስሊሞች “በቃን” እያሉ ከእስልምና የባርነት ቀንበር በመላቀቅ ላይ ናቸው። እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሆን!

የሚገርመው ብዙ ጥቁሮችና የሌላ አገር ተወላጆች እስልምና ውስጥ ተታለው ሲገቡ፣ እስልምና ከዘርና ከዘረኝነት ንፁህ የሆነ ሃይማኖት አድረገው ሲቆጥሩትና ሲናገሩለት እንመለከታለን፡፡

ይሁን እንጂ በቁርአንና በእስልምና ታሪክ ውስጥ በጣም የሚረብሹ ነገሮችን ከእነ በቂ ማስረጃቸው መመልከት እንችላለን፡፡

ለምሳሌ የሙስሊሞችን ቅዱስ መጽሐፍ ቁርዓን የሚለውን የሚከተለውን እንመልከት፡

ፊቶች የሚያበሩበትን (ነጭ የሚሆኑበትን) ፊቶችም የሚጠቁሩበትን ቀን (አስታውስ) እነዚያ ፊቶቻቸው የጠቆሩትማ ከእምነታችሁ በኋላ ካዳችሁን? ትክዱት በነበራችሁት ነገር ቅጣታችሁን ቅመሱ፡፡ (ይባላሉ)፡፡ እነዚያማ ፊቶቻቸው ያበሩትማ በአላህ ችሮታ (ገነት) ውስጥ ናቸው እነርሱ በውስጧ ዘውታሪዎች ናቸው፡3.106-107፡፡

እዚህ ጋ ነጭነት (የሚያበራ ፊት) ተብሎ የተባለው ከመልካም ስራ ጋር ሲያያዝ ጥቁርነት ደግሞ ከክፉ ስራ ጋር ተያይዟል፡፡

እስልምና እስካሁን ድረስ ከታሪክ ምንም ትምህርትን አልወሰደም፤ በእስላም ማዕከላዊ አገሮች ውስጥ፤ እንደ ሳውዲ አረቢያ ባሉት፤ አሁንም እንኳን የሌላ አገር ሰዎች ባሪያዎች ሆነው ይገኛሉና፡፡ ሃያ ሺ እህቶቻችንም በመጭው መጋቢት ወር በባርነት ሊሸጡ ነው። ወገኖች፤ ይህን እናስታውስ! ታሪክ እንደሚወቅሰና ተተኪው ትውልድ እንደሚኮንነን አንጠራጠር!

መጽሐፍ ቅዱስ በክርስቶስ ያመነ ክርስቲያን ሁሉ በዘር፣ በቀለምና በፆታ ሳይለያይ እኩል መሆኑን አውጇል፡

አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና፡፡[ገላ. ፪ ፡ ፳፰]

በተቃራኒው እስልምና ግን ሁሉም ነገሩ በጥላቻ ላይ የተመሠረተ ነው። ሰይጣንን በጥቁር ሰው መመሰል በእስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ የተገለፀ ሲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ግን እንደዚያ የሚል ነገር የለም፡፡

መሀመድ ግን ሰይጣንንና ጥቁርን ሰው እንዲህ ያመሳስላቸዋል፡

ነቢዩ እንዲህ አሉ፡– “ሰይጣንን ማየት የሚፈልግ ሰው ነብጣል ኢብን አልሀሪሥን ይመልከተው!“ ጥቁር ሰው ሲሆን የተንጨባረረ ረጅም ፀጉርና ጥቁር መንጋጋዎች አሉት፡፡

የጥንት ሙስሊሞች መሀመድ ጥቁር ነበር ብለው ከተናገሩ ይገድሉ ነበር፡

የሰህኑን ወዳጅ የነበረው አህመድ ኢብን አቢ ሱለይመን እንዲህ አለ፡– “ማንኛውም ነቢዩ ጥቁር እንደሆኑ የሚናገር ሰው ይገደላል፡፡ ነቢዩ ጥቁር አልነበሩም፡፡

መሀመድ ጥቁር ባርያዎች እንደነበሩት በብዙ እስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ በተደጋጋሚ ተዘግቧል፡፡ ጥቁር ባርያዎችንም በስጦታ ይቀበል እንደነበር ተነግሯል፡፡

በአንድ ወቅት አንድ ባርያ በሁለት ጥቁር ባርያዎች እንደለወጠ እስላማዊ ትውፊቶች ውስጥ ተጽፏል፡

ጃቢር ኢብን አብዱላህ እንዳስተላለፈው፡አንድ ባርያ ወደ አላህ መልእክተኛ (...) በመምጣት ቃል ኪዳን ያዘ፡፡ ነቢዩም ባርያ መሆኑን አላወቁም ነበር፡፡ አሳዳሪው በመምጣት ባርያው እንዲመለስለት በጠየቀ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ (...) ‹‹ሽጥልኝ›› አሉት? በሁለት ጥቁር ባርያዎችም ገዙት፡፡

ጥቁር አፍሪካውያን በአረብ ሙስሊሞች ዘንድ እንዴት እንደሚታዩ ይታወቃል፡፡ ቁርአን የሰው ልጆችን እኩልነት በሚክዱ መልእክቶች የተሞላ ነው፡፡

ታዲያ ይሄ፡ ኡ!! አያሰኝም!?

ምንጭ

_________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , | Leave a Comment »