ነገር ግን፡ ሁሉም አንድ በአንድ ተፍረከሰከሱ!
ቁጥር ፪ ቪዲዮው ላይ የገዳሙን ውብ ደን፣ የፀበል ኩሬ፣ የዘጉ አባቶች ይኖሩበት የነበርውን ቦታ ፥ እንዲሁም በተዋሕዶ ልጆች ላይ የዘመቱት የፋሽስት ጣልያን እና ደርግ መንግሥታት ገዳይ ሠራዊቶቻቸውን አስፍረውባቸው የነበሩባቸውን ምሽጎች አብረን እናያለን።
ይገርማል! እነዚህ እርኩሶች እዚህ ቅዱስ የሆነ ቦታችን ላይ በድፍረትና በንቀት ምሽግ ሰርተውበ ነበር።
አዎ! ቅዱሱ አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያም የዓለም ብርሐን ናቸው፤ ይኽው ለዘላለም ያበራል ስራቸው።
አባታችን አቡነ ሐብተ ማርያም ከዕለታት በአንድ ቀን በሌሊት መብራት ለአባ ሳሙኤል እያበራ ሳለ መብራቱ ከእጁ ወድቆ ጠፋ። ስለ መምህሩ ስለ አባ ሳሙኤል ቁጣ፣ ፍራቻ፣ ታላቅ ድንጋጤ ደንግጦ ፈጥኖ ባነሳው ጊዜ በእግዚአብሔር ተዓምር ራሱ በራ፡ አባ ሳሙኤልም ይህን ተዓምራት አይተው የዚህ ቅዱስ ልጅ የዓለም ሁሉ የጥበብ መብራት ይሆናል ሲሉ ትንቢት ተናገሩ።
እንኳን አደረሰን!
የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡