የዓለማችን ቁጥር ፩ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቿ፤ ናኦሚ ኦሳካ የዘንድሮውን የአውስትራሊያ ክፍት ውድድር (ከአራቱ አንጋፋ የቴኒስ ውድድሮች፥ ማለትም፤ ከፈረንሳይ፣ ከእንግሊዝ፣ እና አሜሪካ ክፍት ውድድሮች ጋር አብሮ ይደመራል)ዋንጫ በመውሰድ ከነገሠች በኋላ፡ ጃፓናዊው የፓስታ አምራች ድርጅት በሠራው ማስታወቂያ ላይ ፈረንጅ ሆና እንድትታይ አድርጓታል። ይህ ቅሌታማ ማስታወቂያ ብዙዎችን ስላስቆጣ አሁን ተነስቷል።
ናኦሚ ኦሳካ ከጃፓናዊት እናቷ እና ከሃይቲያዊ አባቷ በጃፓን ተወልዳ በኒው ዮርክ አድጋለች። ባጭር ጊዜ ውስጥ በጃፓኖች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈችው ናኦሚ የጃፓን እና የአሜሪካ ዜግነቶች አላት።
የቆዳዋ መጥቆር ግን አናዳንድ በዘረኝነት ጋኔን የተለከፉትን ይከነክናቸዋል። ዓይነ–አፋርነቷ እና ትህትናዋ እንደ ኢትዮጵያውያን ነው፤ ደስ ይላል። ይህች የግብዘኞች ዓለም ግን ቆዳቸው ጥቁር በሆኑ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አላት፤ ንጉሥ/ንግሥት ሲኮን መከራ፥ ለማኝ ሲኮን መከራ…