Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2019
  M T W T F S S
   123
  45678910
  11121314151617
  18192021222324
  25262728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Archive for February 16th, 2019

ዶ/ር አህመድ ጥምቀታችንን ሊነጥቀን ቃጣ፤ ካናዳዊው ጴንጤ ወንድሙ ደግሞ ቅዱሳኖቻችንን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 16, 2019

666ቱ ዘመቻ በሰባቱ ሚስጥራተ ቤተክርስቲያን ላይ እንደሆነ እያየን ነው፡፡ በ፦

 1. + ጥምቀት

 2. + ሜሮን

 3. + ቁርባን

 4. + ክህነት

 5. + ንስሀ

 6. + ቀንዲል

 7. + ተክሊል

ላይ አንድ በአንድ ይዘምታሉ። ቸኩላችሁ የወደዳችሁት ዶ/ሩ መሪያችሁ ዘመቻውን በጥምቀት ላይ ጀምሯል፤ ዓብያተክርስቲያናቱ የባሕረ ጥምቀት ቦታዎቻቸውን ቀስበቀስ እየተነጠቁ ነው፤ የጸበላት ቦታዎች አካባቢ ፋብሪካዎችና ጋራጆች እንዲሠሩ እየተደረገ ነው ወዘተ. ወዴት! ወዴት!

ያው እንግዲህ፤ የግራኝ አህመድ አቢሲኒያ፤ የእንጭጮቹ ጴንጤዎች መናኸሪያ ሆናለች። ከባድ ኃጢዓት እየሠሩ እንደሆነ አያውቁትም፤ እስኪ ይታየን፤ ክርስትና ወይም አምልኮተ እግዚአብሔር ሙልጭ ብሎ ከጠፋባት፡ በመንፈስ ድኻዋ፡ ካናዳ የመጣው ጓደኛችን በዓለም አንደኛ ፈሪህ እግዚአብሔር የሆነውን ሕዝብ “ለማስተማር” ብሎም እግዚአብሔር አምላካቸውን እና ቅዱሳኑን ሊነጥቃቸው ሲደፈር፤ ይህ እኮ ትልቅ ኃጢዓት ነው፡ ዴቪድ። ገና የመንፈሳዊ ጨቅላ ነህ፡ ጓደኛችን፤ በዚህ ርዕስ ላይ ኦሮቶዶክሳውያን ከሺህ ዓመታት በፊት (Iconoclasm) በጥልቁ አስበውበትና ልምዱን ወስደውበት እስከ ዘመናችን ድረስ ለመዝለቅ በቅተዋል፤ በምድር ላይ የቀሩት ብቸኞቹ ክርስቲያኖች ኦርቶዶክሳውያን ናቸው። ይህን ሁሉም እየመሰከረ ነው፤ እንደ ታዋቂው Hank Hanegraaff (“The Bible Man”) ወደ ኦርቶዶክስ የገቡ ጴንጤዎች ሳይቀሩ።

ዴቪድ ጓደኛችን፡ ግማሽ ሃቅ ይዘህ መጥተሃል፤ ትክክል ነህ፡ ጌታችንን እና እናቱን ፈረንጅ አድርገን ማሳየት የለብንም፤ የቀድሞዋ ኢትዮጵያም ቅዱሳኑን ነጮች አታደርጋቸውም ነበር፤ ነገር ግን፤ ኢትዮጵያውያን አድርገን ብንስላቸው ሃቁ ያ ነው፤ ኢትዮጵያውያን ነበሩና፤ ይህን ከኢትዮጵያውያን አባቶች አብልጦ ሊያውቅ የሚችል ሌላ ሰው የለም።

የቅዱሳት ስእላት እንጅ ምስሎች አይደሉም፤ እያንዳንዱ ስእል የቅዱሳኑን ሕይወት፣ ሥራና ማንነት ያንጸባርቃል፤ የፈረንጅ ገጽታ እንዲኖራቸው ተደርገው ቢሳሉም እንኳን። ለምሳሌ እኔ፡ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ቅድስት ማርያም ወይም መላዕክቱና ሰማዕታቱ ስእል ፊት ለጸሎት ስንበረከክ፤ አምላካችን ለኃጢዓታችን ሞቶ መነሳቱን፣ እናቱ መዳኛችንንን መውለዷን፣ መላዕክቱና ሰማዕታቱ ለእኛ ለክርስቲያኖች መታገላቸውን ነው የማስበው።

ከሰማይ በታች ምንም አዲስ ነገር የለም፦ ሌላ ብዙ ማለት አያስፈልግም፤ የሺህ ዓመት ልምዱ አለ፤ በተለይ አሁን እንደምናየው፡ ለቅዱሳን ተገቢውን ክብር የማይሰጡ እንዲሁም ክርስትናን የማይከተሉት ማሕበረሰባት በአጭር ጊዜ ውስጥ (በአራት መቶ ዓመት) ዓማንያን ለመሆን በመብቃታቸው ስብርብር ብለው እየወደቁ ነው፦ ፕሮቴስታንት አውሮፓ እና አሜሪካ። አሁን እነዚህ ማሕበረሰቦች ወደ ጣዖት አምልኮ እየተመለሱ ነው፤ ዴቪድ፡ እስኪ ለምን እንደሆነ እራስህን በትህትና ጠይቅ።

በአለማችን የእምነት ፒራሚድ ዝቅተኛውን ቦታ የያዙት እንደ እስልምና፣ ቩዱ፣ ሂንዱ፣ ዋቄዮ የመሳሰሉት የጣዖት አምልኮዎች ሲሆኑ፤ ትንሽ ከፍ ብለው የተቀመጡት፤ ፕሮቴስታንቶችና ቡድሂስቶች፤ ከእነርሱ ከፍ የሚሉት ደግሞ ካቶሊኮች ናቸው፤ የፒራሚዱ ጫፍ ላይ የሚቀመጡትና ከሁሉም ከፍ ያሉት ኦርቶዶክሶች ናቸው። ይህን እውነተኛ የሆነ ሰው ሁሉ በደንብ የሚያየው ነው።

ይህን ሃቅ ከኢትዮጵያ ሳትወጣ በድንብ አድርገህ መርምረው፤ ጴንጤው ጓደኛችን፤ ንስሃ መግባት፣ መጠመቅና መንፈስ ቅዱስን መቀበል የሚገባህ አንተና ባለቤትህ ናችሁ፤ ትሁት ሆናችሁ በመጓዝ አጋጣሚውን አሁኑኑ ቶሎ ተጠቀሙበት

_________

Posted in Ethiopia, Faith | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: