ቴዲ ‘ርዕዮት’፤ “የትግራይ ሕዝብ የሕወሓት ንብረት ነው ያለው ማን ነው? ሕወሓት ምን እየሠራ ነው?”
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 17, 2022
💭 ቴዲና ጌቾ ያነሳችኋቸው ነጥቦች በጣም አንገብጋቢዎች ናቸው።
😈 ሁሉም ተናብበው እየሠሩ ነው። ሁሉም በጆርጅ ሄገለ ዲያብሎሳዊ ሂደት ፤ “Thesis-Antithesis-Synthesis (ተሲስ ፣ ፀረ-ፀረስታ እና ውህደት/መደመር) የሚመሩ ናቸው።
ዛሬ ሕወሓቶች ምን እንደሚያደርጉ ወይንም ስለምን እንደሚደራደሩ ከመጠየቅ አልፈን ከሕወሓት ጀርባ ያሉት ግለሰቦች/ገዥዎች ማንና እነማን እንደሆኑ መመርመር ያለብን ይመስለኛል። እኛ ‘ስህተት‘ የምንለው በእነርሱ ዘንድ ተፈላጊና ተቀባይነት ያለው ነገር ሆኖ ነው የሚታየው። ደግመው ደጋግመው የሚያደርጉት ነገር እኮ የትግራይን ጽዮናዊ ሕዝብ በእጅጉ የሚጎዳ እንደሆነ በተደጋጋሚ አይተነዋል። “ድንጋዩ አንዴ ካደናቀፈህ በድንጋዩ ታሳብባለሁ ሁለቴና ሦስቴ ካደናቀፈህ ግን ድንጋዩ አንተነህ” እንዲሉ፤ ዛሬ ሕዝባችንን እየጨፈጨፈ ያለውን የፋሺስት ኦሮሞ አገዛዝ ሥልጣን ላይ አውጥተው፣ ታንኩንና ባንኩን ሁሉ አስረክበው ለአሥር ሚሊየን ጽዮናውያን ምንም ዓይነት ነገር እንዳይደርሳቸው፣ ከትግራይም፤“ምርኮኞች” በኬክና ማንጎ ጭማቂ ልደታቸውን ሲያከብሩ የሚያሳዩ ቪዲዮዎችን ከመልቀቅ፣ እህል የጫኑ መኪናዎችን ቁጥር ከመዘገብ፣ ብሎም አሰልቺ የሆኑ መግለጫዎችን ከማውጣት በቀር ስለሕዝቡ ሁኔታ ምንም ዓይነት መረጃ እንዳይወጣ አፍነው የያዙትን የሕወሓት አመራሮች አጥብቀን እንመረምራቸው ዘንድ ግድ ነው።
ቴዲ፤ አንተም ስትለው የነበረው ነው፤ ኢ–አማንያኑ ሕወሓቶች እየገዙት ያሉትን ክርስቲያን ሕዝብ አይወክሉትም፤ ስለዚህ ትግራይን ከጽዮናውያን አጽድተው እንደ ሰሜን ኮርያና ቀድሞዋ አልባንያ በራሳቸው ኮሙኒስታዊ ርዕዮተ ዓለም በታነጸ ማሕበረሰብ የመተካት ምኞት ዛሬም እንዳላቸው ብዙ ማስረጃዎች አሉ።
የሉሲሲሲፈርን/ቻይናን ባንዲራን በሰፊው ለማስተዋወቅ መብቃታቸውና በኅዳር ጽዮን አስኩም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ላይ ለመስቀል መድፈራቸው አንዱ ማስረጃ ነው። ከዚህ ሁሉ ‘ብዙ አሰቃቂ ዕልቂት ያመጣ‘ ስህተታቸው በኋላ እንኳን እነ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ሥልጣኑን አስረክበው ለንሰሐ ወደ ገዳም እንደ መግባት፤ “ሕወሓት የትም አይሄድም፤ ሁላችሁም በሕወሓት የመገዛት ግዴታ አለባችሁ፤ የሕወሓት ታሪክ ከአክሱማውያኑ ታሪክ ጋር እኩል ነው” ለማለት የደፈሩ አምባገነኖች እኮ ናቸው። ጤንነታቸውም በጣም የታወከ መሆኑን እየሰማን ነው።
ቴዲ፡ አንተ ባለፈው ጊዜ የጋበዝካቸው አምባሳደርም፤ “የሚደራደረው በሕዝብ የተመረጠው ሕወሓት ብቻ ነው!” ሲሉህ ነበር። ይህን ስሰማ “ወቸውጉድ!” በማለት ቃለ መጠየቁን ወዲያው አቋረጥኩት። ዛሬም እንዲህ ማለታቸው፣ በተቀሩት የኢትዮጵያ ግዛቶች በአስከፊ ሁኔታ ለሚገኙትና በምዕራብ ትግራይ ለሚጨፈጨፉት ጽዮናውያን አለመቆማቸው፣ (ሂውማን ራይትስ ዋች ዛሬ ተጨማሪ መረጃ አውጥቷል) Ethiopia’s Invisible Ethnic Cleansing The World Can’t Afford to Ignore Tigray በሱዳን ስለሚገኙት የትግራይ ስደተኛ ወገኖቻችን ስለሚገኙበት ሁኔታ ዘገባዎችን ለመስራት እንኳን አለመፈለጋቸው፤ ብሎም ወደ ኤርትራ ገብተው አረመኔውን ኢሳያስን፣ ወደ አዲስ አበባ አምርተው ቆሻሻውን ግራኝ አብዮት አህመድ አሊን፣ ወደ ባሕር ዳር አምርተው እነ ቧያለውን ለመያዝ አለመሞከራቸው/አለመሻታቸው እንዲሁም መቀሌ ከገቡ ከዓመት በኋላ ዛሬም ትግራይን አፍነው ሕዝቡ ዘሩ ለማይታወቅ ስንዴና ብስኩት ባሪያ እንዲሆን ማድረጋቸው የሚጠቁሙን፤ ዶ/ር ደብረ ጽዮን + ኢሳያስ አፈወርቂ + ግራኝ አብዮት አህመድ ገና ከጅምሩ በጋራ ተናብበው እንደሚሠሩ ነው። ይህ ጉዳይ በቅርቡ ግልጽ ይሆናል። በእኔ በኩል አብረው እንደሚሠሩና ዳግማዊ ኢሳያስ አፈወርቂን በትግራይ ተክለው ወጣቱን እንደ ኤርትራ ጽዮናውያን ወታደር አድርጎና ለስደት ዳርጎ ለመጨረስ እንዳቀዱ እርግጠኛ ነኝ። አካሄዳቸው አንድ ዓይነት ነው። የሕዝብ ቁጥር ቀናሿ ይህች እርጉም ዓለምም ኢሳያስንና ግራኝን እንደደገፈቻቸው እነ ደብረ ጽዮንንም በዚህ ዓይነቱ ራስን-ጠል ተልዕኮ ላይ ድጋፏን ትሰጣቸዋለች።
ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናዊን የገደሏቸው ስለነቁና ከስህተታቸው ተምረው ይህን ምንሊካዊ የብሔር ብሔረሰብ ተረትተረት ርዕዮተ ዓለም ለማስወገድ እንዲሁም ‘ኦሮሞ፣ አማራና ሶማሌ’ የተባሉትን ሕገ-ወጥ ክልሎች ለማፈራረስ ባውጠነጠኑበትና የአፄ ዮሐንስን ፈለግ ለመከተል ባሰላሰሉበት ወቅት ነበር። አዎ! ይህ ያስደነግጣል፤ ግን ኢ-አማንያኑ (ለአንድ የትግራይ ሰው ይህ ትልቅ ክህደት ነው!) እነ ዶ/ር ደብረ ጽዮን የትግራይን ጽዮናዊ ሕዝብ በጣም ይንቁታል! ይጠሉታል! ጥንታውያኑን ገዳማትና ዓብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አውድመው ፋብሪካዎችን ቢገነቡ ይመርጣሉ። የጦርነቱ አንዱ ዲያብሎሳዊ ተልዕኮ ይህ ነው! ገና ከጅምሩ እኮ ሰፋፊ ክልሎችን ለኦሮሞ + አማራ + ሶማሌ ሰጥተው የትግራይን ያሳነሷት እኮ “ብዙ ሕዝብ ያላቸው እነርሱ ስለሆኑ ግማሽ ኢትዮጵያን ስንሰጣቸውና ምድሩንም ስናለማላቸው ጸጥ ለጥ ብለው ይገዙልናል ከሥልጣናችን አያስወግዱንም!” በሚል አርቆ-አሳቢነት የጎደለው ድንቁርና ነበር። እኔን ሁሌ የሚቆጠቁጠኝና የሚያናድደኝ አንድ ወቅት፤ ከአስራ አምስት ዓመት ገደማ ወደ አዲስ አበባ አምርቼና ሕወሓት ውስጥ ያሉ ዘመዶቼን ሰብስቤ፤ “ይህ የብሔር ብሔርሰብ ሥርዓት መፍረስ አለበት፤ በተለይ የኦሮሞና ሶማሌ የተባሉትን ክልሎች አፈራርሷቸው፤ አለዚያ ዋና ተጠቂ የሚሆነው የትግራይ ሰው ነው…” ስላቸው “ይህ ሥርዓት ለሁሉም ብሔር ብሔረሰቦች ተስማምቷቸዋል፤ ሁሉም በቋንቋው ቢናገርና ባሕሉንም ቢያዳብር ምናለበት?!” ብለው ሊያስምኑኝ የሞከሩበት ወቅት ነው። እስኪ ይታየን ብዙ የተለያዩ ጎሳዎችና ነገዶች የሚኖሩበትን ግዛት “ሰላማዊ ናቸው አይፎካከሩንም!” በሚል ተንኮል ይመስላል እንደው በጅምላ’የደቡብ ክልል’ ለማለት የደፈሩት፣ የብሔር ብሔረሰቦች ጠላት ለሆነውና ቀደም ሲል እስከ ፳፯/27 የሚጠጉ ጥንታውያን የኢትዮጵያን ብርቅዬ ነገዶችን ከምድረ ገጽ ላጠፋው ‘አሃዳዊ’ ኦሮሞ ግን፤ “ጌዲዮን፣ ሲዳማን፣ ጉራጌን፣ አማራን፣ ትግሬን፣ ወላይታን፣ ሐመርን፣ ሙርሲን፣ ኮንሶን፣ ጋምቤላን ወዘተ ጨፍጭፍልን” በሚል ሤራ ይመስላል ግማሽ ኢትዮጵያን ቆርሰው ‘ኦሮሞ’ የተባለውን ክልል ፈጠሩለት። በዚህም ሕወሓቶችን የብሔር ብሔረሰብ፤ በተለይ የሰሜን ኢትዮጵያውያን ጠላት ያደርጋቸዋል። ላለፉት አራት ዓመታት በደቡብ ኢትዮጵያ በሚገኙት ቁጥራቸው ዝቅ ባለ ጎሳዎችና ነገዶች ላይ ኦሮሞው ለሚፈጽመውና ወደፊትም ሊፈጽመው ለተዘጋጀው ጭፍጨፋ ዋና ተጠያቂ የሚሆኑት ለመላዋ ምስራቅና ሰሜን ምስራቅ አፍሪካ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰሜን ኢትዮጵያውያን ይሆናሉ።
ዲያስፐራ ‘ተጋሩን’ በተመለከተ በተደጋጋሚ የምንለው ነው፤ ተጋሩ ለትግራይ ባዕዳዊ የሆነውን የሉሲፈርን/የቻይናን ባንዲራ ከማውለብለብ እስካልተቆጠቡና የጽዮንን/የንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስን ሰንደቅ እስካላውለበለቡ ድረስ የሚያካሂዷቸው ሰላማዊ ሰልፎችና ክብረ በዓላት ምንም በጎ ነገር አያመጡም፤ 100%! ቴዲ ወንድሜ፤ አንተም ስቱዲዮህ ውስጥ ሰንደቁን መስቀል ማቆምህ ትክክል አይደለምና ትመልሰው ዘንድ እንድጠቁምህ ፍቀድልኝ። እንዴት የማንነታችን መገለጫ የሆኑትን ምልክቶች አሳልፈን እንሰጣለን? ስንቱን ንብረታችንን እንነጠቅ? ምንስ ሊቀረን? በኬሚካል የተመረዘ/ የተበከለ መሬት፣ አየርና ውሃ ተረክበን ዝግ ድንክዬ ሃገር ልንመሠርት? ለማን ስንል? በኤርትራም ያየነው ይህን ነውና አባቶቻችን እነ ቅዱስ ያሬድ፣ ንጉሠ ነገሥታት ኢዛና እና ዮሐንስ፤ እነ ራስ አሉላ ይህን ትውልድ እንዳይረግሙት በጣም እሰጋለሁ።
እነ ዶ/ር ደብረ ጽዮን ይበቃቸዋል! ተፈትነዋል፤ ፈተናውንም ክፉኛ ወድቀዋል፤ አሁን ሥልጣኑን ሕዝቡን ለሚወድ አዲስ ትውልድ ባፋጣኝ አስረክበው ከግራኝ አብዮት አህመድ አሊ + ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለፍርድ መቅረብ አለባቸው!
______________
Leave a Reply