Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • July 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for July 4th, 2020

መንግስት አለ ይለኛል ገዳይ ለማኝ ሁላ ፊት ለፊቱ እያየ እጅ እግሩ ተቆርጦ ወገኑ ሲቀላ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 4, 2020

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት ተዘግቷል፤ ሁሉም ማለት ይቻላል ተቀማጭነታቸው በኢትዮጵያ የሆነ ድሕረ ገጾች መረጃ ማቅረብ ካቆሙ አራተኛ ቀናቸውን አስቆጥረዋል፤ የሚከተሉት ሁለት የገዳይ ዐቢይ ቅጥረኞች ግን አሁንም “መልካም ዜና! ብራቮ ዐቢይ! ቅብርጥሴ” እያሉ መቀበጣጠሩን አላቆሙም። ለእነርሱ ብቻ ተፈቀደላቸው? ተቋማቱን፣ ቴሌቪዥኑን፣ ራዲዮውን፣ ፌስቡኩን፣ ብዙ ተከታዮች ያሏቸውን ዩቲውበሮችን ሁሉ በእጃቸው አስገብተዋል፤ እዚያም ላይ ተቀጥረው አስተያየት የሚሰጡትን በሺህ የሚቆጠሩት የመልስ ሮቦቶችን (የተዋሕዶ እና የእስላም ስም ተሰጥቷቸዋል)ሁሉንም ይገለገላል ገዳይ ዐቢይ፤ አቤት ስንቱን እንደ በግ የሚዳ ሞኝ እንዳፈቀደው እያታለለው ነው ይህ አውሬ!

ኢትዮጵያውያን የዐቢይ ጠላቶች፡ ከእነዚህ ሁለት ገለልተኛ-መሳይ ቅጥረኞቹ ተጠንቀቁ!

  • 👉 አቤል ብርሃኑ
  • 👉 Top Media Official

____________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ዐቢይ አህመድ እስክንድር ነጋን በረሃብ ቀጥቶ አሰደበደበው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 4, 2020

ወገኖቼ፡ እጅግ በጣም የከፋ ግፍ በሃገራችን እየተፈጸመ ነው። ኦሮሚያ በተባለው ሲዖል በናዚዎች ጊዜ እንኳን ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልክና እጅግ ዘግናኝ በሆነ የግድያ ዘመቻ ወገኖቻችን አካላቸው ተቆራርጦ፣ ተጠብሶና ተሰቅሎ እየታየ እንደሆነ ምንጮች ጠቁመዋል። ባካችሁ ወገኖች እያንዳንዷን ነገር መዝግቡልን፣ ቅረጹልን!

በሌላ በኩል የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ከፍተኛ አመራሮች አቶ እስክንድር ነጋ እና አቶ ስንታየሁ ቸኮል መታሰራቸው የሚታወስ ነው ነገር ግን በአሁን ሰአት ከፍተኛ ድብደባ እና እንግልት እየደረሰባቸው ነው። ከውስጥ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ለ ሁለት ቀናት ምንም አይነት ምግብ እንዳልቀረበለት እና በረሀብም ጭምር እየቀጡት ነው። ልብ በሉ፦ እንድ እምነስቲ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ነንየሚሉት ግብዝ ድርጅቶች ጸጥ ብለዋል። ኢትዮጵያውያን የሚፈተኑበት ወቅት አሁን ነው!

“…ጦርነት ውስጥ እንገባለን!” ብሏል እኮ ገዳይ አብይ አስቀድሞ። እስካሁን የተናገራቸውን ጽንፈኛ ንግግሮች ሁሉ በተግባር ላይ እያዋላቸው ነው። ከጀግናው ኢንጂነር ስመኘው እስከ ጽንፈኛው አጫሉ ሁሉንም የገደላቸው ዐቢይ አህመድ አሊ ነው። 100%! እርግጠኛ ነኝ።

የበሻሻ ቆሻሻን የባሌ ንግግር እናስታውስ፦

ኦሮሞ እስኪነቃ ነው እንጂ፣ እስኪነሳ ነው እንጂ ሲነሳ ሚዳቋ አትበላንም፤ እኛ ዝሆን ነን፤ እንሰብራለን፤ እንበላለን፤ እንገዛለን። ሃሳብ አለን፤ ድርጅት አለን፤ ከአለም ጋር ግንኙነት አለን፤ ህዝባችን በስራ ያውቀናል፤ እኛም ህዝባችንን እናውቃለን፤ ሽማግሌዎቻችንን እናውቃለን፤ ተያይዘን መላውን አፍሪካን ለመለወጥ፣ ይሄ ዘመን የእኛ ስለሆነ፣ ይህን ዘመን የሰጠን እግዝያብሄር በመሆኑ አሳልፈን ሰጥተን ዳግም ወደ ባርነት ለመመለስ አንፈልግም፤ ያ ደግሞ ተመልሶ አይመጣም። እጃችሁ የገባውን ነገር ጠብቁ፤ ቆጥቡ፤ አጠንክሩ፤ ጉድለት (ስህተት) ካለ ምከሩ። ያለበለዚያ ይህን ከጅ ካወጣን አጥር ውስጥ ተቀምጠው እንደሚያለቅሱት ዓይነት ለቅሶ ስለሚሆን፣ ከዚህ በኋላ ለኦሮሞ ለቅሶ የማይሆንለት ስለሆነ፣ ያገኘነውን ይዘን፣ የቀረውን ሞልተን፣ ወደ ፊት መሄድ እንድንችል”

_________________________________________

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »