Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • July 2020
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for July 17th, 2020

ዲያስፐራ ትናንትና እና ዛሬ | ጀነሳይድ እየፈጸመ ከመንግስት ጋር መስለፍ? | ነፍሳቸውን ሸጡ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 17, 2020

አንድ “ስቶኮልም ሲንድሮም/Stockholm Syndrome የተባለ ስነልቦናዊ ሕመም አለ፦

ኦሮሞው” ግራኝ ዐቢይ አህመድ አሊ በኢትዮጵያውያን ላይ በእስር ቤቶችም ሆነ በውጭ ስቅየት፣ እንግልት፣ መደፈር፣ ማገት፣ ማፈናቀል፣ ግድያ እና ደብዛ መጥፋት፤ በአጠቃላይ አስከፊ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት በይፋ እውቅና ወይም ይቅርታ ባልሰጠበትሁኔታ፡ “ከዐቢይ ጋር ነን!” የሚል መፈክር ማሰማት ሕመምና ዕብደት እንጅ ጤናማ የሆነ ዜጋ ሊያደርገው የሚችለው ነገር አይደለም። የዚህ ክስተት መጠሪያ “ስቶኮልም ሲንድሮም” ይባላል። ብዙ ጊዜ በሥነልቦናዊ ቀውስ የሚሰቃይ ሰው በአብዛኛው ለበዳዮቹ ወይም ላሰቃዮቹ የማዘን እና ድጋፍ የመስጠት ባሕርይ ያሳያል። ይህ ባሕርይ የሞትና ባርነት ማንነትና ምንነት መገለጫ ነው።

በአለፈው ዓመትና ከስድስት ወራት በፊት በዋሽንግተን የተካሄዱትን የተቃውሞ ሰልፎች ትናንትና ዛሬ በዚሁ ከተማ ከሚካሄዱት ሰልፎች ጋር እናነጻጽራቸው። ይህ ህገወጥ “መንግስት” ሥልጣኑን ከያዘበት ዕለት ጀምሮ ምን በጎ ነገር ታይቶ ነው? ነፃነት ባለበት ሃገር“መንግስትን እንደግፋለን!” ለማለት የደፈሩት? ማን አስገድዷቸው ነው? ለመሆኑ እነዚህ ሰዎች እነማን ናቸው? በኮካ እና በርገር ተበክለው ይሆን? ሰልፎቹስ በዐቢይ አገዛዝ ወኪሎች እየተጠለፉ፤ ወይንም የተለመደው የእነ ሲ.አይ.ኤ አዕምሮ ቁጥጥር ሰለባ ሆነው ይሆን? ዐቢይ በሲ.አይ.ኤ የተመረጠ ከሃዲ አይደል!

እንግዲህ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት አገራችን አይታቸው የማታውቃቸውን የግድያ፣ የእገታ፣ የማፈናቀልና የዓብያተ ክርስቲያናት ውድመት ሄደቶች ገጥመዋት አይተናል። አስራ ሰባት የምስኪን ገበሬ ልጆች ዕልም ብለው በጠፉበት፣ እናቶች ተፈናቅለው ለኮሮና በተጋለጡበት፣ የኦሮሞዎች ወረራ በሚጧጧፍበት፣ እነ እስክንድር ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ ተደርገው በሚደበደቡበት በእዚህ ክፉ ወቅት እነማን ናቸው ከዚህ “መንግስት” ተብዬው ጋር እንቆማለን” ለማለት የደፈረ? ምን ዓይነት መርገም ነው?! ምናልባትም

ይህን ቅሌት አንዲት ጦማሪ በጥሩ መልክ እንደሚከተለው ገልጻዋለች፦

የተለመደዉ የሰሞኑ የዲያስፖራዉ አስመሣይ ሰልፍ ምን እንደነበረ ለመረዳት ሞክሬ አሳቀኝ ግድቡ ዉኃ ሲሞላ አይተናል! አዎ! አይተናል!” ሆዱን የወደደ ማዕረጉን የጠላ የሰማያዊ ዉስኪና የቁርጥ ጥሬ ሥጋ አርበኞችን አደናጋሪ የሰልፍ ፉገራ በትናንትናዉ ዕለት እንደገና ለመታዘብ ዕድሜን አግኝቻለሁ። ለገዳዩ ያነጣጠሩትቀስት በማህበራዊ ሚዲያ እዪጎበጠ እነሱን ሲሰካባቸዉ ታዝቢያለሁ። ግፉና ግድያዉ የሚፈፀመዉ ኢትዮጵያ ግን የ28 ዓመቱ ጩኸት የነጮች መንደሮችን ነዉ የሚያደነቁረዉ። ገዳዩዎች ጠባብ ገዥዎች ናቸዉ ግን መፍትሄ የሚፈለገዉ ከገዳዩ ነዉ። ጥያቄዉ የህልዉና መኖርና ያለመኖሮ ግን እልል የሚባለዉ የአባይ ነገር ዉኃ በወንፊት ተቋጥሯል ነዉ። በዉነቱ ዉኃ በወንፊት መያዝ ይቻላል? ግድቡ ለዓሥር አመት እንደማይጠናቀቅ ራሱ አብይ አልተናገረም? ግድቡስ መቸ ተጠናቀቀ? የፈረደበት አባይ በዪ ጊዜዉ ጅላጅል ሕዝብ አግኝተዉ የፖለቲካ ሴራ ፍጆታ የህዉከትም መካካሻ እያደረጉ ኮሺ ባለ ቁጥር ያደነቁሩናል። ሀምሌና ነሀሴ ባለቀሱ ቁጥር ጉድጓዱ ዉኃ ሞላ ይሉናል እኔ ከተፈጥሯቸዉና ከባሀሪያቸዉ የሚሉት ምንም መጨበጫ የለዉም። ተቃወሞዉ እስክንድር ይፈታ ሰዉ ተጨረሰ ይሉና ፍታሀዊነት ከሌለዉ ግን ከመንግስት ጎን ስለመቆም ቅስቀሳ ይሰጣሉ። ጋሪዉ ወደ ፊት ፈረሱ በስተጀርባ።ኢትዮጵያ ከእስክንድር በላይ ነች የሚልም መፈክር ሰምቻለሁ ግን ሰዉ አለቀን ያሰማሉ። እስክንድር ሰዉ አይደለም? እረ ያሳፍራል። በሁለት ባላ የመንጠልጠል በሁለት ቢላም እዪመተሩ መጉረስ ምን አለ ቢቀር። እሺ እሰዪዉ አባይም ይሙላ ከሞላ ምን አስጨነቀን ገዳዩ ይደገፍ ቅስቀሴ ካልሆነ በስተቀር። ዉኃ የሚይዘዉ ገድቡ የሚሞሉትም ኢንጂኔሮች አብይን ከዚህ የሚያካትት ነገር ምን ይሆን?

________________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »