Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

ዱባይ | በጥምቀት የታየችንን ኢትዮጵያ ካርታ ኢትዮጵያውያን በመያዛቸው የግራኝ አህመድ መንግስት አዘነ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 28, 2019

የኤሚራቶች ሜዲያ እንደጠቆመው ከሆነ፤ ባለፈው ዓርብ በተካሄድው የዱባይ ማራቶን ትውልደ ኢትዮጵያውያን እግዚአብሔር የሰጣቸውን የኢትዮጵያን ካርታ በመያዛቸውና “ኤርትራውያን” የተባሉትን ወገኖች በማስቆጣቱ “ኢትዮጵያን የሚወክለው” ኤምባሲ ይቅርታ ጠይቋል። ዋውው! ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው፡ በቦታው ከኢትዮጵያ ካርታ እና ቀለማት ከያዙ ኢትዮጵያውያን ሌላ የግራኝ አህምደን ፎቶ የያዙ፣ ኮከብ ያረፈበትን የአቢሲኒያ ባንዲራ የተሸከሙ፣ እንዲሁም “የኦሮሚያ” ነው የተባለውን ጨርቅ የሚያውለበልቡ ወገኖች ይታያሉ።

በኤሚራትስ የኢትዮጵያ አምባሳደር፡ ሱሌማን ደደፎ ይባላል፤ አዎ! አዎ! ምንም አዲስ ነገር የለም!

በበረሃው የዱባይ ማራቶን ውድድር ጀግናው ኢትዮጵያዊ የተዋሕዶ ልጅ፡ ጌታነህ ሞላ፡ በአዲስ የዱባይ ሬከርድ ድል ተቀዳጅቷል። 2:03:34። ድንቅ ነው፤ ያውም በበረሃ አየር!

ጀግና! የአህዛብን ጥቁር ድንጋይ እናፈርሰው ዘንድ በቅርብ ለሚካሄደው የ መካ ማራቶን ያብቃህ!

ይድረስ ለአመፀኛውና ምስጋናቢሱ ትውልድ

እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ የጠቀሳት የመጀመሪያዋ ሃገር ኢትዮጵያ ናት፦

[ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ ፪፥፲፫]

የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።”

እግዚአብሔር አምላክኤርትራጂቡቲሱዳንሶማሊያኬኒያ ወይም ኦሮሚያ የሚባሉትን ቦታዎች በጭራሽ አያውቃቸውም። እነዚህ ስሞች ሁሉ ኤዶማውያኑ ምዕራባውያን ያወጡላችሁ የማታለያ ስሞች ናቸው። እግዚአብሔር እነዚህን ቦታዎች የማያውቃቸው ከሆነ ለእነዚህ ቦታዎች ባንዲራ ይዛችሁ የምትወጡትንም ከሃዲዎች አያውቃችሁም፤ በስንዴ መካከል እንደተዘራችሁ እንክርዳድ ናችሁና። አቤት ጉዳችሁ!

ኢትዮጵያውያን እን´ድንባት ዘንድ ፈጣሪአችን የሰጠንን እና የተረፈችውን አንዲት ኢትዮጵያ የሚያሳይ ካርታ ይዘው በመውጣታቻው የኢትዮጵያ መንግስት “ኤርትራውያን” ለተባሉት ወገኖቻችን ይቅርታ መጠየቅ አይገባውም ነበር። እንዲያውም ለኢትዮጵያውያን ነበር ይቅርታ መጠየቅ የነበረበት፤ “የኦሮሞ” ነው የተባለውን ባንዲራ ይዘው በወጡት ከሃዲዎች ተግባር መሆን ነበር ማዘን የነበረበት።

ኧረ ወገን ተማሩ! በኤርትራ ላይ ላለፉት ፳፭ ዓመታት ከደረሰው መቅሰፍት ልምድ ውሰዱ!

__________________

Leave a Reply

Fill in your details below or click an icon to log in:

WordPress.com Logo

You are commenting using your WordPress.com account. Log Out /  Change )

Facebook photo

You are commenting using your Facebook account. Log Out /  Change )

Connecting to %s

 
%d bloggers like this: