እስኪ አስቡበት…አብረን እናስብበት…አንድ የኢትዮጵያ መሪ የክርስቶስ የሆነችውን እናት ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። ዋው!
የኮሙኒዝምን ሥርዓት ሲያገለግሉ የነበሩት የሩሲያው ፕሬዚደንት ቭላዲሚር ፑቲን የሉሲፈራውያኑን ርዕዮተ ዓለም እርግፍ አድርገው በመተው ወደ ክርስቶስ መጥተዋል። በሶቪየት ኮሙኒዝም ጊዜ የቭላዲሚር ፑቲን እናት በቅዱስ ፒተርስቡርግ ከተማ ወደሚገኘው ቤተክርስቲያን በድብቅ ቭላዲሚር ፑቲንን አምጥተዋቸው አስጠምቀዋቸው ነበር። (ቤተክርስቲያን የሚሄዱ ሩሲያውያን ክትትልና አድሎ ይደረግባቸው ነበርና)።
በአንድ ወቅት፤ “አንገቴ ላይ ያደርግኳት ይህች መስቀል ሕይወቴን አድናታለች” በማለት መስክረው የነበሩት ፕሬዚደንት ፑቲን በዚሁ በተጠመቁበት ቤተክርስቲያን ነበር ባለፈው እሑድ የገና በዓልን ተመስጠው ሲያከብሩ የሚታዩት። ጠቅላይ ሚንስትር ሚድቪዴም ለፀሎት ሦስት ጊዜ ሲያማትቡ ይታያሉ።
ወደ አገራችን ስንመጣ፤ ቪዲዮው ላይ እንደሚታየው፡ አንድ የአገራችን መሪ ለመጨረሻ ጊዜ ኢትዮጵያዊቷን ቤተክርስቲያን የጎበኘው ከአርባ አምስት ዓመታት በፊት ነበር። እንዴት ነው…ይህ ክስተት እርርይ! ኡ! ኡ! አያሰኘንምን። ምን ዓይነት ኃጢዓት ብንሠራ ነው ኢትዮጵያን እና አምላኳን የሚጠሉ መሪዎች የተሰጡን?! እንደ መስቀል፣ ገና እና ጥምቀት በመሳሰሉት አንጋፋ የኢትዮጵያውያን ክብረ በዓላት (ሰባ ሚሊዬን ኢትዮጵያውያን የሚያከብሯቸው) ላይ ለመሳተፍ ፈቃደኛ የሆኑ መሪዎች እንኳን የሉንም። በመስከረሙ የመስቀል ደመራ በዓል ወቅት ዶ/ር አብይ በመስቀል አደባባይ ይገኙ ይሆናል የሚል ጭምጭምታ ነበር፤ ነገር ግን እርሳቸውም ያው ከ666ቱ ስለሆኑ ሳይሳተፉ ቀሩ።
ባለፈው ጊዜ፡ በዚምባብዌ፡ ለገዳዩ መንግስቱ ኃይለማርያም የሰገዱት የቀድሞው ጠ/ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን ከመውረዳቸው በፊት በኢየሩሳሌም የምትገኘውን የኢትዮጵያ ቤትከርስቲያን በእስራኤል መንግስት ግፊት ለመጎብኘት ሲገደዱ ጫማቸውን እንኳን ሳያወልቁ ነበር የገቡት፤ አቤት ድፍረት! አቤት ትዕቢት አቤት ቅሌት!
ዋ! ለሉሲፈራውያኑ ወኪሎች፤ ሕዝባችንን ኋለኞች ለማድረግ ተግተው ለሚሠሩት፤ ዋ!
እኛ የተዋሕዶ ልጆች ግን በገዢዎች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ በእግዚአብሔር ተስፋ ማድረጉን እንመርጣለን፦
[ ፪ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕራፍ ፮፥፩፡፲]
“አብረንም እየሠራን የእግዚአብሔርን ጸጋ በከንቱ እንዳትቀበሉ ደግሞ እንለምናለን፤ በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ በመዳንም ቀን ረዳሁህ ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳን ቀን አሁን ነው። አገልግሎታችንም እንዳይነቀፍ በአንዳች ነገር ማሰናከያ ከቶ አንሰጥም። ነገር ግን በሁሉ እንደ እግዚአብሔር አገልጋዮች ራሳችንን እናማጥናለን፤ በብዙ መጽናት፥ በመከራ፥ በችግር፥ በጭንቀት፥ በመገረፍ፥ በወኅኒ፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመጦም፥ በንጽህና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ ግብዝነት በሌለው ፍቅር፥ በእውነት ቃል፥ በእግዚአብሔር ኃይል፥ ለቀኝና ለግራ በሚሆን በጽድቅ የጦር ዕቃ፥ በክብርና በውርደት፥ በክፉ ወሬና በመልካም ወሬ ራሳችንን እናማጥናለን፤ አሳቾች ስንባል እውነተኞች ነን፤ ያልታወቁ ስንባል የታወቅን ነን፤ የምንሞት ስንመስል እነሆ ሕያዋን ነን፤ የተቀጣን ስንሆን አንገደልም፤ ኀዘንተኞች ስንሆን ዘወትር ደስ ይለናል፤ ድሆች ስንሆን ብዙዎችን ባለ ጠጎች እናደርጋለን፤ አንዳች የሌለን ስንሆን ሁሉ የእኛ ነው።”