እኛን እርስበርስ እያባሉ መቶ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎችን በአገራችን ፈጥረው የሚያውኩን የአሜሪካ ፈላጭ ቆራጮች፡ ሁለት ፓርቲ ብቻ ባላት አሜሪካ አሁን እራሳቸው እርስበርስ እየተባሉ ነው።
የሪፓብሊካን እና ዲሞክራቲክ ፓርቲዎች አውሬዎች ከሜክሲኮ ጋር ሊገነባ በታሰበው “የግንብ አጥንት” በሚያሳፈር መልክ በመናከስ ላይ ናቸው።
በአሜሪካ ውጥረቱ ከሮ የመንግስት እንቅስቃሴ ሩብ የሚሆነው ከተዘጋ ዛሬ 32ኛ ቀኑን ይዟል፤ በአሚሪካ ፖለቲካ ህይወት ታሪክ ይህ ታይቶ አይታወቅም፦ በሚሊየን የሚቆጠሩ የአሜሪካ የመንግስት ሰራተኞች ደሞዝ ለመቀበል አይሄዱም፤ ደሞዝ የለም፤ መንግስት ተዘግቷል።
ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕን በመተናኮል ላይ ያለውና ከስለላ ድርጅቶቹ አንዱ የሆነው “ኤፍ. ቢ. አይ” “እንዳንቸገር ፈርተናል፤ ገንዘብ ጎድሎናል ቅብርጥሴ” በማለት ስጋቱን በመግለጽ ላይ ነው።
አዎ! ኢትዮጵያ አገራችንን አይኖቻችን እያዩ በግልጽ ከሚተናኮሉት ሉሲፈራውያን ተቋማት አንዱ ነው። ከወራት በፊት በመስቀል አደባባይ በፈነዳው ቦምብ የማጣራት ጉዳይ ፈጥኖ ለመሳተፍ የወሰነው ይህ የአሜሪካ የስለላ ተቋም “ኤፍ. ቢ. አይ” ነበር።
“FBI ፣ CIA እድንዲሁም ሌሎቹ የ “አምስት ዓይኖች” አገራት የስለላ ተቋማት (የእንግሊዝ፣ አውርስትራሊያ፣ ኒው ዚላንድ፣ ካናዳ እና አሜሪካ) ባለፉት 50 ዓመታት ብቻ ከመቶ በላይ በሚሆኑ አገራት መንግሥታትን አፍርሰዋል፣ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ንፁሐን እንዲያልቁ ምክንያት ሆነዋል። በማንም የውጭ ሐይል ቁጥጥር ስር ገብታ የማታውቀው ኢትዮጵያችን እንድትከፋፈል የተደረገችው በአሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይና ጀርመን ቁጥጥር ሥር ለማድረግ ነው። ይህም በግልጽ እየታየ ነው። እስኪ እነዚህ አገራት የት የት እንደሚሄዱ እነመልከት፤ አንዱ ወደ ጅማ፣ ሌላው ወደ ሐረር….
እንደምሳሌ በመውስድ እስኪ የሚከተሉትን አርዕስተ ዜናዎች ቅደም ተከተል በጥሞና እንመልከት፦
“ጅማ ጥቅምት ፳፫/፪ሺ፲፩ ዓ.ም –
“የአሜሪካን መንግስት ለጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት ዕድሳት የሚውል መቶ ሃያ አምስት ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገ።”
ልብ እንበል የፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ መንግስት አይደለም ድጋፍ የሚያደርገው፤ የእነ “ሲ. አይ. ኤና” “ኤፍ. ቢ. አይ.” ጥልቅ መንግስት እንጅ። አዲስ አበባ የሚገኙትም ኤምባሲ እና ሌሎች ድርጅቶች ሁሉ የዚህ ሉሲፈራውያን ጥልቅ መንግስት ወኪሎች ናቸው።
ጥር/ ፪ሺ፲፩ ዓ.ም – ጠ/ቅ/ሚ ዶ/ር አብይ፦
“የማክበረው የማደንቀው መሪ አባጅፋር ነው።”
ዋውው! ምን ዓይነት ዓለም ነች?!
የከሃዲዎች የሆነ ዘምን ላይ እንደደረስን እስኪ እንመልከት፦
የጂማው አባጅፋር ምናልባትም በመላው አለም ተዋዳዳሪ የማይገኝለት የባሪያ ፈንጋይና ነጋዴ ነበር።
በአባጅፋር ዘመን ከኢትዮጵያ አምስት መቶ ሺህ – አዎ! ግማሽ ሚሊዬን የሚሆኑ ባርያዎች ወደ አረብ አገራት እንደተሸጡ ተመዝግቧል። ባሪያዎቹ የተፈነገሉት በአብዛኛው ከዚሁ የከፋ ግዛት ወይም ተባባሪ ግዛት ከነበሩት ሁሉ ነው። ከሁሉም የሚደንቀው አባጂፋር ለጥርስ ሀኪማቸው የከፈሉት አምስት ባሪያ ነው። አባጅፋር አንድ ውሻ በሁለት ባሪያ ለውጧል። የሰውን ልጅ በውሻ ሲለውጥ የነበረ ሰው አሁን “የሚደነቅ መሪ” ሆኗል፡ አባጅፋር የተባለና የኢትዮጵያ ቻምፒዮን የሆነ የእገር ኳስ ቡድን አለን። ቀጥለውም ግራኝ አህመድን የኢትዮጵያ ጀግና ለማድረግ ሲሞክሩ እናያለን።
የአሜሪካ መንግስት አሁን እየደጎመለት ያለው ይህ የጅማ አባጅፋር ቤተመንግስት የሚገኝበት ቦታ ምንልባትም በዓለም ደርጃ ትልቁ የባሪያ መሸጫ ገበያ ነበር። ከዚህ ገበያ የተገዙ ባሪያዎች በመተማ፣ በታጁራ፣ በምጽዋ በኩል ለአርብ አገራት ገበያ ይቀርቡ ነበር፤ ልክ እህቶቻችን በቤት ሠራተኛ መልክ እየተሸጡ እንዳሉበት እንደ ዛሬው ዘመን ማለት ነው።
ዶ/ር አብይ አሜሪካን ሲጎበኙና ወደ ሚነሶታ “ዘመዶቻቸው” ጎራ ሲሉ፤ ፕሬዚደንት ትራምፕ ሊቀበሏቸው ፈቃደኛ አልነበሩም። ይህ ምን ይጠቁመናል?