Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2019
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 20th, 2019

ደም የለበሰችው ጨረቃ | የሆነ ኃይል ከ ቍጥር ፳፩ / 21 ጋር ትልቅ ጕዳይ አለው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2019

ጃንዋሪ 21ን በጣም የሚፈልጋት ኃይል ባለፉት ቀናት ብዙ የግድያ መስዋዕቶች እንዲፈጸሙ አድርጓል

ኬኒያ፥ ጃንዋሪ 15 /2019

  • ሆቴል ውስጥ 21 ሰዎች ተሰው፥ ከመስከረም ፩ ጥቃት የዳነውን አሜሪካዊ ጨምሮ

ኮሎምቢያ፥  ጃንዋሪ 17 / 2019

  • በቦምብ ፍንዳታ 21 ሰዎች ተገደሉ

ሜክሲኮ፥ ጃንዋሪ 18 / 2019

ኃይለኛ የእሳት ቃጠሎ በመቀስቀሱ፤

  • መጀመሪያ፦ 66 ሰዎች ሞቱ
  • ቀጥሎ፦ 73 ሆኑ 7×3 = 21
  • ቀጥሎ፦ 79 ሆኑ፤ 7+9 = 16
  • 666

የጨረቃ ግርዶሽ፡ ጃንዋሪ 21/2019

ጨረቃዋ በመሬት እና በፀሐይ መካከል ትሆናለች፦ ቀይ ደም የለበሰችው ጨረቃ በተለይ በአሜሪካ ላይ ስትሽከረከር ትታያለች።

አስገራሚ የሆነውን የእሳት ገጽታ እንመልከት፦

ዔሳውያኑ አሜሪካ እና አውሮፓ ኢትዮጵያን መተናኮል ከጀመሩ ቆይተዋል፤ በየጊዜው ምልክትና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶዋቸዋል ግን እንደ እስማኤላውያኑ አጋራቾቻቸው በፈረዖናዊ ትዕቢት ስለተወጠሩ እጆቻቸውን ከአገራችን ላይ ማንሳት ተስኗቸዋል።

በዚህ የፈረንጆች ዓመት ሉሲፈራውያኑ በፕሬዚደንት ትራምፕ ላይ ምናልባት አስከፊ ጥቃት ሊፈጽሙ ይሆናል፤ ሥልጣኑን ሙሉ በሙል ለመቆጠጠር። ስለዚህ የአገራችን ጠላቶች ባለፈው ዓመት ልክ በዚህ ጊዜ ሚነሶታ ውስጥ የጠነሱስትን ተንኮል ይገፉበት ይሆናል። በዚህም በአሜሪካ ላይ ከመስከረም ፩ ከበድ ያለ ፍርድ ይመጣል!!!

_________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

አንዲት ክርስቲያን እናት እሁድ እሁድ ለመሥራት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው 21 ሚሊዮን ዶላር ተሸለሙ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2019

የ60 ዓመቷ እናት “ማሪ ጄን ፒዬር”፡ በፍሎሪዳዋ ማያሚ ሂልተን ሆቴል ቅርንጫፍ እቃ አጣቢ ሆነው ለአሥር ዓመታት ያህል ሠርተዋል። ትውልደ ሃይቲዋ ማሪ ጄን ሰንበት ሰንበት ለመሥራት ፈቃደኛ ያልነበሩ አጥብቂ ክርስቲያን በመሆናቸው፡ ወደ ቤተክርስቲያን መሄድ ይችሉ ዘንድ ለስድስት ሰንበታት ያህል ወደ መሥሪያ ቤት አልሄዱም ስላሉ በሆቴሉ አለቃዋ ከሥራቸው ተሰናበቱ። በዚህም ምክኒያት በቀድሞ አሠሪዋ ላይ ክስ ለመመስረት ተገደዱ።

ጉዳዩም ለፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት እናት ማሪ የሚከተለውን ብለው ነበር፦

እግዚአብሔርን ስለምወደው ሰንበት ሥራ የለም በእሑድ እግዚአብሔር መከበር አለበትና”

የማሪ ጠበቃም በማከል፦

ማሪ የክርስቶስ ወታደር ናት፤ በተመሳሳይ መልክ አድልዎ እየደረሰባቸው ላሉት ለሁሉም ሠራተኞች አርአያ ትሆናለች

ብለዋል።

ባለፈው ሰኞ ዕለት ፍርድ ቤቱ የማሪድሞ አሠሪ፡ ሂልተን 21 ሚልዮን ዶላር እንዲከፍል እንዲሁም ለቀጣይ ክፍያ 35,000 ዶላር እና ለደረሰባቸው ስሜታዊ እና አእምሯዊ ህመም $ 500,000 ተጨማሪ መክፈል እንዳለበት ወስኗል።

ጠበቃዋም ውሳኔውን አስመልክቶ የሚከተለውን ብሎ ነበር፦

ይህ ጉዳይ ገንዘብን የሚያመለክት ጉዳይ አልነበረም፣ እንደ ሂልተን ሆቴል ትላልቅ ለሆኑ ድርጅቶች መልእክት ለመላክ እንጂ” “የፈለግከውን ያህል አንጋፋ ብትሆን፣ የሰራተኞቹን ደም እና ላብ መውሰድ ከፈለጉ እነሱን በተሻለ ሁኔታ መንከባከብ ይገባቸዋል ወይም ቢያንስ በእምነታቸው ባይጋፏቸው ጥሩ ነው።”

አርአያችን ሊሆኑ የሚገባቸው ጎበዝ እናት ናቸው! ግሩም የፍርድ ቤት ውሳኔ!

ሁሌ የሚያሳስበኝ በአገራችን፡ ሰንበትን ጨምሮ በበዓላቱ ሁላ ሱቆች፣ ገባያዎችና ዳንኪራ ቤቶች ገንዘብ ሲያሽከረክሩና ሲጯጯሁ መታዘቤ ነው። እመነተቢስ የሆኑት ብዙ የምዕራባውያን አገራት እንኳን ለሰንበትና ለበዓላት ሱቆቻቸውን እንዲዘጉ ያደርጋሉ።

____________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ዋ! ከ ቅዱስ ሚካኤል ወዳጆች ላይ እጆቻችሁን አንሱ!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 20, 2019

____________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: