የዛሬዋ ኢትዮጵያ ከማን ጋር ናት? ከሙስሊም ቱርክ/አዘርበጃን ወይንስ ከክርስቲያን አርሜኒያ?
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 29, 2020
የግራኝ ቄሮ-ኦሮሞ አገዛዝና አህዛብ ዜጎቹ ከሙስሊም አዘርበጃን ጎን እንደሚቆሙ አያጠራጥርም፤ ኢትዮጵያውያን ከማን ጎን ይሰለፋሉ?
በክርስቲያን አርሜኒያ እና ሙስሊም አዘርበጃን መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት የዓለማችን ሃገራት የሚደግፉትን ወገን በመምረጥ ላይ ናቸው። አዘርበጃንን በቱርክ የሚመራው የሙስሊም ዓለም ይደግፋል፤ ቱርክ፣ ኢራን እና ፓኪስታን በይፋ ለመደገፍ ቀዳሚዎቹ ናቸው። ፓኪስታን የኑክሌር ፈንጅ ባለቤት ናት። ከአርሜኒያ ጎን እስካሁን ሩሲያ እና ህንድ አሉ። ሁለቱም የኑክሌር ፈንጅ ባለቤቶች ናቸው። በጉ ከፍየሎች በሚለይበት በዚህ ዘመን ማን ከማን ጋር እንደሚሰለፍ ማየቱ አስገራሚ ይሆናል። ሌላው የሚገርመው ነገር እስራኤል ከአዘርበጃን ጋር ጥሩ ግኑኝነት ያላት መሆኑ ነው፤ ለአዘርበጃን ሠራዊትም መሳሪያ ታቀብላለች፤ በተመሳሳይ ሰዓት የአዘርበጃን ደጋፊዎች ቱርክ እና ፓኪስታን ቀንደኛ የአይሁዶች ጠላቶች መሆናቸው እስራኤል ከአዘርበጃን ጋር በፈጠረችው ግኑኝነት ላይ በጥልቁ ታስብበት ዘንድ ትገደዳለች። ወሸከቲያሙ የስትራቴጂካዊ አጋርነት ዘመን አክትሟልና!
_____________________________
Leave a Reply