በዝሙት፣ በክፋት፣ በተንኮልና በስጋት የኖራችሁበት ያለፈው ዘመን ይበቃል ፤ ያለዚያ የእሳት ዝናብ ይዘንባል
👉 ደመናው ላይ
ድንቅ ነው! ከስብከቱ ጋር፡ ሰማዩ ላይ ደመናው የተከማቸው በአንድ ትንሽ ቦታ ላይ ብቻ ነበር ፤ ሌላ ቦታ ደመና አልነበረም። ጥቂት የደመና ክምችት መብረቁን ሲያብለጨለጭውም ብዙ ጊዜ አይታይም። የደመናው ቅርጽም ያስገርማል፤ መጀመሪያ ላይ የአንበሳ አስከሬን እና የሰው ፊት ቅርጽ ያለውን ታላቁን የግብጽን ስፊንክስ ሃውልት ሠርቶ ሲበታተን አቶም ቦምብ የሠራ የጅብ ጥላ ይመስላል።
[ትንቢተ ኢዮኤል ምዕራፍ ፪ ፥ ፩ ፡ ፫]
፩ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፥ እርሱም ቀርቦአልና በጽዮን መለከትን ንፉ፥ በቅዱሱም ተራራዬ ላይ እሪ በሉ፤ በምድርም የሚኖሩ ሁሉ ይንቀጥቀጡ፤ የእግዚአብሔር ቀን መጥቶአልና፤
፪ የጨለማና የጭጋግ ቀን፥ የደመናና የድቅድቅ ጨለማ ቀን ነው፤ ታላቅና ብርቱ ሕዝብ በተራሮች ላይ እንደ ወገግታ ተዘርግቶአል፤ ከዘላለምም ጀምሮ እንደ እነርሱ ያለ አልነበረም፥ ከእነርሱም በኋላ እስከ ብዙ ትውልድ ድረስ እንደ እነርሱ ያለ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም።
፫ እሳት በፊታቸው ትባላለች፥ በኋላቸውም ነበልባል ታቃጥላለች፤ ምድሪቱ በፊታቸው እንደ ዔድን ገነት፥ በኋላቸውም የምድረ በዳ በረሃ ናት፤ ከእነርሱም የሚያመልጥ የለም።
[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯፥፳፮ ፡ ፳፯]
በኖኅ ዘመንም እንደ ሆነ፥ በሰው ልጅ ዘመን ደግሞ እንዲሁ ይሆናል።
ኖኅ ወደ መርከብ እስከ ገባበት ቀን ድረስ፥ ይበሉና ይጠጡ ያገቡና ይጋቡም ነበር፥
የጥፋት ውኃም መጣ ሁሉንም አጠፋ።
______________________________