Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2024
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for June 2nd, 2024

The Ark of the Covenant Uncovered in the Book of Axum | ታቦተ ጽዮን / የቃል ኪዳኑ ታቦት በመፅሐፈ አክሱም ተገለጠ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 2, 2024

ገብርኤል 🧕 ማርያም ❖ ኡራኤል ❖ ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት 😇 መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም

📖 “መፅሐፍ አክሱም” በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን በአክሱም ንቡረ-ዕድ የተፃፈ መፅሐፍ ነው።

  • 00:00:00 – ጥንታዊ ማስተጋቢያ
  • 00:00:47 – የይሁዳ አንበሣ
  • 00:01:47 – የቃል ኪዳኑ ታቦት
  • 00:02:49 – የጊዜ ሹክሹክታ
  • 00:03:38 – የንግስተ ሳባ ቅርስ
  • 00:04:26 – ዘላቂ እንቆቅልሽ

መጽሐፈ አክሱም፤ የአክሱም ጽዮንን ታሪክ እና የርስት ጉልቷን ሥሪት የሚናገር ሲሆን ስለ ቅ/ያሬድ ዜማ ድርሰት ይናገራል። እንዲሁም በድርሳነ ዑራኤል የተገለጸውን ታሪክ (እመቤታችን ተገልጻ ቅ/ኤፍሬምንና አባ ሕርያቆስን “ዜማ እንዲደርስልኝ ውዳሴዬንና ቅዳሴዬን ለያሬድ ስጡት” ያለችውን) መዝግቧል።

“መጽሐፈ አክሱም”ትውፊትንና ታሪክን መሠረት አድርጎ የአክሱምን አመሠራረትና ታሪካዊ እድገት፣ ሃይማኖታዊና ሀገራዊ ማዕከልነት ይናገራል፡፡ ስለ አክሱም አመሠራረት፣ ሰፊ ትውፊታዊ ትንታኔ ይሰጣል፡፡ የአኹኖቹ የግሪክ እና የሮም ከተሞች እጅግ ሰፊ የነበረው የግሪክ ወሮም ግዛትና መንግሥት ታሪክ ማሳያዎች እንደመኾናቸው፤ የአኹኗ አክሱምም፣ ምሥራቅ አፍሪቃን ከደቡብ አረብ አጣምራ ትገዛ ለነበረችው የጥንታዊቷ ኢትዮጵያ (ዘመነ አክሱም) ታሪክ መዘክር ነች፡፡

‘ኢትዮጲስ’ በመጽሐፈ አክሱም ዘንድ ኑቢያን የመሠረተው የካም ልጅ ኩሽ ልጅ ነበር። በዚህ መሠረት በኢትዮጵያ የሚኖሩት ኩሺቲክ ብሔሮች አባት በመሆኑ አገሩ ‘ኢትዮጵያ’ መባሉ እንደሚገባው ይታመናል።

በመጽሐፈ አክሱም መሠረት ኩሽ የርስቱን ድርሻ ለማመልከት የአክሱምን ታላቅ ኃውልት እንዳቆመ፣ ልጁም ኢትዮጲስ በዚያ እንደተቀበረ ይታመናል። ዘራፉው የስኮትላንድ ነፃ ግንበኛ/ፍሪሜሰን ጀምስ ብሩስም በኖረበት ዘመን ይህ መጽሐፍ በኢትዮጵያ ከክብረ ነገሥት ጋር እኩል ሆኖ እንደ ከበረ ጽፎ መሰክሯል።

👉 ማሳሰቢያ

ይህን መጽሐፍ ዋቢ በማድረግ በተለይ በጎንደር አካባቢ የተዳቀሉት የዋቄዮ-በዓል-አላህ-ባፎሜት-ሉሲፈር ባሪያዎች/ እባቦች እና ደቡባውያን አጋሮቻቸው ታሪክን እየበረዙ የአክሱማዊቷን ኢትዮጵያ ማንነትና ምንነት ብሎም ግዛታዊ አንድነትን ለመጻረር/ለመዋጋት በመታገል ላይ መሆናቸውን ልብ እንበል።

እነዚህ የጎንደር እና ሐረር አካባቢ ዲቃላዎች ናቸው በተለይ ‘አማራ’ የተሰኘውን ማህበረሰብ እንደ በሬው ሳሩን እያሳዩ ወደ ገደል በመውሰድ ላይ ያሉት። ለዚህም ነው ይህ’ኢትዮጵያዊና ክርስቲያን ነኝ!’ የሚለው የወደቀ ወገን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ቀንደኛ ጠላቶች ጋር አብሮ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመጨፍጨፍ፣ ለማስራብ፣ ለማፈናቀልና ለማሳደድ ወደ አክሱም ጽዮን የዘመተው። ይህ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ የሆነ ታሪካዊ ስህተት ደግሞ ጠላቶቻችንን እንኳን ሳይቀር ያስገረመና ያበረታታ ነው። እንደ ዓይኑ ብሌን ሊንከባከባት በሚገባው በአክሱም ጽዮንን ላይ ከእስማኤላውያኑ የክርስቶስ ተቃዋሚ የኢትዮጵያ ጠላቶች ጋር ሆኖ ዘመተባት። ከአምስት መቶ ዓመታት በፊትም የግራኝ ቀዳማዊ ጂሃዳዊ ጦር ከሐረር ኤሚራት ተነስቶ እስከ አክሱም ጽዮን ድረስ ሊገባ የቻለው በእነዚሁ ዲቃላዎች ተመሳሳይ ክህደት ስለተፈጸመ ይሆን? ይመስላል!

👉 Courtesy: https://www.youtube.com/@MysteriousThingsUntold

Dive into the rich and mysterious history of Ethiopia as we explore the secrets revealed in the Book of Axum. This ancient text offers fascinating insights into the legendary past of this African nation.

👉 Outline:

  • 00:00:00 – An Ancient Echo
  • 00:00:47 – The Lion of Judah
  • 00:01:47 – The Ark of the Covenant
  • 00:02:49 – Whispers of Time
  • 00:03:38 – The Queen of Sheba’s Legacy
  • 00:04:26 – An Enduring Enigma

In this video, we uncover the untold history of Ethiopia, delving into the powerful symbolism of the Lion of Judah, the enigmatic Ark of the Covenant, and the whispers of time that echo through ancient tales. Learn about the legacy of the Queen of Sheba and the enduring mysteries that make Ethiopia a land of legends. Perfect for history enthusiasts, this video brings to light the rich heritage and profound cultural significance of Ethiopia as documented in the Book of Axum.

The Book of Axum (Ge’ez መጽሐፈ ፡ አክሱም maṣḥafa aksūm, Amharic: meṣhafe aksūm, Tigrinya: meṣḥafe aksūm, Latin: Liber Axumae) is the name accepted since the time of James Bruce in the latter part of the 18th century CE for a collection of documents from Saint Mary’s Cathedral of Axum providing information on Ethiopian history. The earliest parts of the collection date to the mid-15th century during the reign of Zar’a Ya`qob (r. 1434-1468).

The book’s editor Carlo Conti Rossini classified the book into three parts: the first, earlier, section describes the Church Maryam Seyon in Axum prior to it being damaged in the mid-16th century, the topography of Axum and its history, and contains a list of services and the like regarding Maryam Seyon and its clergy.

The second part is dated to the early 17th century and contains 104 historical and legal texts, many dealing with land grants, along with their protocols, while the third text dates to the late 17th century and contains 14 miscellaneous legal and historical texts regarding Axum’s history. The book was also supplemented in the mid-19th century with further later documents.

The book derives the name Ethiopia from Itiyopp’is, an (otherwise unmentioned) son of the Biblical Cush. According to the Book of Axum Itiyopp’is built Mazaber, the Kingdom of Axum’s first capital.

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

መዝሙረ ዳዊት ፲፩፤ አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 2, 2024

ገብርኤል 🧕 ማርያም ❖ ኡራኤል ❖ ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት 😇 መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም

ዛሬም ሆነ ላለፉት ሺህ ዘመናት ሁሌ እየተጨፈጨፈ ያለው እኮ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ክርስቲያን ሕዝብ ነው። እኔን በጣም የሚያሳዝነኝ እና የሚያስቆጣኝ ሕዝበ ክርስቲያኑ እንደሚሳደድ፣ እንደሚራብ እና እንደሚጨፈጨፍ በግልጽ ተናግሮ ተገቢውን ክርስቲያናዊ አንድነትና እርምጃ ለመውሰድ ምንም ዓይነት ምልክት የማያሳየው የዚህ ትውልድ ጉዳይ ነው። እንዲያውም በተቃራኒው ብዙ ‘ኢትዮጵያዊ ነኝ’ የሚል የወደቀ ወገን ከኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት ቀንደኛ ጠላቶች ጋር አብሮ ሕዝበ ክርስቲያኑን ለመጨፍጨፍ፣ ለማስራብ፣ ለማፈናቀልና ለማሳደድ ወደ አክሱም ጽዮን ዘመተ። ይህ እጅግ በጣም አስገራሚና አሳዛኝ የሆነ ታሪካዊ ስህተት ደግሞ ጠላቶቻችንን እንኳን ሳይቀር ያስገረመና ያበረታታ ነው። በዳዮቻችን ዛሬም ግፋቸውንና በደላቸውን ያለምንም የፍትሕ እና ተጠያቂነት ሥራ በስላቅና በድፍረት የቀጠሉበት እኮ ይህን ስላዩ ነው። የበዳዮቻችን ድምጽ ከእኛ ተበዳዮቹ ከፍ ብሎ በመላው ዓለም ሊሰተጋባ የቻለውም ዓለም ከንቱ ስለሆነች ብቻ ሳይሆን እንደዚህ ዓይነት በጭራሽ መፈጸም የሌለበት ከባድ ስህተት “ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ክርስቲያን ነኝ!” በሚለው ወገን ዘንድ በመፈጸሙ ነው። “ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ?” ብሎ እራሱን በመጠየቅ ከስህተቱ ለመማርና ኃላፊነቱን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆነ ሰነፍና ወንድ ያልሆነ ትውልድ በመብዛቱ እኮ ነው። ይህ ከንቱ ዓለምም እኮ መኖራችንን እስከመርሳት ድረስ ዝም ያለንም በዚህ ምክኒያት ነው። ታዲያ ይህ ሁሉ የማን ጥፋት ነው? ለራሱ የማያስብ ሌላ ማን ሊያስብለት? በደሉ በግል ወደ ቤተሰባችን እስካልመጣ ድረስ የማንተነፍሰውና የወገናችን ስቃይ እና መከራ ብዙም የማያሳስበን፣ የማያስቆጣን እና በተገቢው መልክ ለበቀል የማየነሳሳን የእኛ ትውልድ ድክመትና ስህተት ስለሆነ አይደለምን?! በደንብ እንጂ!

ክርስቲያናዊ አንድነትየመንፈስ ማንነታችንና ምንነታችን/ክርስትናችን ጥንካሬ ሙቀት መለኪያ ነው!

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፩]❖❖❖

  • ፩ አቤቱ፥ አድነኝ፤ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።
  • ፪ እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።
  • ፫ የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ፤
  • ፬ ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።
  • ፭ ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር። አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።
  • ፮ በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
  • ፯ አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።
  • ፰ በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።

❖❖❖[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፬]❖❖❖

  • ፩ ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።
  • ፪ የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
  • ፫ ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
  • ፬ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
  • ፭ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤
  • ፮ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
  • ፯ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።
  • ፰ በዚያ በታላቅ ፍርሃት እጅግ ፈሩ፥ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።
  • ፱ የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።
  • ፲ ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »