Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2024
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728293031
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for March 2nd, 2024

Arabs Ride CAMELS Down a Busy Street in Wintry London | Symbolic of Conquest of Londonistan

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 2, 2024

ገብርኤል 🧕 ማርያም ❖ ኡራኤል 😇 ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት ❖ መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም

🐪 አረቦች በክረምታማዋ ለንደን የተጨናነቀ መንገድ ላይ ግመሎችን መጋለብ ጀምረዋል | “ሎንዶኒስታን ‘ኬኛ’” የድል ምልክት

መሀመዳውያኑ ለንደንን የመውረጣቸው ምሳሌ ነው። የፎርሙላ አንድ/ F1 መኪኖች በአረብ በረሃ (በዚህ ሳምንት በባህሬን + ሳውዲ አረቢያ) – ግመሎች በአውሮፓ ከተሞች! ምን ሊበላሽ ይችላል?!

🐪 It is symbolic of their conquest of London. F1 cars drive through the Arabian Desert (This week in Bahrain + Saudi Arabia) – Camels through European cities! What could go wrong?!

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የመንፈሥ ማንነትና ምንነት ያላቸው የአፄ ዮሐንስ እና የሥጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 2, 2024

ገብርኤል 🧕 ማርያም ❖ ኡራኤል 😇 ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት ❖ መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም

❖ የአደዋ ሕዝብ ከፍተኛ መስዋዕት ያደረገበትና ብዙ ዋጋ የከፈለበት ፻፳፰ / 128ኛው የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ የአድዋ ድል

አዎ! እስከ ዛሬ በታሪክ ትምሕርት እንደተማርነው እና የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ታሪክ ነጣቂዎች እንደተረቱልን ሳይሆን የአድዋውም ሆነ የተቀሩት ሃያ ሰባት የሚሆኑ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሄዱት ጦርነቶች ድሎች ባለቤቶች የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ልጆች ብቻ ናቸው። ጃካ ማኬሎአብዲስ አጋባልቻ አባ ነፍሶቅብርጥሴ ታሪክ ለመስረቅ ስጋውያኑ የፈጠሩት የቅጥፈት ትርክት ነው። ለሌቦቹ ወዮላቸው!

የአድዋ ድል ከእግዚአብሔር የተገኘ ድል ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 1, 2014

😈 የዲያብሎስ ዙፋን በኢትዮጵያ የተተከለው ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዮሐንስ ፬ኛን ገድለው ቤተ ክርስቲያንን እና ኢትዮጵያን ለመቆጣጠር ከበቁ በኋላ ነው

የሚከተለው የድንቁ ማሞ ውድነህ የያኔው የታሪክ ዘገባ ልክ ዛሬ በኢትዮጵያ የሚታየውን ክስተት ነው እንደ መስተዋት ገልጦ የሚያሳየን፤ አዎ! ታሪክ እራሷን እየደገመች ነው። ከፍተኛ መንፈሳዊ ጽጋ የነበራቸው ጀግናው እና የዋሁ ንጉሠ ነገሥት አፄ ዮሐንስ የስጋ ማንነትና ምንነት በነበራቸው በዲቃላውዳግማዊ ምንሊክ እንዴት ተከድተው፣ ተታለው እንደተገደሉ ግልጽ አድርጎ ይነግረናል።

ያኔ ገና የእርስበርስ ዕልቂት ሳይመጣ እና በኋላም ላይ ዳግማዊ ምንሊክ በባዕዳውያኑ አማካሪነት፣ እርዳታና ጥቆማ ከጣሊያን ጋር ተማክረው በአድዋ የዘር አጥፊ፣ የተፈጥሮ አውዳሚ ጦርነት ከመከፈቱ በፊት ታላቁ አፄ ዮሐንስ ለዳግማዊ ምንሊክ የሚከተልውን ብለዋቸው ነበር፤

“መቼስ አባቴ ሌላ ምን ምርጫ አለኝ? ኢትዮጵያን የሚመኛት ጠላት በበዛበት በዛሬው ወቅት እርስ-በርሳችን ጦር ከተማዘዝንለትማ፥ ደስታው የላቀ ይሆናል! የሚጠባበቀውም ይህንኑ ነውና ተወቃቅሰን መታረቁ ነው የሚበጀን፥ ‘ወንድም ወንድሙን አይበልጠው፤ ምላጭ ምላጭን አይቆርጠው’ የሚባለውስ ለዚሁ አይደለም? በሉ ተነሡ ተእኔ ይቅር ብያለሁና ይምጡ!” ሲሉ ከወለሉ ላይ ተነጥፈው የነበሩት ሁሉ ተነሡ። እጨጌው፡ መነኮሳቱና ሽማግሌዎቹ ምኒልክ ወደ ደረሱበት ሲሔዱ፡ አፄ ዮሐንስም በከፍተኛ ቅሬታ ተውጠው ሲተክዙ ቆዩና፤

“አዬ አገሬ፡ አዬ ኢትዮጵያ መች ይሆን? መኳንንቶችሽ ስለ አንች አንድነትና ክብር የሚተባበሩልሽ?” ብለው አጉረመረሙና ሲያጨበጭቡ አጋፋሪ ገቡ። “

ዛሬ ግን የዳግማዊ ምንሊክ ልጆች እስከ ሁለት ሚሊየን ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖችን ከጨፈጨፉና ካስጨፈጨፉ በኋላ፤ “ድርድር” እያሉ ሞኙን የሰሚን ሕዝብ ደግመው ደጋግመው በማታለል ላይ ይገኛሉ።

የአድዋው ድል የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ/አድዋውያን ድል እንጂ የኢትዮጵያ ነቀርሣዎች የሆኑትና የስጋ ማንነትንና ምንነትን የወረሱትየአራቱ የዳግማዊ ምንሊክ’ብሔር በሔረሰቦች’ትውልዶች፦

  • ፩ኛ. የሻዕቢያ/ህወሓት/የኢሕአዴግ/ኦነግ/ብልጽግና/ኢዜማ/አብን/ቄሮ/ፋኖ/ ትውልድ
  • ፪ኛ. የደርግ መንግስቱ ኃይለ ማርያም ትውልድ
  • ፫ኛ. የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ትውልድ
  • ፬ኛ. የአፄ ምኒልክ ፪ኛ/አቴቴ ጣይቱ ትውልድ

ድል አይደለም። ይህም እግዚአብሔር አምላክ በቪዲዮ የቀረጸው እና ዛሬ በገሃድ እየታየ ያለ ሃቅ ነው!

የአድዋን ድል ከእግዚአብሔር፣ ከቅዱስ ጊዮርጊስና ከአድዋ ሕዝብ ነጥቀህ፣ ለከሃዲዎቹ ጋላኦሮሞዎቹ ስትሰጥና ታሪካዊ ጠላት ቱርክንና አረብን ጋብዘህ የአድዋን ሕዝብ ስታስጨፈጭፍ እግዚአብሔር አምላክ ምን የሚያስብ ይመስለናል?!

የአፄ ዮሐንስ እና የንጉሥ ምኒልክ ዕርቅ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 27, 2011

*ከማሞ ውድነህ*

አፄ ዮሐንስ “ከእናንተ ቃልማ እንደምን እወጣለሁ?” ብለው ደብረ ሊባኖስ ሔደው የቤተክርስቲያኑን ሥራ እንደ ጀመሩ፥ የክርስቲያኑን ድጋፍ በይበልጥ ማግኘት ቻሉ። ያም ሁኔታ እርቁን ሊያፈጥነው ምክንያት ሆኗል። ምኒልክ አፄ ተብለው ከነገሡ በኋላ ዮሐንስ ያሠሩትን ባለ ዐሥራ ስምንት ቁንጮ ቤተክርስቲያን አስፈርሱት!

“የእስበሳችን ነገር ያለ ማክረሩ ነው የሚሻለው። ጠንካራ ክንድና ብርቱ ትኩረት የሚገባው ግን እንደ አዞ ከውሀ ውስጥ ብቅ የሚለው ነው” (አሉላ አባነጋ)

አፄ ዮሐንስ ከጉራዕ ጦርነት በኋላ ሐማሴን ውስጥ ሰነባብተው ወደ ዐደዋ ከመመለሳቸው በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ በር የተከበረና የታፈረም እንዲሆን ሲሉ ደጃዝማች ኃይሉ ተወልደ መድኅንና ራስ ባርያውን በገዥነት ሲሾሙ፡ ስመ-ጥሩውን አዋጊያቸውን ሊጋባ አሉላን በራስነት ማዕረግ አስኮፍውሰና አስጊጠው ከመረብ ማዶ ያለውን አገር በጦር አበጋዝነት እንዲጠብቁ ሾሙዋቸው።

ከዚያ በኋላም የአፄ ዮሐንስ ትልቁ የሥራ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ ማደላደልና ማለሳለስ አንድነቷን ማጽናትና ሕዝቡ ፍትሕ አግኝቶ አርሶና ነግዶ እንዲተዳደር የማድረጉ ጉዳይ ነበር።

ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉባቸው እንደሚችሉ አሥግተዋቸው ከነበሩት ሁኔታዎችም ጋር መፋጠጡን ተያያዙት። በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የውስጡን ተቀናቃኝ ቀርቶ የውጭውንም ወራሪ ጠላት ከአንዴም ሁለቴ ኃያሉ ክንዳቸውን ስለአሳረፉበት ለጊዜው ረጭ ብሎላቸዋል። በምዕራብና በመካከል ኢትዮጵያም በኩል የቤገምድር የወሎና የጐጃም ሁኔታ ጋብ ብሎላቸዋል። የጥርጣሬና የሥጋት ትኩረታቸውን የሳበባቸው ግን ሸዋ ሆነ። የወጣትነት ጓደኛቸውና ምስጢረኛቸው ምኒልክ “አፄ” ተብለው ቁጥሩ እስከ ሰባ ሺህ በሚደርስ ሠራዊት ጐልብተው፡ ከሸዋም አልፈው ወሎንና ጐጃምን ለመደረብ ከሚያስፈራሩበት ደረጃ ላይ ወጥተዋል።

አፄ ዮሐንስ ግን፡ የምኒልክን ሁኔታ አንሥተው ከመኳንንቶቻቸውና ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር በሚወያዩበት ሰዓት ሁሉ ደጋግመው የሚያነሡት ጉዳይ ነበራቸው።

“ዋናው ሥጋቱና ችግሬ የሠራዊቱ ብዛት አይደለም። ለዚህ ለዚህስ እኔም ላቅ ያለ እንጅ ከእርሱ ዝቅ ያለ ሠራዊት የለኝም። ግን እንደዚያ ማሳያ እንደሚሉት የሰይጣን መልእክተኛ የመሰለ ፈረንጅ ከአጠገቡ አስቀምጦ፡ ከነሙንዚንገር ጋርም የሚያደርገው መላላክና መስማማት ነው።

ከዚያ ሌላ ደግሞ እነዚህ ሚሲዮኖችም በዚያ በኩል ገብተዋል፡. ዋናው ዓላማቸውም ምኒልክን አሳስተውና ጦር አስመዝዘው ከኔ ጋር ለማጋጨት መሆኑን አላጣሁትም። ግዴለም የማደርገውን ዐውቃለሁ” እያሉ ዛቻ አዘልና ትካዜ-ለበስ አነጋገር ያሰሙ ነበር። እርግጥም ነው በዚያ ዘመን ፒዬር አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ የምኒልክ ባለሟል ሆኖ የእርሳቸውንም መልእክት ይዞ ወደ ግብጽና ፈረንሣይ እየሔደ ‘ዮሐንስን ለመጣል ትልቅ መሣሪያ ይሆናችኋል’ እያለ ያሽቃብጥ ነበር። ከእርሱም ሌላ ደግሞ በምሕጻረ ቃል “አባ ማስያስ” እየተባለ የሚጠራው ሎሬንዞ ጉልየሞ ማሳያ የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮን አባል በሸዋና በከፋ ውስጥ ድርጅቱን አቋቁሞ የምኒልክን ባለሟልነትም አትርፎ ከሚሲዮናዊነቱ ይልቅ በዲፕሎማቲክና በስለላው ሙያ ተሠማርቶ ዮሐንስንና ምኒልክን ለማራራቅና ለማጋጨት በመካከላቸው ገብቶ ነበር።

እነዚሁ ሁለቱ አውሮጳውያን የምኒልክን ጉልበት ከዮሐንስ ጉልበት የጠነከረ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ሲከታተሉት የነበሩት ዮሐንስም ክንዳቸውን በቀላሉ የማይታጠፍ ለማድረግና ምኒልክንም ለማስገበር ሲሉ የሠራዊታቸውን ቁጥር እስከ አንድ መቶ ሺህ ከአደረሱት በኋላ፥ ክዚሁ ውስጥ እስከ ዐርባ ሰባት ሺህ የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አስታጠቁት። ከጉንደትና ጉራዕ ጦርነቶች የተገኘው ቀላል መካከለኛና ከባድ መሣሪያም የበላይነታቸውን ያረጋገጡበት ዋናው ትጥቃቸው ነበር።

በዮሐንስ ቤተ መንግሥት እንደአባት ይታዩ የንበሩት ራስ አርአያም በበኩላቸው፤ “የሁለት ወንድማማች ጠብ ማንን ጐድቶ ማንን ይጠቅም ይመስላችሁ? ኢትዮጵያን እኮ ነው የሚያዳክማት!

ኢትዮጵያን እኮነው የሚያሳንሳት! ኢትዮጵያን እኮ ነው የጠላቶቿ መሳቂያ የሚያደርጋት! ታሪክ ይወቅሰናል፤ ትውልድ ያፍርብናል፤ ታቦትና መስቀል አስይዘን ካህናትን ወደ ምኒልክ እንስደድ እንጂ ጦር መምዘዙን አልስማማበትም” እያሉ የእህታቸውን ልጅ ከነጦር አበጋዞቻቸው ይቆጡ ነበር።

አፄ ዮሐንስ “ከእናንተ ቃልማ እንደምን እወጣለሁ?” ብለው ደብረ ሊባኖስ ሔደው የቤተክርስቲያኑን ሥራ እንደ ጀመሩ፥ የክርስቲያኑን ድጋፍ በይበልጥ ማግኘት ቻሉ። ያም ሁኔታ እርቁን ሊያፈጥነው ምክንያት ሆኗል። ምኒልክ አፄ ተብለው ከነገሡ በኋላ ዮሐንስ ያሠሩትን ባለ ዐሥራ ስምንት ቁንጮ ቤተክርስቲያን አስፈርስው ሌላ ለማሠራት ሦስት ወራት ሙሉ ታግለውበታል።

ከሰነባበቱማ ሌላም ይሠራሉና ይገብሩላቸው ፈቅደናል” እያሉ ምኒልክን ወጥረው ያዙ። የተደረገው ጥረት ሁሉ ለፍሬ በመብቃቱ ሁለቱ ተፎካካሪዎችም ለእርቁ ፈቃደኞች በመሆናቸው ንጉሥ ምኒልክ ወደ ሰላሌ ሔደው ከአፄ ዮሐንስ ሠፈር ተዳረሱ፤ አፄ ዮሐንስም ሠፈራቸውን አሳምረው ድግሳቸውን አዘጋጅተው ሲጠባበቁ ነበርና የምኒልክ መቃረብ እንደ ተሰማ እጨጌው መነኮሳቱንና ካህናቱን አሰልፈው ወደ አፄ ዮሐንስ ድንኳን ገብተው፤

“ጃንሆይ ለታቦተ ጽዮን ሲሉ ለኢትዮጵያ አንድነትና ነጻነት ሲሉ ወንድምዎን ምኒልክን ይቅር እንዲሉልን በራሷ በኢትዮጵያ ስም እንለምንዎታለን!” ብለው እጨጌው ጐንበስ ሲሉ አብረዋቸው የነበሩት መነኮሳትና ካህናት ከወለሉ ላይ ተነጠፉ።

“መቼስ አባቴ ሌላ ምን ምርጫ አለኝ? ኢትዮጵያን የሚመኛት ጠላት በበዛበት በዛሬው ወቅት እርስ-በርሳችን ጦር ከተማዘዝንለትማ፥ ደስታው የላቀ ይሆናል! የሚጠባበቀውም ይህንኑ ነውና ተወቃቅሰን መታረቁ ነው የሚበጀን፥ ‘ወንድም ወንድሙን አይበልጠው፤ ምላጭ ምላጭን አይቆርጠው’ የሚባለውስ ለዚሁ አይደለም? በሉ ተነሡ ተእኔ ይቅር ብያለሁና ይምጡ!” ሲሉ ከወለሉ ላይ ተነጥፈው የነበሩት ሁሉ ተነሡ። እጨጌው፡ መነኮሳቱና ሽማግሌዎቹ ምኒልክ ወደ ደረሱበት ሲሔዱ፡ አፄ ዮሐንስም በከፍተኛ ቅሬታ ተውጠው ሲተክዙ ቆዩና፤

“አዬ አገሬ፡ አዬ ኢትዮጵያ መች ይሆን? መኳንንቶችሽ ስለ አንች አንድነትና ክብር የሚተባበሩልሽ?” ብለው አጉረመረሙና ሲያጨበጭቡ አጋፋሪ ገቡ።

“መኳንንቱን አስገባ” አሉና አዘዙ። አጋፋሪ መኳንንቱንና የጦር አለቆቹን ተራ በተራ እያስገቡ እንደ

የማዕረጋቸው አስቀመጡዋቸው። “ያው እንደምታውቁትና እንዳሰባችሁበት ከወንድሜና ከወንድማችሁ ከምኒልክ ጋር መታረቃችን ነውና ጦሩም በየመንደሩና በየቤቱ እየገባ እንዳይዘርፍ ከልክያለሁ። የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኖ አሥግቶ የነበረው ክፉ ነገር በሰላም የሚያልቅ ስለሆነ ከሠራዊቱ ገሚሱ ወደየመጣበት ይመለስ” ብለው እያንዳንዳቸውን እያተኮሩ ተመለካከቷቸው። ሁሉም ፈገግታና የስምምነት ስሜት አሳዩዋቸው።

ራስ አርአያም ቀልጥፈው ተነሡና፤ “የወንድማማቾች ደም በከንቱ እንዳይፈስና በትውልድ መካከል ቂም በቀል እንዳይመሠረት በእያንዳንዳችን ላይ አድሮብን የነበረው ጭንቀት ይህ ነው አይባልም ነበር። የአባቶቻችን ጸሎትና ድካም ረድቶን ግን ከእርቅ ላይ ደርሰናል። እንግዲህ እርቃችን ዘላቂ እንዲሆን ሁላችሁም ከልባችሁ አስቡበት” ብለው ተቀመጡ።

“አዎ ይገባል፤ አገር ያለፍቅር ሠራዊት ያለ አንድነት ንጉሥም ያለ መካርና ተቆጭ በነጻነት ውለው ለማደር አይቻላቸውምና የኢትዮጵያ ትልቅነትና አንድነት ጸንቶ የሚኖረው በዚሁ ዓላማ ነውና የዛሬውም እርቅ የሁላችን ደስታ ነው” አሉ ራስ አሉላም።

ምኒልክ አብዛኛውን ሠራዊታቸውን ራቅ አድርገው አሥፍረው በመጠነኛ ወታደሮች ብቻ ታጅበው በወርቅ መረሸት በተጫነች ስናር በቅሎዋቸው ተቀምጠው አጐታቸውን ራስ ዳርጌን አስከትለው ወደ አፄ ዮሐንስ ሠፈር ሲቃረቡ፥ በራስ አርአያ ድምፁ መሪነት በሰልፍ የወጡት የአፄ ዮሐንስ መኳንንት የእንግት ጠመንጃ ጠመንጃቸውን በየትከሻቸው ተሸክመው እጅ እየነሡ ተቀበሉዋቸው። ምኒልክና ራስ ዳርጌም ከየበቅሎዎቻቸው እየወረዱ ተሳሳሙ። በተለይም ራስ ዳርጌ ከመቅደላው ጓደኛቸው ከራስ አርአያ ጋር ተቃቅፈው ደስታና ናፍቆት ባጥለቀለቀው ስሜት ተሳሳሙ።

ከዚያ በኋላ ጉዞው ወደፊት ቀጠለና ከአፄ ዮሐንስ ድንኳን አጠገብ ሲደርስ ምኒልክ ከበቅሎዋቸው ወርደው ወደ አፄ ዮሐንስ ድንኳን በራፍ ሲደርሱ እጨጌ የሰጡዋቸውን ድቡልቡል ድንጋይ ተቀብለው ከትከሻቸው ላይ ጣል አድርገው ከአፄ ዮሐንስ ዙፋን ፊት ጐንበስ ብለው፤

“ጃንሆይ! ባጠፋሁ ይማሩኝ” አሉ። አፄ ዮሐንስም ከዙፋናቸው ተነሥተው፤ “ለእግዚአብሔር ስል፡ ጠላት ባሰፈሰፈባት ኢትዮጵያ ስል ይቅር ብያለሁ። እስዎም ይቅር ይበሉኝ” ብለው ጐንበስ ሲሉ እጨጌ ጠጋ ብለው ምኒልክ የተሸከሙትን ድንጊያ ተቀብለው ለአሽከር ከሰጡ በኋላ፥ ጸሎት አድርገው ሲያበቁ ሁለቱንም ተፎካካሪዎች አሳሳሙዋቸው።

አፄ ዮሐንስ ከዙፋናቸው እንደ ተቀመጡ ምኒልክም በስተቀኝ ከተዘጋጀው አልጋ እንዲቀመጡ አዘዙ።

እጨጌውና መኳንንቱም እንደየማዕረጋቸው ተቀመጡ።

“አብረን እንዳልኖርን፥ አብረን እንዳልበላን አብረን ብዙ ብዙ እንዳልተጫወትን ሰይጣን በመካከላችን ገብቶ እኛን አሳስቶ ሕዝብ ሊያጨራርስ ጠንስሶት የነበረው አሳዛኝና አሳፋሪም ነገር ከሽፎ ለዚህ ለእውነተኛው ፍቅርና ወንድማማችነት በመብቃታችን ከልብ ተደስቻለሁ። ከእንግዲህም ቢሆን ክፉ ሐሳብና ክፉ ነገር በመካከላችን እንዳይገባ መጠንቀቅ አለብን” አሉ፡ አፄ ዮሐንስ ምኒልክንና የሁለታቸውንም አጎቶች ተራ በተራ እየተመለከቱ።

“አዎ ጃንሆይ!” ብለው ምኒልክም እጨጌውንና መኳንንቱን ቃኝተው ፊታቸውን ወደ አፄ ዮሐንስ መለስ አደረጉና፤ “አዎ ጃንሆይ ጐንደር ሳለነ ስለሁለታችን ወንድምነትና ስለ አገራችንም ትልቅነት ያ- ሁሉ ምሥጢር በመካከላችን እንዳልነበረ ሁል፥ ለአስነዋሪ ነገር ትውልድ ለሚያፍርበት ሥራ መሰላለፋችን ቀርቶ ዛሬ ለዚህ ድልና ኅብረት በመድረሳችን ደስታው የመላው ያገሩ ደስታ ነው። ለወደፊቱም ቢሆን እንደዚሁ እንዲቀጥል እኔም ሆንኩ መኳንንቱና ካህናቱ ልንደክምበት የሚገባን ጉዳይ ነው” አሉ።

እጨጌም ከወንበራቸው ተነስተው ከሁለቱ ነገሥታት ፊት ቆሙና፥ ወንጌል አስመጥተው ከሁለቱ ፊት

አስቀምጠው፤ “ከዛሬ ጀምሮ ንጉሥ ምኒልክ ‘የሸዋ ንጉሥ’ እንጂ ንጉሠ ነገሥት እየተባሉ ላይገዙ ላይነዱ፤ በየዓመቱም ለጃንሆይ ግምጃ ቤት ሊዘጉ፥ የገቡትንም ሚሲዮኖች ሊያስወጡ፥ የጃንሆይ ሠራዊት እርዳታ በጠየቀ ጊዜ ሊረዱና የሚገባዎን ሊያደርጉ፥ ንጉሥ ምኒልክ ተስማምተው የለም?” ብለው ጠየቁ።

“አዎ አባቴ! ቃልዎ ይድረሰኝ” አሉ ምኒልክ። እጨጌም ወደ አፄ ዮሐንስ መለስ ብለው፤

“ጃንሆይም በበኩልዎ ያለ ንጉሥ ምኒልክ ሸዋ ሌላ ንጉሥ እንደማይሾምባት ወሎንም በበላይነት ምኒልክ ሊያዙባት፥ ንጉሥ ምኒልክም ጠላት ቢመጣባቸው ሠራዊት ልከው ወንድምዎን ሊረዱ ተስማምተው የለም?” ብለው ጠየቋቸው።

“አዎን አባቴ! ቃልዎ ይድረሰኝ” አሉ ዮሐንስ። ከዚህ ውል በኋላ ሁለቱንም አስምለው ነገሩን ከጨረሱ በኋላ ጸሎት አድርሰው ተቀመጡ።

ቀጥሎ ዮሐንስና ምኒልክ ከነመኳንንቶቻቸው፥ እንደዚሁም የሁለቱም ወገን ሠራዊት ግብር ገባ። የሁለቱም ሠራዊት ለእርስ በእርስ መገዳደያ ጠመንጃውን ሁሉ አጉርሶት የነበረውን ጥይት ለደስ-ደሱ ሲያንጣጣው ዋለ።

የስላሴ ሜዳም የሰላም የወንድማማችነት የፈንጠዝያ ሜዳ ሁና ሰነበተች። ካሣና ምኒልክ በጐንደር ቤተ

መንግሥት በነበሩበት ጊዜ ያሳለፉትን የወንድማማችነት ትዝታ እያነሡ ሲጨዋወቱ ውለው አደሩ። የሁለቱ መፋቀር እጅግ ያስደሰታቸው እጨጌ ቴዎፍሎስም በዚያ አጋጣሚ የነበረባቸውን የሃይማኖት ጣጣ መፍትሔ ሊያሰጡት ፈልጉና፤

“ከቅባቶችና ከጸጐች እንደዚሁም ከሚሲዮኖቹ ጋር ያለን ችግር ታይቶ አንድ እልባት እንዲደረግበት ይጠይቁልኝ። ከእነርሱ ሌላ ደግሞ ሐጅ አማን የተባለ የዐረብ ሀብታም ነጋዴ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ በርካታ ገንዘብም እየበተነ፥ “ሁሉም ሰው እስላም ካልሆነ ወዮለት!” እያለ እያስፈራራም ሃይማኖታችንን ሊያጠፋብን ተነሥቶብናልና ተይዞ እንዲመጣና እንዲጠየቅልን በቤተክርስቲያናችን ስም እለምናለሁ” ብለው አመለከቱ።

በዚህ ጊዜም ራስ አርአያ ነገሩን ቀበል አድርገው፤ “አባታችን ያነሡት ጉዳይ በዋዛ የሚታለፍ አይደለም። ግን የሃይማኖታችን ነገር እዚህ እንዳለን አይተን አንጨርሰውምና ይቅረቡልን የምትሏቸው ሁሉ ተጠርተው እስቲመጡ ሠራዊቱም አገሩም ይቸገሩብናልና ቀን ተቆርጦ ወይ ወሎ ላይ ያለዚያም ጐንደር ላይ ቢታይ ይሻላል” ብለው አሳሰቡ።

አፄ ዮሐንስ በመሐል ኢትዮጵያ ሆነው በሰሜን፥ በምዕራብ፥ በደቡብና በምሥራቅ አቅጣጫዎች የነበረውን የሀገሪቱን ሁኔታ በማዳመጥ ላይ እንዳሉ ንጉሥ ምኒልክና ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት በግንቦት ወር 1874 ዓመተ ምሕረት እምባቦ ላይ መዋጋታቸውንና ለምኒልክ ጉልበት ተፎካካሪ እንዲሆኑላቸው ሲያጐለብቱዋቸው የነበሩት ተክለ ሃይማኖት መማረካቸውን ሲሰሙ ምርር ብለው አዘኑ።

“ምን ይደረግ! ከባዕድ ጋር ገጥመው እንደኔ አልተሰቃዩ! የኢትዮጵያ ጉዳይ አያሳሰባቸው! እርስ በርስ

ሕዝብ ያፋጁ እንጂ?” ብለውም ምሬታቸውን ሰነዘሩ። ሁለቱ ንጉሦች የተዋጉበትን ምክንያት ለማወቅና

ቀጥተው ለማስታረቅ፥ እንደዚሁም በሸዋ የነበሩም ሚሲዮናውያንና በየቦታው የነበሩትም የጸጋ ሃይማኖት አማኞች ወሎ ድረስ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላለፉ።

በዚሁም መሠረት ምኒልክም ምርኮኛቸውን ይዘው በነሐሴ ወር 1874 ዓ.ም. ወሎ ተሻገሩ። ሚሲዮኛውያኑና የጸጋ ሃይማኖት ተከታታዮችም በዚሁ ጊዜ ነበር የተሰበሰቡት። ሁለቱ ንጉሦች ማለት ንጉሥ ምኒልክና ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ከንጉሠ ነገሥቱ ችሎት እንደቀረቡ፤

“የተጣላችሁትና ከግራ ቀኛችሁም ብዙ ሰው ያለቀው በግዛት ገፋኽኝ ገፋኽኝ የተነሣ ነው። የቸገረን ፍቅርና ሰላም አንተ ትብስ አንተ ትብስ መባባል እንጂ አገራችን ሰፊ ናት። ግን እርሷንም በሚመኙዋት ጠላቶች ለማስደፈር እርስ በእርሳችን እየተፋጀንላት ነው። የግብጥ ጦር ሁለት ጊዜ ሲመጣብኝ ወንድሞቼ ናቸውና የኢትዮጵያም ጠላት ጠላታቸው ነውና ‘ድረሱልኝ እርዱኝ’ ብዬ ብልክባቸው ችላ ብላችሁ ቀራችሁ። ያን ጊዜ እናንተን እወጋለሁ ብዬ ጦሬን ወደ እናንተ አዙሬው ቢሆን ኖሮ ግብጥም ገብቶ ይህን ጊዜ ተደላድሎ ነበር።

ጠላታችንን ድል ያደረገው ሠራዊቱም ከወንድሞቹ ጋር ተዋግቶ እጥፍ ድርብ ጉዳት በደረሰብን ነበር። የእናንተን ቸልተኝነት በትዕግሥት በማሳለፌ ግን ያን የመሰለ ድል ለሀገራችን አስገኘሁ። መቼም ያለፈው አለፈ፥ ለወደፊቱ ግን የአንድነታችንን ነገር አደራ! አስቡበት። በሉ አሁንም ሁለታችሁ ከልብ ታረቁልኝ” ብለው ከተቀመጡበት ተነሥተው ሁለቱን “ይቅር ይቅር” አባብለው አስታረቁዋቸው።

ቀጠል አድርገውም፤ “ስለ አገሩ ድልድል ጉዳይ የሆነ እንደሆነ ወሎ ከሁለት ተከፍሎ ገሚሱ ለራስ አርአያ፥ ገሚሱ ለራስ ሚካኤል እንዲሰጥ ይሁን። ሰባት ቤት አገው ምድርም ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት ተወስዶ ለራስ መንገሻ ዮሐንስ እንዲደረብለት፥ ንጉሥ ምኒልክ ከንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የማረኩትን የጦር መሣሪያ ለራስ አሉላ እንዲያስረክቡ አዝዣለሁ። እንግዲህ በዚህ ነገር ቅር የሚላችሁ ነገር ቢኖር ንገሩኝ” አሉና ግራ ቀኙንም ተመለከቱዋቸው።

ንጉሠ ምኒልክም ተነሡና፤

“ጃንሆይ! የግብጥ ጦር መጥቶብኛልና ድረሱልኝ ብለው ሲልኩብኝ ያለመምጣቴ በሐረርጌ በኩል ያለው ጠላት ወደ መሐል አገር እንዳይገባ ሠግቼ ነው። ሆኖም ከሸዋ በርካታ ጦር ሰድኛለሁ። አሁንም ከፈቀዱልኝና መሣሪያ ካገኘሁ ወደ ምሥራቅና ደቡብ እየሔድኩ አስገብራለሁ” ብለው ምርኮኛቸውን ራስ አዳልን ተመለካከቱና፤

“እኔና ጌታ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት በመዋጋታችንም አዎን ጥፋት ሠርተናል። አስቀድሞ ግን እባክዎ አንተላለቅ እጅዎን ይስጡኝ ብዬ ልኬ ነበር። ጠቡንም ፈልገው የተነሡት እሳቸው ናቸው። ቆስለውም እንደ ተማረኩ ቁስላቸውን ራሴ እያጠብኩ ከጐኔ ሳይለዩ ከክብራቸው ዝቅ ሳይሉ በክብርና በወንድምነት ጠብቄ ይኽው አምጥቻለሁ” ብለው አመለከቱ።

አፄ ዮሐንስም፤

“ወንድሜ ወዳጄ ምኒልክ ለእኔና ለአንተ ፍቅርና ወንድማማችነት፥ ለአንድነታችን ማጠናከሪያ እንዲሆንልን ልጅህን ዘውዲቱን ለልጄ ለአርአያ ሥላሴ ስጥልኝ” ብለው ነጉሠ ነገሥቱ ዘውድ ጭነው ‘ንጉሠ ሸዋ’ ካሉዋቸው ምኒልክ ፊት ጐንበስ አሉ።

“እህ?” አሉና ምኒልክ እንደ መደንገጥም ብለው ከፊታቸው ከአጎነበሱት ንጉሠ ነገሥት ላይ አፍጥጠው ቆዩና መኳንንቱን ገለማምጠው፡ “እህ? ልጅቱ የስድስት ዓመት ሕፃን ናት፥ አልደረሰችም እንጂ ምን ከፋኝ? ጋብቻው ግን ያማረ ነው” ብለው ሲሉ፤

“የንጉሥ ልጅ ባንቀልባ በማደጎም ይሔዳል ግዴለም! እኔም አባቷ ነኝ ፍቀድልኝ” አሉ ንጉሠ ነገሥቱም። “መቼስ ልጅህን ለልጄ ብሎ መጠየቅ በጃንሆይ አልተጀመረም፥ የቆየ ያባቶቻችን ወግና ሥርዓት ነውና እሽ እንጂ! ከኔ አብራክ ብትገኝም የጃንሆይስ ልጅ አይደለች?” ብለው ፈቀዱ።

“እግዚአብሔር ያክብርልኝ! ሸዋ ድረስ መጥቶ ለምን አልለመነኝም ብለህ እንደማትከፋብኝ እተማመናለሁ” ብለው አፄ ዮሐንስ ሲቀመጡ፥ ከኋላቸው ቁመው የነበሩት እነ ራስ አሉላም የምኒልክን ጫማ እየሳሙ ተቀመጡ። አጋፋሪውም ከዚያ ቀጠል አድርገው ደግሞ ወደ አፄ ዮሐንስ ጠጋ ብለው፡

“ጃንሆይ የሸዋው ንጉሥ ባሉበት እናያቸዋለን ብለው ያዘዙኝን ጉዳዮች አሁን ላቅርባቸው?” ብለው አመለከቱ። “ማለፊያ ነው፤ መልካም አድርገሃል፤ እንግዲያ የቀሩትንም መኳንንትና ነገር ዐዋቂዎች አስጠራና ሁሉም ባሉበት ይሰማ” ብለው አዘዙ።ዕጨጌም ቀጠል አድርገው ተነሡና፤

“ጃንሆይ! የዛሬዋ ቀን የተባረከች የተቀደሰች ናት። እንደምን ቢሉ? ታላቅ እርቀ-ሰላም የወረደባት ታላቅ ጋብቻ የተመሠረተባት የሸዋው፡ የወሎው፥ የጐጃሙ፥ የቤጌምድሩና የሐማሴኑ መኳንንት የተገናኛችሁበት ስለሆነች ነው። ነገር ግን ሀገሩን የሚያበጣብጠው የሃይማኖቱ ነገርም ዛሬ ከፊታችሁ ቀርቦ እንዲታይና እንዲያልቅለት ስለተስማማን፥ ንጉሥ ምኒልክም ሚሲዮኖቹን ይዘው ስለመጡ ሁሉም ከዙፋንዎ እንዲቀርቡና ነገራቸውን እንዲያሰሙ እለምናለሁ” ብለው ሲያመለክቱ፥ መኳንንቱ ሁሉ እርሱ በርስ ተያዩና የስምምነት ምልክት አሳዩ።

አፄ ዮሐንስም ወደ ንጉሥ ምኒልክ ዘወር ብለው፤

“በኔ በኩል አባታችን እንደ ተናገሩት ቢያልቅ እስማማለሁ፥ ምን ይመስልሃል?” ብለው ጠየቋቸው።

“ይሁን እንጂ ማለፊያ ነው፥ ነገሩ ይታይ” ሲሉ ምኒልክ፡ አፄ ዮሐንስ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው፤

“ አዎ እውነትዎን ነው። በአገራችን ውስጥ ‘ተዋህዶ፡ ጸጋ ቀባት’ እያሉ ካህናቱ ሕዝቡን እሱ በሱ

ያዋክቡታል። ከውጭ ደግሞ የሚሲዮን ዘመሚት ገብቶ ያገሬን ሕዝብ ያተረማምሰዋል። እኔ እማውቀው አንድ አምላክና እንዲት ኢትዮጵያን ነው። ሕዝቤን የሚለይብኝና አገሬን የሚያደክምብኝ ሃይማኖት አልፈቅድም።

እንግዲህ ሁሉም ይምጡና ጣጣው ይለቅለት” ሲሉ ከንጉሥ ምኒልክ ጀምሮ ብችሎቱ የነበረው መኳንንትና ካህናት ሁሉ ተስማማ። ዕጨጌው ቀጠል አድርገው፤ “እንግዲህ የሚሲዮኖች አለቆች ይቅረቡልኝ” ብለው አመለከቱ። “ማለፊያ ነው ይቅረቡ” ብለው አፄ ዮሐንስ ለአጋፋኢ ትእዛዝ ሰጡና እንደገና ወደ እጨጌ መለስ ብለው፤

“ለመሆኑስ ከሚሲዮኖቹ ከዋና ዋናዎቹ እነማን መጥተዋል?” ብለው ጠየቁ።

“መቼስ ጃንሆይ የሚሲዮኖቹ ዋናውም አድራጊ ፈጣሪውም አባ ማስያስ ነው እርሱም ከነሰዎቹ ንጉሥ ምኒልክን ተከትሎ መጥቷል አሉ ዕጨጌ።

“አዎ መቼ አጣሁት? ዋናው አተራማሽ እሱ አይደል? ከሱዳን ጠረፍ እስከ ሸዋ አገሬን ሰላምና ጤና የነሣት እሱ አይደለም? እርስዎስ ነገርዎን በሚገባ አጠናቅረው የለም?” ብለው አፄ ዮሐንስ ዕጨጌን ጠየቁ።

ዕጨጌው እጅ ነሡና፤

“ጃንሆይ!’ነገር ከሥሩ ውሃ ከጥሩ’ እንዲሉ የሚሲዮኖችን ጉዳይ ከሥሩ ጀምሬ ላመጣው ነውና ልብ ብላችሁ አድምጡኝ፤ ጥንት በአባቶችዎ ዘመን እንደዛሬዎቹ ሁሉ እነ አባ ሜንዶዝ፥ እነ አባ አልፎንሱ እነ ፓኤዝ በሃይማኖት ምክንያት ወደ አገራችን ገብተው፡ የውጭ ጠላት ለማስገባት፡ ሕዝቡን እሱ በሱ ለማበጣበጥ ብዙ ብዙ የተንኮል ሥራ በመሥራታቸው አፄ ፋሲል ሁሉንም ሰብስበው በምጥዋ በኩል ወደ አገራቸው እንዲሔዱ አዘዙ። ሜንዶዝ ግን ሐማሴን ሲደርስ “አመመኝ” ብሎ ቀርቶ የቅባቶችንና የጸጎችን ሃይማኖት ከርሱ ሃይማኖት ጋር አመሳስሎ “ክርስቶስ በቅብዓተ መንፈስ ቅዱስ ከብሮ አንደኛ የጸጋ ልጅ ሆነ” ብሎ በግልጽ አስተማረ። ካስተማረም በኋላ ወደ ሀገሩ ሲሔድ “ለኢትዮጵያ ሁለት እሾህ ትክዬባታለሁ፥ ብባረርም አይቆጨኝም” ብሎ ወጣ።

ከእርሱም በኋላ አባ ያዕቆብ የተባለ ተንኮለኛ በምጥዋ በኩል ገብቶ እስከ ጐንደር ዘልቆ የሜንዶዝን ትምህርት ማስፋፋት በመጀመሩና ሀገሪቱንም ሰላም በመንሣቱ አፄ ቶዎድሮስ ነቅተውበት፡ “ያገሬን ሕዝብ የሚለያይና ለጠላት አሳልፎ የሚሰጥ ሃይማኖት አልፈልግም” ብለው ሰባኪውን አባ ያዕቆብን በምጥዋ በኩል አባረውታል።

እነዚህም ሰዎች ‘ወንጌል እናስተምራለን፥ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እንናገራለን’ ብለው ወደ አገርዎ ከገቡ ዓመታት ሆኗቸዋል። ዳሩ ግን ከወንጌል አስተማሪነታቸው ይልቅ የወንጌል በራዥነታቸው አመዝኖ ይገኛል። ለማስረጃም ያህል የደንከልን የባሕር በር ለሃይማኖታዊ ሥራ ነው ብለው ባላባቱን አታለው ከገዚ በኋላ፤ በመጀመሪያ ለጣሊያን የንግድ ኩባንያ፥ ቀጥለው ለመንግሥት ሰጥተዋል። ከረንም ውስጥ የትንባሆ እርሻ አስፋፍተው ሕዝቡን የትንባሆ ሱሰኛ አድርገውታል።

ከዚህም አልፈው ተርፈው ከእስክንድርያ ጳጳስ እንዳናስመጣ፥ ኢትዮጵያ በውጭ ጠላት እንድትወረር፥

ከአንዳንድ የባዕድ መንግሥታት ጋር ሲጻጻፉ ሲያደፋፍሩ እንደ ኖሩ አረጋግጫለሁና ሕዝብዎንና አገርዎን ወደ ብርቱ ፈተና ከመጣላቸው በፊት አባቶችዎ እንዳደረጉት ካገራችን እንዲባረሩልን ፍርድ እጠይቃለሁ” አሉ።

በዚህም አነጋገራቸው ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ መኳንንቱና ካህናቱ የረካበት በመሆኑ አድናቆቱን በሳቅና

በመጠቃቀስ ገለጸላቸው። አፄ ዮሐንስ ከንጉሥ ምኒልክ ጋር በቀስታ ተነጋገሩና ወደ ተከሳሾቹ ዘወር ብለው፤

“በሉዋ መልሱላቸው፤ አባታችን የተናገሩትን ሁሉ ታምናላችሁ? ትክዳላችሁ?” ብለው ጠየቁዋቸው። ተከሳሾቹ ከዕጨጌ ጀምረው ችሎቱን ገለማመጡትና፤ “እኛ ወደ አገርዎ የመጣነው በሀገርዎ ውስጥ የሚኖሩትን አይሁድና እስላሞች የክርስቶስን ትምህርት አስተምረን ወደ ክርስትና ሃይማኖት ለመመለስ ከአውሮፓ መንግሥታትም ጋር አስተዋውቀንዎና አቀራርበንዎ የጸና ወዳጅነት እንዲመሠርቱ ለማድረግ ነው” አሉና አባ ማስያስ መልስ ሰጡ።

“አሁንኮ አባታችን ያቀረቡልዎ ክስ የደንከልን በር ለሃይማኖት ተግባር ነው ብላችሁ ከገዛችሁ በኋላ ለንግድ ሥራና ለመንግሥት መገልገያ እንዲሆን አደረጋችሁ፤ የትንባሆ ነገር በሕዝቡ ዘንድ እንዲለመድ አድርጋችኋል ነውና ለዚህ መልስ ይስጡ” ብለው ጠየቋቸው።

አባ ማስያስ በጸጉር የተሸፈነ የዱር ድመት የመሰለ ፊታቸውን ወደ ዕጨጌው ዘወር አድርገው፤

“እሳቸውኮ እኛን በሆነ ባልሆነ የሚወነጅሉን አገራችሁ ከአውሮፓ መንግሥታት ጋር ተወዳጅታ በጥበብ እንዳትኮራ እንደ እነርሱ በመሳሰሉ ከእስክንድርያ በሚላኩ ሰባኪዎች አማካይነት አገራችሁ የግብጽ ጥገኛ ሆና እንድትኖር ከግብጽም ፈቃድ እንዳትወጣባቸው፡ በዚህ አገሩ የሚኖሩ እስላሞች ክርስቲያይኖች እንዳይሆኑባቸው የግብጽ ከዲብ ባለሟልነት እንዳይቀርባቸው ብለው ነው” ብለው ሲሳለቁ ዕጨጌውን ቁጣ ቱግ አድርጎ አስቆጣቸውና፤

“ስሙ ወይ ማስያስ! ማንነትዎንኮ አሳምሬ ደርሼበታለሁ! የጣሊያኑ ንጉሥ ነፍስ አባት አይደሉም? ይህን ያምናሉ? ወይስ ይክዱኛል?” ብለው አፈጠጡባቸው። “ይኽ ነገር እውነት ነው?” ብለው ዮሐንስም ተጨመሩ። የችሎቱ ፍጥጫ ከአባ ማስያስ ላይ ተከመረ። “ብሆንስ ምንድነው ነውሩና ጥፋቱ?” አሉና አባ አንገታቸውን ደፉ።

“ነውሩና ጥፋቱማ” ብለው እጨጌም አባን ገለማምጠው፡ የችሎቱንም ሁኔታ ቃኝተው ክርክራቸውን

ቀጠሉበት። “ነውሩና ጥፋቱማ እንደ አባትነትዎ ከንጉሥዎ አጠገብ ሆነው መምከርና ማስተማር ሲገባዎ በወንጌል ስም፡ በክርስቶስ ስም ከሰው አገር ገብተው ሃይማኖት እየበረዙ ወንድምና ወንድም ለማፋጀት ተንኮል እየሠሩ መገኘትዎ ነው” ብለው ሲመልሱላቸው ችሎቱ “ይበል ይበል” ብሎ አስተጋባላቸው።

አፄ ዮሐንስ አንገታቸውን አቀርቅረው ሲተክዙ ቆዩና በሆዳቸው ውስጥ ሲጤስ የነበረውን ንዴት ደጋግመው በመተንፈስ ካስወጡት በኋላ፤ “እኮ ለዚህስ የሚሰጡት ምላሽ አለዎት?” ብለው ጠየቋቸው የዐይኖቻቸውን ቅንድቦች ዘግተው። “የንጉሥ ነፍስ አባትነት ከሀገራቸው ወጥታችሁ አታስተምሩ ብሎ አይከለከልም፡ እርሳቸውስ የከዲቡ” ብለው ተናግረው ሳይጨርሱ እጨጌ አቋረጧቸውና፤

“ጃንሆይ! በዚህ ችሎት የምትገኙ መኳንንትና ሊቃውንት! ልብ በሉልኝ! ‘ስሱ ሲበላ ይታነቃል! ሐሰተኛ በአነጋገሩ ይታወቃል እንዲሉ፥ የግብጽን ጦርና የመኳንንት ወስላቶች የምትረዱስ እናንተ አይደላችሁም? እውነተኞቹ የወንጌል ሰባኪዎች ከሆናችሁ ቀደም ሲል የቱርክ ጦር ዛሬም ግብጾች ክርስቲያኑን ሁሉ “እስላም ካልሆንክ” እያሉ ሲያስጨንቁት ለምን አልገላገላችሁም?” ብለው አንገታቸውን አሰገጉባቸው።

“እኮ? የደንከልን የባሕር በርስ ለንግድና ለወታደር ተግባር እንዲውል አሳልፋችሁ አልሰጣችሁም? የትንባሆ ዘርስ በእርሻ ላይ እየዘራችሁ ሕዝቡን እያስለመዳችሁት አይደለም? ለግብጥ ጦርና እኔን ካሎረፉ ወስላቶችስ ጥግና ጋሻ ሁናችሁ የለም? ይህን ሁሉ ታምናላችሁ? ትክዳላችሁ?” ብለው አፄ ዮሐንስም ቁጣና ፍጥጫ ጨመሩበት።

“ጃንሆይ!” አሉና አባ ማስያስ መኳንንቱን ጭምር በአስተያየታቸው እንደ መለማመጥ ብለው፤ “ጃንሆይ! ይህን ሁሉ ነገር አንዳንድ ሚሲዮናውያን በስሕተት ሠርተውት ይሆናል። ግን ዋናው የመጣንበቱ ጉዳይ ቅድም እንደ ተናገርኩት፡ አይሁዳውያንና እስላሞችን ወንጌል ለማስተማር ጥበብ ለማስፋፋት ነው” ብለው እንደለመዱት አንገታቸውን ቆለመሙት።

በዚያ አነጋገራቸው፡ ከንጉሠ ነገሥቱ ጀምሮ ሁሉም የሰላቅ ሳቅ ሲያሳዩዋቸው የወሎው ባላባት ይማሙ

ሙሐመድ አሊ ተነሡና፤ “ስሙኝ ወይ አባ?” ‘አፍ ያበዛ ጥበቡ ዋዛ’ እንዲሉ እስከ ዛሬ የአፋችሁን እንጂ የእጃችሁን ጥበብኮ አላየነውም?’ ብለው በተራቸው ከአባው ላይ አፈጠጡ። አባ ቀና ብለው ጠያቂውን ለማወቅ ዐይኖቻቸውን ተከሉባቸው። ነጭ በነጭ የተጎናጸፉ፥ ነጭ የጠመጠሙ ዐይነ- ፈጣጣ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ተጠሪ የሆኑ አዛውንት ከዮሐንስ በስተኋላ ተጎብረው በማየታቸው ተገረሙ።

“ለመሐመድ ተከታዮች ቁርዓንን ማስተማር ተገቢ እንደሆነ ሁሉ፡ ለክርስቶስ ተከታዮችም ወንጌልን

ማስተማርኮ የመጀመሪያው ጥበብ ነው” ብለው አባ ማስያስ መለሱ።

“የወንጌል አባት፡ የክርስትና መሥራች ክርስቶስ የተሰቀለው የትና በእነማን አገር ነው? ደግሞስ በልጅነቱ ወራት ራሱ ክርስቶስ የባረከውንና በኋላም ሊቀጳጳስ የሆነውን አግናጢዎስን ያህል አባት ከአንበሳ ጋር አታግላችሁ የገደላችሁ እናንተ አይደላችሁም? በኔ አገር እንደሆነ የአንድም ሐዋርያ ደም አልፈሰሰም፤ ታዲያስ ምን አድርጉ ነው የምትሉን? የይሁዳዎችን አገር ኢየሩሳሌምን፥ የእስላሞችን አገር ግብጥንና ሌሎችንም እንደምን አልፋችሁ መጣችሁ? የጥበብ ነገር የሚያስተምሩስ ከእናንተ መካከል የታሉና? ለተንኮል እንደ መጣችሁ አላጣሁትም። ወዴት ወዴት?” አሉ አፄ ዮሐንስ።

“ጃንሆይ! የእነርሱ ተንኮል መች ተዘርዝሮ ያልቃል? ዋግሹም ጉበዜን ለማንገሥ ሲሠሩት የነበረውን ተንኮል አገር ምድሩ ያውቀው የለም? አሁንም እንደ ሆነ…” ብለው ዕጨጌ ፊታቸውን ወደ ተከሳሾቹ መለስ ሲያደርጉ አፄ ዮሐንስ ንግግራቸውን ቀበል አድርገው፤

“መቼ አጣነው? እንዳውስ ጳጳስ ከእስክንድርያ እንዳይመጣልኝ ውስጥ ውስጡን ስታሳድሙብኝ

አልነበራችሁም?”ብለው ሲገላምጧቸው ቆዩና። “መኳንንት ሊቃውንት በሉ ፍረዱኝ?” ብለው ፍርድ ጠየቁ።

“ለመሆኑስ በየሥፍራው ስንት ስንት ሚሲዮኖች እንዳሉሳ ይታወቃል?” ብለው ንጉሥ ምኒልክ ዕጨጌን ጠየቁ። “ምን ሥፍር ቁጥር አላቸው? ጠመንጃኮ ቢይዙ ያንድ ራስ ጦር ያክላሉ” አሉ እጨጌ።

“ይኽ የጠላት ወሬ ነው። የኛ ቁጥር ይኽን ያህል አይሞላም፤ ሐሰት ነው” አሉ አባ ማስያስ።

“ደግሞ ዐይን በዐይን ሊክድ ነው? በሐማሴን በደጋውና በቆላው በትግራይም እንደዚሁ በየሠፈራችሁበት ቦታ ያለው ተንኮል ሠሪያችሁ ቢደምር ያንድ ንጉሥ ጦር አይሆንም?” አሉ አፄ ዮሐንስ ቁጣቸው ይበልጥ እየናረ።

“ኧረ ጃንሆይ! ካንድ ንጉሠ ነገሥት ጦርም ሳይበልጥ አይቀርም? አገርዎንኮ ከጫፍ – እስከጫፍ

ሠፍረውበታል?” አሉ እጨጌ።

“ዋናው ነገር ብዛታቸው ሳይሆን ድፍረታቸው ነው የሚመዝነው!” አሉ ይማሙ መሐመድ በትዝብት።

“መኳንንት፥ ሊቃውንት በሉ ፍርዳችሁን ስጡኝ!” አሉ አፄ ዮሐንስ።

“ጃንሆይ! በርስ-በርሳችንና በሀገራችን ጉዳይ ጣልቃ ላይገቡ፥ ወንጌል ከማስተማር በቀር ሌላ ነገር ላይሠሩ ይፈጠሙ” ብለው ሐሳብ ሰነዘሩ ይማሙ መሐመድ።

“የሰባኪዎች ብዛት ተቀንሶ ጥበብ የሚይስተምሩት ቢበዙ ይሻላል” አሉ ንጉሥ ምኒልክም።

“ከስብከት ሌላ የሚሠሩትን ተንኮል ገልጠን ወደያገራቸው መንግሥታት እናስተላልፍና እነርሱ

ቢቆጣጠሩዋቸው አይሻልም?” አሉ ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት፥ የምኒልክ ምርኮኛ ሆነው በአፄ ዮሐንስ ችሎት ተገኝተው የፍርድ ሐሳብ ለመሰንዘር በመብቃታቸው ልዩ ኩራት እየተሰማቸው።

አፄ ዮሐንስም በአክብሮት ሲመለከቱዋቸው ቆዩና አስተያየታቸውንም በአክብሮት የተቀበሉላቸው መሆናቸውን በመግለጽ አንገታቸውን ደፋ ቀና እያደረጉ ቆይተው፤ “ሐሳባችሁን ከልብ አዳምጨዋለሁ። በእነዚህ ተንኮለኞች ሥራ ልቤ ቆስሏል፤ አገሬ ተበድሏል፤ ወንጌል የሚያስተምሩ መምህራን ከእስክንድርያ አስመጣለሁ። እነሱው ይበቃሉ።

የሀገሬን ሕዝብ የእጅ ሥራና ጥበብ የሚያስተምሩ ሥጋጃ ሠሪዎችን ነጋዴዎችን ብረት ሠሪዎች የሆኑትን ነው የምፈልግ እንጂ እንደ እናንተ ያሉ በወንጌል ስም እየመጡ ሕዝቡን የሚከፋፍሉ አይደሉም። አገሬን ለጠላት አሳልፋችሁ ለመስጠት ባደረጋችሁትም ተንኮል እጅ እጃችሁንና ምላሳችሁን እየቆረጥኩ ብቀጣችሁ ማስጠንቀቂያ በሆናችሁ ነበር። ግን ራሴንም ሆነ ሕዝቤን ከትዝብት ላይ አልጥልም” ብለው ተከሳሾቹን አንድ በአንድ ሲመለካከቱዋቸው፥ ተከሳሾቹ ወደ መሬት አቀርቅረው መሬቷን ሲማፀኑዋት አዩዋቸውና፤ “ሳትውሉ ሳታድሩ ከሀገሬ ውጡልኝ” ሲሉ ተከሳሾቹ መሬት መሳም ጀመሩ።

አፄ ዮሐንስም ወደ አጋፋሪያቸው ዘወር አሉና፤ “ንሣ አጋፋሪ በመጣበት እግሩ አገሬን የረገጠበትን ጫማውን አራግፈህ፥ ያረከሳትን አገሬን አፈር አስመህ አባርልኝ!” አሉ በኃይለኛ ቁጣ ተውጠው! አጋፋሪ እንደ ታዘዙት ተከሳሾቹን እያዳፉ ሲያስወጡ ዕጨጌም፤

“ዕድሜዎን ያርዝምልኝ” ብለው ወደ ወንበራቸው ተመለሱ። አጋፋሪው ተከሳሾቹን ካስወጡ በኋላ ተመለሰው ወደ ችሎቱ ገቡና፤ “ጃንሆይ! ሱረት ባፍንጫቸው፥ ትንባሆ ባፋቸው እየጐረሱ መጥፎ ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ተይዘው መጥተዋል?” ብለው አመለከቱ።

“አስገባቸው” አሉ ዮሐንስ ከቁጣቸው እጅግም ሳይበርዱ ሌላ ነገር በመቀጠሉ እንደ መቆጣት ብለው። አጋፋሪ ትእዛዙን ተቀብለው ሲወጡ ዕጨጌ ቀጠል አደረጉና፤ ” እነዚሁ ወንጌል እንሰብካለን የሚሉ ያስለመዱዋቸው ይሆናሉ!” ብለው ጉዳዩን ሰቀሉት።

ወዲያው አጋፋሪው እጅ-ለእጅ የተቆራኙ ሰዎች ያቀርቡና፤ “ጃንሆይ! እነዚህ ሰዎች ተመክረው፥ ተለምነውና ተገዝተው ከዚያች የተረገመች የሰይጣን ቅጠል መላቀቅ ያቃታቸው፥ ለሕዝብ መጥፎ ነገር የሚያሳዩ የተበላሹ ናቸው” ብለው ክሳቸውንም ተከሳሾቹንም አቀረቡ።

“እንዲያ ሕዝቤን እስቲበክሉት ነው የምታዮዋቸው? አጋድምና ግረፍልኝ” አሉ ራሳቸውም ከዙፋናቸው ተነሥተው ሊገርፉ እየቃጣቸው። አጋፋሪ ገራፊውን ከነመግረፊያው አስጠሩ። ከአፄ ዮሐንስ ጋር በያገሩ ከሚዞሩት አምስት ገራፊዎች በዚያ ዕለት ተረኛ የነበረው ገራፊ በቅጠል ስሙ “ሰጣርጋቸው” በመባል የታወቀው የአሸንጌው ተወላጅ አረሩ መሆኑ ነበር። ግድንግድ ነው፤ ከቁመቱ የውፍረቱ፥ ከውረቱም የመጐልበቱ የተትረፈረፍ ነበር። ቅቤ የጠገበው ጅራፍም በወፍራሙ የተገመደ የበሬ ጅማት ነበር።

ጅራፍ ተፈርዶባቸው ሳይገረፉ ውለው ያደሩትን ወይም ‘የነእገሌ ዘር’ የሚባሉትን የጅራፉን ጡሉዳ ከመሬት ላይ እያስጮኽ የተገራፊውን ጀርባ ነካ ነካ የሚያደርግበትና የማይጐዳበት ዘዴ አለው።

ሳይውል ሳያድር የሚገረፈውንና ማንነቱን አስቀድሞ ያላወቀውን ግን አረሩ ተሸላልጦ ይለቀዋሎ። በተለይም አፄ ዮሐንስ የተቆጡባቸው ከሆኑ በእነርሱ ገመድ ላለመግባት ሲል ጅማቶቹን ገታትሮ ዐይኖቹን ጐልጉሎ የጃንሆይን ቁጣ ያበርድላቸዋሎኦ በዚያች ዕለት ከጁ የገቡት ሲሰኞችም ንጉሠ ነገሥቱን ያስቆጡበት ናቸውና ከልቡ ተልትሎ ተልትሎ ለቀቃቸው።

ማንኛውም ጥፋተኛ ከተገረፈ በኋላ ሰውነቱ እንዳይቆስል ተብሎ በቅባትና መድኃኒት ይታሻል። እነዚያን ሱሰኞች ግን፥ “ቁስላቸው እንደ ዓመላቸው እነሱንም እንዲከረፋቸው አትቀቡዋቸው” ብለው አፄ ዮሐንስ ስላዘዙ ከግርፋት ወደ እስር ተላለፉ።

“ይህን ሙያ ብሎ የሰይጣን ቅጠል ይምጋል? አገር አሰዳቢ ሁሉ ጥበብ እንደ መቅሰም፥ ጠመንጃ፥ ጥይት፥ መድፍ፥ መርከብ እንደ መሥራት? ይህን ሙያ ብሎ የለመደውን ሁሉ እያስፈለጋቸሁ እጅና እግሩን ቁረጡልኝ” ብለው በዚያች ዕለት አዘዙ ንጉሠ ነገሥቱ።

ዕጨጌም ቀጠል አደረጉና፤ “ጃንሆይ! የዛሬዋ ዕለት መቼስ የሀገርዎን መርዝ የተነቀሉባት በአዕምሮአቸውና በአካላቸው የላሸቁ መንፈስ-ደካሞችን የቀጡባት ስለሆነች ስትመሰገንና ስትወደስ የምትኖር ናት። ነገር ግን ‘ከተለሙ ያርሷል፤ በጀመሩ ይጨርሷል’ ነውና ጅምርዎን ይጨርሱልን” አሉ ከተቀመጡበት ተነሥተው።

“ሌላ ምን ነገር ቀርቷል” አሉ አፄ ዮሐንስ።

“ተዚህ በፊት” ብለው ዕጨጌ ከቆሙበት ወደፊት ራመድ ብለው ከንጉሠ ነገሥቱ ፊት ቆሙና ንግግራቸውን ቀጥለው፤ “ተዚህ በፊት አክሱም ላይ ቅብዐቶችና ተዋህዶዎች ተከራክረው ቅባቶች ተረትተው ተዋህዶዎች ረትተው ሕዝብዎ እፎይ ብሎ ነበር” ብለው መኳንንቱንና ካህናቱን ሲቃኙ ሁሉም በአነጋገራቸው የሚስማማላቸው መሆኑን በየአስተያየቱ ገለጸላቸው።

እርሳቸውም የችሎቱን ድጋፍ ያገኙ መሆናቸውን ከአረጋገጡ በኋላ ንግግራቸውን ቀጠሉበትና፤

“ክርስቶስ ‘በጥምቀት የጸጋ ልጅ እንጂ የአብ የባሕርይ ልጅ አይ ደለም’ የሚለውን የተሳሳተ እምነታቸውን እያስተማሩ ሕዝቡንም በማሳሳት ላይ ናቸው። በየአድባራቱ ብዙ ብዙ ስሕተት ደርሷል።

ይህንኑ ችግር ለጃንሆይ ነግሬ ግራ – ቀኙም እንዲቀርቡ ባዘዙት መሠረት ከጸጐችም፥ ከተዋህዶዎችም የተመረጡ ሊቃውንት መጥተዋልና ቀርበው ነገሩ እንዲታይልን እለምናለሁ ብለው እጅ ነሡ።

“’የጦጣን ልጅ በዛፍ፥ የጸጋን ልጅ በመጣፍ’ ተብሏልና ትችሏቸዋላችሁ?” ብለው ጠየቁ አጼ ዮሐንስ፥

መኳንንቱንም፥ ካህናቱንም ጭምር በጨረፍታቸው እየጐበኙ።

“ጃንሆይ እንዲህ እያሰኙ የሚያስወሩትኮ ለብልሀታቸው ነው! ሥረ-መሠረቱ ያማረ የሠመረ የተጣራ

መጽሐፍኮ የላቸውም!” አሉ እጨጌም በልበ-ሙሉነት።

“ሊቃውንቱስ መጥተዋል?” አሉ ንጉሠ ነገሥቱ።

“አዎ ከኛም ከእነሱም መጥተዋል።”

“ከእናንተ በኩል የተመረጡት እነማን ናቸው?”

“ከኛ በኩል አፈ ጉባኤያቸውን አለቃ ኪዳነ ወልድ ከባለ ቀረኛቸው ከአለቃ ተክለ ሥላሴና ከመልአከ ብርሃን ወልደ ሥላሴ ጋር መጥተዋል” አሉ ዕጨጌ።

“እንዴ? እውነትም ዛሬ አስባችሁበታል! እነዚህ ሊቆች ከመጡማ በሀገራችን ውስጥ ያለው የሃይማኖት ልዩነት ጉዳይ እልባት ማግኘቱ ነው?” አሉ ንጉሥ ምኒልክም እየተፍነከነኩ።

“ጌታዬ ድሮስ ቢሆን ደጋግመን ረትተናቸው፡ ደጋግመው ተፈጥመው አልነበር? ጊዜና ቦታ እየለወጡ

መርዛቸውን እየረጩብን ተቸገርን እንጂ? አሉ ዕጨጌም። “ለመሆኑስ ከእነርሱስ በኩል ማን ማን ተመርጠዋል?” አሉና ጠየቁ አፄ ዮሐንስ። “ከእነሱ አለቃ ተክለጽዮን ፎክሮ ማን ይችለኛል? ብሎ መጥቷል” አሉ ዕጨጌ፤

“ምን ተክለጽዮን ነው? ተክለልዮን ነው እንጂ? ብቻ በል ሁለቱንም ወገን ባለጉዳዮችን ሌሎችም መኳንንትና ሊቃውንት ጭምር አስገባ” ብለው አፄ ዮሐንስ ለአጋፋሪ ትእዛዝ ነገሩና ወደ ዕጨጌ መለስ ብለው ደግሞ፤

“ከጸጎችስ ወገን እነማን መጥተዋል?” ብለው ጠየቋቸው። “ከእነሱማ በኩል አፈጉባኤያቸው አለቃ ሥነ ጊዮርጊስ፥ አለቃ ሀብተ ወልድ መጥተውላቸዋል” አሉ ዕጨጌ።

“እስቲ እግዚአብሔር ያሳያችሁ?” ብለው አፄ ዮሐንስ የችሎቱን ተሳታፊዎች ቃኝተው ዐይኖቻቸውን ከዕጨጌ ላይ አሳርፈው፤ “እስቲ እግዚአብሔር ያሳያችሁ? እነዚህ ሁሉ ሊቆች ተስማምተውና ተግባብተው የአንዱን የአምላክን መንገድና ወንጌል ለሕዝብ ቢያስተምሩ ኖሮ የውጭ ተንኮለኞች በየጊዜው እየገቡ ሕዝቡን ባላስቸገሩብን ነበር። ግን ምን ይሆናል? እነርሱስ ራሳቸው ከውጭው ተንኮል መች አመለጡ?” ብለው መተከዝ ሲጀምሩ ዕጨጌም ቀበል አደረጉና፤

“እኛንስ ያስቸገረን ይኽው አይደል? ኑ አንድ ሆነን እናስተምር፥ በውጭው ተንኮል ሕዝቡ እንዳይበጣበጥ እንከላከልለት ስንላቸው ልባቸው ወደ ውጭው ተንኮል እያደላበን እኮ ነው የተቸገርነው…” ብለው ንግግራቸውን ሳያጠቃልሉ አጋፋሪ ሁለቱን ተሟጋቾች እያስገቡ እጅ እያስነሡ በቀኝና በግራ አሰለፉዋቸው።

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »