Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Emperor Yohannes’

በጤፍ እንጀራ ፈንታ የቻይና/ሉሲፈር ባንዲራ | እነ ደብረ ጽዮን የጽዮን ልጆች ወይንስ የዋቄዮአላህ ጭፍሮች?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 15, 2022

🛑 ማንነትን የማጥፋት ጅሃድ

✞ የጽዮንን ቀለማትና ክቡር መሰቀሉን በሉሲፈር ቀለማትና ኮከብ ☆ መተካት

💭 በተለይ ጽዮናውያን፤ ትንሽ ጊዜ ገዝተን ውይይቱን በጥሞና እናዳምጠው።

👉 የከበረ ምስጋና ለዶ/ር አረጋዊ መብርሃቱ እና ቡድናቸው

ግእዛዊት ኢትዮጵያ (Geez Ethiopia with its Red Sea) (ANU)

@OTNAAWorldwide

💭 በቪዲዮው ላይ የቀረቡ አንዳንድ ጽሑፎች

👉 ያለፈው ሐሙስ ፭ ዕለት የጀግናው የኢትዮጵያ ንጉሥ እና የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስትና አርበኛው

የአፄ ዮሐንስ ፬ኛ የልደት ቀን ነበር። እንኳን ተወለዱልን! አፄ ዮሐንስ እንዳይረግሙንና ለተተኪው ትውልድም ከእኛ የተሻለ ሕይወት ይኖረው ዘንድ እሳቸው በመንፈሳዊ አንደበታቸው ሲነግሩን ሲያስጠነቅቁንና ሲያቅዷቸው የነበሩትን ነገሮች ሁሉ መፈጸም ይኖርብናል።

👉 ሕወሓቶች ያዳናቸውን የአክሱም ጽዮን ሕዝብን የሚወዱትና የሚጠብቁት ቢሆኑ ኖሮ፤ ዛሬ ይህን የቻይና/ሉሲፈርን ባንዲራ አሽቀንጥረው በጣሉት ነበር። ፈተናውን ሁሉ የወደቁት እነ ደብረ ጽዮንም ተጸጽተውና “በቃን!” ብለው አጋሮቻቸውን እነ ግራኝ አብዮት አህመድን በእሳት በጠረጓቸው ነበር። እስካሁን አንድም የዚህ ጨፍጫፊ አገዛዝ ባለስልጣን አልተነካም! እነ ደብረ ጽዮን፤ ኦሮሞ፣ ሶማሌና አማራ የተባሉት ክልሎች ይፈርሱ ዘንድ ሥልጣናቸውን እንደ አፄ ዮሐንስ ፈሪሃ-እግዚአብሔር ላላቸው ለትክክለኞቹ ጽዮናውያን ባስረከቡም ነበር። የሩሲያው ቦሪስ የልሲን ለአገሩና ለሕዝቡ ሲል ለቭላዲሚር ፑቲን እንዳስረከቡት፣ ወይንም የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚንስትር ቦሪስ ጆንሰን “ጭፈራ ላይ ተገኝቷል” በሚል ክስ ከሥልጣናቸው ተወግደው በሴቲቱ እንዲተኩ ዛሬ በመሠራት ላይ እንዳሉት። ሕወሓቶች ግን በየትም ዓለም ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ መልክ ስልጣኑን፣ ታንኩን፣ አውሮፕላኑን፣ ባንኩን፣ አዲስ አበባን፣ ግድቦቹን፣ ሜዲያውን ሁሉ ለነጣቂ ጋላ-ኦሮሞ አውሬ አስረክበው “ሕዝባቸውን” በጭካኔ ያስጨፈፈጭፋሉ በረሃብ እንዲቆላ ያደርጋሉ። እነ ደብረ ጽዮን አክሱም ጽዮን በተወረረችበት ማግስት ከስልጣን መወገድ ነበረባቸው።

👉 አክሱም ጽዮናውያን እናቶቻችን የሚለብሱትን ነጭ ቀሚስ እና ክቡር መስቀሉን

በሉሲፈር ቀለማትና ባለ አምስት ፈርጥ ኮከብ መተካት የሕወሓቶች ዋና ዓላማ መሆኑን እያየነው ነው። ከዚህ ሁሉ ግፍና በደል በኋላ ምናልባት ከስህተታቸው ተምረው ሊሆን ይችላል የሚል ትንሽ የተስፋ ጭላንጭል ነበር። ነገር ግን ዛሬም ሉሲፈራውያኑ ሞግዚቶቻቸው የሚያዟቸውን ነገር ሁሉ በመፈጸም ላይ ናቸው። እውነት ሕወሓቶች በትግራይ ሕዝብ ተምርጠው ከነበረ የመረጣቸውን ሕዝብ ከነጣቂ ጋላ-ኦሮሞ እና አህዛብ ተኩላ ሙሉ በሙሉ ሊጠብቁት በቻሉ ነበር። ግን “ፈንቅል” በተሰኘው የግራኝና ደብረጽዮን መፈተኛ ድራማ የተፈተነው የትግራይ ሕዝብ አልመረጣቸውም፤ ስለዚህም እየተበቀሉት ነው፣ እንዲንበረከክላቸው ሁሉም በጋራ እየሠሩ ነው።

👉 ሕወሓቶች፤ በተለይ በዲያስፐራ ያሉት ከሁሉም ነገር አብልጠው በትጋት የሚያስተዋውቁት ይህን የቻይና/ሉሲፈርን ባንዲራ ነው። ላለፉት አሥራ አምስት ወራት ስለ ጋላ-ኦሮሞ “ምርኮኞች” እንጅ አክሱም ጽዮናውያን አባቶቻችንና እናቶቻችን ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ የሚናገሩ መረጃዎችን ከማውጣት ተቆጥበዋል። በሱዳን ስደት ላይ ስለሚገኙት ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን እንኳን በጭራሽ አይናገሩም። በአክሱም ጽዮን፣ በደብረ ዳሞ፣ በማርያም ደንገላት፣ በደብረ ዓባይ፣ በውቅሮ አማኑኤል፣ በዛላምበሳ ጨርቆስ ወዘተ የተፈጸሙትን ጭፍጨፋዎችና ግፎች ዝም ጭጭ ብለዋል። ስለዚህ ጉዳይ በየቀኑ መናገር ነበረባቸው።

👉 ለመሆኑ በፋሺስቱ የጋላ-ኦሮሞ ደርግ አገዛዝ አውሮፕላኖች በሐውዜን ለተጨፈጨፉት ሦስት ሺህ ወገኖቻችን የመታሰቢያ ኃውልት፣ ቀን ወይም መሰል ነገር ተዘጋጅቶላቸዋልን? የለም፤ እኔ አላውቅም! የማውቀው ግን የዚህ ጭፍጨፋ ወንጀል ፈጻሚዎቹ እነ ለገሰ አስፋው፣ ፍቅረሥላሴ ወግደረስ ለእስር ቢበቁም በቀን ሦስት ጊዜ እየተመገቡ፣ ሐኪሞች እንዲጎበኟቸውና ከዘመዶቻቸውም ጋር እንዲገናኙ ተፈቅዶላቸው፤ “ተንደላቅቀው” መኖራቸው፣ ከሁለት ዓመታት በፊት ሲሞቱም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እንዲፈጸም መደረጉን ነው።

👉 የአሜሪካ ድምጽ በቻይና/ሉሲፈር ባንዲራ የተሸፈነውን የአክሱም ጽዮንን ቤተክርስቲያንን ምስል ማሳየቱ ያለምክኒያት አልነበረም! ሉሲፈራውያኑ የሚፈልጉት ይህን ስለሆነ።

👉 በዘመነ ፍጻሜ፤ በጀነሳይድ ማግስት፤ ዘፈን፣ ዳንኪራና ፌስቲቫል!

አዎ! ሊሲፈርና ጭፍሮቹ ተደስተዋል፣ ባንዲራውንም ለማስተዋወቅ አጋጣሚ አግኝተዋል! በቪዲዮ ለማቅረብ እሞክራለሁ፤ ባለፈው በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮን የወደመው ወፍጮ የዋልድባ ገዳም ንብረት ነው | ፲፱ እናቶች ተሰውተዋል

😠😠😠 የጨለማ ዘመን ኢትዮጵያ😢😢😢

💭 ባለፈው የጌታችን ልደት በዓል ዕለት በደደቢት ከተማ፤ ሃምሳ ዘጠኝ እናቶችና ሕፃናት በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮኖች ተጨፍጭፈው የሰማዕትነትን አክሊል በተቀዳጁበት ማግስት ሕወሓቶች በጨፍጫፊዋ ቱርክ ከተሞች የቱርክንና የቻይና/ሉሲፈርን ባንዲራን የሚያውለበልቡበት በዓል ላይ ተገኝተው ነበር። በፍጻሜ ዘመን ማግስት ዳንኪራ። ይህን ሳይ እጅግ ከፍተኛ ሃዘን ውስጥ ገብቼ ነበር።

👉 በኅዳር ጽዮን ክብረ በዓል ዕለት ሕወሓቶች በአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ላይ

የሉሲፈርን/ቻይናን ባንዲራ በመስቀል ከባድ የድፍረት ወንጀል ፈጽመዋልና አብቅቶላቸዋል።

👉 በጽዮን ቀለማት ያሸበረቀው ጥንታዊው የደብረ ዓባይ ገዳም

👉 ሰሜናውያኑን ዲያብሎሳዊ በሆነ የእልህ ባህል ውስጥ እንዲገባ ያደረጉት እባቦቹ ጋላ ኦሮሞዎች በመቀሌ የቻይናን/ሕወሓትን/ሉሲፈርን ባንዲራ እንዲህ ሲያወርዱ በቪዲዮው ቀርጸው ልከውት ነበር። ጽዮናውያን ከሕወሓትና ባንዲራው ጋር በእልህ እንዲጣበቁ!

👉 ነፍሳቸውን ይማርላቸውና፤ በአረመኔው ኦሮሞ ግራኝና በኮሙኒስቱ ደብረጽዮን ሤራ የተሰውት የጄነራል አሳምነው ጽጌ ምስክርነት።

💭 በጽዮናውያን ላይ የዘር ማጥፋት ጦርነቱ እንደጀመረ ይህን ጥያቄና መልስ አቅርቤ ነበር፤

👉 ለመሆኑ ይህ ጦርነት ማንን ነው “የሚጠቅመው”?

፩ኛ. የምዕራቡን ኤዶማውያንን እና የምስራቁን እስማኤላውያንን(ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ እስላም፣ ኢአማኒ፣ ግብረሰዶም)

👉 ምክኒያቱ፦ ሁለቱም ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ዲያብሎሳዊ ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋትና በኢትዮጵያ የሚገኘውን የሕይወት ዛፍም ለሳጥናኤል ስም፣ ክብርና ዝና ሲሉ መውረስ ይሻሉና ነው።

፪ኛ. ዋቀፌታን/ኦሮሙማን

👉 ምክኒያቱ፦ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን አጥፍተው የራሳቸውን ርዕዮተ ዓለማት ማስፋፋት ይሻሉና ነው። የፕሮቴስታንቲዝም አባት ማርቲን ሉተር ወደ ጀርመንኛ በተረጎመው መጽሐፍ ቅዱስ ኢትዮጵያን‘ ‘ኩሽብሎ ነው የጻፋት። ይህ ቀላል ነገር እንዳይመስለን። እ..አ ከ 1837 እስከ 1843 .ም ባለው ጊዜ ፕሮቴስታንቱ ጀርመናዊ ዮኻን ክራፕፍ ኦሮሚያ የተባለውን ግዛት ለመመሥረት የተነሳሳው ክርስትናን ለማስፋፋት ሳይሆን፡ እንደ አንድ ፕሮቴስታንት የኢትዮጵያ ቀጥተኛ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ለመዋጋት ነው። ለዚህም በወራሪነት ባሕርይ ከጀርመኖች ጋር ይስማማሉ በሚል ሃሳብ “ጋላ” ተብለው ሲጠሩ የነበሩትን ጎሳዎች ለማደራጀት በመነሳሳት በ ኢትዮጵያፋንታ ኩሽየሚለው ትርጉም ያለበትን መጽሐፍ ቅዱስ ይዞ ወደ ምስራቅ አፍሪቃ/ኢትዮጵያ ተጓዝ፤ በዚህም የኦሮሙማ እንቅስቃሴን ጀመረው። ተልዕኮው ፀረኢትዮጵያ፣ ፀረተዋሕዶ እና የክርስቶስ ተቃዋሚ ተልዕኮ መሆኑን ዛሬ እያየነው ነው። ዋናው ዲያብሎሳዊ ዓላማቸው፤ ኢትዮጵያን አፍርሰው ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትንም በተለይ ከአማራና ትግሬ በመንጠቅ “መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰችው ኩሽ እኛ ነን” የሚለው ነው።

ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም”[የዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፥፲]

፫ኛ. የአማራ ብሔርተኝነትን

👉 ምክኒያቱ፦ ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ትግሬዎችንና ትግርኛን አጥፍተው ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ግዕዝን፣ ሰንደቁን፣ አክሱም ጽዮንን፣ ቅዱስ ያሬድና አቡነ አረጋዊን ከተቻለም መላው ትግራይንና ኤርትራን ወርሰው ለራሳቸው ብቻ ለማድረግ ይሻሉና ነው። በነገራችን ላይ፤ ኦሮሞዎች በኬኛ ቅዠታቸው ሙጭጭ ያሉበትንና “ፊንፊኔ/ ፊልፊሌ” የሚለውን ስያሜ ለአዲስ አበባ ፍልወሃ ክፍለ ከተማ እቴጌ ጣይቱ እንደሰጡት፤ “አማራ” የተባለውን የአማራ ከንቱ ብሔርተኞች ክልልን መጠሪያ ስም የሰጡት ደግሞትግሬው/ሚ መለስ ዜናዊ ነበሩ። የሕይወት ምፀት!

፬ኛ. የትግሬ ብሔርተኝነትን

👉 ምክኒያቱ፦ ኢአማንያኑ ሻእቢያ እና ህዋሀት ቡድኖች ከኦሮሙማዎች፣ ከኤዶማውያኑ እና እስማኤላውያኑ ጋር በማበር ኢትዮጵያን፣ ኢትዮጵያዊነትንና ተዋሕዶ ክርስትናን፣ ቅዱስ ያሬድን፣ አቡነ አረጋዊን፣አባ ዓቢየ እግዚእን፣ነገሥታቱን ኢዛናን፣ ዮሐንስን፣ ሰንደቁን፣ ግዕዝን፣ አክሱምን አጥፍተው በሃምሳ ዓመታት ውስጥ በተገኘ ጣዖታዊ ማንነት “ኢአማኒ የትግራይ ሶሻሊምዝብልጽግና” ርዕዮተ ዓለምን በመከተልና የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ባንዲራም በማውለብለብ ከኤርትራ ጋር ለብቻቸው መኖር ይሻሉና ነው። በትግራይ እየተካሄደ ያለው ጦርነት የግራኝ አብዮት አህመድ እና የስብሃት ነጋ ጦርነት ነው። መንግስቱን ለኦሮሙማዎች እንዳስረከቡት፣ ቤተ ክህነትንም ለእነ ኤሬቻ በላይ በማስረክብ ላይ ያሉ ይመስላሉ። በትግራይ ላይ የተከፈተውን ጦርነት የደገፉበት አንዱ ምክኒያትም ይህ ሊሆን ይችላል፤ ዋናው ፍላጎታቸው ግን የትግርኛ ተናጋሪ ተዋሕዶ ኢትዮጵያውያንን ልብ በመስበርና ተስፋ በማስቆረጥ፡ ተዋሕዶ ክርስትናን እና ኢትዮጵያን እንዲተው ማድረግ ነው። በነገራችን ላይ፤ ዛሬ የትግራይ ከንቱ “ትግራይ! ትግራይ!” ብሔርተኞች ለሚጮሁለት ክፍለሃገር “ትግራይ” የሚለውን መጠሪያ የሰጡት ድንቁ አማርኛ ተናጋሪ ጽዮናዊኢትዮጵያዊ ንጉሥ አፄ አምደ ጽዮን ናቸው። የሕይወት ምፀት!

ሉሲፈራውያኑ እና ቆሻሻው ወኪላቸው አብዮት አህመድ አሊ ትግራይን ከኢትዮጵያ ገንጥለው የስጋ ማንነትና ምንነት ባላቸው ጠላቶቿ የምትመራዋን የዛሬዋን ኢትዮጵያን አፈራርሰው ከሞያሌ እስከ መተከልና ጎንደር ያለውን ግዛት ለኦሮሞዎች ለማስረከብ ተግተው በመሥራት ላይ ናቸው። አማራው የስጋ ማንነትና ምንነት ካላቸው ኦሮሞዎቹ ጎን ተሰልፎ የመንፈስ ማንነትና ምንነት ባላቸው ትግሬ ወንድሞቹ ላይ በመቶ ዓመት ውስጥ ለሦስተኛ ጊዜ ጦርነት በማወጁ አብቅቶለታል! አክሱም ጽዮንን ክዷልና የሆነ ተዓምር ካልመጣ በቀር ምንም ተስፋ የለውም፤ በቅርቡ ሃገር አልባ ነው የሚሆነው። እነ ግራኝ እየሠሩ ያሉት ትግርኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያን ከኢትዮጵያዊነታቸው፣ ከአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ ሰንደቃቸው እና ከተዋሕዶ ክርስትናቸው እንዲላቀቁ ብሎም አእምሯቸውን ተቆጣጥረው፣ መንፈሳቸውን አድክመውና ሞራላቸውን ሰብረው ልክ እንደ “ኤርትራውያን” ለአውሮፓውያን አረጋውያን የኩላሊትና መቅኒ መለዋወጫ እንዲሆኑ ማድረግ ነው። ሰሞኑን “አማራ” የተባለው ክልል ባንዲራውን ለመቀየር መወሰኑ ከዚህ ሤራ ጋር የተያያዘ ነው። ከኦሮሞዎቹ ከእነ አብዮት አህመድ ጋር ተናበው በመስራት ላይ ያሉት ሀወሃቶች የዚህ ዲያብሎሳዊ ሤራ አካል ቢሆኑ አይገርመንም። ዋ! ! !

በዓለማችን ያሉ ብዙ ሕዝቦች በተቻለ መጠን በሃይማኖት፣ በቋንቋ፣ በባህልና በመልክ የሚመስሏቸውንና የሚቀርቧቸውን ሕዝቦች እየፈለጉ ማስጠጋትና መውደድ በጀመሩበት በዚህ ዘመን ትንሿ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ብሔሮች ግን ጥላቻን አንግሦ አንዱ ከሌላው የሚለይበትንና የሚረቅበትን፣ አንዱ ሌላውን የሚጠላበትንና የሚያርቅበትን ሰበባ ሰበብ እየፈላለገ እርስበርስ መባላቱንና ውድቀቱን መርጧል። ሞቃዲሾን አልፎ ኪጋሊንና ካምፓላን፣ ቀይ ባሕርን ተሻግሮ ኤደንና ሙስካትን “ የኛ ነበሩ! የኛ ይሆናሉ!” በሚል ወኔ ታላቅነትንና አርቆ አሳቢነትን እንደ ቀደሙት አያቶቹ ይዞ “ኢትዮጵያ እርስቴ” በማለት ፈንታ እራሱን አጥብቦና በጣም አውርዶ በወልቃይትና ራያ ሚጢጢ“እርስቶች” ላንቅው እስኪበጠስ ይነታረካል። ዛሬማ ሰው ከ“አዲስ አበባ የማን ናት?” አሰልቺና አላስፈላጊ ንትርክ ወርዶ ጉልበቱንና ጊዜውን በመስቀል አደባባይና ጃን ሜዳ ላይ ብቻ እንዲያጠፋ ተደርጓል። ጃን ሜዳን እና መስቀል አደባባይን ያረከሱትን ግራኝ አብዮት አህመድን እና ታከል ዑማን አድኖ እንደመድፋት፤ “ጮኸን ጮኸን ጃን ሜዳ ተፈቀደልን!” ይልና ሆያሆየን ጨፍሮ ለቀጣዩ እንቅልፉ ወደ አልጋው ይመለሳል። በከሃዲዎቹ የሉሲፈራውያኑ ባሪያ ልሂቃኖቹ አዕምሮው እስኪጠብብ ድረስ መታጠቡ ከዚህ የበለጠ ማስረጃ የለም።

የሕዝቡን ስነልቦና በልተውታል፤ ስለዚህ “አዲስ አበባ ኬኝ” ይሉና መስቀል አደባባይን እና ጃን ሜዳን በመቆፈር የተዋሕዷውያኑን ሃሳብ በነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ላይ ብቻ እንዲቀር ያስሩታል፣ ወደ ወልቃይት፣ ራያና ሁመራ ልጆቹን እየላከ ትግሬዎች ወገኖቹን እንዲገድል፣ የራሱንም ደም እንዲያፈስ፣ የአክቲቪስቱ ሃሳብም በእነዚህ ትንንሽ ቦታዎች ብቻ ተወስኖና ታስሮ እንዲቀር፣ የቀረውም እንዲኮላሽና ሰፊዋን ኢትዮጵያን ከጠላቶቿ ነፃ ለማውጣት አቅም እንዳይኖረው፤ ብዙም እንዳይጠይቅ፣ በጥቃቅን ነገሮች ላይ ብቻ ጊዜና ጉልበቱን እያባከነ ለባርነት እንዲዘጋጅ አድርገውታል። ትልቅ ቅሌት! ወዮላችሁ!

👉 አንድን ሀገር/ሕዝብ ለመቆጣጠር ሉሲፊራውያኑ የሚጠቀሙባቸው መሳሪያዎች፦

  • ተስፋ ማስቆረጥ/ሞራል መስበር
  • አለመረጋጋትን መፍጠር
  • አመፅ መቀስቀስ
  • መደበኛነትን/መረጋጋትን ማምጣት

👉 A Luciferian Plan of Controlling a nation by the tools of

  • Demoralization
  • Destabilization
  • Insurgency
  • Normalization

______________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ጀግና ኢትዮጵያውያን – አፄ ዮሐንስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 10, 2011

ዮሐንስ‘ – በማሞ ውድነህ፡ ፲፱፻፹፭ ዓ.

የግብጽ ወታደሮች በምስራቅ ግንባር ሙሉ በሙሉ መደምሰሳቸው የሰሙት የግብጹ ሼህ ገዢ፡ አማካሪያቸው የነበረውን አሜሪካዊ ጀኔራል ሎሪንግ ጠርተው ምክር ይቀበሉ ጀመር፡ በወቅቱም ከግብጽ ጋር የተሰለፉ ኢትዮጽያውያን መኮንኖች ሸሆች አብረዋቸው ነበሩ። እንደነ ደጃጅማች ሚካኤል የመሳሰሉት።

በኛ በአሜሪካኖች ዘንድ አንድ ምሳሌ አለ። አንድ ጊዜ ሞክረህ ቢከሽፍብህ ሁለተኛ ሞክር፡ ሁለተኛውም ባይሳካልህ ሦስተኛ ሞክር፡ ሦስተኛውም ካልተሳካልህ ደግሞ ሞክር፡ ዕድሜህን ሙሉ ሞክር፡ ሞክርይላል። ታላቂቱ ግብጽ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ወታደሮች ባልሠለጠኑ ሕዝቦች ቢያልቁባትም፡ ከሰላሣ ሺህ በላይ የሚሆን ወታደር ያላት ናትና እንድገና ይሞክርብሎ ደነፋ።

በዚህ አነጋገሩ የግብጹ ገዢ ከዲብ እስማኤል የተደሰተበት መሆኑን በአካኋኑ ጭምር ሲያረጋግጥ የተመለከተው ልጁ ሑሴን እስማኤልም ተነሣና፡ በቱርኮች እግር ተተክተን ግብጽን እጅግ የላቀች ሰፊ ግዛት ያላት አገር ለማድረግ ታጥቀን ተነሥተናል። ስለዚህ በአንድ ያልሠለጠነ ንጉሥ መዋረዳችንን ልንታገሠው የማይገባን ጉዳይ ስለሆነ ዛሬውኑ እንዝመትብሎ ለአባቱም ወታደራዊ ንቃቱን አሳይቶ ተቀመጠ።

ፓሻም፡ የደረሰብን ውርደት መራራ ቢሆንም ዛሬውኑ መበቀል አለብንና በፍጥነት ወደ አበሾች አገርን እንገስግስአለ።

ይህን ውርደት የግብጽ ሕዝብ ከመስማቱ በፊት ራሴ ዘምቼ እበቀልለታለሁአለ ከዲብ እስማኤል።

ስማኝ ታላቁ አባቴ፡ ምንም እንኳን ከታላቁ ክንድህ አበሾች የማያመልጡም ቢሆኑ የአንተ መዝመት ከእነርሱ ታላቅ ክብራቸው ነውና እኔ እዘምታለሁ…” ብሎ ሑሴን እስማኤልም ፎከረ።

ከዲብ እስማኤል ፍሬ ነገሩን ከልጁ ሑሴን አንድበት ቀበል አደረገና፡

ጠላትህን አትናቀውተብሏልና ከእንግዲህ ወዲያ አበሾችን አንንቅም፡ ራሴ እዘምትባቸዋለሁብሎ ነገሩን አጠነከረው።

ከዲብ ቀጠል አረገና፡ “ለመሆኑ ዮሐንስን የሚረዳ የውጭ መንግሥት ይኖር ይሆን?” ብሎ ጄነራል ሎሪንግን ጠየቀው።

ምናልባት ፈረንሣዮች ይረዱ ይሆናልአለ ሎሪንግ።

ፈረንሣዮችማ ዮሐንስ በአገሩ የሚኖሩትን ሚሲዮናውያን ዜጎቻችንን አስቸግሮብናልና ጠበቅ ያለ ርምጃ ውሰዱበት። ጳጳስም አትላኩለትእያሉ ሲወተውቱኝ አልነበር? እንዴት ይረዱታል?” አለ ከዲቡ።

ምናልባት እንግሊዞችስ?” አለና ሎሪንግ ጠየቀ።

ለእንግሊዞችም ቢሆን የምንሻላቸው እኛ ነን። ቀይ ባሕርንና የአባይን ወንዝ ብንይዝላቸው ይደሰቱበታል እንጂ ቅር አይሰኙም። በኛስ ላይ ዐይኖቻቸውን እንደ ጣሉብን ያሉት እነርሱው አይደሉም? በኛ መሥዋዕትነት ለምለምና አስፈላጊ የሆነች አገር ብንይዝ ቅር ይላቸው ይመስልሃል?” አለ ከዲብ ሎሪንግን እያስተዋለው።

እንግዲያውማ?” ብሎ ሊሪንግ ከዲቡንና ከዳተኛ ኢትዮጵያውያን መኮንኖቹን ተመልክቶ እንግዲያውማ ጀርመኖችም በአበሻ ጉዳይ እጅግም የሚያስቡበት አይመስሉም። የሩስያው ንጉሥም ስለ አበሻ አገርና መንግሥት ሰፋ ያለ ጥናት ያደረጉ አይመስሉምና ለማንኛውም የሚያዋጣው በፍጥነት መዝመቱ ይመስለኛልአለ።

በዚሁ ውሳኔና በወጣው ስልት መሠረትም ግብጽ ለሁለተኛ ጊዜ በሐሰን እስማኤል ጠቅላይ አዛዥነት በራቲቮ ፓሻና በጀነራል ሎሪንግ አዝማችነት ከዐሥራ ሦስት ሺህ በላይ የሆነ ጦር ወደ ኢትዮጵያ አዘመተች። በአዋጊነታቸው እምነት የተጣለባቸው ስድስት አሜሪካውያን ከፍተኛ መኮንኖችና በርካታ የመስመር መኮንኖችም ተደለደሉ።

አንዳንዶቹ የመስመር መኮንኖች፡ ግብጽ የያዘችውን የራስዋን ግዛት ምን ሠራችበትና ነው? የአበሻን አገር እይዛለሁ ብላ የምትዋጋው? ትላንት ጉንደት ላይ የደረሰባት ሽንፈት መች አነሰና ነው ዛሬ ደግሞ ቁጥሩ ወደ ሁለት መቶ ሺህ ከሚጠጋ ሠራዊት ጋር ጦርነት ግጠሙ ብላ የላከችን?” እያሉ ያነሡትን ጥያቄ ጦሩ የሚደግፈው ሆነ።

ምንም እንኳን ከዲብ እስማኤል ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ቢልክም በመኮንኖቹ መካከል የተነሣውን ውዝግብና ጦሩም ያነሣውን ጥያቄ ሊሽረው ባለመቻሉ አዛዦች ከውጊያ ስልት፡ ከሥነ ሥርዓትና ከተዋጊነት ሞራል እንደ ተራራቁ ከምጽዋ ወደ ደጋው ሐማሴን የሚወጡበትን የጉዞ እቅድ ነደፉ።

ግብጾች ዘንድ ሰርጎ በመግባት ይህ ነው የማይባል የስለላ አገልግሎት ለጀግናው ራስ አሉላ ብሎም ለአፄ ዮሐንስ ሲያበረክት የነበረው ቅኑ ኢትዮጵያዊ ገብረ መስቀልም በወጥቤትነቱና በአሽከርነቱ ከግብጽ ጦር ጋር ሐማሴን ገብቶ የደጃዝማች ወልደ ሚካኤልንና አብረዋቸው ወደ ግብጽ ጦር የገቡትን መኳንንትና ሼሆች ዝርዝር ለሊጋባ አሉላ አስተላለፈ። የሐማሴንን መያዝና የወልደ ሚካኤልንም መክዳት አጼ ዮሐንስ እንደሰሙ፡ ሁለተኛውንና የመጨረሻውን የመከላከል ዝግጅታቸውን ጀመሩ፡ ኢትዮጵያዊ ሁሉ እንዲከተላቸው የመጨረሻውን ዐዋጅ ዐወጁ።

ዐዋጅ ዐዋጅ ዐዋጅ ስማ ብለውሃል ስማ፤

በበጌምድር፡ በወሎ፡ በጎጃም፡ በሐማሴን፡ በትግራይ፡ በሸዋ ፡ በዳር አገር ያለህ ያገሬ ሰው ሁሉ ስማ፤ የእርስ በርሳችንን መናናቅና መጋጨት ጠላት ዐውቆ በመካከላችን ገብቶ አገር ለመውረር ቢመጣ ጀግናውን ሠራዊቴን አሰልፌ ጉንደት ላይ ብገጥመው ድል ሆነ። ብትንትኑ ወጣ፤ ግን ምን ይሆናል፤ በቃኝ አላለምና እንደገና ደግሞ መጣ። የግብጡ ንጉሥ ደሜን እመልሳለሁ ብሎ ርስትህን፡ ሚስትህን፡ አገርህን፡ ቤት ንብረትህን ሊቀማ እንደገና ጦሩን ልኮብናል።

እኔ ዮሐንስ እንደሆንኩ ሐሳቤም፡ ነፍሴም፡ ሃይማኖቴም አንዲት ናት፡ የሀገሬን መደፈር የሕዝቤን መዋረድ በሕይወቴ ቁሜ አላይም፤ አልሰማም፡ የሚንቁኝንና አንበገርልህም የሚሉኝን እገጥማለሁ፤ ብዬ ጦሬን ወደ ወንድሞቼ አላዞርም። ወደ መጣብኝ ጠላት ዘምቻለሁና ክተት። ስንቅህን ስንቅ፡ ጋሻ ጦርህን አንግበህ ተከተለኝ፡ የመጣው ጠላት የኔ ብቻ ጠላት መስሎህ ዝም ብትል አገርህን ማስወሰድህን ዕወቅ። ይህን ቃል ሰምተህ እንዳልሰማህ ሆነህ ብትቀር ሥጋህን ለአራዊት፡ ነፍስህን ለገሀነም እሳት ዳርጌዋለሁ።

አባትህና ንጉሠ ነገሥትህ

ዮሐንስ ንጉሠ ጽዮን።

ቀሳውስቱም በጳጳሱ በአቡነ አትናቴዎስ ስም አስመስለው ቀጥሎ ያለውን ቃል አሳወጁ።

ሃይማኖትህን ሊያጠፋ፡ ርስትህንና ሚስትህን ሊቀማ የመጣውን የግብጥ ጦር ባትወጋ እስከ ሰባት ትውልድህ ድረስ ርጉም ሁን። የንጉሠ ነገሥትህን የዮሐንስን ዐዋጅ እንዳትጥስ ገዝቼሃለሁ።

 

Continue readingAtseYohannesV

 

 

 

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: