Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • September 2023
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    252627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for September 7th, 2023

A Mystery ‘US Open Bug’ Taking Down Top Tennis Players | ክትባቱ ይሆን?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 7, 2023

🎾 ከፍተኛ የሜዳ ቴኒስ ተጫዋቾችን የሚያሳምም ምስጢራዊ ሳንካ ነገር በዘንድሮው ‘የዩ ኤስ ክፍት ቴኒስ ውድድር/ US Open ላይ በመከስት ላይ ነው።

በዚህም ምክንያት አትሌቶቹ በሜዳው ላይ፤ በማጥወልወል፣ በሳል እና በሆድ ህመም ሲሰቃዩ ብሎም ያልጠበቁትን ሽንፈት በጫዋታ ወቅት ሲቀበሉ እና ራሳቸውን ሲያግልሉ ታይተዋል። አንዳንድ ተጫዋቾች ውድድሩን ትተው ሄደዋል።

👉 መንስኤው ያ የኮቪድ ክትባት ይሆን? የቱኒዚያዋ ቴኒስ ተጫዋች ኦንስ ጃበር የዛሬውን ጨዋታዋን ካሸነፈች በኋላ፤ “ ጉንፋን ስላለብኝ ዞምቢ ነኝብላለች። ምንን እየጠቆመችን ይሆን? ክትባቱ ሰብዓዊነትን ከሰው ልጅ የሚገፍፍና ዞምቢ የሚያደርግ ክትባት ይሆን? ባቅራቢያችን ያሉ ብዙ ሰዎች መጨረሻ ጊዜ በጣም ያልተለመደ ወይንም ባይተዋር የሆነ ባሕርይ ይዘው ነው የሚታዩት። እግዚኦ!

👉 Courtesy: NYPost

🎾 Even The Top Players In Tennis Are No Match For This Bug.

A Troubling “US Open bug” is making the rounds among star athletes at this year’s tournament, resulting in shocking upsets and withdrawals as the athletes struggle to fight on the court through coughing fits and stomachaches.

“I’m a zombie because I have a flu,” Tunisian tennis star Ons Jabeur, 29, said at a news conference Thursday after defeating Linda Noskova in three sets.

The No. 5 seed was visibly unwell during the match, and was seen coughing and sometimes even struggling to reach the ball on difficult shots.

“I’m taking a lot of medicine,” the No. 5 seed admitted at the conference, adding that she “basically took every medication” the tournament doctors could offer.

Jabeur — who was upset by Zheng Qinwen of China over the weekend — is one of many players felled by the so-called “US Open bug” since the tournament opened at the USTA Billie Jean King National Tennis Center on Aug. 28.

Emil Ruusuvuori, 24, of Finland, withdrew ahead of his first-round match due to an unspecified illness.

Austrian Dominic Thiem, 30, subsequently retired in the second set of his second-round match on Wednesday after collapsing onto the net with a stomach issue, the outlet reported.

Czech player Petra Kvitová, 33, also complained of stomach pains before ultimately losing to Caroline Wozniacki on Wednesday, Tennis World reported.

I got the us open bug.. in a way still feels like I’m in the tournament but at home

“I got the us open bug.. in a way still feels like I’m in the tournament but at home,” Tennys Sandgren, 32, who failed to advance past the qualifiers, tweeted on Thursday.

“Def a bug going around [at the Open],” he added in a separate post.

Also on Thursday, Polish player Hubert Hurkacz, 26, struggled on the court and was treated by medical staff before ultimately falling to Jack Draper, the New York Times reported.

During the match, sniffles, coughs and other signs of illness were heard throughout the tennis grounds, the outlet added.

Posted in Curiosity, Ethiopia, Health, Sports - ስፖርት | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

በበሽታ ሁሉ እና በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ወሊቃነ መላእክት መናብርት ቅዱስ ሩፋኤል ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 7, 2023

በየዓመቱ ጳጕሜን ፫ ቀን የሊቀ መላእክት የቅዱስ ሩፋኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አብያተ ክርስቲያናት፣ በልዩ ልዩ መንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ይከበራል፡፡

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሩፋኤል ከከበሩት ቅዱሳን መላእክት ሦስተኛው ነው፡፡ “ከከበሩ ከሰባቱ አለቆች አንዱ አለቃ እኔ ሩፋኤል ነኝ” እንዲል /ጦቢት ፲፪፥፲፭/፡፡

ያለማቋረጥ ፈጣሪያቸውን ልዑል እግዚአብሔርን ከሚያመሰግኑ ቅዱሳን መላእክት መካከል አንዱ መልአከ ጥዒና ወሰላም /የሰላምና የጤና መልአክ/ የሚባለው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሩፋኤልየሚለው የስሙ ትርጓሜ ደስ የሚያሰኝ፣ ቸር፣ መሐሪ፣ ቅን የዋህ ማለት ነው፡፡

የሰው ልጆች ከተያዙበት የኀጢአት ቁስል ይፈወሱ ዘንድ በአማላጅነቱና በጸሎቱ የማይለይ መልአክ ነው፡፡ “በበሽታ ኹሉ ላይ በሰው ልጆችም ቍስል ላይ የተሾመው ቅዱስ ሩፋኤል ነው” በማለት ሄኖክ ከእግዚአብሔር መልአክ ያገኘውን የምስክርነት ቃል ጽፏል /ሄኖክ ፲፥፲፫/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል በሰውነታችን ላይ የሚወጣውን ደዌም ኾነ ቍስል ይፈውስ ዘንድ ከልዑል እግዚአብሔር ሥልጣን ተሰጥቶታል፡፡ “በሰው ቍስል ላይ የተሾመ ከከበሩ መላእክት አንዱ ቅዱስ ሩፋኤል ነው” እንዳለ ሄኖክ /ሄኖክ ፮፥፫/፡፡

ለቈሰሉ ፈውስን የሚያሰጣቸው ለማኅፀን ችግር ኹሉ ለሴቶች ረዳታቸው ቅዱስ ሩፋኤል ነው፡፡ ሴት በፀነሰችበት ወቅት ቅዱስ ሩፋኤል አይለያትም ሕፃኑ ዐርባ ቀን ሞልቶት፣ በማኅፀን እያለ ተሥዕሎተ መልክዕ” (በ አርአያ መልኩ መሳል) ከጀመረበት ቀን አንሥቶ እስከሚወለድበት ቀን ድረስ ቅዱስ ሩፋኤል አይለየውም፡፡ በወሊዳቸው ቀን ሴቶች ከሚደርስባቸው ጭንቀትና ሕመም ስሙን ጠርተው ይማጸኑታል፡፡ ፈታሔ ማኅፀን ነውና ቅዱስ ሩፋኤልም ጭንቀታቸውን ያቀላል፡፡

አስማንድዮስ የተባለ ጋኔን በወለተ ራጉኤል ላይ አድሮ ባሎቿን እየገደለ ቢያሰቃያት ቅዱስ ሩፋኤል ጋኔኑን አስጨንቆ አስወጥቶላታል /ጦቢት ፫፥፰-፲፯/፡፡ ቅዱስ ሩፋኤል “ዳግመኛም እግዚአብሔር ሩፋኤልን፣ አዛዝኤልን እጁን እግሩን አስረህ በጨለማ ውስጥ ጣለው አለው” ተብሎ እንደ ተጻፈ /ሄኖክ ፫፥፭-፯/ ለቃየን ልጆች ሰይፍና ሾተል መሥራትን፣ የምንዝር ጌጥ ማጌጥን፣ መቀንደብን ያስተማረ አዛዝኤል የተባለውን ጋኔን በእሳት ሰይፍ እየቀጣ በረቂቅ አስሮ ወደ ጥልቁ የጣለው ይኸው መልአክ ቅዱስ ሩፋኤል ነው /ሄኖክ ፪፥፲፰/፡፡

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »