Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • January 2013
    M T W T F S S
     123456
    78910111213
    14151617181920
    21222324252627
    28293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for January 18th, 2013

Happy Epiphany — እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 18, 2013

ሌላ ጊዜ የምመለስበት፡ ወቅታዊና አንገብጋቢ አጭር የጥምቀት መልዕክት፡

  • አገር ቤት ያላችሁ ታታሪ መንፈሳውያን መሪዎች፣ አባቶች፤ ባካችሁ ቅድስት አገራችንን ለቃችሁ (ለስብሰባም ቢሆን)፡ በተለይ ወደ ሰሜን አሜሪካ መሄዱን አቁሙ 

  • ውጭ ያላችሁ ታታሪ ኢትዮጵያውያን መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች ባላችሁበት ቦታ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ የማትሠሩ ወይም የተዋሕዶ ክርስትናንን ለአገሬው የማታስተዋውቁና ተመሳሳይ ኃላፊነት የሌላችሁ ከሆነ፡ ባካችሁ ወደ አገራችሁ ቶሎ ተመልሳችሁ ነፍሳችሁን ከአውሬው ወጥመድ አድኑ

በ ሊቀ ካህናት ክንፈ ገብርኤል አልታየ

የጥምቀት ዓይነት ልዩ ልዩ ነው፤ አማናዊ ጥምቀት ግን፡BerukTimket

  • በውሀ

  • በመንፈስ ቅዱስ

  • በሥቃይ

መጠመቅ ነው። (ሉቃ. 3161250)

የዮሐንስ ጥምቀት ወደፊት የሚመጣውን ያመለክት ነበር (ማቴ. 311-12)

የክርስቲያን ጥምቀት የተፈጸመውን የክርስቶስን የአዳኝነት ሥራ ያሳስባል (ሮሜ. 63-4)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በበዓለ 50 ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተደረገ (የሐዋ. 1521-4)

ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምእመናን ሁሉ አንድ አካል እንዲሆኑ በመንፈስ ይጠመቃሉ። (1ቆሮ. 1213) “እለ ጥሙቃን በመንፈስ ቅዱስ” (ቀሌምንጦስ)

ክርስቶስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ መውረዱ ለእኛ ጥምቀት ምስጢር ማስረጃ ነው። (ሉቃ. 321-22፣ የሐዋ. 238፣ ቲቶ. 35)

የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የውሀን ጥምቀት ሊከተል ይችላል። (ዮሐ. 84-171044-48)

ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ ያደርገናልና በዚህ መሠረት ከኅጢአት እንደ ተለየን ቈጥረን በአዲስ ሕይወት እንኖራለን (ሮሜ. 61-11) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 245 ተመልከት።

ጌታ እየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት ዋና ምክንያት፦

  • በጥምቀቱ ጥምቀተ ክርስትናን ሊመሠርትልን

  • ውሀውን ሊባርክልንና ሊቀድስልን

  • ከእግዚአብሔር የመወለድን ጸጋ ሊያድለን

  • ስርየተ ኅጢአትን ሊሰጠን

  • ጽድቀ ተስብኦንና ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽም

ነው።

ዛሬ በቤተ ክርስቲያን በሚፈጸመው ምስጢረ ጥምቀት አማካኝነት ከጌታ ጐን በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከኅጢአትና ከመርገም እንድናለን። ማንም ሰው ሳይጠመቅ የሠራው ኅጢአት የሚሠረይለት በጥመቀት ነው። ሁለተኛም በጥምቀት ከእግዚአብሔር ይወለዳል።

በዓለ ጥምቀት

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው ጥር ፲፩ ቀን ከሌሊቱ ፲ ሰዓት ላይ ነው። በዓለ ጥምቀት በልሳነ ዮናኒ ወይም በግሪክኛ ቋንቋ ኤጲፋኒያ (Epiphania) ይባላል። ኤጲፋኒያ ማለት አስተርእዮ (መገለጥ) ማለት ነው። ምክኒያቱም በዚህ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ስለ ተገለጠ ነው። አብ በሰማይ ሆኖ ይህ የምወድደው ልጄ ነው፤ብሎ መሰከረ። ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቆሞ በዮሐንስ ሲጠመቅ ታየ፤ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ተቀምጦ ታየ።

ለዚህም መጥምቁ ዮሐንስና ወንጌላውያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀና ከውሀው በወጣ ጊዜ ያን ጊዜ ሰማይ ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በላዩ ላይ ተቀመጠ፤ ቃልም ከሰማይ መጣ፤ ይህ የምወድደው ልጄ ነውብሎ መስክሩዋል በዚች ዕለትም ጌታችን ራሱን ገልጦአል፤ ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር፡ ግን በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ። እነሆ የዓለምን ኅጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግብሎ ዮሐንስ እንደ መሰከረ ለምሥዋዕት ቀረበ እኔ አላውቀውም ነበር። ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁአለ ዮሐንስ።

ዮሐንስ ክርስቶስን ከእስራኤል ጋር በማስተዋወቅ ያጠምቅ እንደነበረ እኛም አምላክነቱን፥ መድኅኒትነቱን ከአይሁድና ከተንባላት፥ ከአሕዛብና ከአረማውያን ጋር ለማስተዋወቅ ወንጌልን እንስበክ፥ ጥምቀተክርስትናንም እናጥምቅ፣ ምስጋና ለእግዚአብሔር!

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »