Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • February 2013
    M T W T F S S
     123
    45678910
    11121314151617
    18192021222324
    25262728  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Archive for February, 2013

Abune Mathias is The 6th Patriarch of The Ethiopian Orthodox Church

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 28, 2013

(FILEminimizer) AbounaMathias

In the Vatican, Non HABEMUS PAPAM, in Ethiopia, HABEMUS PAPAM!!

It is with gratitude to God that we congratulate on the election of Archbishop of Ethiopian Orthodox Tewahdo Church (EOTC) in Jerusalem, Abune Mathias as the 6th patriarch.

We were aware of your striving towards unity and love among the Ethiopian and other Christian communities in the Holy land, and we pray that your election, in these uncertain times, will be strong in the quest for the welfare and strength of our Mother Church and its ever dedicated flock

We pray for peaceful and harmonious time to accompany our Holy Church

May God multiply the fruits of love entrusted to you. “Blessed are the meek, for they will inherit the earth” (Matthew 5:5).

Axios! Axios! Axios!

የኢትዮጵ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ መረጠች

ዛሬ ከጧት ጀምሮ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ በተደረገው ሂደት መሠረት 806 መራጮች ድምጽ የሰጡ ሲሆን ከሰዓት በኋላ በተደረገው ድምጽ ቆጠራ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ገዳማት ሊቀ ጳጳስ በ500 ድምጽ በመመረጥ የመጀመሪያውን ድምጽ በማግኘት 6ኛው ፓትርያርክ ሆነዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ 39 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ 98 ድምጽ፤ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል 70 ድምጽ በማምጣት ምርጫው ተጠናቋል፡፡ አንደ ድምፅ በትክክል ባለመሞላቱ ውድቅ ሆኗል፡፡

ፓትርያርክ ሆነው የተመረጡት ብፁዕ አቡነ ማትያስ በመጨረሻ ባስተላለፉት መልእክት “ከእግዚአብሔርና ከሕዝበ ክርስቲያኑ የተሰጠኝን አደራ ለመወጣት ከብፁዓን አባቶች፣ ካህናትና ከምእመናን ጋር አብረን ስንለምንሠራ ሥራው የቀለለ ይሁናል ብዬ አምናለሁ” ብለዋል፡፡

ምንጭ

 __

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | 2 Comments »

ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መገሰጽና ለእነርሱ መጸለይም ይገባናል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2013

ዳኛው ፈራጁ ሁሉን ነገር የሚያየው እርሱ ንጉሡ ክርስቶስ ብቻ ነው!

በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።”[ትንቢተ ሶፎንያስ.118]

ባዕዳውያኑ የአገራችን ጠYonasNAsaላቶች ምንም ሳናደርጋቸው፤ ሳንደርስባቸው በሕዝባችን ላይ ያደረሱት በደል በዓይነቱ በጣም አስከፊ በመጠኑም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡ ለሃሳብ እንኳ የሚያንገፈግፍ ነው። አንመኝላቸውም፡ ግን የፍትህ አምላክ፡ ኅያሉ ፈጣሪያችን መቅሰፍቱን ያወርድባቸዋል፤ ሌላ አማራጭም ያለ አይመስልም።

በመጪዎቹ የጾምና የጸሎት ቀናት እንድንድንና እንዲድኑ ልዩውን ጸሉት ልናደርስ ይገባናል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅም በክህደታዊ መንገድ ከጠላቶች ጋር በመመሳጠርና በመተባበር ወንድሞቹን፣ እህቶቹን እንዲሁም ልጆቹን ለአውሬው አሳልፎ ለሚሰጠው ኢትዮጵያዊጊዜው ሳይረፍድ እንጸልይላቸው፤

ማንነታቸውን ክደው የክርስቶስ አምላክን ልብ ለሚያቆስሉት፡

  • ለተታለሉት የባዕዳውያን እምነት ተከታዮች ሁሉ እንዲድኑ ፀሎት እናድርስላቸው

  • የክርስቶስን ደናግልት ህፃናት ለባእዳዊ ሰዶማውያን ለሚያስረክቡት እንዲድኑ እንጸልይላቸው

  • የክርስቶስ ልጆች እንዳይበዙ የእህቶቻችንን ማሕፀን ለሚመርዙት ጨካኝ ውገኖች እንዲድኑ እንጸልይላቸው

  • በክርስቶስ ስም የተጠመቁትን እህቶቻችንን ለአረማውያኑ ጣኦትአምላኪ ባዕዳን አሳልፈው ለሚሰጡት የዘመኑ ጂፋሮች እንዲድኑ እንጸልይላቸው

  • የክርስቶስን ገናናነትና ክብር ለመቀነስ የናዝሬትን፣ የደብረ ዘይትንና የመሳሰሉትን የኢትዮጵያ ቦታዎች ስም በዘፈቃድ ለሚቀይሩት ምስጋናቢሶች እንዲድኑ እንጸልይላቸው

  • ውጩ አገር ሆነው፡ ቸሩ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ ቸል በማለት እራሳቸውን በስንፍና የስድብና ጥላቻ ማዕበል ውስጥ ለከተቱና ወገናቸውንና ቅድስት ቤተክርስቲያናቸውን በድፍረትና በትዕቢት ለሚያዋርዱት እንዲድኑ ጸሎቱን እናድርስላቸው።

ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ[ሉቃስ 21:16]

ኒፈሌያዊ የደመና መጋረጃዎች ባገራችን ሰማያት ላይ ተዘርግተዋል፡ ነገር ግን የጽዮን ልጆች በእግዚአብሔር ብርኃን የተከበቡ፡ በፍቅሩ የታጠሩ ናቸውና የእርሱ ኃይል ይጠብቃቸዋል፡ የሚያሸነፋቸውም ኅይል የለም። የቃልኪዳኑ ልጆች ያሉበት ቦታ ሁሉ አምላካችን ስላለ ሁሉ ነገር ጥሩ ነው፡ ቸር ነው፤ በቤቱ ለዘላለም ለመኖር ተመርጠዋልና።

የቅዱሳን አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን፡ ልክ እንደ ክርስቶስ፡ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት በአሣ ሆድ አሳድሮ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ እንዳዳነው እኛንም ከመጥፎ ነገር ይከላከለን ከመቅሰፍት ይጠብቀን። አሜን!

ትንቢተ ዮናስ

ምዕራፍ አራት

የተናገረው ቃል ስላልተፈጸመ

ዮናስ ተቆጥቶ እያጕረመረመ

እንደዚህ እያለ ጸለየ ወደ አምላክ

እኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክ

አስበህ ብታዘኝ ይህንኑ ዐውቄ

ወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄ

ምሕረትህ የበዛ መሓሪና ታጋሽ

በደል የምትረሳ ከቍጣ ተመላሽ

የቍጣህን ያህል ምሕረትህ የጠና

መሆንክን ጥንቱንም እኔ ዐውቃለሁና

እኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበር

ሐሰት ተናግሬ የማይሆን ነገር

አልፈልግምና ቆሜ ለመኖር

ክከተማ ወጥቶ በምሥራቅ በኩል

ከወደ ዳር ሆኖ ነነነዌን ሊያስተውል

ምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስ

ሠርቶ ተቀመጠ አንድ ትንሽ ዳስ

እግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎ

ቅሉም አደገና ከፍ ከፍ ብሎ

የዮናስ ራሱ እንዲያገኝ ጥላ

ለፀሓዩ ንዳድ ሆነለት ከለላ

በዚህ በቅል አገር ዮናስን ደስ አለው

እንዲህ ቶሎ ደርሶ ስላገለገለው

እግዜር በማግሥቱ ጧት በማለዳ

ቅል የሚበላ ትል ፈጣሪ አሰናዳ

ትሉ ቅሉን በልቶ በፍጥነት ደረቀ

ፀሓይ ወጣችና ግዜው በጣም ሞቀ

እግዜር አዘዘና ትኩስ ነፋስ መጣ

የሚከለልበት መጠጊያ ስላጣ

ቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለው

ዮናስ ተበሳጭቶ ላምላክ እንዲህ አለው

እንደዚህስ ሆኜ ቆሜ ከምኖር

እባክህ ግደለኝ ልሙት ለቀበር

ደረቀብኝ ብለህ ይህን ቅል ለማጣት

እውን ይገባል ወይ ያንተ አሁን መቆጣት?

ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስ

በንዴቴ ብዛት እስክሞት ድረስ

አዎን ይገባኛል መናደድ መጤስ

እግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትል

ይህ ያልለፋህበት ያልደከምህበት ቅል

አንተ ስትናደድ ፈጥሬአት እኔማ ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማ

መቶ ሓያ ሺህ ነው የሕዝብዋ ብዛት

ለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንለት

ብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታ

ለዮናስ ነገረው የምሕረቱ ጌታ

ለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይድረስ

ከክቡር አቶ ከበደ ሚካኤል የቅኔ አዝመራ ከሚለው የተወሰደ (1956)

ከምዕራፍ 1-3 PDF እዚህ

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | Leave a Comment »

ኪዳነ ምሕረት

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 23, 2013

በንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ

KidaneMeheretMariamእግዚአብሔር ወልድ፡ ኢየሱስ ክርስቶስተብሎ ከቅድስት ድንግል ማርያም በመወለዱ የተገኘው ዘለዓለማዊ የምሕረት ቃል ኪዳን ኪዳነ ምሕረትይባላል። የዓመቱም በዓል በዛሬው የካቲት ፲፮ ቀን ይውላል።

የመጀመሪያዎቹ አዳምና ሔዋን የፈጣሪያቸውን ፈቃድ መተላለፋቸው በየራሳቸውና በልጆቻቸው ላይ የዲያብሎስን ገዢነት የኃጢኣጥትን ቀንበርና የሞትን ፍዳ አመጣባቸው። በየዘመናቱ ለደጋጎች ልጆቻቸው የተሰጡት አምላካውያት ቃል ኪዳናትና የ፭ሺ፭፻ ዓመታት ንስሓቸው ግን እግዚአብሔር ወልድን ከሰማየ ሰማያት ልዕልናው ወደምድር አውርዶ ሰው ለመኾን አበቃው፡ መለኮታዊውም ፈቃድ በመጨረሻዎቹ ኣዳምና ሔዋን፡ በኢየሱስ ክርስቶስና በድንግል ማርያም ስለተፈጸመ፡ ይህ ፍቅርና ርኅራኄ የሰው ልጆች የእግዚአብሔር ልጆች የሚኾኑበትን የመጨረሻውን ክብር አቀዳጃቸው፤ የኃጢኣት ሥርየትንና የትንሣኤ ሕይወትን አስገኘላቸው። ይህ፡ የልጅነት ጸጋ ይህ የሥርየት ነጻነት ይህ የትንሣኤ ክብር ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖር ዘንድ በመለኮታዊ የምሕረት ቃል ኪዳን ለአንዴና ለመቼውም ጊዜ ታተመ!

ማኅተሙም፡ እግዚአብሔር ወልድ ከድንግል ማርያም፡ ከሥጋዋ ሥጋን፡ ከነፍሷም ነፍስን ነሥቶ የተዋሓደውና በመስቀል ላይ የሠዋው ዛሬም እኛ እውነተኞች ኢትዮጵያውያን በንስሓ ነጽተን ከቅዳሴ ጸሎት በኋላ የምንቀበለው ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው። በእርሱ በልጇ

በኪዳነ ምሕረት ክብረ በዓል መናፍቁ ተጋለጥ

በኪዳነ ምሕረት ቃል ኪዳን የተያዘውን መናፍቅ ስናይ የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆነ ሰው ሁሉ በዘመናችን በተለቀቀው አደገኛ ተኩላ እንዳይበላ ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባው እንገነዘባለን።

የመምጣትህና የዓለሙ መጨረሻ መቼ ይሆናል? በማለት ሐዋርያት ክርስቶስን በጠየቁት ጊዜ ክርስቶስ የመለሰላቸው መልስ፦ ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ ብዙዎችንም ያስታሉየሚል ነበር ማቴ. 24 . 38 ይህ አምላካዊ ቃል ይፈፀም ዘንድ አስመሳዩ ተኩላ በጎቻችንን ሊነጥቅ ሲያደባ ነሐሴ 15 16 አጥቢያ ከሌሊቱ 5 ሰዓት ላይ በሐመረ ኖህ ኪዳነ ምሕረት ገዳም ቅጥር ግቢ ውስጥ ተይዟል።

ይኽ ተኩላ በአዲስ አበባ ውስጥ ያደገ ሲሆን ከሰባዊነት ወደ ተኩላነት ከተለወጠበት ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባና አካባቢዋ በደብረ ዘይት፣ በናዝሬት፣ በቁልቢና፣ በደብረ ሊባኖስ በመሳሰሉት እየተገኘ ዓላማውን ለማሳካት ሲሯሯጥ መቆየቱን በተያዘበት ዕለት ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ሰጥቷል።

ይኽ ተኩላ ርካሽ ዓላማውን ለማሳካት አመች ነው ተብሎ እሱን ከመሳሰሉት እበላ ባዮች የተሰጠው መመሪያ ምንና ምን እንደሆነ ሳይረዳ የሚሰብከው ልብስ የቤተ ክርስቲያናችንን የካህናት ልብስ በቀሚሱ ላይ ካባ በመደረብ በአንገቱ ላይ መስቀል ማንጠልጠል በተጨማሪ ዳዊትና የመሳሰሉት መጻሕፍትን ከነማሕደራቸው በግራና በቀኝ ጎኑ ማንጠልጠል ሆኖ ቁጥጥሩ በላላበት ቦታ ዓላማውን ማራመድ እንደነበር በወቅቱ ሳይሸሽግ ተናግሮአል።

ወዲያውኑ ይኽ አስመሳይ ተኩላ በተለያዩ የሕዝብ ብዛት በሚታይበት በሸንኮራው ጠበል ተገኝቶ ዓላማውን ሲያመቻች እንደነበረ የተደረሰበት መሆኑ ተገልጿል።

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , | 2 Comments »

The Malnourished Sudanese Baby and The Vulture

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 21, 2013

South Africa is in the air, these days. Two weeks ago, when the South African athlete, Oscar Pistorius was jailed for involving himself in a shooting incident against his girl friend, everyone here in the West was talking about the degree of crime among the black population of the country, and that Oscar could only have ‘reacted’ to defend himself from an intruder, who, of course, must be “damn black” burglars. Now, over night, what we hear is a different story, it was murder — namely, Pistorius murdered his girl friend, and the color of his skin is irrelevant.

DepopulationI never forget those sad days back in the 199os when I saw for the first time this horrific and haunting picture. There was no Internet back then, so the image got relatively little attention, yet, the picture captivated the Internet-absent world back in 1993.

The picture was shot by Kevin Carter, a South African photographer who won a Pulitzer Prize (arguably the world’s most famous and prestigious award for journalists) in 1994 for his most hated picture.

Carter’s photograph was of a young child in the Sudan, who was trying to get to a feeding center. But, as it was then reported, before she could get there, she collapsed in hunger. A vulture is in the background, waiting for the child to die.

This haunting photo came to represent the horror of the man-made famine in Southern Sudan which the world ignored for 40 years because South Sudanese are mostly Christians. Up to three million South Sudanese perished. The attention of the ignorant world was more evident when the arabized administration of Khartoum begun massacring its own “black” Muslim populations in the Darfur region of the Sudan.

Since South Sudan gained independence in 2011, the climate in Sudan has even been more hostile towards Christians. In the past two weeks, Sudanese authorities have detained over 55 Christians, following a media campaign against Christianity and the closing of Christian schools in Sudan, which is sometimes called North Sudan.

Coming back to the picture, in 1993, it made the front page of The New York Times and quickly became the symbol of Sudan’s plight, fueling public outrage over the famine ravaging the country.

Carter’s photograph emphasizes the power of the image, and of those who wield it. With this simple photograph, multiple emotions were evoked from those who saw it: horror at the fate of the people in the Sudan; anger at how people can still die of hunger at a time when excess and consumption have become the fashion; awareness of what was happening in the other parts of the world; a need to reach out and help.

The photograph affected the photographer too. Some two months after winning the Pulitzer Prize in May 1994, Kevin Carter committed suicide by carbon monoxide poisoning. He was 33.

Everyone wanted to talk to the South African snapper about the little girl captured in such a powerful image.

Carter responds he’d chased the vulture away and then sat under a tree and wept. Of the story after that picture was taken, that’s the only part he claims to know.

The Truth about the malnourished baby and the vulture

Two years ago, the Spanish daily, El Mundo went down to South Africa to make a research on the subject, and came back with the following, rather surprising, report.

In 2011 The Spanish newspaper ‘El Mundo’ wrote an article about the truth, the real story behind the photograph. It showed that if one observes the high resolution picture, it can be seen that the baby, whose name was Kong Nyong, is wearing a plastic bracelet on his right hand, one issued by the UN food station. On inspecting it, the code ‘T3′ can be read, This means that the baby had survived the famine, the vulture and the tragic public promotions and predictions.

El Mundo’s’ reporter, Ayod, traveled to the village in search of the whereabouts of the child. His search led him to the boy’s family. The boy’s father confirmed his name and said he was a boy and not a girl as previously believed. He told the reporter that Kong Nyong recovered from the famine and grew up to become an adult, however, he said, he had died four years prior to the reporter’s visit.

__

Posted in Curiosity, Media & Journalism | Tagged: , , , , , , , , , | 1 Comment »

Elder Paisios’ Amazing Prophecies About Constantinople

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 20, 2013

The famous Greek Monk, Elder Paisios, who was recently mentioned by the Wall Street Journal, made the following remarkable, and likely-to-happen prophesies about the City of Constantinople (modern day Istanbul).

“The Russians will soon take Turkey. The Chinese will cross the Euphrates. Providence tells me that many events will happen: The Russians will take Turkey and Turkey will disappear from the world map because a third of the Turks will become Christians, another third will die in the war and another third will leave for Mesopotamia.

The Mid-East will become a theater of a war in which the Russians will take place. Much blood will be spilled. The sign that this event is approaching will be the destruction of the Mosque of Omar, for its destruction will mark the beginning of work by the Jews to rebuild the Temple of Solomon, which was built on the same spot. There will be a great war between Russians and Europeans, and much blood will be spilled.

Greece won’t play a leading role in that war, but they’ll give her back Constantinople. Not because the Russians adore the Greeks, but because no better solution will be found. The city will be handed over to the Greek Army even before it has a chance to get there.”

Short Biography of Elder Paisios of the Holy Mountains

• Elder Paisios was born in Farasa in Cappadocia, Asia Minor on 25 July 1924.OB-VN687_GKMYST_GV_20121202201332

• He was baptised by St Arsenios the Cappadocian on 7 August 1924.

• After the Greco-Turkish War he emigrated with his family to Epirus, Greece in September 1924.

• He worked as a carpenter in Konitsa, Epirus after completing elementary education.

• In 1945 he was drafted into the army and served during the years of the civil war until 1949 as a radio operator.

• In 1949 he went to Mount Athos to become a monk. He stayed for a few months and returned to his family because his mind was on his sisters who were still unmarried.

• In 1950 he went back to Mount Athos and in 1954 he was tonsured a monk.

• In 1956 his spiritual father, Elder Symeon at Philotheou Monastery gave him the name “Paisios”.

• In 1958 he was asked to go to Stomio in Konitsa.

• In 1962 he went to Sinai for 2 years.

• In 1964 he returned to Mount Athos.

• In 1966 he founded the Monastery of St John the Theologian in Sourote, Thessalonki, Greece which he also guided spiritually for 28 years, from 1967-1994 – which also contains the miraculous relics of St Arsenios of Cappadocia.

• He fell asleep on 12 July 1994.

Elder Paisios’s GiftsMtAthos

While still alive, Elder Paisios was considered a saint by many. There are hundreds of signed witnesses of miracles he performed.

On the Holy Mountain he practised asceticism. The gifts God adorned him with were many:-

(a) Gift of healing – he healed many people from diverse illnesses, cancers, paralytics from birth, etc.

(b) Gift of taking out demons – from people.

(c) Gift of foreknowledge – to many he had told events which would happen to them in the future on a personal level but also prophesised future developments in history.

(d) Gift of clairvoyance – he knew the heart of each person deeper and more clearly than the person himself. For this reason, he also counselled correctly and with precision and each one listened to the word which he needed to hear.

(e) Gift of discretion of spirits – he knew with exactitude if a spiritual event was from God or from the devil who was trying to deceive and lead astray.

(f) Gift of discretion of God’s will – he knew in each case what God’s will was and if he ought to reveal it or not.

(g) Gift of theology – from the many spiritual experiences he had with saints, with angels, with the Virgin Mary, but also with visions of uncreated light, not once, but many times. He had truly become a theologian and deeply knew God’s mysteries.

(h) Gift of love – he had love for everyone, without limits, with absolute self-sacrifice. A love on fire, sweet, almighty, divine. It was this love which gathered people around him. Hundreds of people visited him daily in his cell. The elder gathered the pain, the agony and the problems of the people and gave a solution, joy and peace. He intervened miraculously with divine authority and solved the unsolvable. The Elder was a gift of God to people.

The Elder’s Teachings

MtAthos31. “Before you do something, think what Christ wants you to; then act accordingly. Ask for God’s guidance.”

2. “Do not look at what people do, or examine how, and why they do it.”

3. “Perverse thoughts separate men from God. Our aim is to totally submit our mind to the grace of God.”

4. “If one lives in the world of his pride, that is, his own thoughts, he is filled with illusions and he is in danger. He must ignore both positive and negative thoughts and always confess to his spiritual father, and obey whatever he tells him. He should only trust him and not in his own thoughts.”

5. “As long as man humbly thinks of himself, God’s grace remains with him and protects him.”

6. “In our days, people have lost control over their lives and they do not know what they are doing. They do not wish to be guided. They want to live undisturbed, following their own freewill, which will eventually bring them to total destruction. He becomes deceived. He experiences and interprets everything by using his own logic. Instead of God’s grace, human logic rules his life and his mind is in “confusion”.”

7. “If a passion rules our lives it is because we consent to it. If we remain enslaved by it, we do it because we love our passion and want to be a slave to it. The moment we hate the passion and direct our love towards to God, we immediately become free.”

8. “”Purification” requires the soul to be pure and clean from our own will; to abandon our own will to the will of God. To humble our will and elevate God’s will.”

9. “”Obedience” means not to have a will at all and obey your spiritual father.”

10. “”Philotimo” is the reverent distillation of goodness, the radiant love of the humble man bereft of himself, but a heart full of gratitude to God and his fellow man, and because of spiritual sensitivity he tries to repay even the slightest good which others do to him.”

11. “A person who asks for miracles, in order to believe in God, lacks dignity. If God wishes he could make everyone believe with miracles. But he does not do so because he does not want to exercise force on man’s free will; man will then end up believing in God, not out of gratefulness or due to God’s excessive kindness, but due to his “supernatural power”.”

12. “Our saints had divine justice instead of human justice. When we neglect our spirituality and instead take to court people who treat us unjustly, we consider our material possessions and our pride more valuable than the salvation of our soul.”

13. “Divine Providence is the care that comes from God. He looks after the tiniest detail of the smallest of his creatures. His providence will take care of everything in our lives if we reject everything and become wholly and undistractingly devoted to his love.”

14. “We should constantly and unceasingly repeat The Jesus Prayer. Only the name of Jesus must remain inside our heart and mind. When we neglect our prayer, that is our communication with God, then the devil finds the chance to confuse us with negative thoughts.”

15. “When God sees that we are proud and arrogant, he allows for the presence of afflictions and temptations in our life. He will take them away from us when He sees that we have humbled ourselves.”

16. “Hell and paradise do exist. Our soul experiences both, as they are spiritual states and not places where fires are burning, or birds are singing. The soul experiences fear, terror, agony, anxiety, despair and disappointment. If it has been separated from God in this life. It experiences hell – a torturing experience. Hell is not a place where souls are boiling inside cauldrons, but rather a state is which the soul will be found after the separation from the body. Then, you will realise the truth and suffer tremendously for not believing in Christ and his preaching on life after death. The soul will more intensively feel the guilt for its actions and experience these unpleasant feelings of fear, terror, despair, etc. It becomes a place of hell. The same applies to paradise as well, your soul is filled with joy and love.”

The teachings outlined above are only a short summary of Elder Paisios’s spiritual knowledge and wisdom. Christians who take the time to read this book and put Elder Paisios’s counsels into practice will benefit significantly. “Blessed are they who live the word and not those who only hear it or read it.”

Source

P.S: The Image shows Mount Athos or Agion Oros, as it is locally known, which is the oldest surviving monastic community in the world. It dates back more than a thousand years, to Byzantine times. It is a unique monastic republic, which, although part of Greece, it is governed by its own local administration.

_

Posted in Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , | 16 Comments »

አውሬው ጥርሱን ለሶማሊያዎች ሰጥቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 17, 2013

YawurewMenfes

ጀግናው ኢትዮጵያዊ፡ አፄ ቴዎድሮስ በዘመናቸው፡ በመካከለኛው ምስራቅ፡ በሰሜንና ምስራቅ አፍሪቃ ኃያል ከነበሩት ከኦቶማን ቱርኮች ጋር ይዋጉ ነበር። ታዲያ አፄ ቴዎድሮስ፡ መቼም እንግሊዞች ክርስቲያኖች ስለሆኑ ከቱርክ ይልቅ እኔን ይደግፋሉ በማለት ለብሪታኒያ ንግሥት የጦር መሣርያ እንዲልኩላቸው ከስጦታ ጋር በተደጋጋሚ ደብዳቤ ልከዋል። ነገር ግን እንግሊዝ ከፈረንሳይ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለመቀራመት ዕቅድ ስለነበራት ሁለት መቶ የሚሆኑ አውሮፓውያን ያሉበትና በቱርክ ጦር አዛዥ የሚመራ የግብፅ ቅጥረኛ በመርዳት በዓጼ ቴዎድሮስ ላይ ሴራ ስትጠነስስ ነበር።

ስለዚህ፡ የአውሮፓ ትብብርን የሚያበስር ደብዳቤ ይጠብቁ የነበሩት አፄ ቴዎድሮስ፣ ከእርዳታ ይልቅ ከታላቋ ብሪታኒያ በልዑኳ አንድ የፋርስ ምንጣፍ ስጦታ ተበረከተላቸው። ምንጣፉ ላይ አንድ የአውሮፓውያን ድጋፍ ያለው የአረብ ወታደር አንበሳ ሲገድል የሚያሳይ ምስል ነበረው። ቴዎድሮስ ከአረቡ ወታደር በላይ የሠፈረው የአውሮፓ ጦር ፈረንሳይ እንደሆነችና አንበሳው የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሆነ ተረድተው፡ ፈረንጆች ሁሉ በእርሳቸው ላይ እንደተነሱ በማሰብ ኢትዮጵያ የነበሩትን ፈረንጆች ያስሩ ጀመር።

ከጥቂት ዓመታት በፊት፡ ሞሀመድ ፋራ ወይም ሞ ፋራበመባል የሚታወቀውን ሶማሊያ ሯጭ የእንግሊዝን መለዮ ለብሶ ለረጅም ርቀት ሩጫ ሲሳተፍ፡ ብልጭ ብሎ ወዲያው የታየኝ፡ የኢትዮጵያ ሯጮችን ለማደናቀፍ እንግሊዝ ሆን ብላ አዘጋጅተዋለች የሚለው ፊልም ነበር። ለዚህም ምክኒያት አለው፤ በሩጫው ዓለም በመካከለኛውና በረጅም ርቀት ለብዙ ዘመናት ታዋቂ የነበሩት እንግሊዞች ከሚወዱት የሩጫ ውድድር ዘርፍ በመድከማቸውና በተለይ በኢትዮጵያውያን አትሌቶች (ፓውላ ራድክሊፍ) በመሸነፋቸው በጣም ስለተቆጩና ስለቀኑ እንደምን ብለው ፓውላ ራድክሊፍን ለማራቶን በማብቃት ክብራችንን አስመለስን አሉ።

እንግሊዞች፡ የኢትዮጵያን ጠላቶች ይወክላል ብላ የምታስበውን ሶማሊያዊ፡ ፋራን ወደ አሜሪካ በድብቅ በመላክ ልዩ ላብራቶሪ ውስጥ እንዲዘጋጅና የለንደን ኦሊምፒክስ ጀግና እንዲሆንላቸው አበቁት፤ በዚህም ኢትዮጵያውያኑን እንዲያዋርድላቸው ተጠቀሙበት ማለት ነው። ይህ የተለመደ የእንግሊዞች ባሕርይ ነው። ልብ ብለን ከታዘብን፡ ተሸናፊዎቹ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሞፋራን እንኳን ደስ ያለህ ለማለት ሲጠጉት ወራዳ በሆነ መልክ ነበር ተመናጭቆ የራቃቸው። ሞፋራ ያለ አበረታች መድኃኒት የ5 እና 10 ኪሎሜትሮች ርቀት አሸናፊ ለመሆን ብቃት የለውም። ባለ ብስክሌቱ፡ ላንስ አርምስትሮንግ ገብቶበት የነበረው የዶፒንግ ዋሻ ውስጥ ሞፋራም ደርሶ እንደነበር በጣም የሚያስጠረጥር ጉዳይ ነው። የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሞፋራን ለአመቱ ምርጥ አትሌቶች እጩነት አለማግባቱ የሚነግረን ነገር ይኖር? ለማንኛውም፡ ቀነኒሳ አንበሳ፡ ጎፈሬ ኃይሌ እያለ የገ/ሥላሴን ወኔ በመያዝ የሞፋራን ጥርስ በቅርቡ ማፈራረስ ይኖርበታል!

እንግሊዞች፡ ከአረቦችና ቱርኮች ጋር በማበር ሶማሊያዎችን እየተጠቀሙ በአገራችን ላይ ብዙ በደል ለዘመናት ሲፈጽሙ ቆይተዋል። አሁኑም፡ ትንሽ ለየት ባለና በረቀቀ መልክ ይህንኑ ቀጥለውበታል። ፀረኢትዮጵያ የሆኑትም የቢቢሲ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎች ምንጮቻቸውም ከእንግሊዝ ሶማሌዎች እና ቢቢሲሶማልኛውስጥ ነው። ለዚህም ነው በኢትዮጵያ ሽብር የሚፈጥሩ ሶማሊያውያን ቡድኖች ጽ/ቤቶቻቸውን በእንግሊዝ ለመክፈት የተፈቀደላቸው። ከመቶ ዓመታት በፊት፡ በእነ አፄ ቴዎድሮስ ዘመን፡ ስልክ፣ ራዲዮ፣ ቴሊቪዥን ወይም ኢንተርኔት ስላልነበሩ መሪዎቻችንም ሆኑ ሕዝባችን በአገራችን ላይ የሚጠነሰሰው ሤራ ምን ሊመስል እንደሚችል ለማወቅ እድሉ አልነበራቸውም። አሁን ግን አብዛኞቹን ነገሮች በግልጽ ማየት ስለሚቻል፡ ዝም ተብሎ ሊታለፍ አይገባም፤ እንደገና መታለልም የለብንም።

አደጉ በሚባሉት አገሮች፡ በመንግሥት፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በባንኮች፣ በኢኮኖሚና ሕግ ተቋማት እንዲሁም በወሬ ማሠራጫ ዘዴዎች ቁልፍ ቁልፍ የሆኑትን ቦታዎች የያዙት የ68ቱ ትውልድ (1968) በመባል የሚታወቁት አመጸኛ ኮሙኒስቶች፣ ኢአማንያንና ሰዶማውያን የሆኑት ናቸው። እነዚህ ኃይሎች ተጠሪነታቸው ለዲያብሎስ በመሆኑ፡ ማንኛውንም ክርስቶሳዊ የሆነ ኃይል እንደጠላት በመቁጠር የትግል ዘመቻቸውን ቀስ በቀስ ማካሄድ ከጀመሩ ቆይተዋል። አሁን በምዕራቡ ዓለም እየታየ ያለው ክስተት፡ ልክ በሌኒን ጊዜ የቦለሸቪክ አብዮተኞች ሲያሳዩት የነበረውን ዓይነት ባሕርይ በድጋሚ ያንጸባርቃል። ቦልሸቪስቶች በሃይማኖት ላይ በተለይ የሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ላይ ነበር በቅድሚያ ጦርነትን ያወጁት። ቦልሸቪስቶች በዚያን ጊዜ እስያውያንን እንደተጠቀሙት አሁንም የምዕራቡ ኢአማንያን ኒኦቦልሸቪስቶች ለትግላቸው ጥሩ መገልገያ መሣሪያ እንዲሆኗቸው አድርገው የወሰዷቸው እስልምናን እና ሙስሊሞችን ነው። እነ ቢቢሲ የሚነዙትን በጣም ዓይን ያወጣ፣ አሳዛኝና አደገኛ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ እዚህ እና እዚህ እንመልከት።

ለዚህም ነው ላለፉት40 ዓመታት ሙስሊም ከሆኑት አገሮች ብዙ ስደተኞች ወደ አውሮፓና አሜሪካ እንዲገቡ የተደረጉት። አቅሟ የማይፈቅድላት ኢትዮጵያም ብትሆን፡ ሶማሊያ ውስጥ ሰውሰራሽ የሆነ ብጥብጥ ከተፈጠረ በኋላ በሚሊየን የሚቆጠሩ ሶማሊያውያን ስደተኞችን ተቀብላ እንድታስተናግድ የተገደደችው ለዚሁ ሲባል ነው፤ በሶማሊያዎቹ በኩል ኢትዮጵያ የበለጠ ትዳከማለች የሚል አጀንዳ አላቸውና። እንዳሰቡትም፡ ሕዝባችን ታጋሽ ስለሆነ ሁኔታው በግልጽ አይታወቅም እንጂ፡ ደስ የማይሉ መንፈሳዊ ሁከቶች አልፎ አልፎ በሕዝባችን ላይ ይታይበታል።

የሶማሊያ ስደተኞች በሕዝቡ ላይ ሆነ በተፈጥሯዊው አካባቢ ላይ ከፍተኛ ጫና እያደረሱ መምጣታቸውን ይህ ሪፖርት ይገልጻል። ጸጥታንም በሚመለከት፡ አንድ አመቺ የሆነ ሁኔታ ከተፈጠረላቸው ለወደፊት በኢትዮጵያ ላይ ጥቃት ከሚያደርሱ ኃይሎች ጋር ቀድመው የሚሰለፉት ሶማሌዎችና የእምነት ወንድሞቻቸው መሆናቸውን ሁላችንም የምናውቀውና በታሪክም የታየ ክስተት ነው።

አውሮፓና አሜሪካም ላለፉት ዓመታት ሶማሊያውያን ስደተኞችን በብዛት ተቀብለዋል፤ ለምሳሌ ይህን ጽሑፍ እንመልከት። ባለፈው ሣምንት ስዊደን ሶማሊያውያን ስደተኞችን ወዳገሯ ለማምጣት የሚያስችል አንድ የአሠሪዎች ጽሕፈት ቤት አዲስ አበባ ለመክፈት መወሰኗን አስታወቀች፡ ይህን እንመልከት

ታዲያ ለምንድን ነው የሕዝቦቻችን ዋና ጠላቶች ለሆኑት እንደ ሶማሊያ፡ ግብጽና ፓኪስታን ለመሳሰሉት አጥፊዎች በሩን የምንከፍትላቸው?

መልሱ፡ እላይ እንደጠቀስኩት፡ የማይፈልጓቸውን የሕብረተሰብ ክፍሎች እንዲዋጉላቸው ነው። እነዚህም ክፍሎች፡ አይሁዶች፣ ክርስቲያኖች እንዲሁም እስላም ያልሆኑ ጥቁር ሕዝቦች ናቸው።

ቪዲዮው ላይ በግልጽ እንደሚታየው፡ እንግሊዝ ውስጥ ሶማሊያዎችና ፓኪስታኖች በቀጥታ የሚዋጓቸው እስላም ያልሆኑትን ምዕራብሕንዶች (ከካሪቢክ ባሕር አካባቢ ከ100 ዓመታት በላይ በእንግሊዝ የኖሩ ጥቁር ሕዝቦች) በአሜሪካ ደግሞ እስላም ያልሆኑትንና ለ400 ዓመታት ያህል እዚያ የሚኖሩትን ጥቁር አሜሪካውያን ነው። ነጮቹ በጥቁሩ ላይ ጽንስን በማስወረድ ወይም ሱስ የሚያስይዝ መድኃኒት ቀምሞ በመስጠት የፈለጉትን ግብ ለመምታት ስላልቻሉ አሁን በሶማሊያዎችና በፓኪስታኖች በኩል እንደገና እየሞከሩ ነው።

በቆዳ ቀለም ለሚያምን የሚከተለው በጣም ረባሽ ነው…..ቪዲዮው ላይ ሴትዮዋ ይህን ይላሉ፡

ሶማሊያዎችን እጠላቸዋለሁ፣ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው፣ ጦረኞች ናቸው፣ ስለ ሰላምና ፍቅር ምንም አያውቁም፣ ልብ የላቸውም፣ ለእኔ እንደ እንስሶች ናቸው...”

 

Massive Cafeteria Brawl Between Muslim and African-American Students

A food fight quickly turned into a brawl involving hundreds of students at a Minneapolis high school on Thursday, forcing police to use chemical spray to break up the melee. Students are saying the melee was the result of tensions between 8 percent of students who are Somali Muslims and the 20 percent who are African Americans.

Continue reading…

__

Posted in Ethiopia, Faith, Media & Journalism | Leave a Comment »

Saudi Arabia Arrests 53 Ethiopian Christians at Private Worship Service

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 16, 2013

My note: of course, no good-news over the Arabian desert, and, as usual, no word from the Christian-biased mainstream media! CNN, BBC & Co seem to be more concerned about the fate of an Indian rape-victim, gay rights or Burmese Muslim invaders than about the increasing persecution of “fellow” Christians. How ungrateful!

Saudis finances and supports the evil Wahhabi movements across the globe, including Ethiopia, brainwash weak citizens of Ethiopia to murder fellow Ethiopian Christians, kidnap little girls, burn down their Holy Christian Churches, and desecrate Bibles and Icons like the one we see in the above heart-breaking video from the year 2012. All these things are happening to the very same Ethiopian people who once gave asylum and protection to the followers of their Prophet. All soon be in our school books. Well, Christians have in history suffered much persecution and their faith has been strengthened in those times. So, whether they like it or not, many Christians will begin to demonstrate acts of power by faith – many non-Christians will come to faith in the Living God, through witnessing the acts of power, and through experiencing a manifestation of the presence of Eyesus Chrstos, through the Spirit of the Almighty Egziabher. Let’s pray for our persecuted brothers and sisters.

Saudi authorities on Feb. 8 arrested 53 Ethiopian Christians, mostly women, who were attending a worship service in the private, rented home of an Ethiopian believer in Dammam, the capital of the Eastern Province of Saudi Arabia, WEA-RLC has learnt from sources inside the Arab kingdom.

The Christians – 46 women and six men including three church leaders – were arrested at about 10 a.m. last Friday, a close relative of one of those arrested told WEA-RLC. The three church leaders – two of them women – were produced in an Islamic court in Dammam the same day when authorities alleged they were converting Muslims to Christianity, the source added.

Authorities are likely to release two of the Ethiopian Christians who have residential permits on Monday, and the others are expected to be deported.

Dammam, a center for petroleum and natural gas and all commerce in the eastern parts of the kingdom, is a large metropolitan, industrial area and a major seaport. However, religious freedom is not granted to the numerous visitors or expats in the region, like elsewhere in the nation. A Saudi girl who embraced Christianity and fled Dammam in September 2012 was granted asylum in Sweden last month, according to Al-Yaum newspaper.

In December 2011, Saudi authorities arrested 35 Ethiopian Christians, 29 of them women, for “illicit mingling,” after police arrested them when they raided a private prayer gathering in Jeddah. Of those arrested 29 were women, who were subjected to arbitrary body cavity searches in custody

Source

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | 3 Comments »

Leaders & Leadership — መሪና አመራር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 15, 2013

EthioCoronationአባ ሳሙኤል፡ መሪና አመራርበሚለውና በ2003 .ም የወጣው መጽሐፋቸው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ወቅታዊ ኹኔታ ያገናዘቡ ብልህነት የተሞላባቸውን ነጥቦች ለአንባቢው አቅርበዋል።

ከአድናቆትና ክብር የተሞላበት ምስጋና ጋር ከመጽሐፉ ቀንጨብ አድርጌ የሚከተሉትን ሓሳቦቻቸውን እንሆ አቅርቤአለሁ።

ምናልባት ለቤተክርስቲያናችን መሪነት በእጩነት ከቀረቡት አባቶች መካከል አባ ሳሙኤል አንዱ ከሆኑ የኔን ድምጽ አግኝተዋል።

6ኛውን ፓትርያርክ ለመምረጥ የሚካሄድበት ሣምንት ለእናት ኢትዮጵያ ልዩ ጸሎት የምናደርግበት የ ነነዌ ጾም ወቅት ስለሆነ መንፈስ ቅዱስ ስራውን እንዲሰራ፡ አባቶችንም እንዲረዳ በአንድነት ልባችንን ልናርገበግብ ይገባናል። ኢትዮጵያ የ6ኛውን ፓትርያርክ ፍለጋ በጀመረችበት ወቅት የሮማ ካቶሊክ ጳጳስም 112 ኛውን (100 + 6 + 6) ጳጳስ ለመምረጥ በመዘጋጀት ላይ ትገኛለች። አጋጣሚ? የሮማው መብረቅ፡ የሩሲያው በራሪ ኮከብ ምን እየነገሩን ይሆን? አባታችህ ሔኖክ በመጽሐፉ ላይ አሁን ጎርፍ ሳይሆን እሳት ነው ከላይ የሚመጣውያለን የመጨረሻው ዘምን ደርሶ ይሆን? እግዚአብሔር ይጠብቀን! የሚገርመውና የማይገርመው ግን ሊቃውንቱ አውቀነዋል፣ ዓይተነዋል፣ አግኝተነዋል በማለት ምድራችንን በ20ሺህ ኪሎሜትር ርቀት ዛሬ ማታ እንደሚያልፍ የተነበዩልንን ተለቅ ያለ በራሪ ኮከብ (Meteor > Metéora Eastern Orthodox Monasteries) በኩራት ሲጠባበቁ ይህ ያልታየው ሌላ ኮከብ ሹልክ ብሎ በሩስያ አረፈ። ይህም የሚያሳየው ምንም እውቀት የሌለን ግብዞች መሆናችን ነው። 10% ብቻ የሚሆነውን ነገር በዙሪያችን ማየት እንደምንችል ይህ ሌላ ትልቅ ማስረጃ ነው።

ለማንኛውም፡ ወደ መጽሐፉ፦

እግዚአብሔር አምላክ ታላላቅ ሥራዎችን ለማስፈጸም መሪዎችን እንዲመርጥና በእነርሱም አማካይነት ሥራውን እንደሚያስፈጽም ግልጽ ነው።

የማናቸውንም መሪ ተግባር በግልጽና በቀላል ኹኔታ ለመረዳት አገልግሎትን ለመስጠትና ሓላፊነትን ለመቀበል ዝግጁና ፈቃደኛ መሆንን መሠረት ማድረግ ይጠይቃል።

መሪነት ካለፈው ትውልድ ወደ አዲሱ ትውልድ መተላለፍ አለበት። ይሁን እንጂ የሽግግሩ ሒደት አባት ለልጁ የሚያደርገውን የሓላፊነት ሽግግር ዝግጅትና ጊዜ ሊጠይቅ ይችላል። የሚሴና የኢያሱ የመሪነት ቅብብሎሽም ለዚህ አባባል ዓይነተኛ ምሳሌ ነው። ንገር ግን እኛ ሰዎች ታሪክ እንማራለን እንጂ ከታሪክ አንማርም!” … መሪነት ማለት ሰዎች በፈቃደኝነት ለአንድ ዓላማና ግብ ለማሰለፍና የማግባባት ችሎታ ያላቸው ማለት ነው።

ኅይልና ሥልጣን

የመሪነትን ተግባር በአግባቡ ለማወቅ ኅይልና ሥልጣን (Power & Authority) የተባሉትን ጽንስሐሳቦች መገንዘብ ያስፈልጋል።

ኅይል (Power)

አንድ ሰው ሌሎችን ለመምራት ያለው ዕምቅ ችሎታ የሚታወቅበት (የሚገለጽበት) ሲሆን ዋና ዋና ዘዴዎቹም፦

  • በሕግ መሠረት በሚሰጡ ሓላፊነቶች
  • ግለሰቡ ለመግባባት የሚጠቀምባቸው ዘዴዎች
  • ለማስፈጸም በሚፈጥራቸው ጤናማ የሆኑ ጫናዎች
  • ከችሎታው፣ ከልምዱና ከእውቀቱ በሚመነጩ ኹኔታዎች

የመሳሰሉትን የሚያጠቃለል ነው።

. ሥልጣን (Authority)

አመራር ለመስጠትና በሥሩ ባሉት መሠረታዊ ሀብቶች ለመጠቀም የሚሰጥ ሕጋዊ መብት ማለት ነው።

ስለሆነም አንድ መሪ ተገቢውን የመሪነት ሚና ለመጫወት ኅይልና ሥልጣንን በየዐውዳቸው መጠቀም ይጠበቅበታል ማለት ነው። ሐዋርያው እንዳለው የእግዚአብሔርን ቤት እንዴት እንደምታስተዳድር ታውቅ ዘንድ እጽፍልሀአለሁ፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ የእውነት ዓምድና መሠረት የሕያው እግዚአብሔር ቤት ናት። (1. ጢሞ. 315)

የቤተ ክርስቲያን ኅልውና በሥራ የሚገለጥ ሃይማኖት ነው፤ የሃይማኖት ፍሬም እውነተኛ የአስተዳደር ፍቅር ነው። በቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርንና ሰውን ሊያስደስት የሚችለው ሥልጣንና ገንዘብ አይደለም። ሊሆን የሚገባውን ፍሬ ሊያፈራ የሚችለው በእውነት በተመደበበት የሓላፊነት ሥራ በታማኝነት ሲያገለግል ብቻ ነው።

ውጤታማ የኾነ አመራር መስጠት የሚቻለው የሰዎችን ፈቃደኝነት በተመረኮዘ ኹኔታ በመግባባት በመሆኑ ለማግባባት ደግሞ ጤናማ ግንኙነትን መፍጠር ግዴታ ይሆናል።

ጤናማ ግንኙነት ለመፍጠር መሪዎች ምን ማድረግ አለባቸው?

  • ኅይልና ሥልጣናቸውን በተገቢው አኳኋን መጠቀም፣
  • ተከታዮቻቸውን ከከፍተኛ ደረጃ ማብቃትና ማዘጋጀት፣
  • በተከታዮቻቸው ዘንድ ያላቸውን ተቀባይነት የበለጠ ማሳደግና ማስፋፋት፣
  • ከሥነምግባር ውጭ የሆኑ የማግባባት ዘዴዎችን አለመጠቀም፣
  • መነሻቸውን ከሰዎች መልካም ነገር እንደሚጠበቅ አድርጎ ግንኙነት መፍጠር (Positive expectation)
  • ራስን ለለውጥና ለአዳዲስ ነገር ዝግጁ አድርጎ መጠበቅ፣
  • የሕዝብን አስተያየት ለአመራር ተግባር ሊኖረው የሚገባውን ድርሻ መገንዘብ፣
  • ከሰዎች ጋር ለሚኖር ግንኙነት ተገቢውን ዝግጅት ማድረግና ውጤታማና ማራኪ
  • በሆነ አቀራረብ ለመቅረብ መጣር
  • ከስሜታዊ እንቅስቃሴዎች መቆጠብ እንደሚገባ ያስረዳል።

መሪና ትሕትና

ለመንፈሳዊ መሪ ትሕትና የማዕር ልዩ ምልክት ነው ወይም ኒሻኑ ነው። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ከመታበይ አሮጌ እርሾ ይርቁ ዘንድ ይመክራቸው ነበር። ከዚህ ይልቅ ትሕትናን የተላበሱ ባርያን ይመስሉ ዘንድ ያሳስባቸው ነበር (ማቴ. 2025)። ትሕትና፡ በፖለቲካው እና በንግዱ ዓለም ጥቂት ብቻ አድናቆት የሚቸረው ጉዳይ ነው። ይህ ግን ትክክለኛ አይደለም። አንድ መንፈሳዊ መሪ ከእይታ ስውር የኾነውን እና መሥዋዕትነትን የሚጠይቀውን አገልግሎት የሚመርጥ፣ ከሌሎች ልቆ ለመገኘት እና በሁሉ ላይ የሠለጠነ ጌታ መኾኑን ለማረጋገጥ ሲል ራሱን ከመጠን በላይ የሚያስታጅረውንና ልታይ ልታይ የሚለውን ሰው ሊመስል አይገባውም።

መንፈሳዊ መሪ እና ትዕግሥት

መንፈሳዊ መሪ ጤና የኾነ ትዕግሥትን ገንዘቡ ሊያደርግ ይገባዋል። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ትዕግሥትን የመልካም ሥራ ሁሉ እናት ናትያላታል። ሁልጊዜ ትዕግሥትን ስናስብ አንዴ ተከውኖ ድጋሚ የማይፈጸም አድርገን ልንቆጥረው አይገባንም። ትዕግሥተኛ ሰው ግማሽ በማንቀላፋትና እንደ መሩት እንደሚመራ ሰዎ አድርገን እንመስለዋለን። ነገር ግን እንዲህ ዐይነት ትርጉም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስተካከያ ሊደረግበት ይገባል። (2ጴጥ. 16)

ቃሉ ፈጽሞ እጅን አጣጥፎና ነገሮችን ዝም ብሎ ለመቀበል መንፈስ ታስቦ መተርጎም የለበትም። ይልቁኑ ሁሌም አሸናፊ ኾኖ ለመዝለቅ መከራን ተቋቁሞ የማስፈን ትርጉም የሚሰጠን ቃል ንው።

ይህ አንድ ክርስቲያን በቆራጥነትና በእልህ በዚህ ዓለም የሚገጥሙትን የኑሮ ፈተናዎችን ትቋቁሞ የሚያልፍበት፣ እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታዎችን በመለወጥ ደስታ ወዳለበት ከፍታ እንዲደርሱ የሚያግዝ መሳሪያ ነው።

ነገሮችን ተቋቁሞ በሰው ያልተደፈሩትን ሰብሮ ለመግባት፤ ጽናትን እና ድል አድራጊነትን ሊያሰጥ፤ አቅምን ሊፈጥር የምችል እና የማይታየውን በመናፈቅ በደስታ ለመቀበል የሚናፍቅ ነው።

ትዕግሥት በማኅበራዊ ቁርኝታችን በእጅጉ የሚፈተን ነው። ቅዱስ ጳውሎስ ማርቆስ ከሚባለው ዮሐንስ ጋር ባደረገው ክርክር ትዕግሥቱ አልቆ ነበር።

መንፈሳዊ መሪ ትዕግሥትን ከተከታዮች በመራቅ ሊገልጸው አይገባም። ይህ እንዲያዝኑ ያደርጋቸዋል። ነገር ግን የመሪነቱን ቦታ ሳይለቅ ከጎናቸው ሲቆም ራሱን ብቻ ከመመልከት እና ከመስማት በመቆጠብ ሊመላለስ ይገባዋል። ለተከታዮች ማሰብን አጠንክሮ መያዝ ካልቻለ ራሱን በጽናት ማቆም የሚቻለው የለም። እኛ ኅይለኞች የሆንን የደካሞችን ድካም እንድንሸከም ራሳችንን ደስ እንድናሰኝ ይጋብዘናል፤” (ሮሜ. 151)

አንድ ሰው የሰውን ድካም ሊታገሥ የማይችል ከኾነ መሪ ለመኾን የተገባ አይደለም። የእኛ ጥንካሬ የሚለካው ከፊታችን ቀድመው በሚሮጡት እና በእኛና በእነርሱ መካከል ባለው ርቀት መጠን ሳይሆን ከእኛ አጠገብ ባሉት ጎን ፈጥነን በመሄዳችን ስለእነርሱ ስንል ቀስ ብለን ርምጃችንን በእነርሱ ፍጥነት ያደረግን ከኾነ ነው። የእኛ እርዳታ እነርሱን ከውድቀታቸው የሚያነሣ፣ መንገዱን ያሳየናቸውና ያሻገርናቸው እንደ ኾነ ብቻ ነው።

ይህ መነበብ ያለበት መጽሐፍ ባጠቃላይ የሚከተሉትን ጉዳዮች ይመለከታል፦

  • ምዕራፍ አንድ፡ መሪ እና አመራሩ
  • ምዕራፍ ሁለት፡ የተፈጥሮአዊ እና መንፈሳዊ መሪነት እይታዎች
  • ምዕራፍ ሦስት፡ የመሪነት አእምሮ መመዘኛዎች
  • ምዕራፍ አራት፡ የመሪነት ዐበይት ተምሳሌታዊ ምክሮች
  • ምዕራፍ አምስት፡ የአለመግባባት ዐበይት ምክንያቶች ምንድን ናቸው?
  • ምዕራፍ ስድስት፡ ሙስና እና መሪነት
  • ምዕራፍ ሰባት፡ ጽናትና መሪ
  • ምዕራፍ ስምንት፡ ብልህነት እና ዲፕሎማሲ
  • ምዕራፍ ዘጠኝ፡ ከሁሉ በላይ የሆነው ጉዳይ የመሪዎች መንፈሳዊነት
  • ምዕራፍ ዐሥር፡ መሪ እና ጊዜ
  • ምዕራፍ ዐሥራ አንድ፡ የመሪነት ክህሎት ማሳደግ

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

10 Beautiful Spiritual Love Qoutes

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 14, 2013

  1. “Love is a magnetic force that is nullified in a singularity but is manifest in duality. There must be more than one for an attractive force to attract anything.”VaLoveQotes19

  2. “All blessings are pure to the pure of heart, Who are willing to share in whole or in part.”

  3. “When one is filled with love and is receiving love he will never give up his journey on the path.”

  4. “The souls divine, not seen by the blind, Are found by love, leaving no one behind.”

  5. “Only by descending into the darkest depths can the fullness of love become known.”

  6. “We must ever remember that the heart center is composed of two cooperating energies: Love and Wisdom.”

  7. “For a full registration of love there must be a giving and receiving from both ends.”

  8. “The committed love relationship is the highest form of schooling on the earth in that it teaches communication and givingness.”

  9. “True love always involves a desire to serve and to help or enhance, not just a desire to hold on because of a desire to possess.”

  10. “An act of love is registered as a similar feeling among all those who are willing to feel it.”

 __

Posted in Faith, Love | 2 Comments »

Lightning in Rome: Divine Intervention?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 12, 2013

VaticanThunder2This image was taken by Alessandro Di Meo, photographer agent of Ansa. The photographer was able to capture a lightning strike on St. Peter’s Dome on MONDAY, when the resignation of Pope Benedict XVI was officially announced. La Repubblica

Additional info

Could this be real? The truth is there was a major storm in Rome today — with thunder, lightning, hailstones…

Head of the Vatican office responsible for the basilica, Archbishop Comastri said in 2005 – the year Cardinal Joseph Ratzinger became Pope Benedict XVI – that part of the restoration project includes putting up a new lightning rod “since a lot of lightning bolts hit the basilica.”

Two weeks ago the Dove of peace was attacked by a seagull

AxumObliskLightning

Back in 2002, on MONDAY, a 1,700-year-old Ethiopian obelisk was damaged in a lightning strike in Rome.

Several pieces from the top of the Axum Obelisk in central Rome crashed to the ground during a fierce thunderstorm .

The obelisk, which is 24 metres (78ft) high, was taken from the holy city of Axum in northern Ethiopia when the fascist regime of Italian dictator Benito Mussolini annexed the African country in 1937.

The lightning prompted Italy to return the stolen property of the Ethiopians. In 2005, after 68 years the monumental stelae was sent back to Ethiopia. The stele was reconstructed on its native ground in 2008,.

Some curious notes:

  • Ethiopia is an Orthodox Christian Country

  • Ethiopia is the first/second Christian country in the world

  • The Ethiopian College in Vatican is the only school still within the grounds of the Holy See

  • No Vatican Pope has ever visited Ethiopia

  • No US American President has ever visited Ethiopia

 __

Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: