Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2024
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Tree of Life’

በኢትዮጵያ የተባባሰው ጦርነት የአይሁድን ማህበረሰብ አደጋ ላይ ይጥላል | ጽላተ ሙሴ?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 4, 2021

Worsening War in Ethiopia Endangers Jewish Community

እስራኤል የሚኖሩ ቤተ እስራኤላውያን በትግራይ ያሉት ዘመዶቻቸው ወደ እስራኤል እንዲመጡ ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው።

በዓለም ኃያሉ ጦር ሰራዊት ጽላተ ሙሴን የያዘ ሰራዊት ነው” ይላሉ አሜሪካውያኑ ጽላተ ሙሴን አዳኞቹ ልሂቃን እና ተቋማት

የሕይወት ዛፍ ❖ ጽላተ ሙሴ ❖ ንጉሥ ቴዎድሮስ

ከሦስት ሺህ ዓመታት በፊት ጽላተ ሙሴ የአባይ ወንዝን ተከትሎ በጣና ሐይቅ በኩል ወደ አክሱም ተወሰደ። ከሰላሳ ዓምስት ዓመታት በፊት ቤተ እስራኤላውያን ከትግራይ እና ጎንደር አካባቢ በሱዳን በኩል አባይን ተክትለው ወደ እስራኤል ተወሰዱ።

ዛሬም የተወሰኑትን በቀጥታ ከአዲስ አበባ ወደ እስራኤል ከወሰዷቸው በኋል፤ የሁሉም ዓይን ወደ ትግራይ እና ሱዳን ሆኗል። እስራኤል ከሱዳን ጋር የዲፕሎማቲክ ግኑኝነት ጀመረች፣ አሜሪካ የዶላር ጆንያ የተሸከሙትን ጄነራሎቿንና ባለሥልጣናቱን ወደ ሱዳን በተደጋጋሚ ትልካለች፣ ሩሲያ የጦር ሰፈሮችን በፖርት ሱዳን ከፈተች፣ ቱርክ ለትግራይ ስደተኞች የመጠለያ ካምፖችን እሰራለሁ፤ ለሉሲፈር የተሰዋውን ሃላል ምግብ እመግባቸዋለሁ ቁር አንንም እግረ መንገዴን አከፋፍላለሁ እያለች በግራኝ አህመድ ቀዳማዊ ዘመን በሱዳን በኩል ስትሰራው የነበረውን ስራ ዛሬ እንደ እባብ ተለሳልሳ በመስራት ላይ ትገኛለች።

ግራኝ አብዮት አህመድ አሊም በፋሽስት ፋኖ በኩል የአክሱም ጽዮን ልጆች ወደ ሱዳን እንዳይሰደዱ ድንበሩን በመቆጣጠር ላይ ሱዳን ያሉትንም ካልመለስኩ እያለ ነው። ዛሬ የወጣ መረጃ የሚነግረን ኤርትራውያን የጽዮን ልጆች ሰፍረውባቸው የነበሩትን ሁለቱን አንጋፋ ካምፖስ ሆን ብሎ ያቃጠላቸው የአረመኔው አክዓብዮት አህመድ()አራዊት እንደሆነ ነው። ሃያ ሺህ ስደተኞች ጠፍተዋል!!!

ከኢትዮጵያ የሰሜን ተራሮች እየተነሱ አሜሪካን በየዓመቱ የሚያምሱት አውሎ ነፋሳት(ሃሪኬንስ)በጽላተ ሙሴ በኩል ሊቀሰቀሱ እንደሚችሉ ይገምታሉ ወይም ደርሰውበታል። መጭው ኃያሉ የኢትዮጵያ ንጉሥ ቴዎድሮስ ከዚሁ አካባቢ ሊነሳ እንደሚችልም ይገምታሉ ወይም ደርሰውብታል። የሕይወት ዛፍ + ጽላተ ሙሴ + ንጉሥ ቴዎድሮስ ሁሉም ከአክሱም አካባቢ እንደሚገኙ ይገምታሉ ወይም ደርሰውበታል።

ኢየሱስ ክርስቶስን ለመካድ የተመረጠው አስካርዮቱ ይሁዳ ከጌታችን የዘር ሃረግ የተገኘና ከአስራ ሁለቱ የጌታችን ሐዋርያት አንዱ ነበር። ኢየሱስ ክርስቶስን በቀራንዮ የሰቀሉት የጌታችን ዘመዶች የሆኑት የቅድስት ከተማ ኢየሩሳሌም ነዋሪዎች ነበሩ።

የሕይወት ዛፍ + ጽላተ ሙሴ + ንጉሥ ቴዎድሮስ የሚገኙበትን ነዋሪዎችና ቦታ ለመቆጣጠር ከዚሁ አካባቢ የተገኙትን ሰዎች መጠቀም ግድ ነው። የኢትዮጵያን መንፈሳዊ ማንነትና (ኢትዮጵያ ዘመንፈስ) ምንነት በመቆጣጠር ምሰሶዋን አክሱምን ለማናጋት ኢትዮጵያ ዘስጋ የምላቸውን ይሁዳዎች ልክ ከአደዋው ድል በኋላ በአፄ ምኒሊክ አማካኝነት የሦስተኛውን እና የመጨረሻውን ደረጃ ሥራቸውን ጀመሩ። የስጋ ማንነትና ምንነት ያላቸው ኦሮሞዎችም በዚህ ሥራ ቁልፍ የሆነ ሚና እንዲጫወቱ ተደረጉ። የአባ ዘወንጌል አሲምባ ተራሮች አካባቢ የአብዛኛዎቹ የፀረኢትዮጵያ ግራ አክራሪዎች መፈልፈያ መሆን የበቃው። የራያ አዘቦው (ኦሮሞው)ሽፍታ ኃይለ ማርያም ረዳ (ከጌታቸው ጋር ዝምድና ይኖራቸው ይሆን?) እንደ አህዛቡ ሳሞራ ዩኑስ ከህወሃት የጦር መሪዎች አንዱ እንደነበር እናስታውስ። (ኃይለማርያም ረዳ – መንግስቱ ኃይለማርያም – ኃይለማርያም ደሳለኝ – ደብረ ጽዮንጽዮን ማርያምዋው!) ከማርያም መቀነት የተገኙትን የጽዮንን ቀለማት ለማደብዘዝ የሉሲፈራውያኑ ኮከብ ያረፈበትን የቻይና ባንዲራ በብዛት የሚያውለበልቡት የዚሁ የራያ አዘቦው ሽፍታ የኃይለ ማርያም ረዳ ዘሮች ናቸው። በነገራችን ላይ ራይ አዘቦ ልክ እንደዛሬው አካባቢው በቦምብ እና ረሃብ ከተጨፈጨፈ በኋላ ነበር በጋላማራው ንጉስ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ከትግራይ በመነጠል ከወሎ ጋር እንዲጠቃለል የተደረገው። ጋላማራዎች ወዮላችሁ! በዚሁ ጊዜ ልክ አሁን ለትግራይ እንደሚያስቡት በረሃብ የተጠቁትን የወሎና ትግራይ አካባቢዎች ለመርዳት በሚል ከብሪታኒያ፣ ጀርመን፣ ፈረንሳይና ወዘተ የተውጣጡ የናቶ ሰራዊቶች ያቀዱትን ስራ ሲሰሩ ነበር።

በቀድሞዋ የኢትዮጵያ ግዛት በኤርትራ “ቃኛው እስቴሽን” በመባል ይታወቅ የነበረውንና እ..አ ከ1943 እስከ 1977 .ም ድረስ ቀደም ሲል የነበረውን የጣሊያን የባህር ኃይል ሬዲዮ ጣቢያ ተረክቦ በማደስ እንደ የዩኤስ አሜሪካ ጦር ሬዲዮ ጣቢያ ሲሰራ የነበረውን ምስጢራዊ የስለላ እና ምርምር ጣቢያ አስታወሰኝ፡፡ ለሰላሳ አራት ዓመታት ያህል እዚያ ቆይተዋል! ዋው! ላለፉት ሰላሳ ዓመታት በኤርትራ ሕዝብ በተለይ በወጣቱ ላይ እየታየ ያለው ያልተለመደ ኢሃበሻዊ ባሕርይ ይህ ቃኛው ጣቢያ ሲሰራቸው ከነበሩት ምስጢራዊ አካባቢን እና ህሊናን የመቆጣጠሪያ ስራዎች ጋር የተቆራኘ ይሆን? ዛሬ ወደ ትግራይ ገብተው ኢሃበሻዊ ጭካኔ በመፈጸም ላይ ያሉት የኢሳያስ አፈቆርኪ ወታደሮች በዚሁ ጣቢያ ከተገኙ እንቁላሎች የተፈለፈሉ ሮቦቶች ይሆኑ?

ኒው ዮርክ ታይምስ” አንድ ማንነቱ እንዲደበቅለት የፈለገንውን የምዕራባዊ ባለሥልጣንን ንግግር ዋቢ በማድረግ እንዲ ብሏል፤“አቶ አቢይ ከኤርትራ ጋር ያደረገውን የ 2018 የሰላም ስምምነት እስከፈረመበት ዕለት ድረስ ከኤርትራ መሪ እና ለብዙ አስርት ዓመታት የኢትዮጵያ ቀንደኛ ጠላት ከሆነው ከኢሳያስ አፍወርቂ ጋር በትግራይ ላይ ያደረሰውን ጥቃት አስቀድሞ አስተባብሮት እንደነበር ይታመናል። (ትክክል! ገና ስልጣን ላይ እንደወጣ እኮ አስቀድሞ ወደ ኤርትራ ተመላለሰ + አሜሪካ ሄዶ አቡነ መርቆርዮስን አመጣቸው፤ አሁን በትግራይ ጭፍጨፋውን እንደጀመረም ፈጥኖ አክሱምን እና አዲግራትን ማጥቃት ፈለገ። አዎ! አዲግራት አካባቢ የአባ ዘ-ወንጌል አሲምባ ተራሮች አሉ፤ ባቅራቢያውም በተልይ ቱርኮች ከፍተኛ አትኩሮት የሰጡትና የመጀመሪያዎቹ መሀመዳውያን በወረራ ገብተው ንጉሥ አርማህን ያታለሉበት ቦታ ይገኛል።)

👉 አክሱም ጽዮን 👉 አሲምባ መስቀለ ኢየሱስ (አባዘወንጌል) 👉ተንቤን 👉ውቅሮ

ዋው! ልክ በ1666 ዓመቱ የ666ቱ ወኪሎች ግራኝ አብዮት አህመድ እና ኢሳያስ አፈቆርኪ በውቅሮ ውቅር ዓብያተ ክርስቲያናት ላይ ዘመቱ። በዚህ አካባቢ ላይ ለመዝመት መወሰናቸውን እንዲህ መጣደፋቸው። ዋው!

ወገኖች መጨፍጨፋቸው ቅርስ መውደሙ እጅግ በጣም ያስቆጣል። የሚበቀል አምላካችን ይበቀላቸዋል።

👉 ዴር ሽፒገል/Der Spiegel የተሰኘው ታዋቂ መጽሔት ነው ይህን መረጃ ያወጣው።

“ቦንቦች በውቅሮ ሰሜናዊው ጠርዝ ላይ በሚገኘው ታዋቂው የውቅር ቤተክርስቲያን ጨርቆስ ላይ እንደፈነዳ ዓለም ሀዱሽ የወደፊት ሕይወቱን አጣ፡፡ “ባለቤቴ ነፍሰ ጡር ነበረች ፡፡ የመጀመሪያውን ልጃችንን እንጠብቅ ነበር። አሁን ሁለቱም ሞተዋል ”ሲል በስልክ ይናገራል፡፡ ከሳምንታት በኋላ አዲስ አበባ የቴሌኮሙኒኬሽን ግንኙነቶችን ከትግራይ ክልል ክፍሎች ጋር እንደገና ፈቅዳለች፡፡ የኤርትራ መትረየስ ከተማችንን በደበደበ ጊዜ ባለቤቴ ሞተች፡፡ የኤርትራ ኃይሎች ስድስት ጓደኞቹን እንዴት እንደገደሉ የውቅሮ ነዋሪው ተናግሯል ይተርካል።

☆ ሌላው አስገራሚና አሳዛኙ ጉዳይ፤ መቼም ሰይጣን ከቤተ ክርስቲያን አይርቅምና ከሺህ አራት መቶ ዓመታት በፊት ሐሰተኛው ነብይ መሀመድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ለመፈታተን ወደዚህ ቦታ ነበር ተከታይ ጂሃዳውያኑን በስደት መልክ የላካቸው። ሙስሊሞች ዛሬ “አል-ነጃሽ” የተሰኘ መስጊድ ሰርተዋል። የጀርመኑ መጽሔት አክሎ እንዳወሳው ውቅሮ በሚገኘው “አል-ነጃሺ”መስጊድ ውስጥ የነበሩ ሰማንያ አንድ ሙስሊሞች በግራኝ እና አፈወርቂ ቦምብ ተገድለዋል። በከተማዋ ብዙ ጭፍጨፋ እንደተካሄደ ነዋሪዎች በስልክ ተናግረዋል።

❖ በታሪካዊቷ ውቅሮ ከተማ በአብረሐ እና አጽበሐ ዘመን ከአለት ተፈልፍለው ከተሠሩት ድንቃድንቅ ዓብያተ ክርስቲያናት መካከል ውቅሮ ጨርቆስ አንዱ ነው።

ውቅሮ ጨርቆስ ቤ/ክርስቲያን ከአንድ ወጥ ድንጋይ ተፈልፍሎ የተሰራ ውቅር ቤተክርስቲያን ነው። ከተማዋም “ውቅሮ” የሚለውን ስም ከዚህ ሳይሆን አይቀርም ያገኘችው)

ሉሲፈራውያኑ “አሳውን ለማጥመድ ባሕሩን ማድረቅ” እንደሚሉት የአክሱምንና አካባቢዋን ነዋሪዎች በማዳከም፣ በመበታተንና በመጨፍጨፍ የሕይወት ዛፍን ❖ ጽላተ ሙሴን ❖ ንጉሥ ቴዎድሮስን መቆጣጠር እንችላለን የሚል ዕቅድና ተልዕኮ አላቸው። በትግራይ ላይ የተከፈተው ጦርነት የመጨረሻው ዋና ዓላማ ይህ ነው።

በግራኝ አክዓብዮት የጋላማራዎች ሰራዊት፣ በኢሳያስ አፈቆርኪ የሮቦቶች ሰራዊት፣ በራያ ክንፍ የሚመራው የህወሃቶች ሰራዊት፣ በሶማሌዎች ሰራዊት፣ በአረቦችና ቻይናዎች ድሮኖች፣፣ በአሜሪካ ሳተላይቶች እየተደገፈ በትግራይ ላይ ወረራውን በማካሄድ ላይ ያለው የሉሲፈራውያኑ ኃይል የሕይወት ዛፍን + ጽላተ ሙሴን + ንጉሥ ቴዎድሮስን ለመቆጣጠር ላለፉት መቶ ዓመታት ከፍተኛ ዝግጅት በማድረግ የተጠራ ኃይል ነው።

አንድ ሺህ ተዋሕዶ ምዕመናንን በአክሱም ጽዮን በመጨፍጨፍ ለሰማዕትነት እንዲበቁ ያደረጋቸው አሰቃቂ ድርጊት የዚህ የሕይወት ዛፍን ❖ ጽላተ ሙሴን ❖ ንጉሥ ቴዎድሮስን ለመቆጣጠር የሚደረገው ዘመቻ አካል ነው። በአክሱም ጽዮን የተፈጸመውን ከፍተኛ ወንጀል ያልተረዳና የጉዳዩን አጅግ በጣም አሳሳቢነትና ክብደት ያልተረዳ ወገን ትልቅ ፈተና ላይ የሚገኝ ዘላለማዊ ሕይወት ምን እንደሆነ ለማወቅ ያልቻለ ወገን ብቻ ነው። በየቀኑ 24/7 በጥልቁ ልንነጋገርበትና ከፍተኛ ትኩረት ልንሰጠው የሚገባን ጉዳይ ቢኖር ይህ ጉዳይ ነው። ዛሬ በአዲሱ ኪዳን የምንኖር ግን ይህንን የተዘጋጀውን ዘላለማዊ ሕይወት እግዚአብሔርን እንዲሁም የላከውን ክርስቶስን በማወቅ ከማግኘት ይልቅ በኤደን ገነት እንደተከናወነው ያልተፈቀደልንን እና የማይጠቅመንን በማወቅ እና በመመራመር እውነተኛ ከሆነው የእግዚአብሔር ሃሳብ ስንስት እና ስንወጣ እናያለን። ቀደም ሲል አባ ዘወንጌል “ዋ! ፀረትግራዋይ የሆነ አቋም እንዳይኖራችሁ!” ብለው ያስጠነቀቁን በምክኒያት ነበር። እግዚአብሔር ማስተዋልን ይስጠን!

____________________________________

Posted in Conspiracies, Curiosity, Ethiopia, Faith, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »