Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2024
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘ትዕግስት አሰፋ’

Instead of Engaging in Sport, The Hypocrite Climate Activists Disrupted The 2023 Berlin Marathon

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 24, 2023

🏃‍ በስፖርት ከመሳተፍ ይልቅ ግብዝ የአየር ንብረት ርዕዮተ ዓለም አራማጆች የበርሊን ማራቶንን አበላሹት።

Images of runners competing in the Berlin marathon and their supporters. Meanwhile activists of the “Letzte Generation” (Last Generation) movement disrupt the race by throwing orange paint on the track.

ባለፈው ሳምንት ላይ ሰዎቹ “ውሻ ነን!” ብለው ሲጮሁ በነበረባት ውቧ በርሊን ከተማ መሆኑ ደግሞ በይበልጥ ያስደስታል! የዚህም ማራቶን አዘጋጆች ስፖርት አይሥሩና ከተማዋን በግብረሰዶማውያን ቀለማት ቀብተዋታል። እንግዲህ በአውሮፓና አሜሪካ ከተሞች በሩጫዎቹ ሁሉ የበላይነቱን የሚይዙት ምስራቅ አፍሪቃውያን ብቻ ናቸውና፤ በእነርሱ ቤት ብልጥና ብልህ መሆናቸው፣ መሳለቃቸውና ርዕዮተ ዓለማቸውን ለማስተዋወቅ አጋጣሚውን መጠቀማቸው ነው፤ አይማሩምና፤ ወዮላቸው!

🐕 Hundreds of Berliners WHO IDENTIFY AS DOGS Protest at CITY HALL | Whaaat!

Posted in Curiosity, Ethiopia, Sports - ስፖርት | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Ethiopia’s Tigist Assefa Shatters Women’s Marathon Record | 😮 ድንቅ ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 24, 2023

🏃‍ ኢትዮጵያዊቷ ትዕግስት አሰፋ የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰንን ከሁለት ደቂቃ በላይ አሻሻለች 😮

ዛሬ እሑድ መስከረም ፲፫/13/፳፻፲፮/2016 ዓ.ም በጀርመን ዋና ከተማ በ በርሊን በተካሄደ ፵፰/48ኛው የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግሥት አሠፋ የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰንን ከሁለት ደቂቃ በላይ በመስበር አሸነፈች።

የባለፈው ዓመት የበርሊን ማራቶን አሸናፊዋ ትዕግሥት፣ሁለት ሰዓት ከ፲፩/11 ደቂቃ ከ፶፫/53 ሰከንድ በመግባት ነው የዓለም የማራቶን ክብረ ወሰንን መያዝ የቻለችው።

የ፳፱/29 ዓመቷ አትሌት እንደ አውሮፓውያኑ 2019 በተካሄደው የችካጎ ማራቶን በኬንያዊቷ አትሌት ብሪጊድ ኮስጌ ተመዝግቦ የነበረውን 2:14.04 ከሁለት ደቂቃ በላይ አሻሽላለች።

ትዕግሥት በባለፈው ዓመት የበርሊን ውድድር እንደ አውሮፓውያኑ በ2018 በኬንያዊቷ አትሌት ግላዲስ ቼሮኖ ተይዞ የነበረው 2:18:11 ሰዓት በማሻሻል የቦታውን ክብረ ወሰን ማስመዝገቧ ይታወሳል።

በዚህ ውድድር የትዕግሥት ድል ሦስተኛው ፈጣን የማራቶን ሰዓት ለመሆን በቅቶ ነበር።

በሌላ በኩል ዛሬ በተካሄደው የወንዶች ማራቶን የሁለት ጊዜ የኦሊምፒክ ቻምፒዮናው ኬንያዊው ኢሉድ ኪፕቼጌ ውድድሩን 2:02.42 በማጠናቀቅ ለአምስተኛ ጊዜ በማሸነፍ ታሪክ ሰርቷል።

በሴቶች ማራቶን ከትዕግሥት ሌላ፣ ዘይነባ ይመር፣ ሰንበሬ ተፈሪ፣ ደራ ዲዳ፣ ወርቅነሽ ኢዲሳ፣ እና ሔለን በቀለ ከአራተኛ እስከ ስምንተኛ ተከታትለው መግባት ችለዋል።

በወንዶች ደግሞ ታደሰ ተክሌ ሦስተኛ ሆኖ ሲያጠናቅቅ፣ ሀፍቱ ተክሉ እና አንዱዓለም በላይ አምስተኛ እና ስድስተኛ በመሆን አጠናቅቀዋል።

🏃‍ Tigst Assefa beats the existing marathon world record by more than two minutes. An astonishing performance by the now fastest runner in the world.

On the stillest of Berlin mornings, a tsunami of a performance. It came from Ethiopia’s Tigist Assefa, who over 26.2 astonishing miles redefined what many thought was possible in the women’s marathon, as she blew the world record to smithereens in a time of 2hr 11min 53sec.

The fact the 29-year-old Ethiopian shattered the previous best, set by Brigid Kosgei in 2019, by 2min 11sec was remarkable enough. Yet the way she powered home through the Brandenburg Gate suggested she could go even quicker still.

😮 ጀግኒት እኅታችን! ይህኛውም የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ድንቅ ድል ነውና፤ እንኳን ደስ አለን! ባለፈው ሳምንት ላይ ሰዎቹ “ውሻ ነን!” ብለው ሲጮሁ በነበረባት ውቧ በርሊን ከተማ መሆኑ ደግሞ በይበልጥ ያስደስታል!

የዚህም ማራቶን ውድድር አዘጋጆች ስፖርት አይሥሩና ከተማዋን በግብረ-ሰዶማውያን ቀለማት ቀብተዋታል። እንግዲህ በአውሮፓና አሜሪካ ከተሞች በሩጫዎቹ ሁሉ የበላይነቱን የሚይዙት ምስራቅ አፍሪቃውያን ብቻ ናቸውና፤ በእነርሱ ቤት ብልጥና ብልህ መሆናቸው፣ መሳለቃቸውና ርዕዮተ ዓለማቸውን ለማስተዋወቅ አጋጣሚውን መጠቀማቸው ነው፤ አይማሩምና፤ ወዮላቸው!

🐕 Hundreds of Berliners WHO IDENTIFY AS DOGS Protest at CITY HALL | Whaaat!

Posted in Ethiopia, Sports - ስፖርት | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »