Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2024
    M T W T F S S
     12
    3456789
    10111213141516
    17181920212223
    24252627282930
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘General Amir Haskel’

ፖሊሷ ኢትዮ-እስራኤላዊት ጄነራሉን እያንከበከበች አሰረቻቸው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 7, 2020

የፀረ-ኔታንያሁ የተቃውሞ ቡድን መሪ ለፖሊስ አስተያየታቸውን ከሰጡ በኋላ በትናንትናው ዕለት በዘረኝነት ተከሰዋል።

ጄነራል አሚር ሀስከል ለኢትዮእስራኤላዊቱ ፖሊስ ‘ወላጆችሽን ከኢትዮጵያ አመጣኋቸው፤ አታፍሪምን?’ በሚል ቪዲዮ ከተሰሙ በኋላ ከመንግስት ባለሥልጣናት ትችት ገጥሟቸዋል፡፡

የቀድሞው የአየር ኃይል ጄኔራል ታጋይ አክቲቪስት አሚር ሀስከል ነሐሴ ወር በቁጥጥር ስር በዋለ ጊዜ ለኢትዮእስራኤላዊቷ ፖሊስ ሴት አከራካሪ አስተያየት በመስጠቱ በትናንትንው ዕለት ተከስሷል፡፡

በቪዲዮው ላይ እንደሚታየው በፖሊሶች የተከበበው ጄነራል ሀስከል ወደ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሴት ዘወር ብሎ “ወላጆችሽን ከኢትዮጵያ ወደዚህ ያመጣኋቸው እኔ ነኝ ፣ ታዲያ አሁን ትንሽ አታፍሪምን እኔን ስታስሪኝ?” ብሎ በመጮኽ ሲናገራት ይሰማል፡፡

የጄነራል ሃስከል አስተያየቶች መሪ የእስራኤል መንግስት ባለሥልጣናትን ጨምሮ በብዙዎች ዘንድ ቁጣን ቀሰቅሷል፡፡

በእስራኤል ታሪክ የመጀመሪያዋ ትውልደ ኢትዮጵያ የእስራኤል የካቢኔ ሚኒስትር የሆኑት ፕኒና ታማኖሻታ ለቪዲዮው ምላሽ የሰጡ ሲሆን ትውልደ ኢትዮጵያ የሆኑ እስራኤላውያን ይህን መሰል ተልካሻ ነገር በሚናገሩ ሰዎች ፊት ሳይሸማቀቁ ራሳቸውን ከፍ አድርገው እንዲሄዱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ሚንስትሯ፤ “ወላጆቻችን ሕይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ወደ እስራኤል ለመሰደድ በእምነት እና በቁርጠኝነት በብዙ ሺህ ኪሎሜትር የሚቆጠር መንገድ ተጓዙ፡፡ ማንም የጀግንነታችንን እና ያሳለፍነውን ታሪክ ለራሱ አይጥቀስ፡፡ እዚህ ምንም ጌቶች እና አገልጋዮች እንደሌሉ በማይረዱ ሰዎች ዘንድ በቆዳዋ ቀለም ምክንያት የቤተሰብዋን አመላካች ታሪክ መጥቀስ ዘረኝነት ነው፡፡ ሁላችንም እኩል እስራኤላውያን ነን ”ብለዋል፡፡

ምክትል የህዝብ ደህንነት ሚኒስትሩ ጋዲ ዬቫርካንም በቪዲዮው ላይ አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን የጄነራል ሀስክል አስተያየቶችን ዘረኛ እና ሁሉንም ትውልደ ኢትዮጵያዊያንን ዝቅ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ጄነራል ሀስከል እና ጓደኞቹ ከሆነ ምድሪቱ የእነሱ ብቻ መሆኗን እርግጠኛ ናቸው፡፡ እነሱ ጌቶች እንደሆኑ እና ሁሉም ሌላ ሰው እንግዳ እንደሆነ”

ዬቫርካን በጄነራል ሃስከል አስተያየቶች እና ባሰረችው ኢትዮእስራኤላዊቷ ፖሊስ መካከል ያለውን ትይዩነት በማቅረብ እንዲህ ብለዋል፤ “ አንተም እንደ አንድ ጄነራል የተሰጠህን ትዕዛዝ የምትፈጽም ወታደር እንደነበርክ ሁሉ ፖሊሷም የአዛዦቿን ትእዛዝ የምታከናውን የሠራዊት አባል ነች፡፡”

የጤና ጥበቃ ሚኒስትሩ ጁሊ ኤደልሽታይን የጄነራል ሃስከልን አስተያየቶች“ዝቅ የሚያደርግ ፣ ዘረኛ እና ግልፍተኛ” በማለት ለቪዲዮው ምላሽ የሰጡ ሲሆን “ለመጥቀስ እንኳን የሚገባቸው አይደሉም” ብለዋል፡፡

ዘረኝነት ጋኔን ዓለምን እያወካት ነው። ጠቅላይ ሚንስትር ኔተንያሁም ከፍተኛ ውጥረት ላይ ናቸው፤ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከሙስሊም ግብጽ ጎን ተሰልፈዋል፣ በአርሜኒያ ጉዳይም ከሙስሊም አዘርበጃን ጎን ተሰልፈዋል። ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ? ኤሚራቶች፣ ባሕሬን ምናልባትም በቅርቡ ሳውዲ አረቢያ ከእስራኤል ጋር የዲፕሎማቲክ ግኑኝነት እየጀመሩ ነው። ወዴት ጠጋ ጠጋ? ፕሬዚደንት ትራምፕም በኢትዮጵያ እና አርሜኒያ ላይ ተመሳሳይ አቋም ስላላቸው ብዙ ፈተና ይጠብቃቸዋል።

ግን እኔ አንድ የታየኝ ሌላ ነገር፤ በትንሿ እስራኤል ኢትዮጵያዊቷ ፖሊስ ጄነራሉን ታስረዋለች፤ በግዙፏ ሳውዲ አረቢያ ኢትዮጵያውያን እንደ ከብት ታግተው እየተገደሉ ነው፤ እንኳን ፖሊስና ሚንስትር ሆነው ሊኖሩ።

_____________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »