💭 “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት።ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት፤ ሁለተኛ ክብርህ ናት፤ ሶስተኛም ሚስትህ ናት፤ አራተኛም ልጅህ ናት፤ አምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፤ የዘውድ ክብር፤ የሚስት ደግነት፤ የልጅ ደስታ፤ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ።” አፄ ዮሐንስ ፬ኛ
________________
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 28, 2022
💭 “የኢትዮጵያ ልጅ ሆይ ልብ አድርገህ ተመልከት።ኢትዮጵያ የተባለችው አንደኛ እናትህ ናት፤ ሁለተኛ ክብርህ ናት፤ ሶስተኛም ሚስትህ ናት፤ አራተኛም ልጅህ ናት፤ አምስተኛም መቃብርህ ናት። እንግዲህ የእናት ፍቅር፤ የዘውድ ክብር፤ የሚስት ደግነት፤ የልጅ ደስታ፤ የመቃብር ከባቲነት እንደዚህ መሆኑን አውቀህ ተነሳ።” አፄ ዮሐንስ ፬ኛ
________________
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Aksum, Axum, መተማ, ንጉሠ ነገሥት, አረመኔነት, አክሱም, አፄ ዮሐንስ, ክርስቲያን, ጥላቻ, ጦርነት, ጭፍጨፋ, Emperor, Ethiopia, Ethiopianess, Genocide, Tigray, War, Yohannes | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on August 28, 2019
የሉሲፈር ጉዳይ ነውና የአውሮፓውያኑን ቀን አቆጣጠር ልጠቀም። በ 2016 (እ.ኤ.አ.) በ ናይትድ ስቴትስ ውስጥ በሚገኘው ክሊቨላንድ የተፈጥሮ ሣይንስ ቤተ–መዘክር፥ በሰው ዘር አመጣጥ ጥናት ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ “በሚያስደንቅ ሁኔታ የተሟላ” ቅሪተ–አካላት፡ ሉሲ/ ድንቅ ነሽ ተገችታበት በነበረበት የአፋር ቦታ አካባቢ አገኘን ይላሉ። እድሜውም ሶስት ሚሊየን ስምንት መቶ ሽህ ዓመት ነው ተብሏል። መጠሪያው ላኪ/ Lucky ሆኗል። Lucy – Lucky, „k“ ሲነሳ Lucy ይሆናል።
በቅድመ–ታሪክ ጥናት የመስክና የቤተ–መኩራ መስክ ሰፊ ምርም ያደረጉት ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለሥላሴ እስካሁን በተገኙ መረጃዎች እና ጥናቶች መሰረት ኢትዮጵያ የዘመናዊው ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሰው ዘር መገኛ መሆኗን ይገልጣሉ።
ኢትዮጵያዊው “ሉሲ” (እድሜዋ 3.2 ሚሊየን ዓመት) እ.አ.አ በኅዳር 24 / 1974 ዓ.ም ነበር የተገኘችው። እንግዲህ ሉሲ በተገኘችበት ዓመት ሦስት ወራት ቀደም ሲል እ.አ.አ በመስከረም 12 / 1974 ዓ.ም፤ ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ከኤርትራ በመጣው ጴንጤ ጄነራል አማን አንዶም ተተኩ። ያውም በዕለተ ቅዱስ ዮሐንስ። ዶ/ር ሀይሌ ላሬቦ በቀደም ዕለት ” ከአፄ ኃይለ ሥላሴ መስተዳደር በኋላ ኢትዮጵያ ጠንካራ አገር እንዳትሆን መንግስቷ ከጦርነት እንዳይላቀቅ ማድረግ አለብን” ማለታቸው ትክክል ነው። ነጠብጣቦቹን እናገናኝ፦ ቅዱስ ዮሐንስ + አፄ ኃይለ ሥላሴ + ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ
በነገራችን ላይ፡ “ሉሲ” የሚለው ስያሜ የተሰጠው፡ አግኝቷል የተባለው አሜሪካዊ ተመራማሪ፡ ዶናልድ ዮሃንሰን Donald Johanson (ስሙ የ ዮሐንስ ልጅ ማለት ነው) ቅሪተ–አካላቱን ባገኘበት ወቅት “ሉሲ ከአልማዝ ጋር በሰማይ” / “Lucy in the Sky with Diamonds” በመባል የሚታወቀውን የእንግሊዝ የሙዚቃ ቡድን ቢትልስ/ Beatles ዘፈን እያዳመጥኩት ስለነበር ነው ብሏል። የሙዚቃ ቡድኑ ደግሞ ይህን ዘፈን ያወጣው ለሉሲፈር ነው። ሰይጣን አምላኪዎች ይህን የቢትልስ ዝማሬ በጣም ይወዱታል፤ በሰይጣናዊ ሥነ ሥርዓቶቻቸው ላይ ዛሬም ሲዘምሩት ይሰማሉ። በድብቅ “ሉሲፈር ከአጋንንት ጋር በሰማይ / Lucifer In The Sky With Demons” መሆኑ ነው።
[ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ ፲፬፥ ፲፪፡፲፭]
“አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ! አንተን በልብህ። ወደ ሰማይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ። ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ።“
[ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕራፍ ፳፰፥፲፫ ]
“በእግዚአብሔር ገነት በዔድን ነበርህ፤ የከበረ ዕንቍስ ሁሉ፥ ሰርድዮን፥ ቶጳዝዮን፥ አልማዝ፥ ቢረሌ፥ መረግድ፥ ኢያስጲድ፥ ሰንፔር፥ በሉር፥ የሚያብረቀርቅ ዕንቍ፥ ወርቅ፥ ልብስህ ነበረ፤ የከበሮህና የእንቢልታህ ሥራ በአንተ ዘንድ ነበረ፤ በተፈጠርህበት ቀን ተዘጋጅተው ነበር።“
ከአምስት አመት በፊት “ሉሲ / Lucy“ የተባለና ከኢትዮጵያዋ ሉሲ/ Lucy ጋር የተያያዘ ፊልም ተሠርቶ ነበር። የፊልሙ ዋና ተዋናይት ታዋቂዋ ስካርሌት ዮህናሰን / Scarlett Johansson ( የ ዮሐንስ ልጅ) ናት። ከዶናልድ ዮህንሰን ጋር ስጋዊ ዝምድና የላትም። ዮሐንስ + የዮሐንስ ልጅ + ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ።
መጭው ዘመነ ዮሐንስ ነው፤ ብዙ ተዓምራትን የምናይበት ድንቅ ዘመን ነው የሚሆነው።
Posted in Curiosity, Ethiopia, Ethnicity, Genetics & Anthropology, Faith | Tagged: ሉሲ, ሉሲፈር, ሰማይ, ቅሪተ-አካላት, አሜሪካ, ዘመነ ዮሐንስ, ድንቅነሽ, ዶ/ር ዮሐንስ ኃይለ ሥላሴ, Cleveland Museum, Hominin Cranium, Lucifer, Lucy, Yohannes, Yohannes Haile-Selassie | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 27, 2011
*ከማሞ ውድነህ*
“የእስበሳችን ነገር ያለ ማክረሩ ነው የሚሻለው። ጠንካራ ክንድና ብርቱ ትኩረት የሚገባው ግን እንደ አዞ ከውሀ ውስጥ ብቅ የሚለው ነው“ (አሉላ አባነጋ)
አፄ ዮሐንስ ከጉራዕ ጦርነት በኋላ ሐማሴን ውስጥ ሰነባብተው ወደ ዐደዋ ከመመለሳቸው በፊት የሰሜን ኢትዮጵያ በር የተከበረና የታፈረም እንዲሆን ሲሉ ደጃዝማች ኃይሉ ተወልደ መድኅንና ራስ ባርያውን በገዥነት ሲሾሙ፡ ስመ–ጥሩውን አዋጊያቸውን ሊጋባ አሉላን በራስነት ማዕረግ አስኮፍውሰና አስጊጠው ከመረብ ማዶ ያለውን አገር በጦር አበጋዝነት እንዲጠብቁ ሾሙዋቸው። ከዚያ በኋላም የአፄ ዮሐንስ ትልቁ የሥራ ምዕራፍ የኢትዮጵያን የውስጥ ጉዳይ ማደላደልና ማለሳለስ አንድነቷን ማጽናትና ሕዝቡ ፍትሕ አግኝቶ አርሶና ነግዶ እንዲተዳደር የማድረጉ ጉዳይ ነበር።
ይህን ዓላማቸውን ሊያደናቅፉባቸው እንደሚችሉ አሥግተዋቸው ከነበሩት ሁኔታዎችም ጋር መፋጠጡን ተያያዙት። በሰሜን ኢትዮጵያ በኩል የውስጡን ተቀናቃኝ ቀርቶ የውጭውንም ወራሪ ጠላት ከአንዴም ሁለቴ ኃያሉ ክንዳቸውን ስለአሳረፉበት ለጊዜው ረጭ ብሎላቸዋል። በምዕራብና በመካከል ኢትዮጵያም በኩል የቤገምድር የወሎና የጐጃም ሁኔታ ጋብ ብሎላቸዋል። የጥርጣሬና የሥጋት ትኩረታቸውን የሳበባቸው ግን ሸዋ ሆነ። የወጣትነት ጓደኛቸውና ምስጢረኛቸው ምኒልክ “አፄ” ተብለው ቁጥሩ እስከ ሰባ ሺህ በሚደርስ ሠራዊት ጐልብተው፡ ከሸዋም አልፈው ወሎንና ጐጃምን ለመደረብ ከሚያስፈራሩበት ደረጃ ላይ ወጥተዋል።
አፄ ዮሐንስ ግን፡ የምኒልክን ሁኔታ አንሥተው ከመኳንንቶቻቸውና ከጦር አበጋዞቻቸው ጋር በሚወያዩበት ሰዓት ሁሉ ደጋግመው የሚያነሡት ጉዳይ ነበራቸው።
“ዋናው ሥጋቱና ችግሬ የሠራዊቱ ብዛት አይደለም። ለዚህ ለዚህስ እኔም ላቅ ያለ እንጅ ከእርሱ ዝቅ ያለ ሠራዊት የለኝም። ግን እንደዚያ ማሳያ እንደሚሉት የሰይጣን መልእክተኛ የመሰለ ፈረንጅ ከአጠገቡ አስቀምጦ፡ ከነሙንዚንገር ጋርም የሚያደርገው መላላክና መስማማት ነው።
ከዚያ ሌላ ደግሞ እነዚህ ሚሲዮኖችም በዚያ በኩል ገብተዋል፡. ዋናው ዓላማቸውም ምኒልክን አሳስተውና ጦር አስመዝዘው ከኔ ጋር ለማጋጨት መሆኑን አላጣሁትም። ግዴለም የማደርገውን ዐውቃለሁ” እያሉ ዛቻ አዘልና ትካዜ–ለበስ አነጋገር ያሰሙ ነበር። እርግጥም ነው በዚያ ዘመን ፒዬር አርኖ የተባለ ፈረንሳዊ በዘይላ በኩል ወደ ሸዋ ገብቶ የምኒልክ ባለሟል ሆኖ የእርሳቸውንም መልእክት ይዞ ወደ ግብጽና ፈረንሣይ እየሔደ ‘ዮሐንስን ለመጣል ትልቅ መሣሪያ ይሆናችኋል‘ እያለ ያሽቃብጥ ነበር። ከእርሱም ሌላ ደግሞ በምሕጻረ ቃል “አባ ማስያስ” እየተባለ የሚጠራው ሎሬንዞ ጉልየሞ ማሳያ የሚባለው የሮማ ካቶሊክ ሚሲዮን አባል በሸዋና በከፋ ውስጥ ድርጅቱን አቋቁሞ የምኒልክን ባለሟልነትም አትርፎ ከሚሲዮናዊነቱ ይልቅ በዲፕሎማቲክና በስለላው ሙያ ተሠማርቶ ዮሐንስንና ምኒልክን ለማራራቅና ለማጋጨት በመካከላቸው ገብቶ ነበር።
እነዚሁ ሁለቱ አውሮጳውያን የምኒልክን ጉልበት ከዮሐንስ ጉልበት የጠነከረ ለማድረግ ሲያደርጉት የነበረውን ጥረት ሲከታተሉት የነበሩት ዮሐንስም ክንዳቸውን በቀላሉ የማይታጠፍ ለማድረግና ምኒልክንም ለማስገበር ሲሉ የሠራዊታቸውን ቁጥር እስከ አንድ መቶ ሺህ ከአደረሱት በኋላ፥ ክዚሁ ውስጥ እስከ ዐርባ ሰባት ሺህ
የሚደርሰውን ልዩ ልዩ መሣሪያዎች አስታጠቁት። ከጉንደትና ጉራዕ ጦርነቶች የተገኘው ቀላል መካከለኛና ከባድ መሣሪያም የበላይነታቸውን ያረጋገጡበት ዋናው ትጥቃቸው ነበር።
ከመሣሪያው ጥራትና ብዛትም ሌላ በአጼ ተክለ ጊዮርጊስና በግብጾች ላይ ያገኙት ድል ዝናቸውንና ጥንካሬያቸውን “አበሻ መሬት አውጥቶ በአፍሪቃ፡ በእስያና በአውሮጳ ውስጥ አስተጋብቶላቸው ነበር። በአሜሪካም ውስጥ ቢሆን፡ “የኛ የጦር መኮንኖች ያዘመቱትን የግብጽን ጦር ድል ያደረገ ብርቱ ንጉሥ” የሚል ጸጸት–ለበስ ታዋቂነት አትሮላቸው ነበር።
ታዲያ እንደዚያ ሆኖ ስሙ የገነነ ሠራዊት ሸዋ የገባ እንደሆነ ሊያደርስ የሚችለውን ብርቱ ጉዳት አስቀድመው የተረዱትና የተጠነቀቁበት ከጐልማሳው ምኒልክ ይልቅ አዛውንቱ አጐታቸው ዳርጌ ንበሩ። “ጉዳዩን በቀላሉ አትዩት፤ በየልቦናችሁ ምከሩበትና በእርቅ ይለቅ” ሲሉ አዛውንቱ “ጦር ጠማኝ” ይሉ የንበሩት የምኒልክ የጦር አበጋዝ ግን፤
“ወይ እሳቸው መጥተው፥ ያለዚያ እኛ ዘምተንባቸው ሳንሞካከር እንዴት አስቀድመን እንገብራለን” እያሉ ምኒልክን ይወተዉቱ ነበር።
በዮሐንስ ቤተ መንግሥት እንደአባት ይታዩ የንበሩት ራስ አርአያም በበኩላቸው፤
“የሁለት ወንድማማች ጠብ ማንን ጐድቶ ማንን ይጠቅም ይመስላችሁ? ኢትዮጵያን እኮ ነው የሚያዳክማት! ኢትዮጵያን እኮነው የሚያሳንሳት! ኢትዮጵያን እኮ ነው የጠላቶቿ መሳቂያ የሚያደርጋት! ታሪክ ይወቅሰናል፤ ትውልድ ያፍርብናል፤ ታቦትና መስቀል አስይዘን ካህናትን ወደ ምኒልክ እንስደድ እንጂ ጦር መምዘዙን አልስማማበትም” እያሉ የእህታቸውን ልጅ ከነጦር አበጋዞቻቸው ይቆጡ ነበር።
Continue reading…AtseYohannesNegusMenilik
Posted in Ethiopia | Tagged: Atse Yohannes, Emperor, Ethiopia, Ethiopian History, Great Ethiopians, King Menilik, Menelik, Menilik, Yohannes | Leave a Comment »