Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Woolsey fire’

ካሊፎርኒያ ሰዶም እና ገሞራ | በኢትዮጵያ ፀበላት ላይ ሤራ የሚጠነስሱት የ እነ ዊል ስሚዝ ቤቶች በእሳት ጋዩ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 12, 2018

ካሊፎርኒያ (ካሊፍ + ኦርኒያ) እየነደደች ነው። በህይወቴ እንደዚህ የመሰለ ነገር አይቼ አላውቅም

ከጥቂት ወራት በፊት ባቀረብኩት ቪዲዮ ላይ “የአርቲስት ዊል ስሚዝና ባለቤቱ ጄዳ የኢትዮጵያ ጉብኝት

ክቡሩን ፀብል ፍለጋ ወይስ ውሃ ለመጠጥ?“ የሚል ጥያቄ ጠይቄ ነበር። ሁሉም በእርዳታ ስም ወደ አገራችን እየገቡ ዲያብሎሳዊ ሥራዎቻቸውን አሁንም ቀጥለዋል።

በጣና ሐይቅ ያሉትን ብርቅ ገዳማት ለማዘጋት እምቦጩን ተከሉ፣ በላሊበላ መኻን ለሆኑ እህቶቻችን ለመጸንስ እንዲችሉ የሚረዳቸውን ኩሬ “ቢልሃርዝያ” አለበት በማለት አዘጉት፣ በትግራይ ደግሞ ፈውስ የሚሰጡትን ድንቅ ፀበላት በ ”ኮሌራ” አምጭ ባክቴሪያ በመበከል ብዛት ያላቸውን ወገኖቻችን ከገደሏቸው በኋላ ነዋሪው ጸበል እንዳይጠቀም ተደረገ…. እንግዲህ፡ ይህ ለአለፉት ጥቂት ወራት ብቻ መሆኑ ነው። እግዚአብሔር አያይም፥ የያዕቆብ አምላክ አያስተውልም እያሉ እኮ ነው።

ጊዜውን ጠብቆ ልክ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ዕለት የወጣ ዜና፤ የኛዎቹ ፀጥ ብለው ነበር፥ ርዕሱ ላይ እናተኩር፦

+ ‘Holy Water’ Blamed for Cholera Outbreak In Ethiopia

+ Cholera Outbreak ‘sparked By Holy Water’ as Deadly Disease Kills 10 And Infects 1,200

+ Cholera Outbreak Spread By Holy Water Leaves 10 Dead And 1,200 Infected

ታዋቂ የሆኑት የሆሊውድ አርቲስቶች እና የሉሲፈር አምባሳደሮች፤ የእነ ካርዴሺያኖች፣ ሊሊ ፓምፕ፣ ማርቲን ኢጊ አዛሊያ፣ ኬንዳል ጄነር ካትሊን ጄነር ዊል ስሚዝ ሌዲ ጋጋ (ስሞቻቸው ሁሉ ልክ እንደ ጣዖት አምላኪዎቹ፡ ዲያብሎሳዊ ቃና ያላቸው ናቸው) እና የሌሎችም መኖሪያ ቤቶች፡ “ ውልሴይ እሳት” የሚል ቅጽል ስም በተሰጠው በካሊፎርንያው የዱር እሳት በመጋየት ላይ ናቸው። እነዚህ ትዕቢተኞች በእሳት ቃጠሎው ሳቢያ ቤቶቻቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል። ይቅመሷት፤ ማሊቡ የተባለውን መንደር የምድር ገነት ለማድረግ አልመው ነበርና። ዊልሴይ እሳት = ዊል = ዊሎው = ዊል ስሚዝ

አሁን ድሃዎቹም ኃብታሞችም እኩል ናቸው፤ ሁሉም ቤት አልባ ሆነዋል!

እነዚህ ቅብጥብጥ ሀብታም ሰዎች አሁን ለድሆች እና ለቤት አልባዎች የበለጠ ይቆረቆሩ ይሆናል የሚል ተስፋ አለኝ።

የመጭው ዘመን ምን እንደሚመስል እግዚአብሔር እያሳየን ነው።

ከዚህ አሰቃቂ ሁኔታ የምናገኘው ጥልቅ ትምህርት አለሰዶም እና ገሞራም ድራሻቸው እስኪጠፋ ተቃጥለዋል፤ የዘመናችን የሰዶማውያን መናኽሪያ የሆነችው ካሊፎርኒያም ዳግም ሎጥ ለቅቆ ከወጣ በኋላ በመሬት መንቀጥቀጥ ትናወጣለች፣ በእሳትም ትጋያለች።

ካሊፎርኒያ እና ሳዑዲ ባቢሎን ለምንገኝ ወገኖች፡ ዳግም ሎጥ ለመሆን ቶሎ ያብቃን።

______

Posted in Conspiracies, Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: