በጣም ያሳዝናል፤ ብዙ የዜና ማሠራጫዎች ፀጥ ብለዋል…
በካናዳ ጠቅላይ ግዛት በማኒቶባ ዋና ከተማ ዊኒፔግ ባለፈው እሑድ ዕለት የአንድ ቤተክርስቲያን ውሳጤ በክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተበለሻሽቶ እንዲሁም የኢየሱስ ክርስቶስ እና ድንግል ማርያም ኃውልቶች ወድቀው እና ፈራርሰው ተገኝተዋል። ይህን መሰሉ እርኩስ ድርጊት ሲከሰት በሳምንት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑ ነው፤ ባለፈው ሳምንት አንድ ሌላ ቤተክርስቲያን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት ተፈጽሞ ነበር።
ከሦስት ዓመታት በፊትም በዚሁ ጠቅላይ ግዛት በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ህንፃ ላይ የእሳት ቃጠሎ ደርሶ ነበር።