❖❖❖[መዝ.፷፰፥፴፬]❖❖❖
“ሰማይና ምድር ባሕርም በእርስዋም የሚንቀሳቀስ ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግኑታል“
እንግዲህ ምልክቶቹ በሰማዩና በዓየሩ ላይ ናቸው። ከእንግዲህ “አላየንም! አልሰማንም!” የለም።
🛑 አምና ልክ በዚህ ጊዜ ፩ሺህ የዋልድባ አባቶችን የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ አባረራቸው፤ ዘንድሮ በፀሐይ ዙሪያ የማርያም መቀነት ታየ። አሕዛብ ወዮላችሁ! ወዮላቸው!
በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ አባቶች ከሰማይ በማርያም መቀነት አምሳል ከሰማይ ብርሐን ሲወርድላቸው አይተው መጥተው እሙሀይን በረከት በረከትዎ ይድረስብን እናታችን ብለው እጅ ነስተዋል።
❖❖❖[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩፥፳፭፡፳፮]❖❖❖
“በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።”
🛑 ባለፈው ሐሙስ / መጋቢት ፳፱/29 ፳፻፲፬ ዓ.ም ዕለት በታላቁ የቅድስት ድንግል ማርያም በዓል የደስታ ፅንሰት እና በአለ ወልድ/ትስብእት ባለ እግዚአብሔር ቀን በኢትዮጵያ ሰማይ ፀሐይቱ በማርያም መቀነት አክሊል ተከብባ ነበር። ከሳምንት በፊት እዚህ አውሮፓ ፀሐይዋ ላይ የሆነ ምልክት(ታች ምስሉ ላይ መኻል ፀሐይዋ ላይ እንደሚታየው) ታይቶኝ ወደ ሰማይ ሳንጋጥጥ መንገዶች፤ “ምን እየተመለከትክ ነው?” ብለው ሲጠይቁኝ ነበር። ለካስ መጭውን በኢትዮጵያ የታየውን የፀሐይ ክስተት ሊጠቁመኝ ኖሯል። ይህ በአክሱም ጽዮን ላይ ለዘመቱትና ጽዮናውያንን በረሃብ ቆልተው ለመጨረስ ለደፈሩት የምንሊክ ፬ኛ ትውልድ ከሃዲዎች ለሆኑት ለደቡባውያኑ ለኢትዮጵያ ዘ-ስጋ ትልቅ የማስጠንቀቂያ ምልክት ነው! ዋ! ብለን ነበር። በመላው ዓለም ተዓምር እየታየን ነው!

ወንጀለኞቹ የኦሮሞ፣ አማራ እና ኤርትራ ሰአራዊቶች ሆን ብለው ኦርጋኒክ የሆኑትን የጤፍ እንጀራዎች፣ ጥራጥሬዎች፣ አታክልቶችና ፍራፍሬዎች የትግራይ ሕዝብ እንዳይመገብ ነው ማሳዎችን፣ እርሻዎችን፣ የአታክልት ቦታዎችን፣ የእኅል ጎተራዎችን እንዲሁም ቤት ውስጥ ያሉ ሊጦችን ሲያቃጥሉ፣ ሲያበላሹና ሲመርዙ የነበሩት። እንስሳቱን እና ከብቶችንም ገድለዋቸዋል፣ ዘርፈዋቸዋል። እንግዲህ ይህ ሁሉ አረመኔያዊ ተግባር የትግራይን ክርስቲያን ሕዝብ ከማስራብ ዘልቆ የተረፉት በእርዳታ ለሚመጡ የተዳቀሉ/GMO ተጋላጭ እንዲሆኑና ማንም በማይመረመረው የእርዳታ ምግብ፣ መጠጥና ክትባት መንፈሳዊ ፀጋቸውንም እንዲያጡ በማሰብ ነው።ለአሚሪካ አውሎ ነፋሳት ምክኒያት ይሆናሉ የሚሏቸውን ፩ሺህ ትግርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የጸሎት አባቶች/መነኮሳት ከዋልድባ ገዳም እንዲባረሩ የተደረጉበት አንዱ ዓላማቸው ይህ ነው፤ አዎ! አባቶች በእርዳታ ለሚመጡ የተዳቀሉ/GMO ምግቦች ተጋላጭ ሆነው ከእግዚአብሔር እንዲለዩ ለማድረግ በማሰብ ነው።
እርግጠኛ ነኝ ትዕዛዙ የመጣውም በተለይ ከአሜሪካውያኑ የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ሞግዚቶች ነው። በመላው ዓለም ስውርና ኃይለኛ የሆነ መንፈሳዊ ውጊያ እየተካሄደ ነውና፤ በጸሎታቸው አውሎ ነፋሳቱን/ሃሪኬኖቹን/ቶርናዶዎቹን የሚያስነሱት አባቶችን በማፈናቀልና ወደ አክሱም ወስዶ ለረሃብና ለክትባት በማጋለጥ ከመላው የትግራይ ሕዝብ ጋር በጅምላ አብሮ በመጨረስ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ ነው። መንፈሳዊ ውጊያውን አልቻሉትምና! ድራማ እየሠሩ ያሉትም ጊዜ ለመግዛት ነው።
❖ ከዋልድባ ገዳም ሺህ የዋልድባ መነኮሳትን በሑዳዴ ጾም ባበረራቸው በክርስቶስ ተቃዋሚው የፋሺስቱ ኦሮሞ አገዛዝ ላይና ድርጊቱንም በደገፈው ሁሉ ላይ ለተገፉ የሚፈርድ፣ ለተበደሉ የሚበቀል እውነተኛ ዳኛ ልዑል እግዚአብሔር ቁጣውን በቅርቡ ያወርድበታል 😠😠😠
✞✞✞[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፷፯፥፴፡፴፩]✞✞✞
“በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን ጉባኤ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፤ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው። መኳንንት ከግብጽ ይመጣሉ፤ ኢትዮጵያ እጆችዋን ወደ እግዚአብሔር ትዘረጋለች። እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሀ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው። እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፤ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ።”
💭 በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮን የወደመው ወፍጮ የዋልድባ ገዳም ንብረት ነው | ፲፱ እናቶች ተሰውተዋል
😠😠😠 የጨለማ ዘመን ኢትዮጵያ😢😢😢
በደደቢት ከተማ፤ በጌታችን ልደት ዕለት ሃምሳ ዘጠኝ እናቶችና ሕፃናት በክርስቶስ ተቃዋሚ ቱርክ ድሮኖች ተጨፍጭፈው የሰማዕትነትን አክሊል ተቀዳጅተዋል።
ከሁለት ቀናት በኋላ ደግሞ በማይ ጸብሪ ከተማ ግራኝ መሀመዳውያኑን የክርስቶስ ተቃዋሚዎች አጋሮቹን ጋብዞ ለዋልድባ መነኮሳት እህል ሲፈጭ የነበረውን የወፍጮ ቤት አውድሞ እናቶችን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደላቸው። ምን ዓይነት ሰይጣናዊነት ነው፤ ጃል?! እነ ግራኝና ጭፍሮቻቸው ምን ያህል ከሃዲዎች፣ አረመኔዎችና ደፋሮች ቢሆኑ ነው!? ዓይናችን እያየ? ከፕሬዚደንት ጆ ባይደን ፈቃዱን አግኝተው ነውን? ወደ አሜሪካ የሚጓዙት አውሎ ነፋሳት መነሻቸው ይህ አካባቢ መሆንን ደርሰውበታል። ከወራት በፊትም አንድ ሺህ የሚሆኑ ጽዮናውያን አባቶችን ከዋልድባ ገዳም እንዲባረሩ ያደረገውም እርኩሱ ግራኝ አብዮት አህመድ አሊ መሆኑም ግልጽ ነው። ግራኝ በገዳማቱ ላይ ጥቃት እንደሚፈጽም፣ የኑክሌር መሳሪያ ካገኘም (ምናልባት በቅርቡ በቱርክ የሚገኙትን የአሜሪካ የኑክሌር መሣሪያዎች ኦሮሚያ በተሰኘው ሲዖል ለማስፈር ከእብዱ ኤርዶጋን ጋር ሳይስማማ አልቀረም)በአክሱም ጽዮን ላይ ምንም ሳያመነታ ሊጠቀም እንደሚችል ከሦስት ዓመታት በፊት አውስተን ነበር።
✞✞✞“ዋልድባ ሐጢአት አይሻገርብሽ እህል እንዳይበላብሽ”✞✞✞
✞✞✞ደብረ ዋሊ ወይም ዋልድባ ገዳም በ ፬ /4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ አካባቢ ተመሰረተ✞✞✞
✞✞✞ ስለ ዋልድባ ገዳም ታሪክ (አቀማመጥና ስያሜ)✞✞✞
ዋልድባ ገዳም በሰሜን ጎንደር በምዕራብ ትግራይ በተከዜ ወንዝ በዛሬማ ወንዝ በእንስያ ወንዝ በወልቃይት በጠለምት በፅንብላ በስሜን ጃናሞራ በአርማጭሆ በነዚህ ቦታዎችና ወንዞች ተከቦ ተከብሮና ታጥሮ በአስደናቂ የመሬት ተፎጥራዊ አቀማመጥ ልዩ በሆነ የምድር ካርታ በወንዞች ብቻ የታጠረ ነው ዋልድባ አብረንታንት ገዳም በኢየሱስ ክርስቶስ የተገደመ ነው።
ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ ፬ /4ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ከተገደሙት ገዳማት አንዱ የሆነው ይህ ገዳም፤ምድር ስትፈጠር ጌታ ባወቀ ያዘጋጀው ቅዱስ ቦታ ነው። የትንቢቱ ቃል የተነገረለት ዋልድባ ወይም ዋሊ ማለት ምን ማለት ነው? እመቤታችን ዋሊ የሚባል ገዳም ደረስን ብላ ተናገረችው በውስጡ ባለችው ዕፅ ምክንያት ሲሆን፤ ይቺ ዋሊ የተሰኝች ዕፅ በገነት የምተገኝ ናት።
የርሷም ቅጠሎች ሰፋፊና ቅርንጫፎቿ የበዙ፣ ሁል ጊዜ ጠዋት አብባ በ፱ ሰዓት የምታፈራ ዕፅ ናት። ዋሊ ዱባ የሚያክል ፍሬ በመያዟ በተለምዶ ዋሊዱባ በማለት ስትጠራ ቆይታ በኋላ ዋልድባ ለመባል በቅታለች። ዛሬም ቢሆን የቅዱሳን ምግብ ሆና የምታገለግለውን ዕፅ ከሥጋ ህፀፅ የራቀ ሁሉ በዓይነ ኅሊናው የብቃት መጽሔት ሊያያት ይችላል።
በዚች ዕፅ ስያሜ የተጠራው የዋልድባ ገዳም የቆዳ ስፋት ከምስራቅ ወደ ምዕራብ ከ፴ እስከ ፵ ኪሎሜትር ርቀት ስኖረው ከሰሜን ወደ ደቡብ ከ፹—፺ ኪሎ ሜትር ስፋት አለው። ገዳሙን እንደ ገነት ዙሪያውን በአራት አፍላጋት(ወንዞች) የተከበበ ሲሆን በምስራቅ የእንስያ፣በምእራብ የዛሬማ፣በደቡብ የማይወባ፣በሰሜን የተከዜ ወንዞች አጥር ቅጥር ሆነው ገዳሙን ይከልሉታል።አዋሳኝ ቦታዎቹም በምስራቅ የፀለምት ወረዳ፣ በምዕራብ ወልቃይት፣በደቡብ የዛሬማ ወረዳ፣በሰሜን ፅምብላ ናቸው።
በዚህ ስፋት ወስጥ እህል አይበላም፣ጠላና የመሳሰሉት መጠጣት አይፈቀድም፣የሞቀ ደመቀ አይለበስም።ይህ ገዳም ብዙ ዋሻዎች፣ፍርክታዎችና ገደላማ ስፍራዎች ያሉበት ሲሆን፤በየውኃ ምንጮችም ጭምር የጥንት የአበው ቅሪት ምልክቶች እስከ ዛሬ ድረስ ይታዩበታል።
የታተሙ ህንፃዎች፣የምድር ውስጥ ቤቶች፣የታሸጉ ዋሻዎች፣ዝጉሃን የሚኖሩባቸው ጉድጓዶችና የድንጋይ ስር ቤቶች ይገኛሉ።እልፍ አእላፈት ስውራን ይኖሩበታል።እነዚህም ለብቁአን፣ ለእረኞች ይከሰታሉ፣በአብዛኛው ደግሞ ከእይታ ውጭ በድምፅ ብቻ ጽንሐ ደውልና ይሰማል የእጣን ሽታ ይሸታል።
ቀድሞ የነበረው የሁል ጊዜ ምግባቸው፤ ለእመቤታችን ቆፍሮ የሰጣት ባለ ሶስት መቶ አስራ ስምንት ሥር ያለው ገመሎ፣ሣዳ፣ፃሌብ፣አጽግቢት ሲሆኑ፣ከቅጠላ ቅጠሎች ሓምለ አበው የተባለ፣ክረምት ብቻ የሚበቅል፣ጎመንን የሚተካ የፀጋይቶ የሚባል እጅግ መራራ ቅጠል፣ሰብኣ የሚባል ቅጠል ሌሎችም ናቸው። ፀጋይቶ ቅጠል ሁለቴና ሶስቴ ተቀቅሎ ምሬቱና መርዙ ሲቀንስ ሚበላ ነው። እስከመጨረሻው ቢቀቀል ምሬቱ አይጠፋም። ከመሬት ተቆፍሮ ከሚወጡት ውስጥ ፃብሌ የድንች መልክ የያዘ ሆኖ ለጊዜው ቀቅለው ቢበሉት ልብን ያጠፋል፣አምሮን ያናውዛል፣ለእብደት ያደርሳል።ይህ ተቆፍሮ ከወጣ በኋላ ከሳምንት ያለነሰ ጊዜ በውኃ ውስጥ እየተዘፈዘፈና እየታጠበ ተቀቅሎ ከቆየ በኋላ በፀሀይ ደርቆ በማጠራቀሚያ ጎተራ ይቀመጣል። ከዚህ በኋላ ነው ለምግብነት የሚጠቀሙበት። ከላይ የተጠቀሱት ሥራ ሥሮች ዛሬም ቢሆን በመነኮሳቱ እየተዘጋጁ ከሚበላው ቋርፍ በተጨማሪ ለመጠባበቂያ ለእለታዊ ምግብ ይጠቀማሉ።
✞ ከዱር አራዊትና እንስሳት ወገን፤
አጋዘን፣ድኩላ፣ወደምቢ፣ተኩላ፣ዘንዶ፣ጊንጥ፣ቀበሮ፣ጅብ፣ጉሬዛ፣ዝንጀሮ፣ጦጣ፣ሰስ፣ሚዳቋ፣የመሳሰሉት ሲኖሩ፤ አንበሶች(ከስውራኖቹ በስተቀር) እና ዝሆኖች፤በአድን ገዳሙን በየአመቱ ጥርግ አድርጎ በሚበላው ሰድድ እሳትና በአደን ምክንያት ተሰቅቀው በወልቃይት አደርገው ወደ መተማና ሱዳን ተሰደዋል።
✞ ከእጽዋትም ወገን፤
ሰርኪን፣ደማቅ፣እንኮይ፣የእጣን ዛፍ(መቀር)፣ሐሴን፣ሑመር፣ዋንዛ፣ሳላና፣ልዩ ልዩ አበቦች፣የሌሎችም እፅዋት ዝርያ ያለበት ገዳም ነው። በገዳሙ አንድ ክፍል በሆነው በአምርሓ ደጋ /አብርሃ ደጋ/ በተባለው ተራራማ ስፍራ ቁስቋም ማርያም ተብሎ የሚጠራ ስውር ቤተ-ክርስቲያን እንዳለ ይታወቃል።
በአሁኑ ሰአት እጅግ ብዙ ሊሒቃን ሙሁራን መናንያን መነኮሳት ያሉበት ቦታ ነው ዋልድባ እህል አይበላም በገዳሙ ቛርፍ የሚባል ከሙዝ የሚዘጋጅ ምግብ ይመገባሉ በተጨማሪም ግመሎ ሳዳ ጫብሌ ፃብሌ የሚባሉ ስራ ስሮች ከመሬት ከጫካው በመቆፈር መነኮሳቱ የሚመገቡት ምግብ ነው። ሌላ ስኳር ጨው በርበሬ ተልባ ኑግ ማር ብቻ በገዳሙ የሚፈቀዱ ናቸው ሌላ የእህል አይነት ፈፅሞ አይገባም ክልክል ነው።
ዋልድባ በዓለማችን ካሉ ገዳማት በስርአተ ገዳም በመነኮሳት ስምሪት እና በስርአተ ቤተ ክርስቲያን መሰረት የዋልድባ ገዳም ግንባር ቀደም ነው። ዋልድባ ገዳም በሶስት ታላላቅ ቦታዎች በአራት የአንድነት ማህበር ተከፍሎ የሚገኝ ብቸኛው በኢትዮጵያ የምናኔ ቦታ ነው። ዋልድባ በስሩ ብዙ ቅርጫፎች አነስተኛ ገዳማት ያሉት ሲሆን የእርሻ ቤቶች ሞፈር ቤቶች የአትክልት ቦታዎች የንብ ቤቶችና ወፍጮ ቤቶች በመባል የሚታወቁ ብዙ ቦታዎች ይገኛሉ። በአንዱ ሞፈር ቤት ከሁለት መቶ በላይ መነኮሳት ይኖሩበታል። ለምሳሌ በዶንዶሮቛ ሁለት መቶ ሐምሳ መነኮሳት በመዘጋ እጣኖ ማርያም መቶ ሰላሳ፣ በማይ ሐርገፅ መቶ ስድሳ፣ አባነፃ ሰማንያ ቤት ሙሉ በአሁኑ ማይገባ አምሳ በማይለበጣ ሁለት መቶ የሚኖሩ መናንያን አሉ።
በነዚህ ገዳማት የሚኖሩ መነኮሳት ሁሉ ተጠሪነታቸው ለዋናው አብረንታንት ነው። ዋልድባ አንድ አይነት ልብስ ነው የሚለበሰው፤ ስሙ ወይባ ይባላል። ዋልድቦች በምናኔ በመንፈሳዊ አስተዳደር ሊሒቃን ናቸው። ገዳሙ ፍፁም የመናኞች ቦታ ነው። እጅግ ፀሎተኞች ናቸው በስራም ቢሆን ዋልድቦች እጅግ አስደናቂ ተአምር ሰሪ ናቸው የዋልድባ መነኩሴ ሰውነታቸው ቀጫጭን ለፀሎት የሚተጉ አዕምሮአቸው በመንፈስ ሙጡቃን ናቸው። ዋልድባ ስርአተ ዐበው በሚባለው መፅሐፍ እንደተፃፈው “ዋልድባ ሐጢአት አይሻገርብሽ እህል እንዳይበላብሽ” የሚል ትዕዛዝ እስካሁን ገዳሙ ውስጥ እህል አይበላም እርሻም አይታረስም ያረሰ ካለ ራሱ ቀድሞ ይጠፋል።
_____________