የእባብ ቸርች ይሉታል።
አንድ አሜሪካዊ ጴንጤ ፓስተር በአገልግሎት ጊዜ በመርዛማ እባብ ተነደፈ።
ፓስተር ኮዲ ኩይትስ ትልቅ መርዛማ እባብ እየተሸከመ በኬንታኪ ግዛት በሚገኘው የጴንጤኮስታል ቸርቹ ውስጥ አገልግሎት ይሰጣል። ይህ አደገኛ የአምልኮ ሥርዓት የቀድሞውን ፓስተር አባቱን የ 42 ዓመቱን ጄሚ ኮትስን በ 2014 ዓ.ም እንዲሁ በእባብ ተንደፎ እንዲሞት አድርጓል።
በዚህ አስደንጋጭ ቪዲዮ ላይ ፓስተር ኮዲ ኮጽስ በተሸከመው እባብ ከተነደፈ በኋል ሸሚዙ በደም ተቀብቶ፣ እባቡ ሊገድለው ከሚችለው መርዛማ ቁስል ለመነሳት ሲሞክርና ሰዎች ለእርዳታ ሲደግፉት ይታያል።