Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘The Signs’

Hurricane Survival: Ethiopian Angels Protected Me Over the Years

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on October 4, 2016

Hurricanes: Nature and Nature’s God (my post from October 31, 2012 –Donald Trump implicated)

Hurricane Matthew (Updated)

The Real Home of Hurricanes: Ethiopia?

 

__

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | 1 Comment »

የአጋንንት መሰልጠኛ ጊዚያት ላይ ነን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 22, 2012

 

በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ፤ ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር

ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል በአራቱም የምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ ጎግንና ማጎግን እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትላቸው ይወጣል ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው” (ራእ. ዮሐ.297)

ሰይጣንና ሰራዊቱ አጋንንት በዘመን መጨረሻ እንደሚፈቱና በአራቱ የዓለም ማዕዘን ሲብሉን ማኅብረሰብ ሆነ በወታደራዊ ኑሮ የሚኖሩትን ሁሉ እንደሚያሰልፍ ጦርነትን በዓለም ዙሪያ እንደሚያውጅና ክህደት ጥፋት ርኩሰትና በሽታ ምድርን ሁሉ እንደሚሞሉ በእግዚአብሔር ቃል ተረጋግጧል።

ይህ የዓለም ጥፋት ምልክትና መጀመሪያ ሲሆን በይበልጥም የአጋንንት መሰልጠኛ ጊዜ ልንለው እንችላለን፡ አጋንንት ጊዜን እየለዩ እንደሚሰሩና እንደሚሰለጥኑ መጽሐፍ ቅዱስ በቂ ማረጋገጫ ይሰጣል ይህም የጥፋት ሥራ ለመስራት የሚፋጠኑበት ጊዜ ማለት ነው።

በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም” (መዝ.96)

በማለት አጋንንት በጨለማ እንደሚሰለጥኑ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገርብሎ በእኩለ ቀን እንደሚሰለጥኑ ከቀትር ጋኔን አትፈራም ብሎ በእኩለሌሊት እንደሚሰለጥኑከሌሊት ግርማ ብሎ ገልጾታል።

ኢየሱስ ክርስቶስ ልጁን እንዲፈውስልት የለመነው አንድ ሰው ልጁን የያዘው ጋኔን ጊዜ እየለየ እንደሚሰለጥንበት እንዲህ ሲል አረጋግጧል፦

ወደ ሕዝቡም ሲደርስ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀርቦና ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ልጄን ማርልኝ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሰቃያልና” (ማቴ.1717)

ማለት ልጁን የያዘው መንፈስ የጨረቃን መውጣት እየተከተለ በዚያ ግዜ ኃይሉን ሁሉ ይገልጥበትና ያሰቃየው እንደነበር የተናገረው ቃል ተጨማሪ የአጋንንት መሰልጠኛ ጊዜ ማረጋገጫ ነው።

እነዚህ ጊዜያት በቤተክርስቲያን የጸሎት ጊዜያት ተካተዋል፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜና በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ራሳቸውን በጸሎት ሊያስጠብቁ ይገባል።

ይልቁንም አጋንንት በሜሰለጥኑበትና ከእስራቸው በሚፈቱበት ዋዜማ በኛ ዘመን ራሳችንን ከክፉ መንፈስ ሥራ ሁሉ ልንጠብቅ ይገባል፡ ማናቸውንም ህመም ተፈጥሮአዊ ብቻ አድርጐ አለመውሰድና ራሳችንን ወደ ቤተክርስቲያን የፈውስ አገልግሎት (ምስጢረ ቀንዲል/ጠበል) ማቅረብ ይኖርብናል።

______

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: