Posts Tagged ‘The Exorcist’
Morning-after Pill is a Cure for ‘The Unexpected,’ Billboard Tells Ethiopian Girls
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 3, 2013
To the American viewer, the towering billboard’s purpose is ambiguous. But to young Ethiopian women,
Posted in Ethiopia, Infos, Life | Tagged: Abortion, Birth Control, Levonorgestrel-based Contraceptives, Planned Parenthood, Population Control, The Exorcist | 34 Comments »
የአጋንንት መሰልጠኛ ጊዚያት ላይ ነን
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on July 22, 2012
በዲ/ን የሺጥላ ሞገስ፤ ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር
“ሺሁም ዓመት ሲፈጸም ሰይጣን ከእስራቱ ይፈታል በአራቱም የምድር ማዕዘን ያሉትን አሕዛብ ጎግንና ማጎግን እንዲያስታቸው ለሰልፍም እንዲያስከትላቸው ይወጣል ቁጥራቸውም እንደ ባሕር አሸዋ የሚያህል ነው” (ራእ. ዮሐ.29፥7)
ሰይጣንና ሰራዊቱ አጋንንት በዘመን መጨረሻ እንደሚፈቱና በአራቱ የዓለም ማዕዘን ሲብሉን ማኅብረሰብ ሆነ በወታደራዊ ኑሮ የሚኖሩትን ሁሉ እንደሚያሰልፍ ጦርነትን በዓለም ዙሪያ እንደሚያውጅና ክህደት ጥፋት ርኩሰትና በሽታ ምድርን ሁሉ እንደሚሞሉ በእግዚአብሔር ቃል ተረጋግጧል።
ይህ የዓለም ጥፋት ምልክትና መጀመሪያ ሲሆን በይበልጥም የአጋንንት መሰልጠኛ ጊዜ ልንለው እንችላለን፡ አጋንንት ጊዜን እየለዩ እንደሚሰሩና እንደሚሰለጥኑ መጽሐፍ ቅዱስ በቂ ማረጋገጫ ይሰጣል ይህም የጥፋት ሥራ ለመስራት የሚፋጠኑበት ጊዜ ማለት ነው።
“በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም” (መዝ.96)
በማለት አጋንንት በጨለማ እንደሚሰለጥኑ “በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር” ብሎ በእኩለ ቀን እንደሚሰለጥኑ “ከቀትር ጋኔን አትፈራም ብሎ በእኩለሌሊት እንደሚሰለጥኑ” ከሌሊት ግርማ ብሎ ገልጾታል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ልጁን እንዲፈውስልት የለመነው አንድ ሰው ልጁን የያዘው ጋኔን ጊዜ እየለየ እንደሚሰለጥንበት እንዲህ ሲል አረጋግጧል፦
”ወደ ሕዝቡም ሲደርስ አንድ ሰው ወደ እርሱ ቀርቦና ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ልጄን ማርልኝ በጨረቃ እየተነሣበት ክፉኛ ይሰቃያልና” (ማቴ.17፥17)
ማለት ልጁን የያዘው መንፈስ የጨረቃን መውጣት እየተከተለ በዚያ ግዜ ኃይሉን ሁሉ ይገልጥበትና ያሰቃየው እንደነበር የተናገረው ቃል ተጨማሪ የአጋንንት መሰልጠኛ ጊዜ ማረጋገጫ ነው።
እነዚህ ጊዜያት በቤተክርስቲያን የጸሎት ጊዜያት ተካተዋል፡ ክርስቲያኖች ሁልጊዜና በሰባቱ የጸሎት ጊዜያት ራሳቸውን በጸሎት ሊያስጠብቁ ይገባል።
ይልቁንም አጋንንት በሜሰለጥኑበትና ከእስራቸው በሚፈቱበት ዋዜማ በኛ ዘመን ራሳችንን ከክፉ መንፈስ ሥራ ሁሉ ልንጠብቅ ይገባል፡ ማናቸውንም ህመም ተፈጥሮአዊ ብቻ አድርጐ አለመውሰድና ራሳችንን ወደ ቤተክርስቲያን የፈውስ አገልግሎት (ምስጢረ ቀንዲል/ጠበል) ማቅረብ ይኖርብናል።
______
______
Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: አጋንንት, Demonic Spirits, Evil Spirits, Exorcist, Rise of Demonic Possession, The End Times, The Exorcist, The Signs | Leave a Comment »