Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • May 2023
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘The Dove’

ርግቢቱ ዓለም – The Scared Pigeon

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 19, 2012

 

ዓለምእህታችን እ. . አ በማርች 14 2012 .ም ከንጋቱ 1200 ሰዓት ላይ ነው ያረፈችው ተብሏል። ወገኖቻችንና አንዳንድ ብሩክ የሆኑትን የዓለማችን ነዋሪዎችን ያሳዘነው የዓለም አሟሟት እጅግ በጣም ልዪ የሆነ ነገር በሁላችን ዘንድ ሊፈጥር ችሏል። ከሁለት ወራት በፊት ወደ ቤይሩት ከተማ ብቅ ያለችው እህታችን ኃይለኛ የሆነ መልዕክት ይዛልን ነበር ወደዚያኛው ዓለም ያለፈችው። በዓለማችን በመከራ ማዕበል የማይንገላታ ሰው የለም፤ አረመኔ በሆኑት የአረብ ሕዝቦች እጅ የተያዘ ደግሞ ከየተኛውም የዓለም ክፍል በይበልጥ በሥጋም ሆነ በነፍስ እየተቀጠቀጠ ነው ለመኖር የሚበቃው። መከራ የምንቀበለው ነገ በገሃነም እሳት ሳይሆን ዛሬ በምድር ሳለን መሆኑ ትንሽ ሊያጽናናን ይገባል። ለዚህም ነው እህታችን ዓለም በዚህች ምድራዊ ሲኦል በእግረ አጋንንት ተረገጠው ለሚኖሩት እህቶቻችን ሁሉ አሁን መልዕክተኛ ሆና የቀረብችልን። መቼም በመከራና ችግር ጊዜ ድንቅ ነገር ይመጣልና እምብዛም መደነቅ የለብንም። የፈጣሪ ክብር ሲገለጥ ሐሴት በማድረግ ደስ ሊለን ይገባል፡ መንፈሱ በኛ ላይ አርፏልና።

ላይ ቪዲዮው ላይ የምትታየውን ርግብ ያነሳኋት ባለፈው ሣምንት፡ በማርች 14፡ ልክ ከቀኑ 1200 ሰዓት ላይ ነበር። ርግቢቱ በመኖሪያ ቤቴ በመስኮት በኩል ገብታ ጋራጅ መውረጃ ላይ ቁጭ ብላ ነበር ያገኘኋት። እኔን ስታይ እየተንደፋደፈች ወደላይ በመብረር ከቤቱ ለመውጣት መስኮቱ ጋር ትጋጭ ነበር። እኔም ቆም ብየ ለ10 ደቂቃ ያህል ከታዘብኳት በኋላ ልረዳት ጠጋ አልኩኝ። መጀመሪያ ላይ ለመሸሽ ብትሞክርም በመጨረሻ ይዣት በመስኮቱ ላወጣት ችያለሁ።

የርግቢቱ ሁኔታ፡ በዚያ ቀን በጣም ስታሳስበኝ የነበረችውን የእህታችንን፡ የዓለምን ሁኔታ ያሳየኝ መስሎ ነበር የታየኝ። ርግቢቱ ከአካባቢዋ አምልጣ የሆነ ነገር ለማግኘት ወደ ቤቱ ገባች፡ ግን ቤቱ ውስጥ ምንም ነገር ስላላገኘች ወደ መጣችበት ለመመለስ ፈለገች፡ ሆኖም የገባችበት መስኮት ዘንበል ብሎ በጠባቡ የተከፈተ ስለነበር በቀላሉ ከቤቱ መውጣት አልቻለችም። ቆም ብዬ በታዘብኳት ወቅት ርግቢቱ ስታሳየው የነበረው የጭንቀትና የመረበሽ ሁኔታ እጅግ በጣም ያሳዝን ነበር፣ ከታች ጠብጠብ ታደርጋለች፣ በቂ አየር ስላልነበረም ክንፎቿን ዘርግታ እንደልቧ መብረር አልቻለችም፣ ስለደከመችም አፎቿን በጣም ከፍታ አየር ትስብ ነበር። መስኮቱ ላይ ሆና ከውጭ ሌሎች እርግቦችን ሲበሩ ስታይ ከነርሱ ጋር ለመሆን በመንደፋደፍ ከመስተዋቱ ጋር ትጋጫለች። በመጨረሻም ምንም ማድረግ እንደማትችል ስለተገነዘበች ጠጋ ብዬ እንድይዛት ፈቀደችልኝ። በመስኮቱ በኩል እጄን አውጥቼ ስለቃት ከመቅጽበት ነበር ነፃ ሆና እየበረረች ወደሰማይ ለመውጣት የበቃቸው።

እንደ ሪፖርተር ጋዜጣ ዘገባ ፤ ማክሰኞ ማርች 14ለረቡዕ አጥቢያ እህት ዓለምን የምትከታተላት ነርስ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ተኝታ አየቻት፡፡ 11 ሰዓት ላይም ተኝታ ነበር፡፡ ለሦስተኛ ጊዜ በ12 ሰዓት ስትጎበኛት ለአየር ማስገቢያ በተከፈተ ኮሪደር ላይ አንሶላ ቀዳ ራሷን አጥፍታ ተገኘች፡ ስለዚህ የሞተቸው ረቡዕ ማርች 14 ከንጋቱ 12 ሰዓት ላይ እንደሆነ ተገልጧል።

ይህን ዜና ካገኘሁ በኋላ ርግቢቱን ያገኘኋት በ12 ሰዓት ላይ መሆኑ ባጋጣሚ እንዳልሆነ አሁን ገባኝ። ርግብ የ መንፈስ ቅዱስ፥ የሰላምና የነፃነት ምልክት ናት። 12 ቁጥርም ቅዱስ ቁጥር ነው። እህት ዓለም ከእርጉሞች እጅ ነፃ ወጥታለች የእግዚአብሔርን ሰላም አግኝታለች። የበደሏት እርጉም ሕዝቦች ግን የሚቀጡበት ጊዜ ደርሷል፣ አምላክ የሰጣቸውን ዕድል ባለመጠቀማቸውም ተፈርዶባቸዋል ፤ የዘሯትን የጥላቻ ሰብል በቅርቡ ያጭዷታል።

መዝሙር 12

5 ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር፤ አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።

6 በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።

7 አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

8 በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።

 

A well-written song by David, when he was in the cave; a prayer.

Psalm 142

1 To the LORD I cry out; to the LORD I plead for mercy.

2 I pour out my lament before him; I tell him about my troubles.

3 Even when my strength leaves me, you watch my footsteps. In the path where I walk they have hidden a trap for me.

4 Look to the right and see! No one cares about me. I have nowhere to run; no one is concerned about my life.

5 I cry out to you, O LORD; I say, “You are my shelter, my security in the land of the living.”

6 Listen to my cry for help, for I am in serious trouble! Rescue me from those who chase me, for they are stronger than I am.

7 Free me from prison, that I may give thanks to your name. Because of me the godly will assemble, for you will vindicate me.

_________________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: