Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

 • February 2023
  M T W T F S S
   12345
  6789101112
  13141516171819
  20212223242526
  2728  
 • Archives

 • Categories

 • Recent Posts

Posts Tagged ‘The Book of Revelation’

የሳዑዲ ባቢሎንን ጥፋት የሚያዩ ሁሉ ያጉረመርማሉ ያዝናሉ፣ ያለቅሳሉ!!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 8, 2017

የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፲፰

ከዚህ በኋላ ታላቅ ስልጣን ያለው ሌላ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፥ ከክብሩም የተነሣ ምድር በራች።

በብርቱም ድምፅ። ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች፥ ወደቀች፥ የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፥ የርኵሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኵሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤

አሕዛብ ሁሉ ከዝሙትዋ ቍጣ ወይን ጠጅ የተነሳ ወድቀዋልና፥ የምድርም ነገሥታት ከእርስዋ ጋር ሴሰኑ የምድርም ነጋዴዎች ከቅምጥልነትዋ ኃይል የተነሳ ባለ ጠጋዎች ሆኑ ብሎ ጮኸ።

ከሰማይም ሌላ ድምፅ ሰማሁ እንዲህ ሲል። ሕዝቤ ሆይ፥ በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤

ኃጢአትዋ እስከ ሰማይ ድረስ ደርሶአልና፥ እግዚአብሔርም ዓመፃዋን አሰበ።

እርስዋ እንደ ሰጠች መጠን ብድራት መልሱላት፥ እንደ ሥራዋም ሁለት እጥፍ ደርቡባት፤ በቀላቀለችው ጽዋ ሁለት እጥፍ አድርጋችሁ ቀላቅሉባት፤

ራስዋን እንደ አከበረችና እንደ ተቀማጠለች ልክ ሥቃይና ኀዘን ስጡአት። በልብዋ። ንግሥት ሆኜ እቀመጣለሁ ባልቴትም አልሆንም ኀዘንም ከቶ አላይም ስላለች፥

ስለዚህ በአንድ ቀን ሞትና ኀዘን ራብም የሆኑ መቅሰፍቶችዋ ይመጣሉ፥ በእሳትም ትቃጠላለች፤ የሚፈርድባት እግዚአብሔር ብርቱ ነውና።

ከእርስዋም ጋር የሴሰኑና የተቀማጠሉ የምድር ነገሥታት የመቃጠልዋን ጢስ ሲያዩ ስለ እርስዋ ዋይ ዋይ እያሉ ያለቅሳሉ፤

ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው። አንቺ ታላቂቱ ከተማ፥ ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን፥ ወዮልሽ፥ ወዮልሽ፥ በአንድ ሰዓት ፍርድሽ ደርሶአልና እያሉ ይናገራሉ።

፲፩ የመርከባቸውንም ጭነት ከእንግዲህ ወዲህ የሚገዛ የለምና የምድር ነጋዴዎች ያለቅሱላታል ያዝኑላትማል፤

፲፪ ጭነትም ወርቅና ብር የከበረም ድንጋይ ዕንቁም፥ ቀጭንም ተልባ እግር ቀይም ሐርም ሐምራዊም ልብስ የሚሸትም እንጨት ሁሉ፥ ከዝሆን ጥርስም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥ እጅግም ከከበረ እንጨት ከናስም ከብረትም ከዕብነ በረድም የተሰራ ዕቃ ሁሉ፥

፲፫ ቀረፋም ቅመምም የሚቃጠልም ሽቱ ቅባትም ዕጣንም የወይን ጠጅም ዘይትም የተሰለቀ ዱቄትም ስንዴም ከብትም በግም ፈረስም ሰረገላም ባሪያዎችም የሰዎችም ነፍሳት ነው።

፲፬ ነፍስሽም የጎመጀችው ፍሬ ከአንቺ ዘንድ አልፎአል፥ የሚቀማጠልና የሚያጌጥም ነገር ሁሉ ጠፍቶብሻል፥ ሰዎችም ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አያገኙአቸውም።

፲፭፲፯ እነዚህን የነገዱ በእርስዋም ባለ ጠጋዎች የሆኑት እያለቀሱና እያዘኑ። በቀጭን ተልባ እግርና በቀይ ሐምራዊም ልብስ ለተጐናጸፈች በወርቅና በከበረ ድንጋይም በዕንቁም ለተሸለመች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ ይህን የሚያህል ታላቅ ባለ ጠግነት በአንድ ሰዓት ጠፍቶአልና እያሉ ስቃይዋን ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ይቆማሉ። የመርከብም መሪ ሁሉ በመርከብም ወደ ማናቸውም ስፍራ የሚሄድ ሁሉ መርከበኞችም ከባሕርም የሚጠቀሙ ሁሉ በሩቅ ቆሙ፥

፲፰ የመቃጠልዋንም ጢስ ባዩ ጊዜ። ታላቂቱን ከተማ የምትመስላት ምን ከተማ ነበረች? እያሉ ጮኹ።

፲፱ በራሳቸውም ላይ ትቢያ ነስንሰው እያለቀሱና እያዘኑ። በባሕር መርከቦች ያሉአቸውን ሁሉ ከባለ ጠግነትዋ የተነሣ ባለ ጠጋዎች ላደረገች ለታላቂቱ ከተማ ወዮላት፥ ወዮላት፥ በአንድ ሰዓት ጠፍታለችና እያሉ ጮኹ።

ሰማይ ሆይ፥ ቅዱሳን ሐዋርያት ነቢያትም ሆይ፥ በእርስዋ ላይ ደስ ይበላችሁ፥ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።

______

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ምዕራብ ወዴት ነው?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 25, 2011

አድገዋል፡ መጥቀዋል፡ ተራቅቀዋል ወይንም ሁሉንም አውቀዋል፡ ኃብቱንና ሥልጣኔውንም ተክነውታል የምንላቸው አገሮች አሁን እየመጣባቸው ያለው ጣጣ በጣም ትልቅ ነው። ይህ እየመጣባቸው ያለው መዘዝ ለሁላችንም ግልጽ በሆነ መልክ በመከሰት ላይ ይገኛል።

ታዲያ እነዚህ ሠለጠኑ የተባሉት ሕዝቦች፡ መንግሥታትና ተቋማት ሁሉ ይህን መገንዘብ ተስኗቸው ጥቃቅንና ከባድ ባልሆኑ ነገሮች እንዴት በቀላሉ ሊረበሹና ሊጨነቁ ይበቃሉ? ጥሩውንና መጥፎውን፡ ሊጠቅማቸውና ሊጎዳቸው የሚችለውንስ ነገር እንዴት አይለዩም? ጠላቶቻቸውንና ወዳጆቻቸውን ሁሉ ለይተው ለማወቅ ምነው አልተቻላቸውም?

እንደሚታወቀው፡ በኢትዮጵያ አዲስ ዓመት፡ በመስከረም 1 በአሜሪካ ላይ ጥቃት ያደረሱት አብዛኞቹ ሽብር ፈጣሪዎች የሳውዲ አረቢያና የግብጽ ዜግነት ያላቸው፡ በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን የሰለጠኑ፡ እንዲሁም በአውሮጳ ለትምህርት እየተላኩ እውቀት እንዲገበዩ የተደረጉ ግለሰቦች ነበሩ።

ታዲያ ይህ ሆኖ እያለ፡ እነዚህ ምርጥ ናቸው የተባሉት ሕዝቦች በፍርሃት ወሽመጥ ውስጥ ወድቀው ሊያጠፏቸው የተዘጋጁትን ጠላቶቻቸውን መዋጋት ሳይሆን፡ እንዲያውም እያቀረቡ/እየቀረቡ በሰፊ ሰፌድ አጎብድደው ሲያገለግሉ እናያለን። በዕውነት እጅግ በጣም ግራ የሚያጋባ ነገር ነው። ባጎረስኩ ተነከስኩ፡ እንዲሉ፡ እነዚህ በምዕራባውያን የተማሩት፡ በገንዘባቸው የታጠቁት የግብጽ፡ የፓኪስታን፡ የአፍጋኒስታንና የሳውዲ ዜጎች ተመልሰው በምእራቡ ዓለም ላይ ሲያፌዙና ሲሳለቁ፡ ባገኙትም አጋጣሚ ሁሉ ምዕራባውያኑን ከነርሱ ባገኙት ገነዘብና መሳሪያ ሁሉ ሲተናኮሏቸው፡ ሲይስፈራሯቸው ብሎም ሲገድሏቸው፡ እንዴት ቆራጥ የሆነ እርምጃ በመውሰድ በቀጥታ ሊዋጓቸው አልቻሉም የሚያሰኝ ጥያቄ ለመጠየቅ እንበቃለን።

የአሜሪካና የአውሮጳው ሕብረት መንግሥታት ለኢራቃውያን ሆነ ለአፍጋኒስታን ነዋሪዎች፡ ለቱርክ ሆነ ለግብጽና ለሳውዲ አረቢያ መንግሥታት እያደረጉላቸው ያለው የገንዘብና ሰብዓዊ የሆነ መስዋዕት ምናልባት በዓለማችን ታሪክ ታይቶ የሚታወቅ አይደለም።

ከጥቂት ወራት በፊት አሜሪካ ለሳውዲ አረቢያ መንግሥት እስክ 60 ቢልየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ የጦር መሳሪያ ቴክኖሎጂ ለማቀበል መስማማቷ ይታወቃል። ግብጽንና ፓኪስታንንም እስከ አፍንጫቸው ድረስ እያስታጠቀቻቸው ነው።

አሜሪካ፡ ግብጽ ከእስራኤል ጋር የሰላምስምምነት ካደረገችበት 1979 ..(..) ጀምሮ፡ ለግብጽ መንግሥት በየዓመቱ እስከ 2 ቢሊየን ዩኤስ ዶላር የሚጠጋ የውትድርና እንዲሁም እስከ 3ቢሊየን የሚጠጋ የኤኮኖሚ እርዳታ ያው ለ30 ዓመታት ያህል በማበርከት ላይ ትገኛለች። እስከ 2 ሚሊየን የሚቆጠሩ ወታደሮችን ያሰለፈው የግብጽ ሠራዊት በዓለም 10ኛ ጠንካራ ሠራዊት ሲሆን፡ ባጠቃላይ እስክ 11ቢሊየን ዩኤስ ዶላር የሚጠጋ የዓመት በጀት አለው። ይህ ሠራዊት እጅግ በጣም በተራቀቁ ዘመናዊ የአሜሪካ አብራምስ ታንኮች፡ ከ300 በላይ F-16 ተዋጊ አውሮፕላኖች እንዲሁም በተለያዩ ሚሳየሎችና የመገናኛ መሣሪዎች ሁሉ ያሸበረቀ ነው።

አክራሪ እስላሞችን የሚወክለውና የሙስሊም ብራዘርሁድ በመባል የሚታወቀው የእስልምና ቡድን አንድ ቀን ይህን ሁሉ የጦር ኃይል ለመረከብ እንደሚበቃ የሚያጠያይቅ አይደለም። አሜሪካ በተዘዋዋሪ መልክ ለዚህ ቡድን ስጦታ ለማድረግ ለ30 ዓመታት ያህል ደክማለች፡ ደምታለች ማለት ነው። ለግብጽ ጠላት ናት የምትባለው እስራኤል ብቻ ናት፡ ግብጽ ደግሞ ከእስራኤል ጋር የሰላም ስምምነት (እንደነሱ ፡ የተኩስ አቁም ስምምነት) በመፈራረም ግዛቴ ነው የምትለውን ሲናይን ከእስራኤል ተረክባ ለ30 ዓመታት ያህል በሰላም ለመኖር በቅታለች። ታዲያ ይህ ሁሉ የውትድርና ትጥቅ ለምን አስፈለጓት ይሆን? ለዚህ አክራሪ የእስልምና ቡድን አሳልፎ ለመስጠት አይሆንምን?

ለማንኛውም ይህ የአክራሪ እስላሞች ቡድን ስልጣን ላይ ሲወጣ በተለይ እስራኤል፡ ኢትዮጵያና የግብጽ ክርስቲያኖች የመጀመሪያዎቹ ዒላማዎቹ ይሆናሉ። አገራችን የአባይን ውሃ እንደመሳሪያ መጠቀም ግድ ሊሆንባት ነውና አርቆ አሳቢ የሆኑ ኢትዮጵያውያኖች ሁሉ አሁኑኑ በጉዳዩ ላይ አጥብቀው ሊያስቡበት ይገባል።

መቼስ፡ ምእራባውያንን ወደ ሙስሊሙ ዓለም የሚስባቸው ሰይጣን ብቻ ሊሆን እንደሚችል ያልተገነዘብ ሰው የሚኖር አይመስለኝም። በግሪኮች ስልጣኔ የተሰራውን ካባ ለብሰው ዓለማችንን ሲያምሱት የቆዩት አውሮፓና አሜሪካ ከተባባሪዎቻቸው አረቦች ጋር በመሆን ወደ ሦስተኛው የዓለም ጦርነት እያመሩ እንደሆነ ማየት አይሳነንም።

የሰሜን አትላንቲክ ስምምነት ድርጅት በሚል ተሰባስበው በኢራቅና በአፍጋኒስታን፡ በአፍሪቃ ቀንድና በሊባኖስ አካባቢ የሰፈሩት ሠራዊቶች ከ ነጭ ዘር (Caucasian) የተውጣጡ ብቻ ናቸው። እነዚህም ሠራዊቶች በተለይ እስራኤልንና ኢትዮጵያን ነው ከብበው የሚታዩት፡ ለዚህም ቀንደኛ ተባባሪዎቻቸው የእየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ቃልኪዳን ያልተቀበሉት አረብ ሙስሊሞች ናቸው።

ሰሞኑን በሰሜን አፍሪቃ እና በቀሩትም የቅርብ ምስራቅ አገሮች እየታየ ያለው እንቅስቃሴ ያገሮቹን ሰላማዊ እና ዓለማዊ የሆነ ኑሮ ለማመሰቃቀል ሆን ተብሎ የተፈጠረ እንቅስቃሴ ነው። 97% የሚሆነው የግብጽ ምድር በረሃማ ነው፡ ስለሆነም አገሪቱ ምናልባት 5 ሚሊየን የሚጠጋ ነዋሪዎች ብቻ ሊኖራት ሲገባት አሁን እስከ 85 ሚሊየን ግብጻውያን ይኖሩባታል። በተቀሩትም የሰሜን አፍሪቃ አገሮች ተመሳሳይ የሆነ ሁኔታ ይታያል። ታዲያ ይህ ሁሉ ሰሜን አፍሪቃዊ ኑሮውን ወደፊት እንዴት ሊገፋ ይችላል? መልሱም፡ ስደት ነው የሚሆነው። ሕዝብ ደግሞ መሰደድ የሚጀምረው ባገሩ አስከፊ ሁኔታ ሲፈጠር ነው። አዎ፡ አሁን በቱኒዚያ፡ በግብጽ፡ በሊቢያ ሁከት ተፈጥሯል፡ በቅርቡም፡ በሞሮኮ፡ በአልጀሪያም እንዲሁ። በነዚህ አገሮቹም የእስላም አክራሪ ቡድኖች ስልጣን ላይ ይወጣሉ፡ አገሮቻቸውንም እስላም ካልሆኑ ወገኖች ሁሉ ነፃ ያወጣሉ፡ ልክ በኢራን እንደታየው፡ በብዙ ሚሊየን የሚቆጠሩ ሰሜን አፍሪቃውያን ወደ አውሮፓ፡ አሜሪካና አውስትራሊያ በብዛት መሰደድ ይጀምራሉ፡ እነዚህ በስደት የሚገኙትም ሙስሊሞች በሰፈሩባቸው አገሮች ጂሃዳዊ ተልዕኮአቸውን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ለማሟላት ይታገላሉ። ማለትም፡ ለምሳሌ በግብጽ፡ ልክ እንደ ኢራቅና ቱርክ፡ ክርስቲያኖችን ቀስበቀስ ማጥፋቱን ይቀጥሉበታል። ለዚህም ጂሃዳዊ ተልዕኳቸው፡ ምዕራባውያን መንግሥታት በብዙ ሚሊየን የሚጠጋ የኢኮኖሚ ድጎማያቀርቡሏቸዋል።

አቤቱ እንዳንተ ማን ነው? አቤቱ ዝም አትበል ቸልም አትበል። እነሆ፥ ጠላቶችህ ያውካሉና፥ የሚጠሉህም እራሳቸውን አንስተዋልና። ሕዝብህን በምክር ሸነገሏቸው፥ በቅዱሳንህም ላይ ተማከሩ፥ ኑ ከሕዝብ እናጥፋቸው፥ ደግሞም የእስራኤል ስም አይታሰብ አሉ። አንድ ሆነው በአንተ ላይ ተማከሩ፤ በአንተም ላይ ቃል ኪዳን አደረጉ፤ የኤዶማውያን ድንኳኖች እስማኤላውያንም፥ ሞአብም አጋራውያንም፥ ፍልስጤማውያንም ከጢሮስ ሰዎች ጋር፤ አሶርም ከእነርሱ ጋር ተባበረ፤ ለሎጥ ልጆችም ረዳት ሆኗቸው።መዝሙረ ዳዊት 821-9 በግልጽ ይነግረናል።

ትንቢተ ሕዝቅኤል 16:33እና 37-42ደግሞ እነዚህ ኢትዮጵያንና እስራኤልን የከበቧቸው ኃይሎች እነማን እንደሆኑ ይነግረናል፡ ስለዚሁ እነሆ፥ ከእነርሱ (ከዐረቦች) ጋር ደስ ያለሽን የወደድሻቸውንም ውሽሞችሽን (ነጮችን)ሁሉ ከጠላሻቸው (አረቦች) ሁሉ ጋር እሰበስባቸዋቸዋለሁ፡ በአንቺም ላይ በዙሪያሽ እሰበስባቸዋለሁ…“

ድንቁ መጽሐፍ፡ ትንቢተ ዳንኤል 11:32 ደግሞ ቀጠል ያደርግና ኢየሩሳሌምን የሚይዛትን የአረቦችን ሠራዊት (መሪውን)ቃል ኪዳኑን የሚበድሉትንም በማታለል ይስታልንጉሡ (የአረቦች ሠራዊት መሪ) ቀደም ብለው ሃይማኖታቸውን የካዱትን ሁሉ በማታለል የእነርሱን ድጋፍ ያገኛልብሎ ይነግረናል።

ራእይ 1712-13 ደግሞ ይህን ይለናል፡ ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶች ገና መንግሥትን ያልተቀበሉ አሥር ነገሥታት ናቸው፥ ዳሩ ግን ከአውሬው ጋር ለአንድ ሰዓት እንደነገሥታት ሥልጣንን ይቀበላሉ። እነዚህ አንድ አሳብ አላቸው፥ ኃይላቸውንና ሥልጣናቸውንም ለአውሬው ይሰጣሉ።በራእይ 1716-17 ቀጠል ያደርግና፡ ያየሃቸው አሥሩ ቀንዶችና አውሬው ጋለሞታዩትን (ባቢሎን ኢራቅን) ይጣላሉ፤ ባዶዋንና ራቁትዋንም ያደርጉዋታል፥ ሥጋዋንም ይበላሉ በእሳትም ያቃጥሏታል።ይለናል።

አሥሩ ቀንዶች በተለይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃል ኪዳን አባል አገሮች የያዙት አስሩ የአውሮፓው የምጣኔ ኃብት ማህበረሰብ መስራች አባል አገሮች መሆናቸው ናቸው።

የነበረውም፡ ኗሪውም፡ አዲሱም፡ ለወደፊትም ሕያው ሆኖ ለዘላለም የሚኖረው የሙያ ፈራጅ የጥበብ መደምደሚያ በሆነው በቸሩ ፈጣሪአችን በእግዚአብሔር ጸንቶ መኖር በጣም አስፈላጊ ነው።Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , | 3 Comments »

Vision of The Pale Green Horse?

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 6, 2011

Were we able to see a ghostly green pale horse and rider across the screen during a live MSNBC newscast from Egypt last Friday?

While watching the above video coverage of the protests in Egypt one can see what appears to be a skeletal man on horseback, covered in some sort of cloth that is blowing in the wind. What really makes this odd is the green color of the figure, and how it seems to ride through the crowd before the camera cuts away.

“I looked and there was a pale green horse! Its rider’s name was Death, and Hades followed with him; they were given authority over a fourth of the earth, to kill with sword, famine, and pestilence, and by the wild animals of the earth.” (Rev 6:8)

The flag of the former United Arab Republic (left) has the colors of all four horsemen. The two green stars represent Egypt and Syria (remember that the last horse was green and had two riders). The United Arab Republic was a single sovereign country from 1958 to 1961, when Syria seceded from the union. Even after the succession, however, Syria and Egypt remained united; in 1967 they fought together in Six-Day War against Israel. Looking at the map, it does not take a genius to figure out what one main goal of a United Arab Republic would be. I do not know if the United Arab Republic will come back to life, but it is interesting to speculate on.

And the Egyptians will I give over into the hand of a cruel lord; and a fierce king shall rule over them, saith the Lord, the LORD of hosts. – Isaiah 19:4


 

 


 

Posted in Curiosity | Tagged: , , , , , , , , | 2 Comments »

 
%d bloggers like this: