Posts Tagged ‘St. Uriel’
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 29, 2022
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 😇 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
❖ ክፍል ፩
ጸሎት ቤት ውስጥ፤ ፳፪ ሰኔ ፪ሺ፲፬ ዓ.ም ቅዱስ ዑራኤል ይህን የጌታችን መታሰቢያ ከ፭ ዓመታት በፊት አሳይቼው ነበር ዛሬ ከበታቹ ያሉት የሻማ ብርሃናት የጽዮንን ቀለማት/ የማርያም መቀነትን ሠርተው ይታያሉ።
በጽዮን ቀለማት የደመቀው የእናታችን የቅድስት ማርያም ስዕል ዛሬ ከበታቹ ያሉት የሻማ ብርሃናት የጽዮንን ቀለማት/ የማርያም መቀነትን ሠርተው ይታያሉ። ኢትዮጵያዊ ገጽታ ያለውን ስዕል
በጥሞና እንመልከተው!
❖ ክፍል ፪
“ጌታችን የተገኘበት የ፪ሺ፱ ዓ.ም መስቀል ደመራ በመስቀል ዓደባባይ” በሚል ከ፭ ዓመታት በፊት፤ ገና አረመኔው ግራኝ አብዮት አህመድ መኖሩንም ሳናውቅ አቅርቤው የነበረው ድንቅ ቪዲዮ ነው፤ የዋቄዮ-አላህ-ሉሲፈር ባሪያዎች ለጅሃዳቸው በደብረዘይት (ቢሸፍቱ-ሆራ) ዝግጅት ላይ ነበሩ።
✞ አምላካችን ምልክቶቹን አሳይቶናል ፥ ዳግም ምጽአት / ደብረ ዘይት ✞
“እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፣ ወአምላክነሂ ኢያረምም፣ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል፤ አምላካችን ዝምም አይልም ከፊቱም እሳት ይነዳል”
✞ የምጽአት ምልክቶች ✞
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሳለ ደቀመዛሙርቱ ለብቻቸው ወደ እርሱ ቀርበው የዳግም ምጽአት ምልክትን ጠይቀውታል። እርሱም አስቀድሞ «ማንም እንዳያስታችሁ ተጠንቀቁ» ካለ በኋላ የሚከተሉትን ምልክቶች ገልጾላቸዋል።
💭 አስቀድሞ በነቢያት የተነገሩትም ምልክቶች ተጨምረዋል፤
- ☆ ብዙ ሀሰተኛ ነቢያት ይነሳሉ ፣
- ☆ ብዙ ሀሰተኛ ክርስቶሶች ይነሳሉ ፣
- ☆ ታላቅ ክሕደት ይሆናል ፣
- ☆ በብዙዎች ዘንድ ፍቅር ይቀዘቅዛል ፣
- ☆ የጦርነት ፣ የርኃብ ፣ የቸነፈር የምድር መናወጥ ወሬ መሰማት፣
- ☆ ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥት በመንግሥት ላይ መነሳሳት፣
- ☆ ክርስቲያኖች በአሕዛብ የተጠሉ መሆን፣
- ☆ የብዙዎች ለሞት ተላልፈው መሰጠት ፣
- ☆ የብዙዎች ከእውነት መንገድ መሰናከል ፣
- ☆ የጥፋት ርኲሰት በተቀደሰችው ስፍራ መታየት፣
- ☆ የተመረጡት እስኪስቱ ድረስ ድንቅ ተአምራት መደረግ ፣ (ማቴ ፳፬ የመከራ ዘመን ይሆናል)
- ☆ «ስለ ሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታላቁ ሚካኤል ይነሳል።» (ዳን ፲፪ ፥ ፩ )
- ☆ የአመጽ ሰው የክርስቶስ ተቃዋሚ መነሳት ፣ (፪ ተሰ ፪ ፥ ፫ )
- ☆ የአውሬው የስድብ አፍ በገልጽ በብዙዎች ላይ መገለጽ (ራእይ ፲፫፥ ፭ ) ፣ ወዘተ
ከላይ የተገለጹት ምልክቶች በአሁኑ ዘመን በአብዛኛው የታዩ እና እየታዩ ያሉ ናቸው። ትንቢቱን የተናገረው ባለቤቱ ወልደ አምላክ ክርስቶስ በመሆኑ የበለጠ ትኩረት እንድናደርግበት ግድ ይለናል። ከዚህም ተነስተን የክፋት ትንቢት መፈጸሚያ እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል። ከምልክቶቹ ፍጻሜ አንጻር ግን እራሳችንን መታዘዝ በማስተማር ሕይወታችንን በንስሐ ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ብቸኛ መፍትሄ ነው።
✞ ምጽአት ✞
ከብዙ የምጽአት ምልክቶች በኋላ የክርስቶስ ዳግም ምጽአት ይሆናል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ዘይት ተራራ ላይ እንዳረገ እንዲሁ ተመልሶ ይመጣል።
በአጠቃላይ ደብረ ዘይት ሁለት ተቃራኒ ነገሮች የሚፈጽሙበትን የነገረ ዳግም ምጽአት ሁኔታን ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምንማርበት የዓቢይ ጾም ሳምንት ነው። ይኸውም ትንሣኤ ዘለክብር እና ትንሳኤ ዘለሀሳር ነው። አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር የሚሆንበት ሌላው ከሰይጣን ጋር ኑሮው የሚወሰንበት፣ አንዱ መንግሥተ ሰማያትን የሚወርስበት ሌላው ገሀነመ እሳት የሚገባበት፣ አንዱ የሚደሰትበት ፣ ሌላው ዋይታ የሚያሰማበት፣ የበረከትና የመርገም ቀን፣ የተስፋና ተስፋ የመቁረጥ ቀን፣ የደስታና የጭንቅ ቀን፣ የእልልታና የዋይታ ቀን፣ አንዱ ሌላውን የማያድንበት፣ እናት ልጄን የማትልበት፣ ልጅ እናቴን የማይልበት፣ ባልና ሚስት የሚለያዩበት፣ ጓደኞች ዳግም የማይገናኙበት፣ ኃጥእ ከጻድቅ መተያየት የሚያበቁበት የመጨረሻ እለት ዳግም ምጽአት ናት።
ሰሚ ከሆንን የደብረ ዘይትን ጩኸት ልንሰማ ይገባናል። የምትነግረንን የምጽአትን ምልክቶች፣ የምጽአትን ትንቢቶች፥ «እግዚአብሔርሰ ገሀደ ይመጽእ፣ ወአምላክነሂ ኢያረምም፣ እሳት ይነድድ ቅድሜሁ። እግዚአብሔር በግልጽ ይመጣል፤ አምላካችን ዝምም አይልም ከፊቱም እሳት ይነዳል» ፣ ወዘተ የሚለውን ፣ ጌታ በወንጌሉ በፍርድ ቀን ለእያንዳንዱ እከፍለው ዘንድ በቁጣ እመጣለሁ ያለውን ፣.. ከደብረ ዘይት ልንማር ይገባናል። ያለዚያ ግን በመጨረሻው ቀን ዕጣ ፈንታችን ከዲያብሎስ ጋር እሳቱ በማይጠፋ እና ትሉ በማያንቀላፋ በገሃነመ እሳት ሥቃይ ይሆናል ።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን !
💭 ክርስቶስ በደመራ ታየ – እኛን “አትፍሩ” – ጠላቶቻችንን “ተጠንቀቁ”! ይላል
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on September 28, 2016
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: Abiy Ahmed, Addis Ababa, Aksum, Anti-Ethiopia, Axum, ምጽአት, ረሃብ, ቅዱስ ኡራኤል, ቅድስት ማርያም, ትግራይ, አረመኔነት, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢየሱስ ክርስቶስ, ኤዶማውያን, እሳት, እስማኤላውያን, ኦሮሞ, ወንጀል, ዑራኤል, የጦር ወንጀል, የጽዮን ቀለማት, ደመራ, ደብረ ዘይት, ግራኝ አህመድ, ግድያ, ጠላት, ጥላቻ, ጦርነት, ጭካኔ, ጭፍጨፋ, ጽዮናውያን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, Colors of Zion, Famine, Fire, Genocide, Jesus, Massacre, Rape, St. Mary, St. Uriel, The Cross, Tigray, War Crimes | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2022
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 😇 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
❖❖❖ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን የጽዮንን ልጆችን አደራ፤ በእሳት ሰረገላ በነበልባል ታጅበህ ለተልዕኮ የምትፋጠን የአምላካችን አገልጋይ ወራዙተ ኢትዮጵያን በብርሐናዊ ክንፍህ ሸፍነህ ከመርዘኞች የሞት ቀስት ከቀሳፊ ነገር ሁሉ ሰውረን!❖❖❖
😇 የሔኖክ ሰማይ ሰሌዳ በቅዱስ ኡራኤል ዕለት 😇
✞ሐሙስ ሐምሌ ፳፪/፪ሺ፲፫ ዓ.ም✞
😇 ኖኅ እንደ ሔኖክ ቅድመ አያቱ መላ ዘመኑን ከፈጣሪው ጋር በመጓዝ ስለ ፅድቁ ቅዱስ መፅሐፍ የመሰከረለት ሰው ነው። [ዘፍ ፮፥፱]
ቅዱስ ኡራኤል ምስጢረ ሰማይንና እውቀትንም ሁሉ ለሔኖክ እንደገለጸለት ሁሉ ለሔኖክ የልጅ ልጅ ለኖኅም በዚያ መከራ ቀን መርከብ ለመስራት በሚያዘጋጅበት ጊዜ ምክር በመለገስ ቁሳቁስ በማቅረብ ከመርከብም ከወጣ በኃላ በሽምግልናው ዘመን ቅዱስ ኡራኤል አልተለየውም ነበር።
- 👉 ኡራኤል የሚለው ስም `ኡር‘ እና ‘ኤል‘ ከሚሉ ሁለት ቃላት የተመሠረተ ስም ነው።
- 👉 ኡር ማለት በእብራይስጥ ብርሃን ማለት ሲሆን ኤል–ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው ።
- 👉 አንድ ላይ ሲነበብ –ኡራኤል ማለት የብርሃን አምላክ ወይም የብርሃን ጌታ ማለት ነው ።
ቅዱስ ኡራኤል ከ፯/7ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ሲሆን ፣ ከፍጥረተ ዓለም ጀምሮ በመብረቅና በነጎድጓድ ላይ የተሾመ መልዓክ ነዉ። በመሆኑም መባርቅት ለጥጋብና ለበረከት እንዲበርቁ ነጎድጓድም ለሰላም እንዲሆን ያሰማራል። [መጽሐፈ ሔኖክ ፮፥፪] ፣ ምስጢረ ሰማይና እውቀትንም ሁሉ ለሄኖክ የገለጸለት የፀሀይን የጨረቃን የከዋክብትንና የሰማይ ሰራዊትን ብርሃንን የሚመራ እርሱ መሆኑን ለሄኖክ ነግሮታል። ፟[መጽሐፈ ሔኖክ ፳፰፥፲፫]
❖ ❖ ❖ ድርሳነ ኡራኤል ❖ ❖ ❖
ምድረ ኢትዮጵያ ፦ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዮሴፍና ሰሎሜ በደመና ተጭነው ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ናግራን ከተባለ ሀገር ደረሱ። በናግራን ሳሉ ጌታ እንዲህ አለ። ከቀኝ ጎኔ የሚፈሰው ደሜ በብርሃናት አለቃ በዑራኤል እጅ ተቀድቶ በቅድሚያ በዚች ሀገር ይፈሳል ወይም ይረጫል። እናቱንም እንዲህ አላት አንቺ በድንግልና ጸንሰሽ በድንግልና እንደወለድሽኝ አምነው የሚያከብሩሽ በእኔም የሚያምኑ ብዙ የተቀደሱ ሰዎች በዚህ ሀገር ይወለዳሉ። ከናግራን ተነስተው ለትግራይ ትይዩ ከሚሆን ሐማሴን ከሚባለው ሀገር ሲደርሱ በምሥራቅ በኩል ከፍተኛ ተራራ ተመለከቱና ወደ ተራራው ሄዱ። ጌታም በተራራው ላይ ሳሉ እናቱን እንዲህ አላት ይቺ ተራራ ምስጋናሽ የሚነገርባት ቦታ ትሆናለች። የተራራዋም ስም ደብረ ሃሌ ሉያ ወይም ደብረ ዳሞ ይባላል። ትርጓሜውም የአምላክ ልጅ የመስቀሉ ቦታና የስሙ መገኛ ወይም አደባባይ ማለት ነው።ከዚያም በኋላ ታቦተ ጽዮን ወደምትኖርበት ወደ አክሱም ደረሱ። ታቦተ ጽዮን ባለችበት ቦታ ሳሉ ባዚን የተባለው የኢትዮጵያ ንጉሥ ታቦተ ጽዮንን ለመሳለም መጣ። የካህናቱ አለቃ አኪን ለንጉሡ የኢሳይያስን መጽሐፍ አነበበለት። የተነበበውም የመጽሐፍ ክፍል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ወንድ ልጅ ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች የሚል ነበር። ስደተኞቹ ግን ለንጉሡም ሆነ ለካህናቱ ሳይገለጡ የመጽሐፉን ቃል ከሰሙ በኋላ በደመና ተጭነው ወደ ደብረ ዐባይ ሄዱ ። ጌታም እናቱን እንዲህ አላት ይህች ሀገር እንደአክሱም ለስምሽ መጠሪያ ርስት ትሁን በኋላ ዘመን በቀናች ሃይማኖት ጸንተው ሕጌን የሚያስተምሩ አንቺን የሚወዱ ሰዎች ይኖሩባታል። ከዚያም በኋላ ከደብረ ዐባይ ተነስተው ዋሊ ወደ ሚባለው ገዳም /ወደ ዋልድባ / ሄዱ። በዋልድባ በረሃም ሳሉ በራባቸው ጊዜ ጌታ በዮሴፍ ብትር የአንዱን ዕንጨት ስር ቆፈረ። ሦስት መቶ አስራ ስምንት ስሮችን አወጣና ለእናቱ ብይ ብሎ ሰጣት። እናቱም ይህን የሚመር ዕንጨት አልበላም አለችው። ጌታም በኋላ ዘመን ስምሺን የሚጠሩ አንቺን የሚያከብሩ ብዙ መናንያን ይህን እየበሉ በዚህ ቦታ ይኖራሉ። ዕንጨቱም የሚጣፍጥ ይሆንላቸዋል አላት። ከዚህ በኋላ በደመና ተጭነው ከዋልድባ ወደ ጣና የባሕር ወደብ ሄዱ። በጣና ደሴትም ደጋግ ሰዎች ተቀብለዋቸው ሦስት ወር ከአስር ቀን ተቀመጡ። የኢትዮጵያ ሰዎች በደስታ ተቀብለዋቸዋል እንደ ግብፃውያን አላሰቃዩአቸውም ። በጥር አስራ ስምንት /18/ ቀን ዑራኤል መጥቶ የሄሮድስን መሞት ነገራቸው ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ዘንድ በደመና ከተጫኑ በኋላ ጌታ እናቱን እንዲህ አላት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎች ሁሉ ለስምሽ መታሰቢያ ይሆኑሽ ዘንድ አሥራት አድርጌ ሰጥቼሻለሁ ። ብሎ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙትን ተራራዎችን ሜዳዎችን ኮረብታዎችን አሳያት። እመቤታችን ሁሉንም ቦታዎች እየተዘዋወረች እንድታይ ልጅዋን ጠየቀችው። ልጅዋም የሚመለሱበት ጊዜ እንደደረሰ ነገራት። በብሩህ ደመና ላይ ተቀምጠው ክፍላተ አህጉር እየተዘዋወሩ ተራራዎችን ወንዞቸን አስጐበኛት የኢትዮጵያን ምድር ከጐበኙ በኋላ በደመና ተጭነው ጥር 29 ቀን ምድረ ግብፅ ደረሱ። ወደ ኢትዮጵያ የገቡት በቅዱስ ዑራኤል መሪነት ነው። ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ የመግባት ታሪክ በድርሳነ ዑራኤል ላይ በስፋት ተጽፏል።
❖ የሊቀ መለአክት ቅዱስ ዑራኤል ፀሎት በያለንበት ይድረስ! በረከት ረድኤቱ ይደርብን!ምልጃ ጥበቃዉ አይለየን!❖
_______
_______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, Saints/ቅዱሳን, War & Crisis | Tagged: Abiy Ahmed, Addis Ababa, Aksum, Angels, Anti-Ethiopia, Axum, መላዕክት, መጽሐፈ ሔኖክ, ረሃብ, ቅዱስ ኡራኤል, በቀል, ትግራይ, አረመኔነት, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢሳያስ አፈወርቂ, ኤዶማውያን, እስማኤላውያን, ኦሮሚያ, ኦሮሞ, ወንጀል, የጦር ወንጀል, ግራኝ አህመድ, ግድያ, ጠላት, ጥላቻ, ጦርነት, ጭካኔ, ጭፍጨፋ, ጽዮናውያን, ፀረ-ኢትዮጵያ ሤራ, book of Enoch, Famine, Genocide, Massacre, Rape, St. Uriel, Tigray, vengeance, War Crimes | 1 Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 22, 2022
👉 ገብርኤል 👉 ማርያም ❖ ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም
😈 ዲያብሎስ ዝናሩን ፈታ ጥይቱንም ጨረሰ፤ ሆኖም አሁን ክርስቲያኖችን በረሃብ ለመጨረስ ገዳማትን እና ዓብያተ ክርስቲያናትን ለማውደም ተነስቷል
✞ በፍጹም መጠበቅን ጠብቆ ለዚህ ያደረሰን አምላካችን ክብርና ምስጋን አምልኮትና ውዳሴ ይድረሰውና ይህን ታላቅ መልአክ በችሎታችን መጠን እንድናመሰግን እግዚአብሔር ይርዳን፤ አምላክ ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን፤ ምስጢሩን ይግለጥልን አሜን።
“ኡራኤል የተባለ መልአክ ሊረዳኝ መጣ።” [መ/ዕዝ. ሱቱ. ፪፡፩]
በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ።
በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ። ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውለሁ። ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ። [መዝ.፺/፺፩/፥፲፩፡፲፮]
የተከዱትንና የተገፉትን የአክሱም ጽዮን ልጆችን፤ በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ሁሉ ያለ ረሃብ፣ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞች፣ ግፈኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም አህዛብ እና መናፍቃን ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።
_______
______
Like this:
Like Loading...
Posted in Ethiopia, Faith, News/ዜና, War & Crisis | Tagged: Abiy Ahmed, Addis Ababa, Aksum, Amhara, Anti-Ethiopia, Axum, ሉሲፈራውያን, መጽሐፍ ቅዱስ, ሤራ, ረሃብ, ቃጠሎ, ቅዱስ ኡራኤል, ባፎሜት, ትንቢት, ትግራይ, አመፅ, አረመኔነት, አብይ አህመድ, አዲስ አበባ, ኢሳያስ አፈወርቂ, ኢትዮጵያ, ኦሮሞ, ወንጀል, የክርስቶስ ተቃዋሚ, የዘመን ፍጻሜ, የጦር ወንጀል, ድንበር, ግራኝ አህመድ, ግድያ, ግፍ, ጠላት, ጥላቻ, ጦርነት, ጭካኔ, ጭፍጨፋ, ጽዮናውያን, ፀረ-ኢትዮጵያ, ፍርድ, ፍትሕ, Blockade, Ethnic Cleansing, Famine, Fire, Genocide, HumanRights, Oromo, Rape, St. Uriel, Starvation, Tigray, War Crimes | Leave a Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 2, 2019
ኡራኤል – ጊዮርጊስ – ተክለ ሐይማኖት – መርቆርዮስ – ዮሴፍ
ቅዱስ ኡራኤል ኢትዮጵያን አደራ፤ በእሳት ሰረገላ በነበልባል ታጅበህ ለተልዕኮ የምትፋጠን የአምላካችን አገልጋይ ወራዙተ ኢትዮጵያን በብርሐናዊ ክንፍህ ሸፍነህ ከመርዘኞች የሞት ቀስት ከቀሳፊ ነገር ሁሉ ሰውረን!
__________________
Like this:
Like Loading...
Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: American Sky, ሊቀ መለአክት, ሰማይ, ቅዝቃዜ, ቅዱስ ኡራኤል, አሜሪካ, አረንጓዴ ቢጫ ቀይ, የኢትዮጵያ ቀለማት, የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት, Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith, Ethiopian Tricolor, Halo, Polar Vortex, St. Uriel | Leave a Comment »