Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘St.Stephen’s Church’

Ethiopian Exorcist — መምሕር ግርማ በቅዱስ እስጢፋኖስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 6, 2012

መንፈሣዊ ነፃነት ያለው ሰው ሥጋዊ ነፃነትም አለው!

_

 

ቪዲዮው ላይ የምናየው መምሕር ግርማ በቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ተገኝተው ብዛት ካላቸው ምእመናን አጋንንት ሲያወጡ ነው።

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከገጠሙኝ አስደናቂ የሆኑ ሁኔታዎች ይህ አንዱ ነበር።

መምሕር ግርማ በተመሳሳይ ድርጊት ተሠማርተው የቀረጹት ቪዲዮ ከሁለት ዓመታት በፊት እዚህ ብሎግ ላይ አቅርቤ ነበር። ነገር ግን እስከ አሁን ድረስ እሳቸው በአዲስ አበባ እንደሚገኙ አላውቅኩም ነበር።

ዘንድሮ በአዲስ አበባ ከገጠሙኝ አስገራሚና ድንቅ ከሆኑት ሦስት ሁኔታዎች መካከል ይህ አንዱ ነበር። ሦስቱም አጋጣሚዎችበጣም ተመሳሳይ በሆነ መንገድ የተከሰቱ መሆናቸው እስካሁን ድረስ ያስገርመኛል።

ዕለቱ ረቡዕ ነው፤ ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ ጎተራ አካባቢ አውቶብስ ቁጥር 56 (ባልሳሳት) ውስጥ ገብቼ ወደ ሽሮ ሜዳ ለመጓዝ ወሰንኩ። (የአዲስ አበባ አውቶብስ ካልሞላ በቀር በሁሉም መስክ በከተማዋ የተሻለ መጓጓዣ ሆኖ ነው ያገኘሁት)። ትንሽ መጓዝ እንደጀመርን የአውቶብሱ ነጂ እብድነት የተሞላበት ዓይነት አነዳድ ነበረው፡ አውቶብሷን ልክ እንደ ስፖርት መኪና ወዲያና ወዲህ እያዋዥቀ ሌሎች መኪናዎችን በግራና በቀኝ በችኮላ እይቀደመና ጥንቅቃቄ በጎደለበት ሁኔታ ፍሬን እየያዘ በአውቶብስ ውስጥ የነበረነውን 20 የምንሆን ተጓዦች በመረበሽ በደብረዘይት መንገድ መሃል መንገድ ላይ ይነዳ ነበር። ሁኔታው ስላላስቻለኝ ፡ ጠጋ ብዬ ቁጣየን በጩኽት ገለጥኩለት፤ ምናለ ተጠንቅቀህ ብትነዳ፤ ይህን ሁሉ ሰው ጭነህ፤ ከጓደኞችህ ጋር በጎን እያወራህ መንዳት ተገቢ አይደለም፤ ምናለ ይህን ምስኪን መንገደኛ ባክብሮትና ትህትና ብታገለግሉ…” ሌሎች መንገደኞችም የኔን ቁጣ በመደገፍ ይወቅሱት ጀመርሹፌሩ ግን ይባስ ብሎ አውቶብሷን በይበልጥ ያርገበግባት ነበር። እኔም አላስቻለኝም፤ ልክ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት አውቶብሷን ሲያቆማት ወርጄ የአውቶብሷን ታርጋ መዘገብኩ። በእውነት፡ አንበሳ አውቶብስ ድርጅት በቅርብ የማውቃቸው ሰዎች ስለነበሩ የዚህን ሹፌር ጉዳይ እንዲከታተሉ አደርጋለሁ ብዬ ዛትኩ።

እስጢፋኖስ ጋር ከወረድኩ በኋላ ወደ ቤተክርስቲያኗ አመራሁ። እዚያም በጣም ብዙ ሰዎች ተሰባስበው አንዳንዶቹም ሲጮሁና ሲወራጩ አየሁ። ምን ይሆን ብዬ አንዷን እናት ስጠይቃቸው፡ ሰዎቹ መምህር ግርማን ብለው መምጣታቸውን ነገሩኝ። ሙሉ በሙሉ በውሃ ርሰው የነበሩት ሴትዮዋም፡ ና! ልጄ ይህን የመሰለ መቁጠሪያ እዚያ ማግኘት አለብህ ብለው መቁጠሪያው ወደሚገኝበት ቦታ ወሰዱኝ። አባ ግርማ ከሚገኙበትና ብዙ ሰዎች ከተሰበሰቡበት የቤተክርስቲያኗ ቅጥር ግቢ በጥግ በኩል አንድ ተለቅ ያለ መኪና ውስጥ የነበሩ ሴትዮ መቁጠሪያውን በ20 ብር ይሸጡ ነበር። ሴትዮም፡ መቁጠሪያ ነው የምትፈልገው?” አሉና አውጥተው ሰጡኝ። እኔም፡ ይቅርታ ያድርጉልኝና፡ አባ ግርማን ፎቶ ወይም ቪዲዮ ማንሳት ይቻል ይሆን?” ብዬ ሴትዮዋን ስጠይቃቸው፡ ሴትዮዋም በቁጣ፡ አይቻልም! ፈጽሞ አይቻልምብለው መለሱልኝ። ለመሆኑ ጉዳዮ እርስዎን ይመለከታል ወይስ ሌላ ፈቃድ ሊሰጠኝ የሚችል ሰው አለ?” አልኳቸው። እሳቸውም ወደ እኔ ቀና ብለው ሳይመለከቱ ቁጣቸውን ቀጠሉ። እኔም የሴትዮዋ ትህትና አልባነት ገርሞኝ ትንሽ ራቅ ብለው ወደሚገኙ ለአንድ ቄስ አባት ሁኔታውን አወሳኋቸው። ልጄ ከውጭ ነው የመጣኽው መሰለኝ፤ ይህን የመሰለ ቦታ ላይ ብዙ ዓይነት መናፍሳት ስለሚገኙ አንዳንዱ ሰው ሊፈተን ሊረበሽ ይችላልና አይድነቅህ ፡ ዝም ብሎ ማለፉ ነው የሚመረጠው ፡ ፎቶ ለማንሳት ከፈልግህ መምህር ግርማን ሄደህ ጠይቃቸውአሉኝ፡ በትህትና። እኔም ትክክለኛነታቸው ከምስጋና ጋር ካሳወቅኳቸው በኋላ፡ ወደ መምህር ግርማ ጠጋ ብዬ ከበስተኋላቸው ለሚገኙትን ረዳቶቻቸው እሳቸውን ማነጋገር እንደምፈልግ ሹክ አልኳቸው። ጋኔን በማስወጣት ላይ የሚገኙት መምህር ግርማም ዘወር አሉና፡ አንተ ማን ነህ? ከየት ነህ? ምን ፈልገህ ነው?” ብለው በያዙት መስቀል ግንባሬን ገፋ አደርጉት። ቀጥለውም እጃቸውን ወደ አንገቴ ሰደድ አድርገው እዚያ የሚገኘውን መስቀሌን መዳሰስ ጀመሩ፤ ምንድነው መስቀሉ በጨሌ የታሠረው?|” ፡ እሺ፡ ግድ የለም ፊልም ማንሳት ትችላለህበማለት ፈቃዳቸውን ገለጹልኝ። እኔም ከምስጋና ጋር አማተራዊ የፊልም አንሺ ሥራ ውስጥ በመግባት እጅግ በጣም አስገራሚ የሆኑትን ሁኔታዎች መታዘብ ጀመርኩ። ስማ፡ እዚያ ጋር፡ እዚያ ጋር፡ ፊልም ማንሳት አይቻልም!” የሚሉ የተለያዩ ድምጾች ከያቅጣጫው ይመጡብኝ ነበር። ነገር ግን እንደተፈቀደልኝ ሲያውቁ ፀጥ አሉ።

በርግጥ መምህር ግርማ ልዩ ጸጋ የተሰጣቸው፡ እድነስማቸውም ግርማ ሞገስ ያላቸው አባት መሆናቸውን ጠጋ ብሎ በማየት መገንዘብ ይችላል። ጸበሉ በተፈለገው ዓይነት መንገድ ይፍለቅ፡ በሰው ላይ የሚፈጥረው መንፈሳዊ ክስተት ኃያልና እውነትነት የተሞላበት ነው።

ከፍተኛ መንፈሳዊ ጦርነቶች በሚካሄዱባት አገራችን ዲያብሎስ ህዝባችንን እያዘናጋ ወደርሱ ወጥመድ ለማግባት ሌት ተቀን ደፋ ቀና እንደሚል፡ ቤተክርስቲያኖቻችን፡ ጸበላችንና መስቀላችን ከርሱ ጦር መከላከያ ይሆኑን ዘንድ የተሰጡን ውድ በረከቶች መሆናቸውን ይህን በመሳሰሉት አጋጣሚዎች በዓይኔ፡ በአካል ለመታዘብ እድሉ ስለነበረኝ፡ ያው ምስክር ሆኛለሁ።

ከቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያንም ልዩና ቅዱስ ከሆነው መንፍስ ጋር አብሬ ከወጣሁ በኋላ፡ የ 56 ቁጥር አውቶብሱ ሹፌር ሁኔታ ትዝ አለኝ፤ ሹፌሩን መገሠጼ ትክክል ቢሆንም ለቀጣሪው ክስ ላቀርብበት የነበረው ስሜታዊ ኃሳብ ትክክል እንዳልሆነ ገባኝ። እንዲያውም ምስኪኑ ሹፌር እኔን ያለ ፕላኔ በተዘዋዋሪ መንገድ ወደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን ያደርሰኝ ዘንድ የሆነ ኃይል ልኮት መሆኑን በመገንዘቤ፡ በወቅቱ ደግሜ አግኝቼው ቢሆን ኖሮ ሞቅ ያለ የወንድማዊ ሰላምታ ልሰጠው በጣም ተመኝቼ ነበር።

አበው ይናገሩ

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ

የምንኩስና ግብር ምን ነበር ሚስጢሩ

የክርስቲያን ህይወት ምን ነበር ተግባሩ

መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ

እኔስ ሰው አማረኝ የሃይማኖት ጀግና

ወልድ ዋህድ ብሎ በእምነቱ የፀና፡፡

ጀግና ሰው አማረኝ ጠላት አሳፋሪ

ንጽህት ድንግል ብሎ እምነቱን መስካሪ

ነቢያት በመጋዝ የተሰነጠቁት

ሀዋርያት ቁል ቁል የተዘቀዘቁት

ሰማእታት በእሳት የተለበለቡት

ቅዱሳን ገዳም ደርቀው የተገኙት

ሚስጥሩ ምን ነበር አበው ይናገሩት፡፡

ይናገር ዝቋላ ጊሸን ላሊበላ

የቅዱሳንን አጽም ለምን እንዳልበላ፡፡

ዋልድባ ይናገር ዜጋመልም ሳይቀር

እንባቸው መፍሰሱ ለምን እንደነበር፡፡

ነበር ወይ ፈልገው ሹመት ሽልማት

ወይስ ሃብት ንብረት የተሟላ ቤት

ወይስ አምሯቸው ነው ፈልገው መሞት

እናንተ ገዳማት ምስጢሩን አውሩት፡፡

ጎበዝ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና

ምግባር ሃይሞኖቱን በእጅጉ ያቀና፡፡

እንጦንስ የወለደው በምግባር በእምነት

ተምሮ ያደገ ከተክለሃይማኖት፡፡

የጊዮርጊስ ወዳጂ የት ነው የሚገኘው

በመሃል ከተማ በአራዳ ውስጥ ነው

ወይስ በዝቋላ በደብረ ሊባኖስ በደብረ ዳሞ ነው፡፡

ወገን ሰው ናፈቀኝ አይኔን ሰው አማረው

የሃይማኖት ጀግና የት ነው የማገኘው?

ልጋባ ወይ ዋልድባ ጫካ ካለበት

ማህበረ ስላሴ ከቅዱሳ ቤት

አክሱም ጊሸን ማርያም ከቃልኪዳን ቦታ

ይገኛል ወይ ጀግና ጠላት የሚረታ፡፡

ፈርሃ እግዚአብሔር በልቡ ያደረ

ቤተክርስቲያንን ያልተዳፈረ

የት ነው የሚገኘው ለሃይማኖቱ ሟች

ለተዋህዶ እምነት ጠበቃ ተሟጋች

የወገን መመኪያ የከሃዲ መቅሰፍት

ማነው እሱ ጀግና ተኝቶ እንደሆነ ይነሳ ቀስቅሱት

እስኪ ቀስቅሷቸው አበው ይናገሩ

የምንኩስና ግብ ምን ነበር ምስጢሩ

የክርስቲያን ህይወት ምን ነበር ተግባሩ

መቃብሩን ክፈቱት አበው ይመስክሩ፡፡

ወገን ሰው ናፈቀኝ አይኔን ጀግና አማረው

በእምነት የፀና የት ነው የማገኘው፡፡

ወልድ ዋህድ ብሎ በእምነቱ የፀና

ብቅ ይበል እንየው እሱ ማን ነው ጀግና

በጎችን ከተኩላ ነቅቶ የሚጠብቅ

መከራ ቢከበው ከቶ የማይሰቀቅ

የሃይማኖት ጀግና ቆራጥ ሰው ገበሬ

እንደዚያ እንደጥንቱ ይገኛል ወይ ዛሬ፡፡

የወገን የዘመድ ጥቅም ያላወረው

የመናፍቆች እጅ ኪሱን ያልዳበሰው

የዓለም ደስታዋ ልቡን ያልማረከው

የክርስቶስ ወዳጅ እሱ ጀግና ማነው?

ምስጢርን ከምስጢር አንድ አድርጎ ተምሮ

ወልድ ዋህድ ብሎ ሃይማኖት መስክሮ

እንጦንስን መቃርስን በልቡ ያኖረ

ከጳውሎስ ከቄርሎስ ጥበብ የተማረ፡፡

ድንግል እመቤቴ ብሎ የሚመሰክር

መሆኗን የሚያምን ማህደረ እግዚአብሔር

ቋቅ እንትፍ ብሎ የጠላ ክህደትን

ትንታግ ምልስ ጭንግፍግፍን

ልሣነ ጤዛ መናፍቅን

ወልደ አርዮስነ ዲቃላውን

በሰይፈ ሥላሴ የሚቀላ

ጀግና ማን ነው ብቅ ይበላ፡፡

ነበር ወይ ያን ጊዜ ለሹመት መጓጓት

እስኪ ጎርጎርዮስ ይምጣና ጠይቁት፡፡

ፍቅርንም ይጠየቅ አባ ሕርያቆስ

ምስጢርን ጠባቂ ወይም አባ መቃርስ

የክርስቶስ ባሪያ የአጋንንት መቅሰፍት

ወንጌል አስተማሪ የሃይማኖት አባት

ይህንን ጉድ እንዲያይ ይምጣ ተክለሃይማኖት

የፀሎት ገበሬ ገብረመንፈስ ቅዱስንም ይነሳ ቀስቅሱት

ይነሳ ጊዮርጊስ ይመስክር ምስጢር

የሃይማኖት ፍቅር ምን እንደነበር፡፡

ከእናቶቻችንም አሉ ለፍጥረት ያዘኑ

ዲያቢሎስ እንዲማር ጌታን የለመኑ

ስንቱን ልዘርዝረው የአባቶችን ሙያ

እመር ብለው የወጡት ከስጋ ገበያ

ፆም ፀሎት ነበር የሃይማኖት ጋሻ

እንደ መስኖ ውሃ ከነዱት መነዳት

አላማው ምንድን ነው የዘመኑ ወጣት፡፡

እኔስ ሰው አማረኝ በእምነቱ የፀና፡፡

ዐይኔን ሰው አማረው ጀግና ሰው ገበሬ

ሃይማኖት መስካሪ እንደ ጥንቱ ዛሬ፡፡

ምንጭ፡ ደቂቀ ናቡቴ

_

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: