👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 😇 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም
💭 የመጭውን የጌታችንን የልደት በዓል ተከትሎ በሚቀጥሉት ቀናት በመላው ዓለም ትልቅ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡንን ክስተቶች እናያለን
❖ ኢትዮጵያ = የአዲስ ኪዳን ርስት ምድር = እስራኤል ዘ–ነፍስ❖
💭 “ቅዱስ ጳውሎስ” ከሚለው ፊልም የተወሰደው ምስል የሚያሳየን ትክክለኛው ክርስቲያናዊ አለባበስ ኢትዮጵያኛው አለባበስ መሆኑን ነው።
[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ፲፩፥፳፫]
“ከእኔ ጋር ያልሆነ ይቃወመኛል ከእኔ ጋርም የማያከማች ይበትናል።”
ሰባዓሰገል መጥተው ለጌታ ሲሰግዱ ዮሴፍ አየ አምላክ ነህ ሲሉ እጣን ንጉሥ ነህ ሲሉ ወርቅ ፍቅር ነህ ሲሉ ከርቤ ለጌታ ሲገብሩ ዮሴፍ አየ ለካ ይሔ የተወለደው ሕፃን ተራ አይደለም ነገሥታት የሰገዱለት የነገሥታት ንጉሥ ቢሆን ነው ብሎ ድንግል ማርያም የንጉሥ እናት ኢየሱስን የነገሥታት ንጉሥ አምላክ መሆኑን የበኩር ልጅዋን ስትወልደው አወቀ።
ዮሴፍ ታላቅ ነገር ተመለከተ ደማቅ ኮከብ ከሰማይ ዝቅ ከምድር ከፍ ብሎ በቤተልሔም ዋሻ ፊት ለፊት ሲቆም አየ አሀ ልክ ኢያሱ አሞራውያንን በገባዖን ሲዋጋ በጸሎቱ ፀሐይን እንዳቆማት ኢየሱስ ገና በሕፃንነቱ በቤተልሔም ኮኮብን አቁሟል ስለዚህም ይህ ኮከብ የተገዛለት የጌቶች ጌታ ቢሆን ነው ብሎ ኢየሱስ ጌታ ፈጣሪ ድንግል ማርያም እመ ፈጣሪ የጌታ እናት መሆንዋን አወቀ።
________________