Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

Posts Tagged ‘St. George’

የኢትዮጵያ አለኝታ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ፤ ሃገራችን ቅጥሯ ተደፈረ፣ አላዊያን እጅግ በረቱብን፣ ደማችን በከንቱ ፈሰሰ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2019

የትናንቶቹ አባቶቻችን አንተን መከታ አድርገው፣ ታቦትክን ይዘው ድል አደረጉ፤ ጠላትም ይፈር የሞቱንም እዳ ከእጅህ ይቀበሉ፤ ና ቶሎ ና፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ የኢትዮጵያ ገበዝ።

እንኳን አደረሰን! የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከቱ ይደርብን!

___________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ኑ! ወደ ቅ/ ጊዮርጊስ እንሒድና እንዘምር፤ “…ማሕተቤን አልበጥስም፡ ምያለሁ በድንግል ማርያም…“

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2018

ከኢትዮጵያ ጠባቂ እረኞች አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው፤ እንግሊዞችም፡ ንስሐ ሳይገቡ፡ ሊሻሙን ይሻሉ፤ ምነው ቢነቁና ያቺን ብሩኽ የማርያም መቀነት ቢመረምሩ!

እንኳን አደረሰን!!!

እሙሀይ ብርሐን ዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም

የእናታችን በረከት በጣም አስገራሚ እና አስደናቂ ነው፦

በዲማ ቅዱስ ጊዮርጊስ ገዳም ፡ በቤተክርስቲያን ቅፅር ግቢ ውስጥ የሚኖሩት፡ እሙሀይ ብርሐን እናታችን የተሰጣቸው ፀጋ በጣም ለሰሚው ጆሮ በጣም ሊከብድ ይቻላል እናታችን በቤተክርስቲያን ቅፅር ጊቢ መኖር ከጀመሩ ከ (30) መናት በላይ ሆኗቸዋል።

በእነዚህ ዘመናት ባዶ ሜዳ ላይ ተቀምጠው፡ ዝናብ ሲዘንብ እሳቸው የተቀመጡበት ቦታ ደረቅ ሆኖ እሳቸውንም ሆነ የተቀመጡባትን አካባቢ ዝናብ አያገኘውም።

እሙሀይ በዚህ ሲኖሩ፡ የሚመገቡት ቱልት የተባለውን ቅጠል ሲሆን፡ እናታችን ብዙ ተማዕራትን በተለያየ ግዜ ሲያደርጉ በአካባበው ምዕመናን ታይተዋል።

ከዚህ አልፎ በዋልድባ ገዳም የሚኖሩ አባቶች ከሰማይ በማርያም መቀነት አምሳል ከሰማይ ብርሐን ሲወርድላቸው አይተው መጥተው እሙሀይን በረከት በረከትዎ ይድረስብን እናታችን ብለው እጅ ነስተዋል።

እሰኪ ሁላችንም የእሙሀይ ብርሐን በረከት በየአለንበት ይድረሰን እሙሀይንም በቦታው ተገኝተን የበረከቷ ተካፍይ ያድርገን

______

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ትሑት የክርስቶስ አገልጋይ በባዶ እግር

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 2, 2014

ዝንጀሮ፣ ጦጣና ቀበሮ

ዝንጀሮ፣ ጦጣና ቀበሮ በአንድ አለቃ ቤት ይኖሩ ነበር፡፡ ሁልጊዜ አንድ ነገር እንዲያመጡ ሲላኩ ዝንጀሮውና ቀበሮው ከባዱን ሸክም ሲሸከሙ ጦጣው ግን ይህን አያደርግም ነበር፡፡

ከዕለታት አንድ ቀን ታዲያ ሶስቱም ለአለቃቸው አንድ ነገር ይዘው እንዲመጡ ሲላኩ እንደልማዳቸው ዝንጀሮውና ቀበሮው ከባድ ሸክም ሲሸከሙ ጦጣው ቀላል ሸክም ያዘ፡፡ ከጫካውም እንደደረሱ ዝንጀሮውና ቀበሮው ተንኮለኛውን ጦጣ እንዴት እንደሚገድሉት ተማከሩ፡፡ ወደ ቤትም በተመለሱ ጊዜ ቀበሮውና ዝንጀሮው ጦጣውን ወደኋላ በመተው ቀድመው ገብተው አለቃ አንበሣን እንዲህ አሉት “ጫማ ሳታደርግ ለምንድነው ሁልጊዜ በባዶ እግርህ የምትሄደው? በመንደሩ ያሉ ጫማዎች ሁሉ የሚሰሩት በጦጣው ስለሆነ ከሄደበት ሲመለስ ጠርተህ ጫማዎች እንዲሠራልህ ንገረው፡፡”

በዚህም መሠረት አለቃ አንበሣ ጦጣውን ጠርቶ “ጫማ አጥቼ እንዲህ ስሰቃይ እንዴት ዝም ትላለህ? በል አሁን ጫማ ሥፋልኝ::” አለው፡፡

ጦጣውም ጫማ መስፋት ስለማይችል በነገሩ ግራ ቢጋባም ይህንን መናገርና አለቃውን ማበሳጨት አልፈለገም፡፡

ከዚያም ጦጣው “ጫማ መስፋት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን ጫማ የሚሰፋው ከዝንጀሮ ቆዳና ከቀበሮ አከርካሪ ነው፡፡” አለው፡፡

ስለዚህ ዝንጀሮና ቀበሮው ተገደሉ፡፡

ቆዳቸውም ከተገፈፈ በኋላ ለጦጣው ተሰጥቶት ውሃ ውስጥ ተነክሮ እንዲርስ ተደረገ፡፡ ጦጣውም ቆዳቸውን ወደ ጥልቁ ውሃ ከወረወረው በኋላ በውሃው ውስጥ የራሱን ምስል ስላየ ሶስት ቀን እዚያው ቆየ፡፡

ከዚያም አለቃው ጠርቶት “አሁን ቆዳዎቹ ስለለሰለሱ ጫማውን ለመስፋት ዝግጁ ናቸው፡፡” አለው፡፡

ጦጣውም ወደ ወንዙ ተመልሶ ሲሄድ የራሱን ምስል ውሃ ውስጥ እንደገና ሲያየው አንድ ሃሳብ መጣለት፡፡

ወደ አለቃው አንበሳም ሮጦ በመመለስ “ውሃው ውስጥ እንዳንተ ትልቅ አንበሣ አለ፤ ሊገድለኝም ይፈልጋል፡፡” አለው፡፡

አለቃው አንበሣም ቀበሮውን አስከትሎ ወደ ወንዙ ወረደ፡፡ ወንዙ አጠገብ እንደደረሱም ጦጣው ወደ ኋላ ቀረት ሲል አንበሣው የራሱን ምስል ውሃው ውስጥ ተመለከተ፡፡

አንበሣውም ሲያጓራ ምስሉም መልሶ አጓራበት፡፡ በዚህ ጊዜ አንበሣው ውሃው ውስጥ ያለውን አንበሣ ሊገጥም ዘሎ ገብቶ ሞተ፡፡

ቸሩ እግዚአብሔር ገርአንበሳ ወገናችንን ወደ እናት አገራችን በመጉረፍ ላይ ካሉት ፈረንጅ፣ አረብ እና ቱርክ ጦክላዎች ይጠብቅልን።

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2014

StGeorgis19በጥር 20 ቀን በ277 .ም ተወለደ። ሀገሩ ፍልስጤም ሲሆን ልዩ ስሟ ልዳ ይባላል። ጊዮርጊስ ማለት ኮከብ፣ ብሩህ፣ ሐረገወይን፣ ፀሐይ ማለት ነው። አባቱ ዘሮንቶስ (አንስጣስዮስ) ይባላል ከልዳ መኳንንት ተሹሞ ይኖር ነበር፤ እናቱ ቴዎብስታ (አቅሌስያ) ትባላለች። ማርታና እስያ የሚባሉ እህቶች ነበሩት። 10 ዓመት ሲሞላው አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ከቤቱ ወስዶ አሳደገው። በጦር ኃይልም አሠለጠነው። 20 ዓመት ሲሞላው የ15 ዓመት ልጅ ሊያጋቡት ሲሉ እግዚአብሔር የመስፍኑን ነፍስ ወስደ፤ ቅዱስ ዮርጊስም ወደ ቤሩት ሄደ።

በቤሩት ደራጎን ን ያመልኩና ሴት ልጃቸውን ይገብሩለት ነበርና በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ህዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል።

ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ “እኔ ክርስቲያን ነኝ በኢየሱስ ክርስቶስ አምናለሁ” አለው። እርሱም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ በ10 አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ” አለው። ቅዱስ ጊዮርጊስም “ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክድም” አለ። በዚህ ጊዜ እጅግ ተናዶ መከራን አጸናበት እርሱ ግን “ይህን ከሀዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰድ” በማለት እግዚአብሔርን የለመነና እንደጸሎቱ የተደረገለት። በእምነቱም ጽናት የሰው ልጅ ሊሸከም የማይችለውን መከራ የተቀበለ ቅዱስ አባት ነው። ከእነዚህም መከራዎች ውስጥ

 1. በእንጨት አስቀቅሎ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው

 2. ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው። ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል።

 3. በሰባ (70) ችንካር አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ።

 4. ሥጋውን በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነስንሶበት ሥጋው ተቆራርጦ ወደቀ። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ “ገና 6 ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛው ታርፋለህ።” አለው።

 5. ዱድያኖስ ደንግጦ “የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ወርቅ እሰጠዋለሁ” ቢል አትናስዮስ የተባለ መሰርይ ከንጉሱ ላምን በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ገድሏት ፈቃድን ተቀበለ። ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞ ሰጠው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል። ጠንቋዩም ማረኝ ብሎት ከመሬት ውሃን አፍልቆ ወደ ጌታችን ቢያመለክት ሐዋርያው ቶማስን በመንፈስ መጥቶ አጥምቆት በሰማዕትነት አርፏል።

 6. በመንኮራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄዷል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተፈጨውን ሥጋ በእጁ ዳስሶ መንፈሱን መልሶ አንስቶታል፤ ተመልሶም “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” ብሏቸዋል።

 7. በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አንድዶበታል። እሳቱም ደሙ ሲንጠባጠብ ጠፍቷል።

 8. ዱድያኖስ “ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳየኝ” ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነስሰቶ አሳይቶታል። ነገር ግን ልቡ ክፉ ነውና በረሀብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበት ግንድ አፍርቶ ልጇ ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈውሶላት መበለቲቷን ከነልጆቿ አጥምቆ ቅዱስ ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል።

 9. ዳግም በመንኩራኩር ፈጭታችሁ ደብረ ይድራስ ወስዳችሁ ዝሩት ብሎ አስፈጭቶ ሥጋውን ቢዘሩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ “ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር፣” እያሉ አመስግነዋል። ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነስቶታል። ሔዶም “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” አላቸው። ጭፍሮቹ ደንግጸው ከእግሩ ስር ወደቁ። ከመሬት ውሃ አመንጭቶ ቅዱስ ዮሐንስ አጥምቋቸዋል።

 10. ንጉሡ ልሹምህ ለአጵሎን ስገድ” ብሎ ቢለምነው እሺ ብሎ ገብቶ ሲጸልይ የንጉሱ ሚስት እለእስክንድርያ “ምን እያልክ ነው?” ብትለው አስተምሯት አሳምኗታል። ሲነጋ ንጉሱ በአዋጅ ህዝብን አሰብስቦ “ጊዮርጊስ ለጣዖቴ ሊሰግድ ነው’ ብሎ በተሰበሰበ ህዝብ መካከል አንድን ብላቴና (የመበለቷን ልጅ) “የክርስቶስ ኢየሱስ አገልጋይ ጊዮርጊስ ይጠራሃል” በል ብሎ ወደጣዖቱ ቢልከው ጣዖቱ ላይ ያደረው ሰይጣን እየጮኸ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለበት ቦታ መጣ፤ አምላክ አለመሆኑን አናዞት መሬት ተከፍታ እንድትውጠው አደረገ። ብዙ ሰዎች ይህንን ተዓምር አይተው አመኑ። ንጉሱን ሚስቱ እንዲመለስ ብትነግረው በአደባባይ አሰቅሎ አሰይፏት ሞታለች ደሟን ጥምቀት አድርጎላት ሰማዕት ሆናለች።

 11. በመጨረሻም በሰይፍ እንዲመተር አስደረገ። ቅዱስ ጊዮርጊስም ከጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቃልኪዳን ተገብቶለት በ27 ዓመቱ በሚያዝያ 23 ቀን በ900 ሰዓት ሰማዕት ሆኗል። አንገቱ ሲቆረጥ ውሃ፣ ደም እና ወተት ወጥቷል።

__

 

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , | Leave a Comment »

የአድዋ ድል ከእግዚአብሔር የተገኘ ድል ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 1, 2014

EthioFlagLion23118 ዓመታት በፊት ዓድዋ ላይ በኢጣሊያ ላይ አንፀባራቂ ድል የተቀዳጀው የኢትዮጵያ ሠራዊት ጠቅላይ አዛዥ ዳግማዊ አፄ ምኒልክ ለፈረንሣዊው ሙሴ ሞንዶን ከጻፉለት የምሥራች ደብዳቤ እንዲህ ብለው ነበር፦

‹‹የምሥራች በእግዚአብሔር ቸርነት የየካቲት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት ኢጣልያንን ድል አድርጌ መታሁት፡፡ በጨረቃ ሲገሰግስ አድሮ እሰፈሬ ድረስ መጥቶ ገጠመኝ፡፡ አምላከ ኃያላን ረድቶኝ ፈጀሁት፡፡ ደስ ብሎኛል ደስ ይበልህ

የካቲት 23 ቀን 1888 .. ባሕር ተሻግሮ ድንበር አቋርጦ የመጣውን ወራሪው የኢጣሊያ ሠራዊት ድላቸውን አስመልክቶም በወሩ (መጋቢት 23 ቀን 1888 ..) ዳግማዊ ምኒልክ ለሙሴ ሽፋኔም እንዲህ ብለው የዓድዋውን ውሎ ገለጹለት፦

‹‹በጥጋባቸው ዓድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የእነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረግኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም››

አድዋ ላይ በተካሄደው ጦርነት የተገኘው ድል የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የመላው በባርነትና በቅኝ ግዛት የሚማቅቁ አፍሪካውያንና የመላው ጥቁር ሕዝብ እንዲሁም የሕዝበ ክርስቲያን/የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ድል ነው።

የዛሬውንና በመላው ዓለም አንፀባራቂ የሆነውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ያስከበረውን የዓድዋ ድል በዚህ ዕለት መሆኑ አጋጣሚ አይደለም።

ከጥንት ጀምሮ ኢትዮጵያን በአካል ተገኝተው የጎበኙ አያሌ የውጭ ሀገራት ዜጎች ስለ ሀገራችንና ስለ ሕዝቦቿ በጋራ የሚመሰክሩት አንድ እውነት አለ፤ ይኸውም፡

‹‹ኢትዮጵያውያን ለሃይማኖታቸውና ለነጻነታቸው ቀናዒዎች ናቸው፡፡›› የሚል ነው፡፡ በአንድ ወቅት ታዋቂው የፈረንሳይ ጋዜጠኛ ዳንኤል ሮፕስ እ..1963 .ም ‹‹አክሌዥያ›› በሚባል ጋዜጣ፤ ‹‹የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን ታውቃላችሁን?›› በሚል ርዕስ ባሰፈረው ሐተታ እንዲህ ሲል ምስክርነቱን ሰጥቷል፡

‹‹ወራሪዎች ምድርዋን በግፍ የያዙባት መሆኑን ታሪክ ያወሳል፤ ነገር ግን ሃይማኖት የእንቅስቃሴዋ መሣሪያ ሆኖ በመገኘቱ ነጻነቷን መልሳ አግኝታለች፡፡ በማዕከላዊው ክፍለ ዘመን ‹‹የካህን የዮሐንስ ግዛት›› በአረመኔው ዓለም ተከቦ የክርስቲያን ምሽግ ሆነዋል እየተባለ ስለ ኢትዮጵያ ይነገር የነበረው
ሁሉ ፍጹም ልበ ወለድ ታሪክ አይደለም፡፡ ከሁለት ሺ ሜትር በላይ ከፍታ ያለውን ደጋማና ለምለም መሬት ቁልቁል የሚያዩት ቀይ፣ ጥቁርና ሰርጥነት ያላቸው የእሳተ ገሞራ ውጤት ባሕርይ ያላቸው ጠረጴዛ መሰል ተራራዎች የጊዜን ውሽንፍር እንዳሳለፉትና የባሕር ዓሣም ሳይበገርና ሳይላላ ማዕበሉን እንደሚያሳልፍ ክርስቲያኒቷ ኢትዮጵያም በታሪክ ውስጥ ጠንካራ ስፍራዋን ይዛ ቆይታለች
››

ይህ ጋዜጠኛ እንዳለው ኢትዮጵያ ላለፉት ሁለትና ሦስት ሺህ ዓመታት በርካታ ፈተናዎች አጋጥመዋታል፡፡ በኢትዮጵያ ላይ ከተቃጣው አያሌ የውጭ ወራሪዎች ጥቃት አብዛኛው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የተሰነዘረ ነበር፡፡ የዚህም ዋነኛው ምክንያት ደግሞ በኢትዮጵያ የረጅም የስልጣኔና የነጻነት ታሪክ ውስጥ የሕዝቡን ብሔራዊ ንቃተ ኅሊና በመቅረጽ ጠቃሚ ሚና የነበራትን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን በመምታት ሹማምንቱና ሕዝቡ የኢጣሊያንን የበላይ ገዥነት እንዲቀበሉ ለማስገደድ ነበር፡፡

ዛሬም በዩክሬይን እየታየ ያለው ከባድ ውጥረት ነፃነታዊ፣ ዲሞክሪያሳዊ ወይም ግዛታዊ ፍላጎቶችን ይፈልጉ ዘንድ የተከሰተ ሁኔታ አይደለም። ይህ ውጥረት፡ ቀደም ሲል በቀድሞዋ ዩጎዝላቪያ (ሰርቢያ)፣ በአርመኒያ፣ በጆርጂያ፣ በግሪክ፣ በቆጵሮስ፣ በግብጽ እና በሶሪያ መጀመሩን እናስታውሳለን። እነዚህ ሁሉ አገሮች፣ ሩስያን እና ዪክሬንን ጨምሮ የኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አገሮች ናቸው። በተለይ ኢትዮጵያን፣ ግብጽን፣ሶርያን፣ ሩስያን እና ሰርቢያን የሚያስተሳስራቸው ሰምአቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነው። ቅዱስ ጊዮርጊስ የእነዚህ አገሮች ዐቃቤ መልአክ ነው።

ይህ በሩሲያ እና በዮክሬን መካከል የሚታየው ፍጥጫ በዚህ በቅዱስ ጊዮርጊስ ዕለት በዓለማችን ታሪካ ቁልፍ የሆነ ሚና የሚጫወት ይሆናል። ቀደም ሲል በሉሲፈራውያኑ የ ዔሣው እና የ እስማኤል ዘሮች ተጠንስሶ የነበረው ሤራ ለመላው ዓለም ነዋሪ የሚጋለጥበት ወቅት ይሆናል። በአንግሎአሜሪካውያን መሪነት የሚመታው ይህ የጦርነት ከበሮ በምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ከተሰማ በኋላ የኢትዮጵያ ተዋሕዶ ክርስቲያኖችን በር ማንኳኳት ይጀምራል።

ከአድዋ ድል በኋላ፡ መጋቢት 23 1988 .ም አፄ ምኒልክ ለሩሲያው/ ለሞስኮብ ንጉሥ / ዛር ኒቆላዎስ 2 (..1868 – 1918) በጻፉት ደብዳቤያቸው፡

‹‹እንደ አውሮፓ ነገሥታት ሥራት ሁሉ ጠብ መፈለጋቸውን ሳያስታውቀኝ፣ እንደ ወምበዴ ሥራት ሌሊት ሲገሰግስ አድሮ ሲነጋ ግምባር ካደረው ዘበኛ ጋር ጦርነት ጀመረ፤ ጥንት ከአሕዛብና ከአረመኔ አገራችን ጠብቋት የሚኖር አምላክ ከእኛ ባይለይ በእግዚአብሔር ኃይል ድል አደረግሁት››

በማለት ድሉ የእግዚአብሔር መሆኑን አስረግጠው ተናግረው ነበር፡፡

CzarNicholasBell23ዛር ኒቆላዎስ 2ኛ ለኢትዮጵያና ለዐቃቤ መልአኳ፡ ለሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያላቸውን አድናቆትና ክብር ለመግለጽ ግዙፍ የሆነውን ደወል ለአዲስ አበባ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን በስጦታ መልክ አስረክበዋል።

ንጉሥ ኒቆላዎስ 2ኛ የመጨረሻው የሩስያ ትዛር ነበሩ። ነጉሡ የታላቋ ብሪታኒያና የጀርመን ነገሥታት በጠነሱስት የጥቅምቱ የሩስያ አብዮት ከወንበራቸው እንዲለቁ ተደርገው፡ በቅጥረኛው፡ ቭላዲሚር ኢሊይች ሌኒን ቦልሸቪክ ሰይጣኖች ከነቤተሰቦቻቸው ተረሽነዋል። የአፄ ኃይለሥላሴ እና የትዛር ኒኮላዎስ፡ የኢትዮጵያ እና የሩሲያ ታሪካዊ እጣ በጣም ተመሳሳይነት አለው።

የሩሲያው ኮሙኒዝማዊ ሤራ ከጅምሩ ያተኮረው በሩስያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን እና በተከታዩቿ ላይ ነበር። በ ነጭሕዝቦች መካከል ባለ ነፍሶች“(Soul) ሆነው የቀሩት ሩስያውያን ናቸው (በተለይ በሴቶቻቸው ላይ የሚንጸባረቀው ቁንጅና ነፍሳቸው እንደ ዔሳው እና እስማኤል ልጆች ገና ስላልተነጠቀ ነው)

ኢትዮጵያን በመክዳት ለአረቦች እና ሶማሊያውያን መቀለጃ እንድንሆን ያደረገንን አመጸኛ ትውልድ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ እያገዘ ከፍተኛ ሚና ለመጫወት የበቃው የፕሪዚደንት ጂሚ ካርተር መስተዳደር ነበር። ይህን መስተዳደር ከጀርባ ሆነው ሲመሩት የነበሩት፡ በአሁኑ ወቅትም የባራካ ኦባማን መስተዳደር የሚመሩት እርጉሙ የካርተር ብሔራዊጸጥታ አማካሪ፡ ዜቤግኔው ብረዥንስኪ ናቸው። እኚህ ሰው፡ ልክ እንደ ሄንሪ ኪሲንጀር በአፍሪቃውያን፣ በሩሲያውያን እና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አላቸው። ብረዥንስኪ እ..አ በ2007 .ም የሚከተለውን ተናግረው ነበር፦

After the collapse of the USSR, the main enemy of the USA will be the Russian Orthodox Church.

ብረዥንስኪ ፓላንዳዊ ዝርያ ያላቸው ግለሰብ ናቸው። አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን በተወገዱበት ወቅት ሪፖርት ለመስራት ወደ አዲስ አበባ ተልከው የነበሩት ሪቻርድ ካፑቺንስኪ የተባሉት ታዋቂ ፖላንዳዊ ጋዜጠኛ ነበሩ። ፖላን ያካቶሊኮች አገር ነች። ጥቁሯ ማዶና/ማርያምበጣም ከሚከበሩባት አገሮች መካከል አንዷ ፓላንድ ናት። ኦቶማን ቱርኮች አውሮፓን ለመውረር በኦስትሪያዋ ቪየና በር ላይ ሲደረሱ በፖላንድ ጦር ሠራዊት እና ጄነራሏ ነበር ሊገረሰሱ የበቁት። የኢትዮጵያውያን ደም በየመንገዱ በሚፈሱባቸው ዓመታት የሮማው ጳጳስ (ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛው) ከፖላንድ መመረጣቸው አጋጣሚ አልነበረም። በ 110 አገራት ጉብኝት አድርገው የነበሩት እኚህ ጳጳስ ግብጽ እና ሱዳን ደርሰው ወደ ኢትዮጵያ ያልመጡበትም ሌላ ምክኒያት አለው። ለማንኛውም፡ አሁን፡ የአውሮፓው ሕብረት አባል አገር፡ ፖላንድ፡ ልክ የቱርክ ዓይነት ሉሲፈራዊ ሚና በመጫወት ላይ ነች። ጸረክርስቶሷ ቱርክ እስላማውያን ተዋጊዎችን ወደ ሶሪያ በመላክ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች እንደምታስጨፈጭፍ፡ ፓላንድም ፋሽስት የሆኑ ከዳተኛ ዪክሬናውያንን እየረዳች ኦርቶዶክሳውያን በመተናኮል ላይ ናት።

ምዕራባውያኑ በሶቺ የተካሄዱትን የክረምት ኦለምፒክ ጨዋታዎች መሣሪያዎቻቸው በሆኑት የቼችንያ እና ደግስታን ሽብር ፈጣሪዎች በኩል ማሰናከል ስላልቻሉ፤ አሁን በከዳተኛ ዮክሬኒያውያን፣ ሰዶማውያን እና ክራይሚያግማሽደሴት በሚገኙት ቱርክ ታታሮች አማካኝነት ሁከት በመፍጠር ላይ ይገኛሉ። በነገራችን ላይ በዚህ ሳምንት የተዋቀረው የዪክሬን ሽግግር መንግሥት ፕሬዚደንት የባፕቲስት ቸርችተከታይ ነው።

የአድዋ ድል የተገኘው የጊዮርጊስ እለት የካቲት 23 1888 .ም ነበር፤ አፄ ምኒልክም ጦርነቱ እስከሚጀመርበት የመጨረሻዋ ደቂቃ ድረስ በአድዋ ማይጓጓ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ሆነው አምላከ ጊዮርጊስ ከእሳቸውና ከሠራዊታቸው ጋር እንዲሆን በጸሎት እየተማጸኑ እንደነበር በወቅቱ የነበሩ ሰዎች መስክረዋል፡፡ የአፄ ምኒልክ ጸሐፊ የሆኑት ጸሐፌ ትእዛዝ አለቃ ገብረ ሥላሴ ስለ አድዋ ድል በጻፉትና እማኝነታቸውን በሰጡበት የመጽሐፉ ክፍል ድሉ ከእግዚአብሔር የተገኘ እንደሆነ ከመግለፃቸውም በላይ የክርስቲያኖች ደም በከንቱ ስለ መፍሰሱ የተሰማቸውን ሐዘኔታም በመጋቢት 23 1888 .ም ለፈረንሳዊው ሙሴ ሸፍኔ በላኩለት ደብዳቤያቸው ገልጸዋል፡፡

ከአላጌ ጦርነት በኋላ፣ ጣሊያኖችን ጦርነት ይቅር፣ የክርስቲያንም ደም በከንቱ አይፍሰስ፣ እርቅ ይሻላል ብላቸው እምቢ ብለው መጥተው በጥጋባቸው አድዋ ላይ ተዋግተው ድል ሆኑ፡፡ እኔ ግን በድንቁርናቸው ብዛት የነዚያን ሁሉ ክርስቲያን ደም በከንቱ መፍሰሱን እያየሁ ድል አደረኳቸው ብዬ ደስ አይለኝም፡፡ ነገር ግን በግፍ የመጡ ሰዎች ናቸውና እግዚአብሔር ግፉን አነጣጠረን

የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ

(ተክለ ጻድቅ መኩሪያ፤ አፄ ምኒሊክ እና የኢትዮጵያ አንድነት፣ 1983 ..)

ምኒልክ ተወልዶ ባያነሣ ጋሻ

ግብሩ እንቁላል ነበር ይኸን ጊዜ አበሻ፡፡

በሠራው ወጨፎ ባመጣው እርሳስ

ተፈጠመ ጣልያን አበሻ እንዳይደርስ፡፡

ምኒልክ ተጉዞ የምትጠይቁኝ

ፊትም አላለፈ ኋላም አይገኝ፡፡

መድፋን መትረየሱን ባድዋ መሬት ዘርቶ

እንክርዳዱን ነቅሎ ስንዴውን ለይቶ

የዘራውን እህል አጭዶና ወቅቶ

ላንቶኔሊ አሳየው ፍሬውን አምርቶ፡፡

እንዳቀና ብሎ ለምኖ መሬት

ንግድ ሊያሰፋበት ሊዘራ አትክልት

እየመጣ ሊሰጥ ግብሩን ለመንግሥት

ለጓዙ ማረፊያ አገር ቢሰጡት

ተጠማኝ ሰንብቶ ሆኖ ባለርስት

ወሰን እየገፋ ጥቂት በጥቂት

እውነት እርስት ሆነው ተቀበረበት፡፡

ባሕር ዘሎ መምጣት ለማንም አትበጅ

እንደ ተልባ ስፍር ትከዳለች እንጂ

አትረጋምና ያለተወላጅ፡፡

የዳኛው አሽከሮች እየተባባሉ

ብልት መቆራረጥ አንድነትያውቃሉ

ዓድዋ ከከተማው ሥጋ ቆርጠው ጣሉ፡፡

የእስክንድር ፈረስ መቼ ተወለደ

የምኒልክ ፈረስ በክንፎቹ ሔደ፡፡MenilikGiorgis23

ደንገላሳ ሲዘል እየተንጓደደ

የሮማውን ኩራት በእግታ አሰገደ፡፡

አገርህን ምኒልክ እንዳሁን ፈትሻት

እጁን ቀምሼ አላውቅም እያለ ሲያማህ

ቀመሰና እጅህን መጥቶ ጠላትህ

ሮም ላይ ተሰማ ለጋስ መሆንህ፡፡

አባተ በመድፋ አምሳውን ሲገድል

ባልቻ በመትረየስ ነጥሎ ሲጥል

የጐጃሙ ንጉሥ ግፋ በለው ሲል

እቴጌ ጣይቱ እቴጌ ብርሃን

ዳዊቷን ዘርግታ ስምዓኒ ስትል

ተማራኪው ባዙቅ ውሃ ውሃ ሲል

ዳኛው ስጠው አለ ሠላሳ በርሜል፡፡

እንደ በላዔ ሰብአ እንደመቤታችን

ሲቻለው ይምራል የኛማ ጌታችን

የልዳው ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ አባቶቻችንን በአድዋ ጦርነት ሃይማኖት እንዳይበረዝ ሀገር

እንዳይወረር ርስታችን ለባዕዳን እንዳይሆን በተጋደሉበት ዘመን ተራዳኢነቱን ገልፆአል፡፡ የመናገሻ ገነተ ፅጌ ጊዮርጊስ ታቦት ይዘው ጠላትን ድል አድርገዋል በወቅቱ አቡነ ማቴዎስ የእመቤታችን ታቦትና የቅዱስ ጊዮርጊስም ታቦታት ይዘው ዘመቱ የአክሱም ካህናትም የእመቤታችን ሥዕልና ሰንደቅ አላማ ይዘው ተሠለፉ የፅዮን እምቢልተኞችም በእቴጌ ጣይቱ ፊት ይነፋ ነበር፡፡ ከለሊቱ 1100 ሠዓት ጦርነቱ ሲጀመር እቴጌ ጣይቱ በማጅራታቸው ድንጋይ ተሸክመው በጉልበታቸው ተንበርክከው በጋለ ፀሎት ወደ እግዚአብሔር ይፀልዩ ነበር፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም ስራሰላቸው ለሀገሩ ለሃይማኖቱ የተሠለፈውን አላሳፈረውም የሰለጠነውን የወራሪ ጦር  በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳዒነት አባቶቻችን ድል ነሱ፡፡

የሰማዕቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የእመቤታችን አማላጅነት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡

__

Posted in Ethiopia, Faith, Infos | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

ቅዱስ ጊዮርጊስ – ተአምራታዊ ኃይላቸውን የገለጹ ጽላቶች

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2012

 

በደቡብ ጎንደር ሃ/ስብከት በፋርጣ ወረዳ በጋሣይና በክምር ድንጋይ መካከል የሚገኘው ጥንታዊው የድድም ደብረ ጽጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የካቲት 19 ቀን 1982 .. ከቀኑ 3 ሰዓት በሰው ሠራሽ መሣሪያ ከተቃጠለ በኋላ የአጥቢያው ካህናትና ምእመናን አዲስ ለሚሠራው ቤተ ክርስቲያን ቦታ በመቆፈር ሲያደላድሉ የቅ/ጊዮርጊስ፥ የኪዳነ ምሕረት፥ የቅ/ሚካኤል፥ የታቦተ ጽዮን የታቦተ ሩፋኤል ጽላቶች ጥላሸት ሳያርፍባቸው በተአምር መገኘታቸውን ከሰበካ ጽ/ቤት ለመረዳት ተችሏል።

ይህ ቤተ ክርስቲያን የተተከለው በ13ኛው ክፍለ ዘመን ሲሆን ለአራት ጊዜ ተሠርቶ አምስተኛው የተቃጠለው ቤተ ክርስቲያን እንደ ነበር በዕድሜ የገፉ የታሪክ ባለቤት የሆኑ አባቶች ይናገራሉ፤ ቤተ ክርስቲያኑ እንደተቃጠለ ቢቀር የሰበካ ክርስቲያኖችን ብቻ ሳይሆን መላ ምእመናንን የሚያሳዝን እንደሆነ በመገመት አዲስ ቤተክርስቲያን በአራት ዓመታት ሥራው ተጠናቆ ሚያዝያ 23 ቀን 1988 .. ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ቅዳሴ ቤቱ ተከብሯል። ለዚህም ቤተ ክርስቲያን አቶ ዓለማየሁ የአምር ከሃያ ሺህ ብር በላይ የሚገመት አንድ የብረት መንበር ሰጥተዋል።

በዚህ ቤተክርስቲያን ቀደም ያሉ አባቶች እንደሚናገሩት የተለያዩ ተአምራት ይነገሩበታል፡ በቦታውም የሚገኙ ሕሙማን ይድኑበታል፣ ሥዕለት ሰሚ በመሆኑም ክርስቲያኖች የለምኑትን ያገኙበታል አንዳንዶችን ለመጠቆም ያህል ከአንድ ድንጋይ ላይ ጐማዳ መስቀልና ትልቅ ጭራ እንደተገኘ በየጊዜው ይተረካል። ከዬት አቅጣጫ እንደመጣ የማይታወቅ ጠበል ከጭንጫ ላይ ይወርዳል፡ ሕመምተኞች በዚህ ጠበል ተጠምቀው አፍጡነረድኤት ተደግሞላቸው በጐማዳው መስቀል ሲታሹ ከልዩ ልዩ በሽታ የሚድኑ ሕመምተኞች ሥፍር ቁጥር የላቸውም።

በተለይ በየዓመቱ በዚህ በዛሬው እለት፤ በሚያዝያ 23 ቀን የቅ/ጊዮርጊስ ጽላት በክብር ታጅቦ በመውጣት ጠበሉ ስለሚባረክ በበዓሉ የሚገኙት ሁሉ ሰለሚጠመቁ የተለየ ሀብተ በረከትና ፈውስ ይታያል፡ የሚገኙትም ምእመናን ከክብረ በዓሉ ሲመለሱ በየደረሱበት ቦታ መንፈሳዊ ዜናውንና ተአምራታዊ ታሪኩን ይመሰክራሉ።

የአረጋዊው መነኩሴ እንባዎች

በስድሳዎቹ ዓመታት ውስጥ አንድ አረጋዊ መነኩሴ እስክንድርያ ስፓርቲንግ ውስጥ ወደሚገኘው የቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አዘውትረው ይመጡ ነበር። እኚህ አረጋዊ መነኩሴ ቅዳሴው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ፊታቸውን በሁለት እጃቸው በመሸፈን ምርር ብለው ያለቅሱ ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ይህ ሁኔታውን የተመለከተ አንድ ወጣት ከቅዳሴ በኋላ በመኪናው ወደ ዘመዶቹ ይዟቸው ይሄድና ከእነዚህ እንባዎች በስተጀርባ ያለውን ምክንያት አጥብቆ ይጠይቃቸዋል።

አረጋዊው መነኩሴም ለወጣቱ እንዲህ አሉት፦ በወጣትነት ዘመኔ ከሴት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት አልነበረኝም፤ የተሳሳተ ስሜትም አላውቅም ነበር። በቅድስናና በንጽሕና መኖር ያስደስተኝ ነበር። ወደ አንድ ገዳም ገብቼም በእውነተኛ ደስታ ውስጥ እኖር ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን ስለ ታመምሁ በገዳሙ ውስጥ ያሉት ሰዎች ወደ ሆስፒታል መሄድ እንዳለብኝ አጥብቀው ጠየቁኝ። በሆስፒታሉ ውስጥ ሳለሁም አንዲት ነርስ እንደ አባቷ አድርጋ ትንከባከበኝ ነበር እንክብካቤዋ እየጨመረ ሲመጣም የረከሱ አሳቦች በሕሊናዬ ይመላለሱ ጀመር። በዚህ ጊዜ ከሆስፒታሉ እንዲያስወጡኝ ግድ አልኋቸው። ከዚህ ጊዜ አንሥቶ እስከ ዛሬ ድረስ ዘወትር ስለ ድካሜ እያለቀስሁ ነው። ከእንግዲህ በኋላ ድጋሚ እንዳልወድቅም ኃጢአቱን ከፊቴ አስቀምጬዋለሁ።

ወጣቱም ለአረጋዊወ መነኩሴ እንዲህ በማለት ይጠይቃቸዋል፦ እነዚህ አሳቦች የተከሰቱት ከብዙ ዓመታት በፊት ነው። ታዲያ አሁን ይህን ሁሉ እንባ ማፍሰስ ለምን አስፈለገ?”

የእኔ የረከሱ አሳቦች የወደደኝንና እስከ አሁን ድረስ የሚወደኝን ጌታዬን አሳዝነውታልና ለምን አላለቀሰም? ዘላለማዊነቱ እጅግ ውድ ስለሆነች በእግዚአብሔር ዘንድ ያለኝን ክብር እንዳላጣ እሰጋለሁ።

እንባዎችዎ ሰላምዎትን አያስጡብዎትም?”

እንባዎቹ በደስታና በሰላም ይሞሉኛል፤ ሰላምንም በአባቱ እቅፍ ውስጥ ስፍራ ባዘጋጀልኝ በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ያድሉኛል።

አቤቱ ጌታ ሆይ፦ ንጹሕ እንባዎችን አድለኝ።

የንስሓ እንባዎቼን ከደስታ ዕንባዎቼ ጋር ቀላቅላቸው።

ኃጢአቶቼንና ድካሞቼን ሁልጊዜ አስባቸዋለሁ።

የአንተንም ታላቅ ፍቅር ዘወትር አስታውሳለሁ።

የአንተ መንፈስ ደስታና ሰላምን ያጎናጽፈኛል።

በእውነተኛ የንስሓ እንባዎች ልቤን ደስ አሰኛት።

_________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , | Leave a Comment »

The Miracles of St. George

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 2, 2010

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church venerates on this Twenty-third day of the month of Miyazia (Ethiopian calendar) the First day of May (Western calendar) the great among the Martyrs for Christ, Saint George.

Saint George was born to a Christian noble family in Lydia, Palestine during the late third century between about 275 AD and 285 A.D. His father, Gerontius, (or Anastasius) was a Roman Army Official from Cappadocia and his mother Theobaste was from Palestine. They were both Christians and from noble families of Anici; they raised their son with Christian beliefs. They decided to call him Georgius (Latin) or Geōrgios (Greek), meaning “worker of the land”. At the age of Fourteen St. George father died; a few years later, George’s mother also died.

After the death of both his parents St. George decided to go to Nicomedia, the Roman Imperial City of that time, and present himself to the Emperor Diocletian, to apply for a career as a soldier. The Emperor welcomed him with open arms, as he had known his father, Gerontius or Anastasius who was one of his finest soldiers. By his late 20s, the Saint was promoted to the rank of Tribunus and stationed as an Imperial guard of the Emperor at Nicomedia.

In the year AD 302 A.D. the Emperor Diocletian (influenced by Galerius) issued an edict that every Christian soldier in the army should be arrested and every other soldier should offer a sacrifice to the Pagan gods. But St. George objected and with the courage of his faith approached the Emperor. Diocletian was upset, not wanting to lose his best Tribune and the son of his best official. St. George loudly renounced the Emperor’s edict, and in front of his fellow soldiers and Tribunes he claimed himself to be a Christian and declared his worship of Jesus Christ. Diocletian attempted to convert the Saint, even offering gifts of land, money and slaves if he made a sacrifice to the Pagan gods. The Emperor made many offers, but St. George never accepted.

Recognizing the futility of his efforts, the Emperor Diocletian was left with no choice but to have him executed for his refusal. Before the execution St. George gave his wealth to the poor and prepared himself. After various torture sessions, including laceration on a wheel of swords in which he was resuscitated three times, St. George was executed by decapitation before Nicomedia’s city wall, on this date in the year 303 A.D. A witness of his suffering convinced the Empress Alexandra and Athanasius, a pagan priest, to become Christians as well, and so they joined George in Martyrdom. His body was returned to Lydia for burial, where Christians soon came to venerate his relics and ask for his prayers.

Source: Ninesaintsethiopianorthodoxmonastery

The Miracles of St. George—to Muslims!

St. George Greek Orthodox Church of Prescott, AZ

The saints love everyone, and help all. Even among Muslims, who don’t even have saints, the knowledge that the Christian saint, the Greatmartyr George of Lydda, helps those who ask him, brings thousands to ask his aid and intercession. And he responds swiftly to help them. How much more will he aid and protect those fellow disciples of Jesus Christ who call upon him in faith, asking for his powerful intercession before God, and granting the gifts of healing and more through his prayers!

The Monastery of St. George Koudounas

This historic Monastery of Saint George Koudounas, on Prince’s Island outside of Constantinople, was according to tradition built by the Byzantine Emperor Nikephoros Phokas in 963 AD. A miraculous icon of St. George was brought here from the Monastery of Peace, which was founded by Emperor Justin II, in Athens at that time.

The Monastery was later sacked in the Fourth Crusade. Then in 1302 the pirate Giustiniani plundered all the buildings and monasteries of the island. Not wanting their holy icon stolen by the Franks, the monks hid the icon under the earth and place the holy altar above it. The miraculous icon however was lost for many years.

Later, St. George appeared to a shepherd in a dream and told him where to find his icon. When he approached the area, he heard the ringing of bells, and having unearthed the icon, found it decorated with bells. This is the source behind the epithet “Koudouna” which means “bells”.

The Monastery was later attached to Hagia Lavra in Kalavryta, and eventually to the Patriarch of Constantinople.

The current church was built in 1905.

The miracles of the Saint are many, not only towards Christians [Romans], who approached always with great reverence (in olden times there wasn’t a Christian family which had not visited Koudouna at least once a year), but towards everyone without exception, who approach his grace with faith. Thus there is a great mass of people who come from other faiths from throughout Turkey. The pilgrims number about 250,000 a year, the majority being muslim Turks.

The great iron gate of the Monastery, as we learn from its engraving in Greek and Turkish, was offered from the Muslim Rasoul Efenti, as a gift of gratitude towards the Saint for the healing of his wife.

On April 23rd, in other words the day when the Saint is honored and the Monastery celebrates, tens of thousands of pilgrims arrive, not only from Constantinople but from other cities, to venerate the Great Martyr and to seek help in their problems.

Roughly all of these pilgrims are from other faiths.

Many will return later to thank St. George, who heard their prayer and granted their desire, bringing the indispensable oil for his vigil lamp. You hear with passion how he healed this person’s son, how another became a mother after being barren for many years, how a third acquired a house, etc.

The Monastery also celebrates on the feast of Saint Thekla, and on this feast about 10,000 Muslims visit the Monastery seeking the prayer of Saint George.

Some come barefoot up the hill which takes about 30 minutes to climb to the Monastery, others come with offerings of oil, candles, and sugar so that their lives may be sweet. Some do not speak as they climb up to the Monastery until they kiss the icon of St. George. They follow the services with hands lifted in the air holding lit candles. They ask priests for antidron to bring home with them for a blessing. They have great faith and respect for Orthodoxy.

On September 24 I witnessed at 6:00 AM four modern looking Turkish girls approaching the Monastery. I asked them for what purpose they came. They responded: “Faith in the Saint brought us here. It doesn’t matter that we are Muslims. We prayed that he would help us. We have heard so much about the Monastery.”

Oral came from Smyrna in order to venerate the Saint with her vow. She brought three bottles of oil. When I asked why she, as a Muslim woman among the thousands, visit the Orthodox Monastery, she responded: “It is not forbidden by anyone for us to believe in Saint George. Religions have one common agreement, the one and only God. We could be hiding within us a christian.”

Of the many interviews I conducted that day with Muslims, the responses were basically the same.

A different answer was given by Antil however. He said: “Life in Turkey is difficult. The people need something to give them strength. They have turned to religion. They have been bored by everything so they seek help elsewhere. Why not Saint George?”

And one Turkish newspaper reported: “Saint George has distributed hope to the suffering.”

Testimonies of Monks From the Monastery

Hieromonk Ephraim of Xenophontos, who has lived for three years at “Koudouna”, is astonished with the faith of the thousands of Muslims who visit the monastery. “These people live with their heart”, he affirms, “Because faith is the sight and the strength of the heart, for this reason they can and they do experience our Saints.”

Monk Kallinikos of Xenophontos, who serves as a priest, relates: “We are astonished with that which occurs here. Many times we see people who find the Lord with the faith of the Roman centurion.” To our question if the Saint responds to the supplications of the thousands of pilgrims, he replied: “During my three years here, we ourselves are witnesses of miracles, such as the healing of paralytics, mutes, and the giving birth to children.”

Thus, St. George has become a place of worship for thousands of atheists, Christians, Jews, and especially Muslims, who with every means come to the island and bring their tamata (vows), and place them before the Saint, as they place their hopes in him. And the Saint shows that he does not judge and ‘imparts healing’ to every faithful person.”

Miracles

The Sick Turkish Woman

A Turkish woman from Levkochori had a serious health problem. She had heard a lot about St. George and wanted to come [venerate], but they did not let her come into the church because she was Turkish. But this didn’t deter her from remaining outside the church the whole night. In the morning they gave her holy oil from the vigil lamp of the Saint and she became well. After this, her husband gave many gifts to the church.

St. George Saves a Young Muslim Girl

A Muslim woman with her mother were taking a taxi for a long trip. The Muslims, as is well known, respect St. George very much.

On the road the taxi driver abandoned the proper course and began to show a threatening attitude towards the girl—the women apparently were praying—and at some point the taxi driver stopped the car and attempted to rape the girl. Immediately a police officer on horseback appeared, who ordered the taxi driver in a very powerful manner to the nearest police station. He went full of fear with the policeman, and the policeman on horseback went with him to the station, and issued a complaint for attempted rape. He signed the police book and left. When the taxi driver later came out of the interrogation, they looked in the book and said to him:

There is no hope for you to escape! Do you know who brought you here?” Saint George! (Source.)

Note: These and similar miracles and sentiments do not at all vindicate the false religion of Islam, nor the terrible actions of some Turks against Christians, but the faith and love of some simple Muslims towards Christ and His Saints. Similarly, Christ found in the Roman Centurion greater faith than any in Israel (Matthew 8:10). And often, this presence of the Holy Spirit out of love not only acts to heal the bodies of non-Orthodox, but more crucially the souls, as many later embrace the light and are baptized Orthodox. May Christ grant us all repentance, that we all may be saved, and come to the knowledge of the Truth. St. George the Trophy-bearer, intercede for us all and help us! Amen.

More can be read here about Muslims at Koudouna.

Why Do Muslims Venerate Saint George?

According to Archimandrite Damianos, overseer of the Holy Sepulchre, there are three reasons:

 • His green garments, which for Muslims represents “life” and for which reason they call him “the Green One,”
 • Because many Muslims hear about and experience his miracles,
 • Because as a Trophy-bearer with a cape and sword he inspires a certain amount of fear and respect.

It is because of the great respect for St. George that none of the Orthodox churches dedicated to him in Turkey have been demolished, as well as churches dedicated to the Theotokos who also is greatly respected by Muslims.

(For the full history of this Monastery with many pictures, visit this site.)

Ed’s note:

Well, no wonder why one of the richest men on planet Earth, a Saudi Arabian /Ethiopian business magnate, Sheikh Mohammed Hussein Ali Al Amoudi, is seriously involved in the Ethiopian sports club of St. George, for which he is currently building a soccer stadium in Addis Abeba.

_________________________________


Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

Oil-Streaked Icon Miracle – St. George

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 12, 2009


STGiorgisAt the Israeli town of Ramla, Christians have been flocking to see what locals are calling a miracle: streaks of what looks like oil mysteriously dripping down an icon of St. George at a Greek Orthodox church named for the legendary third century dragon slayer.


Continue reading...


The most famous Church in the world of St. George is located at Lalibela, Ethiopia , which was built about 1200 AD.


St. George is one of the 11 rock-hewn monolithic churches which imitates a built- up structure but is cut in one piece from the rock and separated from it all round by a trench. Nowhere else in the world are constructions of this particular kind found.


Lalibela, previously known as Roha, is named after the king. The word itself, which translates to mean the bees, recognizes his sovereignty and the people of the region still recount the legend that explains why.


Lalibela was born in Roha in the second half of the twelfth century, the youngest son of the royal line of the Zagwe dynasty, which then ruled over much of northern Ethiopia. Despite several elder brothers he was destined for greatness from his earliest days. Not long after his birth, his mother found a swarm of bees around his crib and recalled an old belief that the animal world foretold important futures. She cried out: -The bees know that this child will become king.


But trials and tribulations followed. The ruling king feared for his throne and tried to have Lalibela murdered and persecutions continued for several years – culminating in a deadly potion that left the young prince in mortal sleep. During the three-day stupor, Lalibela was transported by angels to the first, second and third heavens where God told him not to worry but to return to Roha and build churches – the like of which the world had never seen before. God also told Lalibela how to design the churches, where to build them and how to decorate them.


Once he was crowned, he gathered masons, carpenters, tools, set down a scale of wages and purchased the land needed for the building. The churches are said to have been built with great speed because angels continued the work at night.


It’s quite interesting that the Lalibela legend describes him entering the heavens and then getting a commission by God, when in fact the same was true of Enoch in his legend. The stories differ but they both have fantastic details. Many of the church fathers made sure the ‘Book of Enoch’ was destroyed, but the civilization in Ethiopia made sure to preserve the text.


There are also numerous legends, myths, stories related to the construction of the 11 temple complex’s in Lalibela, including the Bet Giorgis (Church of St. George):

 • They were built by St. George with the help of angels.

 • St. Geroge “appeared” to King Lalibela and asked the king to provide him a “perfect” home.

 • King Lalbela was instructed by God to build churches for which the world had never seen. God instructed Lalibela where to build them. The King was said to have carved out one meter a day, during the day, and angels, along with St. Gabriel, carved out three meters at night.

LalibelaBeteGiorgis

This is a topside view of the rock-hewn Church of St. George at Lilabela Ethiopia. You can clearly see the Ethiopian style Cross.

TombDarius

This cross is exactly the same as the cross found on the ceramic piece at Susa, Assyria. Susa, in present day Iran, is thought to be one of the oldest cities in the world. The Tomb of Daniel, The Prophet was found here. The Susa Stratum was dated around 3200 B.C. The ceramic disc contains the famous Ethiopian/Greek Cross surrounded by three triple triangles surrounded by triple combs. This dual cross symbol has also been found in caves near Cuba (The Isle of Youth) to where, thousands of Ethiopian orphaned-children were sent during the 1980s.

400px-Chalcatzingo_Monument_1_El_Rey.svg

Another early- preclassic Olmec bas-relief found at Chalcatzingo, south of Puebla, Mexico, which is named “El Rey”, may have been founded around 1500 B.C. At the top of the image are three comb-like clouds with feet prints headed for them. The third element of similarity seems to be the fire cross seated on top of the cave. The fire depicts a bright illumination such as would a multiple cross symbol.


Were these civilizations in contact with each other in ancient times or was there one civilization ruling over all three?


Could King Lalibela be the returned Enoch, the first man to have never died, but went to heaven?


Some people speculate about the similarity between the Mayan and Enoch Calendars. Ethiopians still have a calendar system which was designed by The first ever Prophet, Enoch.

________________________________________________________________


Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: