Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • April 2024
    M T W T F S S
    1234567
    891011121314
    15161718192021
    22232425262728
    2930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘St.George’

መልሲ አሎ | ዘማሪት ብሩክታዊት ገብረመድህን

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 31, 2021

✝✝✝ ለድንቅ ዝማሬው ቃለ ዝማሬ መላዕክት ያሰማልን፤ እኅታችን!✝✝✝

🌞🌞🌞 ጊዮርጊስ ማለት “ኮከብ ብሩህ፣ ፀሐይ” ማለት ነው፡፡🌞🌞🌞

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉መድኃኔ ዓለም

አቤቱ አምላካችን ሆይ፤ ለታላቁ ሰማዕት ለቅዱስ ጊዮርጊስ በአንተ ዘንድ ባለሟልነትን በአላውያን/አህዛብ እና በመናፍቃን ዘንድ የመፈራትን ግርማ እንዳጎናጸፍከው ለእኛ የወንጌል ልጆች የምንሆን አገልጋዮችህም በግዙፍ አካልና በረቂቅ መንፈስ ሊተናኮሉን በሚመጡ ጠላቶቻን ላይ ድል የመንሣትን አክሊል አቀዳጀን፤ አሜን!

ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ሀገሩ ፍልስጤም ልዩ ስሟ ልዳ ሲሆን የተወለደው በ፪፻፸፯/277 ዓ.ም ጥር ፳/20 ቀን ነው፡፡ አባቱ ዞሮንቶስ ወይም አንስጣስዮስ የልዳ መኳንንት ሆኖ ተሹሞ ይኖር ነበር፤ እናቱ ቴዎብስታ ወይም አቅሌስያ ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሌላ ማርታና እስያ የሚባሉ ሁለት ሴት ልጆችን ወልዳለች፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐሥር ዓመት በሆነው ጊዜ አባቱ ስለሞተ ሌላ ደግ ክርስቲያናዊ መስፍን ወስዶ አሳደገው፡፡ መስፍኑም በጦር ኃይል አሰለጠነው፡፡ ፳ ዓመትም በሞላው ጊዜ መስፍኑ የ፲፭/15 ዓመት ቆንጆ ልጅ ነበረችውና እርሷን አግብቶ ሀብቴን ወርሶ ይኑር ብሎ ድግስ ሲያስደግስ ጌታችን ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዚህ አላጨውምና የመስፍኑን ነፍስ ወሰደ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስም ኀዘኑን ጨርሶ ወደ ቤሩት ሀገር ሄደ፡፡ በቤሩት ደራጎንን ያመልኩና ሴት ልጆቻቸውን ይገብሩለት ስለነበር ሰማዕቱ ደራጎኑን በኃይለ መስቀል ድል ነስቶት ሕዝቡን ወደ አምልኮተ እግዚአብሔር አስገብቷቸዋል፡፡

ወደፋርስ ቢመለስ ዱድያኖስ ሰባ ነገሥታት ሰብስቦ ሰባ ጣዖታት አቁሞ ሲሰግድ ሲያሰግድ ቢያገኛቸው ለሃይማኖቱ ቀናዒ ነውና ከቤተመንግስቱ ገብቶ በከሃዲያኑ ሰባው ነገሥታት ፊት ክርስቲያን መሆኑን በመመስከር የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ ዱድያኖስም ማንነቱን ከተረዳ በኋላ “አንተማ የኛ ነህ በዐሥር አህጉር ላይ እሾምሃለሁ የኔን አምላክ አጵሎንን አምልክ” አለው፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም “ሹመት ሽልማትህ ለአንተ ይሁን እኔ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስን አልክደውም” አለው፡፡ በዚህ ጊዜ ዱድያኖስ እጅግ ተናዶ ብዙ አሠቃቂ መከራዎችን አደረሰበት፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ጌታችንን “ይህን ከሃዲ እስካሳፍረው ድረስ ነፍሴን አትውሰዳት” በማለት መከራውን ይታገስ ዘንድ ለመነው፡፡ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ፈቃዱን ይፈጽምለት ብዙ በመከራው ሁሉ ጽናትን ሰጥቶታል፡፡ ሦስት ጊዜም ከሞት አስነሥቶታል፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም የደረሱበት እጅግ አሠቃቂ መከራዎች የሰው ኅሊና ሊያስባቸው እንኳን የማይችላቸው ናቸው፡፡

በመጀመሪያም ዱድያኖስ በእንጨት ላይ ካሰቀለው በኋላ ሥጋውን በመቃን አስፈተተው፣ ረጃጅም ችንካሮች ያሉበት የብረት ጫማ አጫምቶት ሂድ አለው፡፡ ጌታችንም ቅዱስ ሚካኤልን ልኮለት ፈውሶታል፡፡ ዳግመኛም በሰባ ችንካሮች አስቸንክሮ በእሳት አስተኩሶ አናቱን በመዶሻ አስቀጥቅጦ በሆዱ ላይ የደንጊያ ምሰሶ አሳስሮ እንዲያንከባልሉት አደረገ፡፡ ሥጋውንም በመጋዝ አስተልትሎ ጨው ነሰነሰበት፡፡ ሥጋውም ተቆራርጦ መሬት ላይ ወደቀ፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመንፈቀ ሌሊት በእጁ ዳስሶ ከፈወሰውና “ገና ስድስት ዓመት ለስሜ ትጋደላለህ፣ 3 ጊዜ ትሞታለህ፣ በ4ኛውም ታርፋለህ” ካለው በኋላ በመከራውም ሁሉ እርሱ እንደማይለየው ነገረው፡፡

ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከዚያ ካደረሰበት አሠቃቂ መከራዎች ሁሉ ድኖ ፍጹም ጤነኛ መሆኑን በተመለከተ ጊዜ እጅግ ደንግጦ “የሚያሸንፍልኝ ቢኖር ብዙ ወርቅ እሰጠዋለሁ” ብሎ ተናገረ፡፡ አትናስዎስ የተባለ መሰርይ(ጠንቋይ) አንዲትን ላም በጆሮዋ ሲያንሾካሹክባት ለሁለት ተሰንጥቃ ስትሞት ለንጉሡ አሳየውና ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲሚያሸንፍ ምልክት አሳየ፡፡ ንጉሡም ያሸንፍልኛል ብሎ ደስ አለው፡፡ መሰርይውም ሆድ በጥብጦ አንጀት ቆራርጦ የሚገድል መርዝ ቀምሞ አስማተ ሰይጣን ደግሞበት እንዲጠጣው ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሰጠው። ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ ቢጠጣው እንደ ጨረቃ ደምቆ እንደ አበባ አሸብርቆ ተገኝቷል፡፡ በዚህም ጊዜ ጠንቋዩ ማረኝ ብሎ ከእግሩ ሥር ወደቀ፡፡

ቅዱስ ጊዮርጊስ ግን በመንኰራኩር አስፈጭቶ ከትልቅ ጉድጓድ ጥሎት ደንጊያ ዘግቶበት አትሞበት ሄደ፡፡ ጌታችንም የተፈጨውን የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋ በእጁ ዳስሶ ፈውሶታል፡፡ ወደ ከሃዲውም ንጉሥ ተመልሶ “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” በማለት መሰከረ፡፡ ንጉሡም ዳግመኛ በብረት አልጋ አስቸንክሮ ከበታቹ እሳት አነደደበት ነገር ግን እሳቱ ደሙ ሲንጠባጠብበት ጠፍቷል፡፡ ጌታችንም ፈወሰው፡፡ ከዚህም በኋላ ዱድያኖስ ቅዱስ ጊዮርጊስን “ኢየሱስ አምላክ መሆኑን አሳየኝ” ቢለው የለመለሙትን ዕፅ አድርቆ፣ የደረቁትን ደግሞ አለምልሞ፣ ከሞቱ 430 ዓመት የሆናቸውን ሙታንን አስነሥሰቶ አሳይቶታል፡፡ ነገር ግን ንጉሡ ልቡ ክፉ ነውና በርኃብና በጽም ይሙት ብሎ ምንም ከሌላት መበለት ቤት አሳስሮታል። እርሷም የሚቀመስ ስትፈልግ ቤቷን በእህል አትረፍርፎ የታሰረበትን ግንድ ማለትም የቤቱን ምሰሶ አለምልሞታል፡፡ ልጇም ጆሮው የማይሰማ ነበርና ፈወሰላት፡፡ መበለቲቷንም ከነልጆቿ አጥምቆአቸው መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ከእስራቱ ፈትቶት ተመልሷል፡፡

ዳግመኛም ንጉሡ ዱድያኖስ ጭፍሮቹን “በመንኰራኩር ፈጭታችሁ አጥንቱን ደብረ ይድራስ ተራራ ላይ ወስዳችሁ ዝሩት” ብሎ አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም የቅዱስ ጊዮርጊስን ሥጋ በመንኰራኩር ፈጭተው ወስደው በተራራው ላይ ቢረጩት ሥጋው ያረፈበት ሳር፣ ቅጠሉ፣ ደንጊያው፣ እንጨቱ ሁሉ “ጊዮርጊስ ቅዱሱ ለእግዚአብሔር፣ ጊዮርጊስ ሰማዕቱ ለእግዚአብሔር” እያሉ አመስግነዋል፡፡ አሁንም ጌታችን ለሦስተኛ ጊዜ ከሞት አስነሣውና ሥጋውን ፈጭተው በተራራም ላይ ሥጋውን በትነውት ወደ ንጉሡ የሚመለሱትን ወታደሮች በመንገድ ከኋላቸው ሄዶ ደረሰባቸውና “ቆዩኝ ጠብቁኝ” አላቸው፡፡ እነርሱም እጅግ ደንግጠው ይህ እንዴት እንደሆነ ሲጠይቁት “አምላኬ ከሞት አዳነኝ” አላቸው፡፡ ጭፍሮቹም እጅግ ደንግጠው ከእግሩ ስር ወድቀው ይቅር በለን ብለው በአምላኩ እንደሚያምኑ መሰከሩለት፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስም ከመሬት ላይ ውሃ አመንጭቶ በጸሎት ጌታችንን ቢጠይቅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥቶ አጥምቋቸዋል፡፡ እነርሱም በንጉሣቸው ፊት ሄደው ስለጌታችን በመመስከር በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ዐፅሙ ተቃጥሎ አጥንቱ ተፈጭቶ በደብረ ይድራስ ተራራ ላይ የተበተነው በዛሬዋ ዕለት ነው፡፡

አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ማረን፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ራራልን፤ አቤቱ የቅዱስ ጊዮርጊስ አምላክ ሆይ ይቅር በለን። ልዑል እግዚአብሔር አምላካችን ሰማዕታትን በደም ቅዱሳንን በገዳም ሐዋርያትን በአጽናፍ ዓለም መላዕክትን በአጽራርያም እንዳጸናቸው እኛ ሁላችንንም በኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነታችን በቅድስት ቤተክርስቲያን በበጎ ምግባር በጾም በጸሎትና በትሩፋት ያጽናን አሜን።

🌞🌞🌞“ሦስት ፀሐይ” በኦሮሚያ ሲዖል | የፀሎተ ትግራይ ፍሬ? | የዋቄዮአላህ ጭፍሮች ወዮላችሁ!“

______________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Life, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ቀዳም ሥዑር | የቅዱስ እሳት ተአምር በኢየሩሳሌም | The Miracle of the Holy Fire in Jerusalem

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 1, 2021

✞✞✞ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ።✞✞✞

የማያቃጥለው እና የክርስቲያኖችን ነፍስ የሚያስደስተው ይህ ድንቅ ሥነ-ስርዓት በኢየሩሳሌም በሚገኘው የትንሳኤ ቤተክርስቲያን ውስጥ በቅዱስ ቅዳሜ ይካሄዳል።

ፋሲካ የሚውልበት ቀን በየዓመቱ እንደ አዲስ ይወሰናል፡፡ የቀን እና የሌሊት ርዝመት እኩል በሚሆንበት የፀደይ እኩልነት እና ከአይሁድ ፋሲካ በኋላ የመጀመሪያ እሁድ መሆን አለበት። ስለዚህ ብዙ ጊዜ የተለያዩ መስፈርቶችን በመጠቀም ከሚወስነው የካቶሊክና ፕሮቴስታንት ፋሲካ ቀን ይለያል።፡ የቅዱስ እሳት በዓለም ምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ በጣም የታወቀ ተዓምር ነው፡፡ ለዘመናት በየአመቱ በተመሳሳይ ቦታ፣ በተመሳሳይ ጊዜና በተመሳሳይ ሁኔታ ይካሄዳል። ከጊዜ ወደ ጊዜ እንደዚህ በመደበኛነት እና ያለማቋረጥ የሚከሰት ሌላ ተዓምር አይታወቅም። የሚከናወነው በኢየሩሳሌም በሚገኘው የትንሳኤ/ የቅዱስ ጎለጎታ ቤተ ክርስቲያንን ውስጥ ነው ፣ በምድር በጣም በተቀደሰው ስፍራ ፣ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በታሰረበት፣ በተሰቀለበት እና በመጨረሻም ከሞት በተነሳበት፡፡

The ceremony, which awes the souls of Christians, takes place in the Church of the Resurrection in Jerusalem. The date for Pascha is determined anew for every year. It must be a first Sunday after the spring equinox and Jewish Passover. Therefore, most of the time it differs from the date of Papal Protestant and Protestant Easter, which is determined using different criteria. The Holy Fire is the most renowned miracle in the world of Eastern Orthodoxy. It has taken place at the same time, in the same manner, every single year for centuries. No other miracle is known to occur so regularly and so steadily over time. No other miracle is known to occur so regularly and so steadily over time. It happens in the Church of the Holy Sepulchre in Jerusalem, the holiest place on earth, where Christ was crucified, entombed, and where He finally rose from the dead.

Breaking News from #Jerusalem the Resurrection Church :blood is leaking from the stone Jesus body was laid before his burial . You can hear the Israeli police closed the area.

___________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

ሰሙነ ሕማማት ሰኑይ | መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 26, 2021

✞✞✞ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት ስያሜዎች ✞✞✞

ሰኞ፤ መርገመ በለስ የተፈጸመበት ሰኞ፤ አንጽሖተ ቤተ መቅዳስ የተፈጸመበት ሰኞ::

ማግሰኞ፤ የጥያቄና የትምህርት ቀን::

ረቡዕ፤ ምክረ አይሁድ፥ የዕንባ ቀን፥ የመልካም መዓዛ ቀን::

ሐሙስ፤ ጸሎተ ሐሙስ፥ ሕጽበተ ሐሙስ፥ የምሥጢር ሐሙስ፥ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፥ የነጻነት ሐሙስ::

ዐርብ፤ የስቅለት ዐርብ::

ቅዳሜ፤ ቀዳም ሥዑር (ሹር ቅዳሜ)፤ ለምለሚቱ ቅዳሜ፥ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፥ ሰንበት ዐባይ፥ ቅዱስ ቅዳሜ

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »