Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Sister’

The Amazing Myanmar Nun | የምያንማሯ ድንቅ ክርስቲያን መነኩሴ፤ “ወገኖቼን ከምትገድሏቸው እባካችሁ እኔን ግደሉኝ!”

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 8, 2021

👉 በቡድሂስቶች ሃገር በምያንማር/በርማ አመጹና ግድያው ቀጥሏል፤ ፖሊሶችና ወራሪ ሮሂንጋ ሙስሊሞች የዜጋውን ሕይወት ይቀጥፋሉ ክርስቲያኗ ሴት መነኩሴ ግን እራሳቸውን በመሰዋዕት አሳልፈው በመስጠት ለመላው ዓለም እንዲህ አርአያ ለመሆን በቅተዋል።

👉 ሴት ክርስቲያን ካቶሊክ መንኩሴዋ አን ሮዛ ኑ ታውንግ

ወገኖቼን ከምትገድሏቸው እባካችሁ እኔን ግደሉኝ!” እኔ ልንበርከክልዎት፤ የኔ እናት! 😢😢😢

ላለፉት ቀናት በብዛት በመገደል ላይ ላሉት የምያንማር አዲስ ወታደራዊ መንግስት ተቃዋሚዎች ምህረት እንዲያደርጉላቸው ሴት መንኩሴዋአን ሮዛ” ለመማጸን በፖሊሶች ፊትለፊት ተንበርክከው “ወገኖቼ ሲገደሉ ማየት አልፈልግምና ነው!” በማለት ጮኸው ነበር ። መነኩሴዋ ለመሞት ተዘጋጅተውና ሌሎች እንዲኖሩም ሕይወታቸውን መስዋእት ማድረግ ፈቃደኛ እንደነበሩ በማውሳት ድርጊቱን እንዲህ ሲሉ በዝርዝር ገልጸውታል፦

እሁድ ዕለት እኔ ክሊኒኩ ውስጥ ነበርኩ። ሌሎቹ ክሊኒኮች ዝግ ስለነበሩ በዚያ ቀን ሕክምና እሰጥ ነበር።ሰዎች ሲራመዱ አየሁ። ተቃውሞ እያሰሙ ነበር። በድንገት ሰልፈኞቹን ፖሊሶች፣ ወታደሮች እና የውሃ መድፎች ሲከተተሏቸው አየሁ። ከዚያም ተኩስ ከፍተው ሰልፈኞቹን መደብደብ ጀመሩ። ደነገጥኩኝ ዛሬ የምሞትበት ቀን ነው ብዬ አሰብኩ። ለመሞትም ወሰንኩ።

እንዳያደርጉት እየጠየኩኝ እና እየለመንኳቸው ነበር፤ እናም ሰልፈኞቹ ምንም [ወንጀል]አልፈፀሙም አልኳቸው። እንደ እብድ ሰው እያለቀስኩ ነበር። ጫጩቶቹን እንደምትጠብቅ እንደ እናት ዶሮ ነበርኩ ተቃዋሚዎችን ወደደበደቡበት እየሮጥኩ ነበር። ይህም ክሊኒኩ ፊት ለፊት ነበር ። ልክ እንደ ጦርነት ነበር። ከብዙ ሰዎች ይልቅ እኔ ብሞት ይሻላል ብዬ አሰብኩ።

ጮክ ብዬ እያለቀስኩ ነበር። ጉሮሮየም ህመም ላይ ነበር። ዓላማዬ ሰዎች እንዲያመልጡ እና የተቃውሞ ሰልፎችን እንዲያደርጉ እና የፀጥታ ኃይሎችን ለማስቆም ነበር። ሰዎችን ማሰሩን እንዳይቀጥሉ ጠየቅኳቸው። እየለምንኳቸው ነበር። በዚያን ጊዜ አልፈራሁም። እኔ ፈርቼ ብሸሽ ኖሮ ሁሉም በችግር ውስጥ ይገኙ ነበር። በጭራሽ አልፈራሁም። ቀደም ሲል ስለተገደሉት የናይፒታው ልጃገረድ እና ስለ ማንዳላይ ሴት ልጅ እያሰብኩ ነበር። ከገጠር ስለመጡትና ስለ ወደቁትን ነፍሳት ሁሉ እያሰብኩ ነበር። በሚትኪና ሰዎች ላይ ክፉ ነገር እንዳይመጣባቸው ተጨንቄ ነበር።

ወደ ባኒያን ዛፍ ሲደርሱ እኔ [ፖሊሶቹን/ባለሥልጣናቱን]እየጠራኋቸውና እየነገርኳቸው ነበር: – ‘እባካችሁ እኔን ግደሉኝ። ሰዎች ሲገደሉ ማየት አልፈልግም።” ጮክ ብዬ እያለቅስኩ ስል እነርሱ ለጥቂት ጊዜ ቆሙ።

አንደኛው ወደ እኔ መጥቶ “እማማ ፣ ብዙ አይጨነቁ ፣ እኛ በእነሱ ላይ አንተኩስባቸውም” አለኝ ።

እኔ ግን እንዲህ በማለት ነግርኩት፤ “እነሱም በሌሎች መሳሪያዎች ሊገደሉ ይችላሉ። በእነሱ ላይ አይተኩሱ። እነሱ እኮ ዝም ብለው ተቃዋሚዎች ናቸው።”

በብዙ ቦታዎች እንዳየሁት ሰዎችን በጥይት እንደገደሉ በአእምሮዬ ውስጥ ስላለ በእነሱ ላይ አይተኩሱም ብዬ አላመንኩም ነበር። [አንዱን ተቃዋሚ] ወደ ክሊኒኩ አምጥቼ ህክምና ሰጠሁት። ፖሊሶቹ ሌላውን ተቃዋሚ እንደወደቀ ሊይዙት እንደተቃረቡ ፖሊሶቹንን አቁሜ ግብግቡን እንዳይቀጥሉ ጠየቅኳቸው። ለዚያም ነው ፖሊሱ ያላሰረው፤ ያለበለዚያ እነሱ ይይዙትና ከዚያም በጎትተቱ ነበር።

በሕዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ነገር እንዳያችሁት እነሱ[ወታደሮቹ]የሕዝብ ጠባቂዎች እንዳልሆኑ ሆኖ ይሰማኛል። ሰዎች ደህና ሁኔታ አይደለም ያሉት እናም ጭካኔ የተሞላበት እስራት በሌሊት ይካሄዳል። የአንዲት ወጣት እናት ከሞተ አካል አጠገብ ስታለቅስ የሚያሳየውን ቪዲዮ ሳይ በጣም አዘንኩ። እኔ ደግሞ አምቡላንስ ሲወድም እና ባለሞያዎች በጠመንጃ ሲደበደቡም አይቻለሁ። እነሱ እኛን መጠበቅ ነበረባቸው፤ ግን ህዝባችን እራሱን መከላከል አለበት። በጎ አይደለም። እነሱ (የደህንነት ኃይሎች) የማይወዷቸውን ይይዟቸዋል፣ ይደበድቧቸዋል፣ ይገድሏቸዋል። የማያንማር ሕዝብን የሚከላከል ማንም የለም። ሰዎች እራሳቸውን መከላከል እና እርስ በእርስ መረዳዳት አለባቸው።”

ዋው! ድንቅ ድንቅ ነው! በሁዳዴ መግቢያ ይህን ያሳየን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን! የአክሱም ጽዮን ልጆች በአውሬው ላይ ድል የሚቀዳጁበት ጊዜ እየተቃረበ ነው!

አንዲት የምያንማር መነኩሴ በጦርነት ቀጠና ውስጥ ተንበርክከው መሳሪያ ስላልታጠቁ ዜጎች ህይወት ለመማፀን ሲለምኑ ፖሊሶች መንቀሳቀስ አቅቷቸው ቆሙ፤ ይህ ድንቅ ምስል በመላው ዓለም ዞሯል። ቤተክርስቲያኗ እጅግ በጣም እምነት የለሽ በሆነችበት ጊዜ ብቸኛዋ መነኩሴ በሁከት ፣ ሽብር እና ስቃይ በተሞላባት ዓለም ውስጥ ሰላም የሰፈነበትን የእግዚአብሔርን መንግሥት ይመስላሉ። “የሚያስተራርቁ ብፁዓን ናቸው፥ የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።” [የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፭፥፱] የኛዎቹስ አስታራቂዎችና ሰላም ፈጣሪዎች የት አሉ?

መነኩሴአን ሮዛ ኑ ታውንግለዓለም፤ በተለይ ለኢትዮጵያ እውነተኛ እና ታማኝ ምስክር ለመሆን ህይወታቸውን ለመስጠት የተዘጋጁ ጀግና የክርስቶስ ልጅ ናቸው። ሃይማኖታዊ ቅድስና ከፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ጋር ግራ አላጋባቸውም። በሚቀጥሉት መቶ ዘመናት በቤተ መቅደሳቸው ዙሪያ ስለሚያበሩት ሻማዎች እያሰቡም አልነበረም፣ ጸሎት በማድረግና በቅዳሴ ሥርዓት ላይ በመገኘት ብቻ ያለተግባር ፍትህ እንደማይገኝ፣ በዓይናቸው ለማየት በቅተው ነበር፣ መላ ሰውነታቸው በሰው ልጅ ስቃይ ፣ በሰው ልጅ ርህራሄ እና በሰው ልጅ ነፃነት ተውጧልና። አንድ ሰው ከእግዚአብሔር አምላኩ ጎን ነፍሱን ለአባቱና ለእናቱ፣ ለወንድሞቹና ለእህቶቹ፣ ለሚስቱና ለባሏ፣ ለልጆቹና ለጎረቤቶቹ፣ ለጓደኞቹና ለወገኖቹ ከሚሰጠው ፍቅር የበለጠ ፍቅር ሊኖር አይችልም።

እኝህ ድንቅ የምያንማር መነኩሴ ለጊዜያዊ ስልጣን፣ ተወዳጅ ለመሆን ወይም ተፅዕኖ ለመፍጠር ፍላጎት የላቸውም ፣ እማማ አን ሮዛ የራሳቸውን ስጋዊ አካል እንኳን ለማዳን አልፈሩም፣ ፍላጎትም አልነበራቸውም። የተለየ ኃይል እና ተጽዕኖ ያለው ተለዋጭ ታሪክን በመናገር ራሱን በመስቀል ላይ ለሞት አሳልፎ የሰጠውን ኢየሱስ ክርስቶስን ይህ ቅዱስ የሆነ የመነኩሴዋ ተግባር በከፊል ያሳየናል። የአዲስ ኪዳን ትምህርት ለዓለም ምስክር መሆኑን ያስተምረናል። አዎ! በሰይፍ የሚኖሩ በሰይፍ ይወድቃሉ!

በሃገራችን እንዳየነው ክርስቲያን ነን የሚሉት ሳይቀሩ ሰላምን ለማስከበር በሚል የአውሬው ቅጥፈት ተታለው ለጊዚያዊ ጥቅም፣ ለስልጣን እና ኢጎ ሲሉ በትግራይ ሕዝብ ላይ ዓመፅን ተጠቅመው በሰላማዊ ሕዝብ ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንዲካሄድባቸው ፈቀዱ። ጦርነቱ “ፍትሃዊ ጦርነት” ባለመሆኑ፤ ሁከት ሁከትን ይወልዳልና በሰይፍ የሚኖሩ በሰይፍ እየወደቁ እንደሆኑ እያየናቸው ነው።

👉“ተዋሕዶ አባቶች ባካችሁ እንደ በርማ መንኩሴዎች ደጅ ወጥታችሁ የተቃውሞ ስልፉን ምሩት”

______________________________

Posted in Ethiopia, Faith, Infos, Life | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: