Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 5, 2013
ብሪክ ትንሳዔ / A Blessed Pasha
Reblogged from April 5, 2012
E thiopian Orthodox Christians celebrate Easter anywhere from a week to two weeks after the western Church (sometimes, they occur at the same time, due to the vagaries of the Eastern Orthodox calendar, which Ethiopians follows). Fasika (Easter) follows eight weeks of fasting from meat and dairy. On Easter Eve, Ethiopian Christians participate in an hours-long church service that ends around 3 a.m., after which they break their fast and celebrate the risen Christ.
Source: Time Magazine
THE SEVEN WORDS OF JESUS ON THE CROSS
THE FIRST WORD
“Father, forgive them, for they do not know what they do.” Gospel of Luke 23:34
THE SECOND WORD
“Truly, I say to you, today you will be with me in Paradise.” Gospel of Luke 23:43
THE THIRD WORD
“Jesus said to his mother: “Woman, this is your son”. Then he said to the disciple: “This is your mother.” Gospel of John 19:26-27
THE FOURTH WORD
“My God, my God, why have you forsaken me?” Matthew 27:46 and Mark 15:34
THE FIFTH WORD
“I thirst” Gospel of John 19:28
THE SIXTH WORD
When Jesus had received the wine, he said,
“It is finished”; and he bowed his head and handed over the spirit. ” Gospel of John 19:30
THE SEVENTH WORD
Jesus cried out in a loud voice,
“Father, into your hands I commend my spirit” Gospel of Luke 23:46
________________________________________
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia | Tagged: Easter , Ethiopia , Fasika , Good Friday , Passover , Seklet , Siklet , Tensae , The Cross , The Crucifiction | 1 Comment »
Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 3, 2013
VIDEO
ፈጣሪዋ በዕንጨት መስቀል ላይ ተዘርግቶ ተሰቅሎ በአየችው ጊዜ ፀሐይ ጨለመች እርሱም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም የነሣትን ለባዊት ነባቢት የሆነች ነፍሱን ከሥጋው ለያት ሐዋርያ ጴጥሮስ በሥጋ ምውት ሲሆን በመለኮት ሕያው ነው እንዳለ ነፍሱ ከመለኮት ሳትለይ ከሥጋ ተለየች በዚያ ጊዜ ሥጋ ከመለኮት ሳይለይ በዕንጨት መስቀል ላይ ተሰቅሎ ነበር፡፡
እንዲሁም ነፍስ ከመለኮት ጋራ አንድ ሁና እሥረኞች ነፍሳትን ትፈታቸው ዘንድ ወደ ሲኦል ወረደች፡፡
እርሱ ከሰማያት በላይ ከፍ ከፍ ያለ ልዑለ ባሕርይ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋራ በጌትነቱ ዙፋን ተቀምጦ ያለ ለእርሱም ምስጋና የክብር ክብር ገንዘቡ የሆነ ራሱን ሠውቶ አዳነን፣ የመንግስቱን ደጆች በፈሳሽ ደሙ ከፈተልን፡፡
ሐዋርያዊ ቅዱስ አትናቴዎስ እንዳለ የእግዚአብሔር ታላቅ የማዳን ሥራ ለባሕርያዊ ደግነቱ የተገባ ነው፡፡ አንድ ንጉሥ የመሠረተው ከተማ ወይም የሠራው ቤት ከጠባቂዎቹ ስንፍና የተነሣ በሽፍታ ቢጠቃና ቢወረር ሽፍታውን ተበቅሎ ይዞታነቱን ያጸናል እንጂ በጠላት በመወረሩ ምክንያት አይተወውም፡፡ የአብ አካላዊ ቃልም የእጁ ሥራ የሆነውን የሰው ዘር ጠፍቶ እንዲቀር አልተወውም፤ ሞትን የራሱን ሰውነት ለሞት አሳልፎ በመስጠት ሲያስወግድ፣ ለሰው ተሰጥቶት፣ ነገር ግን ሕጉን በመተላለፉ ምክንያት አጥቶት የነበረውን ሁሉ በኃይሉና በሥልጣኑ መለሰ፡፡
ይህንንም በመንፈሰ እግዚአብሔር የተቃኙት የመድኀኒታችን አገልጋዮች የጻፏቸው ቅዱሳን መጻሕፍት እንዲህ በማለት ያረጋግጡልናል፡፡ ‹‹ይህን ስለ ቆረጥን የክርስቶስ ፍቅር ግድ ይለናል፤ አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፣ እንግዲያስ ሁሉ ሞቱ፣ በሕይወትም ያሉት ስለ እነርሱ ለሞተውና ለተነሣው እንጂ ወደ ፊት ለራሳቸው እንዳይኖሩ ስለ ሁሉ ሞተ፡፡›› 2 ቆሮ 5÷14-15
በመቀጠልም ሌላ ማንም ሳይሆን ራሱ የእግዚአብሔር ቃል ለምን ሰው መሆን እንዳስፈለገው ምክንያቱን ይነግረናል፡ – ‹‹ሁሉ ለእርሱ የሆነና ሁሉም በእርሱ ለሆነ ለርእሱ ብዙ ልጆችን ወደ ክብር ሲያመጣ የመዳናቸውን ራስ በመከራ ይፈጽም ዘንድ ተገብቶታልና፡፡›› ዕብ . 2÷9 ይህም ማለት ሰውን ከጀመረው ጥፋት መልሶ ሕይወትን መስጠት ጥንቱን ከፈጠረው ከእግዚአብሔር ቃል በስተቀር ለሌላ ለማንም ተገቢ አይደለምና፡፡
አካላዊ ቃል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደው እንደ እርሱ ሰዎች ለሆኑ ሥጋውያን ሁሉ ቤዛ ይሆን ዘንድ ነበር፡፡ ሐዋርያው ‹‹ልጆቹ በሥጋና በደም እንደሚካፈሉ እርሱም እንዲሁ በሥጋና በደም ተካፈለ፤ በሞቱ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን ይሽረው ዘንድ፣ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፤ በሕይወታቸው ዘመን ስለ ሞት ፍርሃት በባርነት ይታሰሩ የነበሩትን ሁሉ ነጻ ያወጣ ዘንድ›› ዕብ . 2÷14-15 በማለት እንደገለጸው፡፡ የራሱን ሰውነት በመሰዋት በእኛ ላይ የነበረውን ሕግ (ትሞታለህ የሚለውን ) በመፈጸም አስወገደልን፡፡
እርሱ ራሱ በእኛ ላይ የነበረውን እርግማን ሊያስወግድ ከመጣ ለእርግማን የተቀመጠውን ሞት ካልተቀበለ በስተቀር እርግማናችንን እንዴት አድርጎ ይሸምልን ነበር ? ይኸውም መስቀል ነው፡፡ ሰውም ሕጉን በተላለፈ ጊዜ ስለ ተረገመ የዚህ ርግመት ካሣ ሊከፈል የሚችለው የርግመት መገለጫ የሆነውን የመስቀል ሞት በመቀበል በመሆኑ ጌታችን የመስቀል ሞተ ተቀበለልን፡፡ ‹‹በእንጨት ላይ የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፏልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፡፡›› ገላ . 3÷13 ተብሎ እንደተጻፈ፡፡
የሁላችን መድኀኒት ስለ እኛ ሞቶልናልና በእርሱ የምናምን እኛ በሕግ መልክ በማስጠንቀቂያ በተነገረውና ባጠፋን ጊዜም በተግባር በደረሰብን (በተፈጸመብን ) የሞት ፍርድ እንደ ቀድሞው በኩነኔ ሞት አንሞትም፡፡ ክርስቶስ ስለ እኛ ሞትን ተቀብሎ የሕግ አፍራሽነት ዕዳችንን ከከፈለልን በኋላ ይህ ፍርድ ተፈጽሞ አልቋልና፡፡ እንዲሁም ሙስናና ጥፋት በጌታችን የትንሣኤ ኃይል ስለ ተወገደ ዛሬ እኛ እግዚአብሔር በወሰነው ጊዜ የምንሞተው ለሰውነታችን ተፈጥሮ እንደሞስማማ ሞተን የበለጠውን ትንሣኤ እናገኝ ዘንድ ነው፡፡
ደግሞም የጌታችን ሞት ለሁሉም ቤዛ ለመሆንና ሁሉንም ለመቤዠት እስከሆነ ድረስና በሞቱም የጥል ግድግዳን ያፈርስ ዘንድ፣ አሕዛብን ይጠራ ዘንድ እንደመሆኑ መጠን በመስቀል ላይ ባይሰቀል ኖሮ እንዴት ወደ እርሱ ይጠራን ነበር ? ሰው እጆቹ ተዘርግተው ሊሞት የሚችለው በመስቀል ላይ ብቻ ነውና፡፡ በአንድ እጁ ቀደምት ሕዝቡን (አይሁድን )፣ በሌላው እጁ ደግሞ አሕዛብን ይጠራ ዘንድ ሁለቱንም በእርሱ አንድ አድረጎ ያዋሕዳቸው ዘንድ ጌታችን እጆቹን ዘርግቶ በመስቀል ላይ ሊሞት ተገባው፡፡ በምን ዓይነት ሞት ዓለሙን እንደሚቤዥ ሲያመለክት እርሱ ራሱ ያለው እንዲህ ነውና፡ -‹‹እኔ ከምድር ከፍ ባልሁ ጊዜ ሁሉንም ወደ እኔ እስባለሁ››፡፡ እንዲሁም ጌታችን የመጣው ሰይጣንን ድል ለማድረግና ዕንቅፋትነቱን ከመንገዳችን ለማስወገድ፣ አየራትን ለማዘጋጀት ነውና፡፡ ይህስ ከምድር ከፍ ብሎ በአየር ላይ ከሚፈጸም ሞት ማለትም ከመስቀል ሞት በስተቀር በምን ዓይነት ሞት ሊፈጸም ይችል ነበር ? በአየር ላይ ሊሞት የሚችለው በመስቀል ላይ የተሰቀለ ብቻ ነውና፡፡
ሰላም ለሕማማቲከ በተጸፍዖ መልታሕት ከመ እቡስ፡፡ በተቀሥፎ ዘባን ዓዲ ወተኰርዖ ርእስ፡፡ እንዘ መላኪሆሙ አንተ እግዚአብሔር ንጉሥ፡፡ ኢያፍርሁኒ ቀታልያኒሃ ለነፍስ፡፡ እስመ ማኅተምየ ደምከ ቅዱስ፡፡
Source
__
Like this: Like Loading...
Posted in Ethiopia , Faith | Tagged: Easter , Ethiopian Orthodox Tewahedo Faith , Good Friday , Iyesus Kristos , Jesus Christ , Siklet , The Crucifixion | Leave a Comment »