መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፻፴፫]
፩ ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።
፪ ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።
ኦርቶዶክሱ ፕሬዚደንት ፑቲን ለጉብኝት እህት አገር ወደ ሆነችው ወደ ሰርቢያ አምርተዋል። በሚሊየን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች በዝነኛው የቅዱስ ሳቫ (የሰርቢያ ቅዱስ) ቤተክርስቲያን የሞቀ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
በሉሲፈራዊያኑ የቱርክ፣ የናዚዎች እና በቅርቡም የኔቶ ሠራዊት በታሪኳ ብዙ ጥቃት የደረሰባት ኦርቶዶክስ ሰርቢያ መጀመሪያ በእርሷ እርዳታ ኃያል ለመሆን የበቃችውን ዩጎዛላቪያን በታትነው አደከሟት፤ ከዚያም፡ በቅርቡ፡ የክርስትና ስልጣኔዋ ታሪካዊ ቦታ የሆነችውን ኮሶቮን ገንጥለው ወሰዱባት።
እ.አ.አ በ1999 ዓ.ም እሑድ በትንሳኤ በዓል ወቅት የአሜሪካው ፕሬዚደንት ቢል ክሊንተን ዋና ከተማዋን ቤዖግራድን በከፋ መልክ በቦምብ ማስደብደቡን አንረሳም፤ በኦርቶዶክስ ትንሳኤ ዕለት! እዚህ ያንብቡ።
ያው እንግዲህ፤ ሉሲፈራውያኑ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ጦርነቱን ኦርቶዶክስ ክርስቲያን በሆኑት ሰርቢያ፣ ማኬዶኒያ፣ አርሜኒያ፣ ጆርጂያ፣ ሩሲያ፣ ዩክሬይን ቆጵሮስ፣ ሶሪያ፣ ግብጽ እና ኢትዮጵያ ላይ በማጧጧፍ ላይ ናቸው።