እስከ 13ሺህ ይጠጋሉ፤ ከጊኒ፣ ናይጄሪያ፣ ማሊ፣ ኒጀር እና ካሜሩን ወደ አልጀሪያ የገቡ፤ አብዛኞቹም ሙስሊሞች ናቸው።
ላለፉት ጥቂት ዓመታት ከ 30ሺህ እስከ 3ሚሊየን የሚሆኑ ጥቁር አፍሪቃውያንን የበረሃ አሸዋ በልቷቸው ሕይወታቸው አልፋለች።
ያለ ምግብና ውኃ ምድረ በዳ ላይ ተጣሉ፤ እንደምን ተጣሉ? ልበል፤ እንስሳ እንኳን እንዲህ አይጣልም፤ አዎ! እንደ ቆሻሻ ተጣሉ፤ 99% የሚሆኑት ሙስሊም ወገኖቻቸው ናቸው። ይህን የአረብ ሙስሊም አልጀሪያን ጭካኔ የተሞላበት ተግባር አውሮፓውያን ሙሉ በሙሉ ደግፈውታል፤ አንድም የሚያዝን ነዋሪ ድርጊቱን ሲያወግዝ አልሰማሁም፣ አላነበብኩም። እንዲያውም አልጀሪያ ለዚህ እርምጃ መሸለም አለባት ይላሉ፤ እነዚህ “ጥቁር አውሬዎች” አውሮፓ እንዳይገቡ ይፈልጋሉና። አሁን ተረዳን ለምን አንጌል “ኤሊዛቤል” ሜርከል ተጣድፋ በሚሊየን የሚቆጠሩትን በጥባጭ አረቦችንና አፍጋኖችን ወደ አውሮፕ እንዲጎርፉ ያደረገችው? አዎ! የአፍሪቃ ተራ ሲደርስ አሁን ጀልባው ሞልቷል!