Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Resurrection’

Happy Pascha! The Orthodox Easter Holy Fire From Jerusalem to The World

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2023

❖❖❖ ብሩክ ፋሲካ! የኦርቶዶክስ ፋሲካ ቅዱስ እሳት ከኢየሩሳሌም ወደ ዓለም ❖❖❖

በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም በቀራንዮ ጎልጎታ የጌታ መካነ መቃብር በሚገኝበት ቅዱስ ቤተክርስትያን ውስጥ እያንዳንዱ የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚት በዛሬው የሥዑር / ቅዱስ ቅዳሜ ዕለት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በኢየሱስ መቃብር ዙሪያ በተዓምር የሚወርደውን“ነበልባል” ለመመልከት ይሰበሰባሉ፡፡

የእግዚአብሔር እጅግ አስደናቂ ከሆኑት ተዓምራት ውስጥ አንዱ ይህ በቀዳሚት ሥዑር በኢየሩሳሌም በጌታችን መካነ መቃብር ላይ የሚወርደው የተባረከ/ቅዱስ እሳት ነው።

የምስራቅ ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች ይህ የትንሳኤ ጉልህ ምልክት ነው ብለው ያምናሉ።

ይህ ዋና ከሆኑት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ተዓምራት መካከል አንዱ ነው። ይህ ተዓምር ላለፉት ፲፻፪፻/1,200 ዓመታት በየዓመቱ እየተከሰተ እንደሆነ ይታመናል።

ሥነ ሥርዓቱ የሚጀምረው በግሪክ ኦርቶዶክስ ፓትርያርክ (ወይም በሌላ የኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስ) በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ወደ ክርስቶስ ባዶ መካነ መቃብር ወርዶ ልዩ ጸሎቶችን በማንበብ ነው። ኦርቶዶክስ ያልሆነ ክርስቲያን ደግሞ ፓትርያርኩ ሻማዎቹን ለማብራት የሚጠቀሙባቸው የነዳጅ ዘይት መብራቶች በውስጣቸው እንዳይቃጠሉ ለማድረግ መቃብር (አነስተኛ መቃብር ዙሪያ ያለውን ትንሽ መዋቅር) እንደሚመረምሩ ተገልጻል ፡፡

ከመቃብሩ በላይ እና በዙሪያው በተከበበች ቤተክርስቲያን ውስጥ ፣ ምዕመናን በአንድ ድምፅ “ኪራላይሶን”(እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ!)ያሰማሉ፡፡ ቆይታው ረጅም ወይም አጭር ሊሆን ይችላል ግን ውሎ አድሮ ፓትርያርኩ ለብቻቸው በሚጸልዩበት መቃብር ላይ እንደሚታዩ ይነገራል ፡፡ ከዛም ፓትርያርኩ ከዚህ ተዓምራዊ ነበልባል ሻማዎቹን በማቀጣጠል ደወሎችን እየደወሉ በምዕመናኑ መካከል ተገኝተው እሳቱን ወደ ሌሎች ቀሳውስት ያስተላልፋሉ፡፡ በዚህ ወቅት ጨለማ የነበረው የቤተ ክርስቲያን ሕንፃ በተዓምራዊው የተባረክ/ ቅዱስ እሳት ያበራል፡፡

ለመጀመሪያዎቹ በርካታ ደቂቃዎች እሳቱ ይቀጣጠላል ነገር ግን አይባላም ፡፡ በዚህን ጊዜ ፣ ብዙ ምዕመናን ፊታቸውን እና እጆቻቸውን ሳይቃጠሉና ምንም ጉዳት ሳይደርስባቸው በእሳቱ ነበልባል ውስጥ ይታጠባሉ፡፡ እሳቱ ከሻማ ወደ ሻማ ከተላለፈ በኋላ በሩቅ በሰፊው እንዲሰራጭ በመብራት ሳጥን ውስጥ ይቀመጣል፡፡

🔥 Holy Fire 🔥

🔥 Thousands of Christians throng Jerusalem for the traditional Holy Fire rite ahead of the Orthodox Easter, despite a security clampdown in the holy city.

❖ Every Orthodox Holy Saturday in Jerusalem’s Church of the Holy Sepulcher, thousands gather to witness a flame “miraculously” appearing in the tomb of Jesus.

Orthodox Christians believe it’s a potent symbol of the resurrection.

It’s the Church’s most important miracle. And it’s believed to have been happening annually for the past 1,200 years.

The ritual begins with the Greek Orthodox Patriarch of Jerusalem (or another Orthodox archbishop), descending into the empty tomb of Christ within the church and reciting special prayers. A non-Orthodox Christian is also said to examine the edicule (a small structure surrounding the tomb) to make sure no oil lamps have been left burning inside that the patriarch could use to light his candles.

In the crowded church above the tomb and surrounding the edicule, the faithful chant with one voice “Kyrie eleison” (Lord, have mercy). The wait might be long or short but eventually a light is said to appear in the tomb where the patriarch has been praying alone. He then lights his candles from this miraculous flame and, accompanied by the pealing of bells, emerges to spread the fire among the crowd. The oncedark church becomes illuminated by the miraculous Holy Fire.

It is said that for the first several minutes the fire burns, but does not consume. During this time, many of the faithful bathe their faces and hands in the flame, apparently without being harmed. The flame is passed from candle to candle and then placed in lanterns so that it can be spread far and wide.

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የሞት ኃይልን ሰብሮ ተነስቷል የትንሣኤው ጌታ | ሲኦል ተሻረልን ጌታችን ተነስቷል

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 16, 2023

❖❖❖[፩ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች ምዕራፍ ፬፥፲፬]❖❖❖

“ኢየሱስ እንደ ሞተና እንደ ተነሣ ካመንን፥ እንዲሁም በኢየሱስ ያንቀላፉቱን እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ያመጣቸዋልና።”

✞✞✞

ተነስቷል

ወተንሥአ እንበል ………..

ትንሣኤው ልዩ ነው ………..

የመከራ ቀንበር ከእኛ አርቆልናል

✞✞✞እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው አደረሰን!✞✞✞

ጽዮናውያን ለሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጎ ዘመን እየመጣ ነው።

______________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Happy Easter

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 30, 2016

Easter1

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | 2 Comments »

ድል የተቀዳጀንበት እለት ነው – ትንሣኤ ነው / ፋሲካ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 11, 2015

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትከሚለው የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ መጽሐፍ የተወሰደ

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ የተነሣበትን የመታሰቢያ ዕለት እኛ ኢትዮጵያውያን በጥልቅ መንፈሳዊ የደስታ ስሜት እናከብራታለን። ይህም ያለምክንያት አይደለም፡ ይህችው ዕለት ፈጣሪ ሰው ኾኖ ወደዚህ ዓለም የመጣበትን ዓላማ ከግብ አድርሶ የፈጸመባት፡ ማለትም የሰው ልጆችን የዘር ጠላቶች ደምስሶ ለእኛ ዘለዓለማዊ ድልን ማለትም የሰው ልጆችን የዘር ጠላቶች ደምስሶ ለእኛ ዘለዓለማዊ ድልን ያቀዳጀባት፡ ይኽውም ከዲያብሎስ የአገዛዝ ባርነት አውጥቶ በእግዚአብሔር ነጻ ልጅነት የኃጢአትን ቀንበር አስወግዶ ለንስሓ ጽድቅ የሞትን ፍዳ አጥፍቶ ለዘለዓለም ሕይወት ጸጋ እንድንበቃ ያደረገባት ቀን በመኾኗ ነው።

ፋሲካእየተባለ የሚጠራው የትንሣኤ በዓል በአገራችን በኢትዮጵያና በእኛ በኢትዮጵያውያን ዘንድ፡ ከሌሎቹ በዓላት ይልቅ እጅግ ጥልቅ በኾነ፡ የተለየ ሃይማኖታዊ ስሜትና ታሪካዊ ይዘት ይከበራል፤ አከባበሩም ከዘመነ ኦሪት ጀምሮ በሁለት በተያያዘ ደረጃና መልክ ሲካሄድ ኖርዋል፡ ይኽውም፦

፩ኛ. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንቱኑ ለአዳምና ሔዋን በሰጠው የተስፋ ቃሉ፡ ወደዚህ ዓለም መጥቶ በአዲሱ ኪዳነ ምሕረት እውነተኛው የፋሲካ በግ በመሆን በመስቀል ላይ ከመሠዋቱ በፊት ለዚያ ለመጨረሻውና ለዘለዓለማዊው የሰው ልጆች ደኅንነት መሰጋገሪያና ጥላ የሆነ የይቅርታ ቸርነቱን በኪዳነ ኦሪቱ ቀደም አድርጎ ለእሥራኤል ልጆች በሠራው የፋሲካ ሥርዓት ሊሰጥ መቆየቱ ነው።

ያም ሥርዓት እግዚአብሔር አምላክ የእሥራኤልን ሕዝብ ከፈርዖን የባርነት አገዛዝ ነጻ ያወጣቸው ዘንድ ሙሴን ከኢትዮጵያ ወደግብፅ በላከው ጊዜ በአንዲት አስደንጋጭ ሌሊት ከደረሰው ታላቅ መቅሠፍት የተገኘ ንበር፡ አዎን! ጣዖት አምላኪው ፈርዖን እሥራኤላውያኑን ነፃ ይለቅቃቸው ዘንድ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በአገሩ ላይ የተለያየ መዓትን አከታትሎ ቢያወርድበትም እምቢተኛ ልቦናውን ይበልጥ በማደንደን መለኮታዊውን ትእዛዝ ተቀብሎ ለመፈጸም ፈቃደኛ አልሆነም።

ካለመፍቀዱም የተነሳ፡ በመጨረሻ፡ በየቤተሰቡ የተወለዱትን ከሰው እስከ እንስሳ ድረስ ያሉትን የግብፃውያንን የበኵር (የመጀመሪያ) ልጆች ሁሉ የሚቀሥፍ መልአከ ሞት መጥቶ የፈርዖን ዐልጋ ወራሽ በሆነው በኵር ላይ ሳይቀር የግድያ ግዳጁን ከፈጸመበት መቅሠፍት የተገኘው ሥርዓት ነው።

በዚያን ጊዜ ግን የእሥራኤል የበኵር ልጆች ከዚያ የሞት መቅሠፍ የሚድኑበትን መንገድ እግዚአብሔር አዘጋጅቶ ነበር፡ ይኸውም ቀሣፊው መልአከ ሞት በእያንዳንዱ የእሥራኤል ቤተሰብ ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት ሳያደርስ የደም ምልክትን ብቻ እያየ በሰላም ያልፍ ዘንድ ለዚያ ቤተሰብ ቤዛ የሚሆን የመሥዋዕት በግ በዚያ ቤተሰብ ታርዶ የዚያ በግ ደም በዚያው ቤተሰብ የመኖሪያ ቤት በር ሁለት መቃኖችና ጉበን ላይ ለምልክትነት እየተረጨ እንዲቀባ የዚያም ቤተሰብ አባሎች የዚያን በግ አጥንቱን ሳይሰብሩ፡ ሥጋውን ብቻ እየጠበሱ በዚያው ሌሊት ጨርሰው እንዲበሉት እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት ለእሥራኤል ልጆች የሰጣቸና እነርሱም ተቀብለው የፈጸሙት ትእዛዝ ነው።

በዚያች ሌሊት በግብፃውያን ላይ ታላቅ ድንጋጤንና ፍርሃትን ያስከተለው የቁጣው መቅሠፍት በእሥራኤላውያን ላይ ግን ታላቅ ደስታንና ሓሢትን ያወረደው ያ የእግዚአብሔር የማዳኑና የማጥፋቱ፡ የምሕረቱና የመዓቱ ኃይል፡ ፋሲካተብሎ በእግዚአብሔር ሕዝብ ዘንድ በየዓመቱ ሲታሰብና ሲከበር የሚኖር የዘለዓለም ሥርዓት ሆነ።

፪ኛ. ይህ የፋሲካ ሥርዓት፡ በኪዳነ ኦሪቱ መሠረት እንዲህ በየዓመቱ ሲፈጸም ከኖረ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የፋሲካው በግ በሚታረድባት በዚችው የፋሲካ ሌሊት በመስቀል ላይ ራቁቱን ተሰቅሎ፡ ደሙን በማፍሰስ እውነተኛውና ዘለዓለማዊው ፋሲካ በግ ሆኖ ለአንደኛውና ለመጨረሻው ጊዜ መሠዋቱ ነው።

ስለፋሲካው በግ ሥርዓት፡ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ልጆች በሰጠው መመሪያ ውስጥ አጥንቱን አትስበሩ!” ያለው የመለኮት የትንቢት ቃል በዓለም መድኃኒትነቱ፡ ራሱን የመጨረሻው የፋሲካ በግ አድርጎ ለሠዋው ለኢየሱስ ክርስቶስ የተነገረ መሆኑ በወንጌላዊው ዮሓንስ ተጽፎ ይበነበባል፡ ይኽውም ጌታ የሚወድደውና ከሓዋርያት አንዱ የሆነው ይህ ዮሓንስ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር ከጌታ መስቀል አጠገብ ቆሞ በዓይኖቹ ባየው የመሰከረው ነው። አዎን! ከጌታ መስቀል በቀኙና በግራው አብረው የተሰቀሉት ወንበዴዎች ስላልሞቱ ከመምሸቱ በፊት ከተሰቀሉበት ሊያወርዷቸው በዚያ የነበሩት ወታደሮች የሁለቱንም ወንጀለኞች ጭንና ጭናቸውን ሰበሩዋቸው፡ ጌታ ግን ቀደም ብሎ ነፍሱ በሰዓቷ ከሥጋው ሰለተለየች መሞቱን ለማወቅ ከወታደሮቹ አንዱ፡ ለንጊኖስየሚባለው ቀኝ ጎኑን በጦር ከመውጋቱ በቀር ከአጥንቱ አንዱንም ላለመስበራቸው ይኽው ዮሓንስ በዚያ የዓይን ምስክርነቱ በጻፈው የምሥራች ዜናው አረጋግጦታል።

የምስክርነት ቃሉም እንዲ የሚል ነው፦

አይሁድ ግን መሽቷልና የዚች ሰንበት ቀንም ታላቅ ናትና እነዚህ አስከሬኖች ስለሰንበት በየተሰቀሉበት አይደሩ! አሉ፡ ጭን ጭናቸውንም ሰብረው ያወርዷቸው ዘንድ ጲላጦስን ለመኑት። ወታደሮችም መጥተው አብረውት ተሰቅለው የነበሩትን የመጀመሪያውን ወንበዴ ጭን የሁለተኛውንም ሰበሩ። ወደ ጌታችን ኢየሱስም ሄደው ፈጽሞ እንደሞተ ባዩት ጊዜ ጭኑን አልሰበሩም። ነገር ግን ከወታደሮች አንዱ የቀኝ ጎኑን በጦር ወጋው፡ ያን ጊዜም ከእርሱ ደመና ውኃ ወጣ። ያየውም መሰከረ ምስክርነቱም እውነት ነው፡ እናንተም ታምኑ ዘንድ እርሱ እውነትን እንደሚናገር ያውቃል። ይህ ሁሉ የሆነው ከእርሱ አጥንቱን አትስበሩ ያለው የመጽሓፍ ቃል ይደርስ ይፈጸም ዘንድ ነው።

ያ የበጉ ደም የእሥራኤልን የበኵር ልጆች ከመቀሠፍና ከሥጋ ሞት እንዳዳነ ይህም ነዋ በግዑ ለእግዚአብሔር ዘየአትት ኃጥኣተ ዓለም፡ማለትም የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድ እነሆ የእግዚአብሔር በግየተባለው ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሠውቶ ባፈሰሰው ደሙ፡ እኛን ከኃጢአትና ከዘለዓለም ሞት አዳነን። እኒያ የእሥራኤል ሕዝብ በዚያን ጊዜ የታረደውን በግ፡ ደሙን በቤታቸው ውስጥ በልተው ከሰውነታቸው ጋር በማዋሓድ የዚያ ቀሣፊ መልአክ ሠይፍ በልተው ከሰውነታቸው ጋር በማዋሓድ የዚያ ቀሣፊ መልአክ ሠይፍ ካስከተለው ሞት እንደዳኑ ሁሉ እኛም ዛሬ የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውን በልተንና ክቡር ደሙን ጠጥተን ለኃጢአታችን የዘለዓለም ስርየትን ለሰውነታችንም የዘለዓለም ሕይወትን እናገኛለን።

ይህን የፋሲካውን ሥርዓት እንዲህ እንደኪዳን ኦሪቱ በየቤታችን እንደ ኪዳነ ምሕረቱ ደግሞ በቤተ ክርስቲያናችን የምንፈጽም እኛ ኢትዮጵያውያን ብቻ ነን። ይህም ማለት በዚህ የትንሣኤ በዓላችን ለአዲስ ኪዳኑ ፋሲካችን መሥዋዕት ሆኖ ቀርቦ እንድንበላውና እንድንጠጣው የታዘዝነው፡ ለሥጋ ምግብነት በየቤታችን የታረደውን ፍሪዳና የተጠመቀውን መጠጥ ሳይሆን ለሁለንተናችን የሕይወት ምግብ ይኾነን ዘንድ፡ ከሰማይ የወረደውንና ከምድር የተገኘውን እውነተኛውና ዘለዓለማዊው የፋሲካ በጋችን የሆነውን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም መሆኑን አውቀን በየዓመቱ በምትመጣው የትንሣኤ ሌሊት የዚሁ አምላካዊ ጸጋና በረከት ተካፋዮች በመሆን በፍጹም ሥጋዊ ደስታና መንፈሳዊ ሓሴት ልናከብራት ይገባል።

ብሩክ ፋሲካ!

___

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Fasika (Easter) In Ethiopia

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 12, 2012

GOOD FRIDAY

Church of St Mary of Zion , Axum – photo by M.Torres, via Travel-Images.com

The solemn liturgical service of Good Friday is attended by thousands of believers. There is a sense of sorrow and desolation. All the symbols, images and instruments used in the passion of the Saviour are publicly exhibited in the church.

Men and women go to church to prostrate themselves, remaining there from early morning till 3 p.m. the hour of the death of Jesus Christ. Believers confess their greater and lesser offenses to the confessor or sit reading their Psalter. It is believed that on

Good Friday blood fell from Christ on the cross and dripped into the grave of Adam beneath and there rose up from the dead about 500 people; the thief on the left was sent into darkness but the one on the right went before Adam into Paradise.

On this Friday the Devil was bound with cords and Christ descending to purgatory (seol) sent forth to paradise all the souls that were in darkness (Seol). Good Friday is a special day for confession.

Why The Good Thief Was Pardoned

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: