Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Questions’

ሕማማተ እግዚእ †ዕለተ ሰሉስ/ማክሰኞ | ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 27, 2021

👉 ገብርኤል 👉 ማርያም 👉 ኡራኤል 👉 ጊዮርጊስ 👉 ተክለ ሐይማኖት 👉 ዮሴፍ 👉 መድኃኔ ዓለም

✞✞✞ ሰሙነ ሕማማት ዕለተ ማክሰኞ (ዘሰሉስ)✞✞✞

የጥያቄና የትምህርት ቀን❖

በዚህ ዕለት ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱሱ ክርስቶስ ስለ ሥልጣኑ ተጠይቋል፡፡ ጠያቂዎቹ የካህናት አለቆችና የሕዝብ አለቆች ናቸው፡፡ ጥያቄውም “በማን ሥልጣን እነዚህን ታደርጋለህ? ይህንስ ሥልጣን የሰጠህ ማነው?” የሚል ነበር፡፡ የካህናት አለቆች ያቀረቡት ጥያቄ ነበር፡፡ ጌታችን ሰኞ ዕለት ሁለት ነገሮችን ማድረጉን ተያይዞ የተነሣ ጥያቄ ነው፡፡ ሰኞ ከቅጠል ብቻ በቀር ፍሬ ያላገኘባትን ዕፀ በለስ ረግሟል፤ በማስከተል ወደ ቤተ መቅደስ ገብቶ የሚሸጡትንና የሚለውጡትን አስወጥቷል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፫፡፳፭ ፤ ማር.፲፩፥፳፯ ፣ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡ ከላይ እንደ ተገለጸው ጌታችን ሲያደርጋቸው የነበሩት ተአምራትና የኃይል ሥራዎች የካህናት አለቆችን ስላስቀናቸው ጌታችንን ከሮማ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ጋር ለማጋጨት የቀየሱት ስልት ነው፡፡

ጌታችን በቤተ መቅደስ የነበሩትን ነጋዴዎችን አባሯል፤ መደባቸውን ገለባብጧል፡፡ ነጋዴን ማባረርና መደብን ማስለቀቅ መንግሥታዊ ሥራ ነው፡፡ በአንድ አገር የንግድ ቦታን የሚያጸድቅ መንግሥት መሆኑ እሙን ነው፡፡ ጌታችን ፈሪሳውያን ላቀረቡት ጥያቄ ቀጥተኛ መልስ አልመለሰም፡፡ ምክንያቱም ጥያቄው ለከሳሾቹ አመቺ ሁኔታን ስለሚፈጥር ጥያቄውን በጥያቄ መልሷል፡፡ “በመባሕተ መኑ ትገብር ዘንተ፤ በማን ሥልጣን ነው ይህን የምታደርገው?” ነበር ያሉት፡፡ በራሴ ሥልጣን ቢላቸው ፀረ መንግሥት አቋም አለው በማለት ከሮማ መንግሥት ዘንድ ለማሳጣት ነበር ዕቅዳቸው፡፡

ጌታችን እኩይ የሆነውን የፈሪሳውያንን አሳብ በመረዳት “የዮሐንስ ጥምቀት ከየት ነው ከሰማይ ነው ወይስ ከምድር ሲል” ጠይቋቸዋል፡፡ ከሰማይ ያልነው እንደ ሆነ ለምን አላመናችሁበትም ይለናል÷ ከሰው ያልነው ከሆነ ሕዝቡ ይጣላናል፡፡ ምክንያቱም ሕዝቡ ዮሐንስን እንደ አባት ይፈሩት እንደ መምህር ያከብሩት ነበርና ከዚህ የተነሣ ያቀረቡት የፈተና ጥያቄ ግቡን ሳይመታ ከሽፎባቸዋል፡፡ [ማቴ.፳፩፥፳፭]፤ [ማር.፲፩፥፳፯፡፴ ፤ ሉቃ.፳፥፩፡፰]፡፡

ዛሬም ቢሆን መልካም ሥራን በሠራን ጊዜ ከልዩ ልዩ ወገኖች የሚመጡ ፈተናዎች ለመልካም ሥራችን እንቅፋት ሊሆን እንደሚችሉ መገንዘብ አለብን፡፡ ብዙ ወገኖች ለቅን አሳባችን ለምን ሰዎች ክፉ ነገር ይመልሱልናል በማለት ሲጠይቁ ይሰማል፡፡ ለቅን ዐሳባችን ከዓለም ዘንድ የተገላቢጦሽ ነገር እንደ ሚጠብቀን “ዓለም የሚወደው የገዛ ወገኑን ነው” የሚለውን የጌታችንን ትምህርት ልብ ይሏል፡፡ ይህ በመሆኑ በዘመናችን አሳልፈው ሊሰጡን የሚፈልጉ ሰዎች ፈታኝ ጥያቄ እንደሚያቀርቡልን ከወዲሁ ልንገነዘብ ይገባል፡

በፈተና፣ በመከራ፣ በድካምና በስቃይ ላይ ያሉትን ወገኖቻችንን ያለ ደዌና ያለ ከፋ ሕማም ለክርስቶስ ትንሣኤ ያድርሰልን ፤ ቀናተኞችና አረመኔዎች የሆኑትን እርጉም ጠላቶቻቸውን/ጠላቶቻችንን ሁሉ በቶሎ ያንበርክክልን!!! አሜን።

👉መድኅንኤል 👉ሕይውታኤል 👉አውካኤል 👉ተርቡታኤል 👉ግኤል 👉ዝኤል 👉ቡኤል

የቅዱስ ገብርኤል ድርሳን

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ከልዩ ድንጋፄና ፍርሃት እድን ዘንድ ይህን የቅዱስ ገብርኤልን ድርሳን እንዲህ እያልኩ እጸልያለሁ፤ መድኅንኤልሕያውታኤልአውካኤልተርቡታኤልግኤልዝኤልቡኤል ፤ ይህን አስማተ መለኮት እግዚአብሔር ለቅዱስ ገብርኤል የሰጠው መልአኩ ከዲያብሎስ ጋር ክርክር በጀመረ ጊዜ ድል እንዲነሣበት፤ እንዲሁም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን ለማብሠር በተላከ ጊዜ ከቃሉ ግርማ የተነሣ እንዳትደነግጥና እንዳትፈራ መጽንዔ ኃይል እንዲሆናት ነው።

አቤቱ ለእኔ ለአገልጋይህም እንደዚሁ ኃይልና ጽንዕ ሰጥተህ ከመዓልትና ከሌሊት ድንጋፄ አድነኝ፤ አሜን።

ከላይ ከሰማይ ወደ ድንግል የተላክህ ገብርኤል ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ደስታን አብሣሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ፅንሰ ቃልን አስተምረህ የምታሳምን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ሰማያዊ ነደ እሳት ዖፈ ርግብ ሆይ ሰላም እልሃለሁ። ፍጹም ደስታን ተናጋሪ መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። ከእደ ሞት የምታድን መልአክ ሆይ፤ ሰላም እልሃለሁ። የአንተን አማልላጅነት በመዓልትም በሌሊትም ተስፋ ስለምናደርግ ጥበቃህ አይለየን። በነፍስም በሥጋም ታደገን። የእግዚአብሔር ልዩ ባለሟል ነህና፤ ለዘላለሙ አሜን።

አቡነ ዘመሰማያት።

__________________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: