Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Qedus Gebriel’

የታኀሣሥ ገብርኤል — Tahisas Gebriel

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 28, 2013

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነትከሚለው ፡ የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ መጽሓፍ የተወሰደ

ከከበረ ሰላምታ ጋር!

BisrateGabriel6

በዚህ በታኀሣሥ ወር በ፲፱ነኛው ቀን የሚውለው የ ታኀሣሥ ገብርኤልበዓል የሚከበርበት ምክንያት እንዲህ ነው፦

እግዚአብሔር በሙሴ መሪነት የእሥራኤልን ሕዝብ በግብፅ አገር ይገኙበት ከነበረው የባርነት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ቤተ መቅደሳቸውንና ከተማቸውን በኢየሩሳሌም አድርገው በምድረ ከነዓን እንዲኖሩ አበቃቸው። እነርሱ ግን ባካባቢያቸው ያሉትን አሕዛብ እየተከተሉ አምልኮ ባዕድን በመፈጸም አምላካቸውን እግዚአብሔርን አሳዘኑት። በነቢያቱ ቢመክራቸውና ቢገሥፃቸውም በዚያ ኃጢአታቸው እየጨመሩበት ከመኼድ በቀር ከበደላቸው ተጸጽተው ሊመለሱ ጨርሶ የማይቻል ኾነ።

በዚህ መልክ በፈጣሪያቸውና ከእርሱ ጋር በተጋቡት ቃል ኪዳናቸው ላይ በሥውርና በገሃድ ያካኺዱት የነበረው ክህደት ዓመፅና አመንዝራነት በመጨረሻ ጽዋው ስለሞላ እግዚአብሔር ለዚህ ድርጊታቸው ምስክር የኾነችው ታቦተ ጽዮን ከእሥራኤላዊው ንጉሥ ከሰሎሞንና ከኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ከማክዳ በተወለደው በቀዳማዊ ምኒልክ አማካይነት በቅድሚያ ወደ ኢትዮጵያ እንድትሄድ አደረገ። ከዚያ በኋላም ያወረሳቸውን አገርና ከተማ ወርሮ ይበዘብዝ ዘንድ አረማዊውን ንጉሥ፡ ናቡከደነፆርን ታላቅ የሠይፍ ኃይልን አስታጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፡ እርሱም በዚያ የቅጣት ተልእኮውን እንዲፈጽም፡ ኃጢአተኛውንም የእሥራኤል ትውልድ ፈጅቶ የተረፉትን በምርኮ ወደ ምድሩ ወደ ባቢሎን እንዲወስዳቸው ለስደትም እንዲዳርጋቸው አሠለጠነው።

ለዚያ ስደት ከተዳረጉት እሥራኤላውያን መካከል በሃይማኖታቸው የጸኑና በምግባራቸው የተጠናከሩ አካኼዳቸው ከነቢዩ ዳንኤል ጋር የሆነ፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል የተባሉ መንፈሳውያን ወጣቶች ነበሩ። እነዚህ ሠለስቱ ደቂቅየተባሉት ሦስት ልጆች፡ በእውቀታቸውና በብልህነታቸው ተመርጠው የንጉሡ ሹማምንት ሆነው ያገለግሉ ነበር።

የኋላ ኋል ግን የአገሩን አማልክት እንዲያመልኩ ንጉሡ ላቆመውም ጣዖት እንዲያሰግዱ ያን ባያደርጉም በአዋጅና ባደባባይ እየነደደ ባለ አስፈሪ የእሳት ነበልባል ውስጥ የሚጣሉ መሆናቸውን የሚገልጽ የፈተና ጥያቄ ከንጉሡ ቀረበላቸው። እነርሱም ለገንዘብና ለሹመት ጓጉተው የንጉሡን ቍጣም ፈርተው አምላካቸውን የማይክዱ ሃይማኖታቸውንም የማይለውጡ መሆናቸውን በመግለጽ፡ ንጉሥ ሆይ! የምናመልከው አምላካችን ከእጅህም ሆነ፡ ከዚህ ከሚነድደው የእሳት ነበልባል ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳ አማልክትህን እንዳናበልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ጣዖት እንዳንሰግድለት እወቅ!” ሲሉ በድፍረትና በቆራጥነት መልስ ሰጡት።

በዚህ ጊዜ ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ከንጉሡ ታዝዞ ሦስቱም ገድለኞች በሚነድደው እሳት ውስጥ ተጣሉ። ወደ እሳቱ ሊጥሏቸው የወሰዷቸው ኃያላንም በነበልባሉ ብርቱ ወላፈን እየተቃጠሉ ሞቱ።

BisrateGabriel13

Additional pictures of Bisrate Gebriel Orthodox Tewahedo Church

ወደ እሳቱ ውስጥ ታሠረው የተጣሉ እኒህ መንፈሳውያን አርበኞች ግን የእግዚአብሔር መልአክ እሳቱን አቀዝቅዞላቸው በነበልባሉ መካከል ወዲያ ወዲህ ሲመላለሱ ከመታየት በቀር በአካላቸው ቀርቶ በልብሳቸው ላይ እንኳ አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከተፈረደባቸው የቃጠሉ ሞት ድነው በደህና ሊወጡ ችለዋል፡ ይህንም የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከነፆር ተደነቀ፡ ፈጥኖም ተነሳ፡ አማካሪዎቹንም ሦስት ሰዎችን አሥረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን? …እነሆ፡ እኔ፡ የተፈቱ፡ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎችን አያለሁ ምንም አላቆስላቸውም፡ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል። ብሎ መለሰ።የሚለው የመጽሓፍ ቃል ያረጋግጣል።

የአራተኛው መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡የተባለው ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መሆኑን ከትውፊታችን አግኝተነዋል።

በሃይማኖት ሳይወላውሉ በምግባር ተጠናክረው እስከመጨረሻው ማለትም የሞት ጽዋን ለመቀበል ተዘጋጅቶና ቆርጦ እስከመቅረብ ድረስ በጀመሩት ገድል ጸንቶ መገኘት የሚያስከትለው ውጤትና የሚያስገኘው ፍሬ በነፍስ ብቻ ሳይሆን የሥጋ ሞትን ችምር በማስቀረት የምሕረት ሕይወትን በክፋት ኃይላትም ላይ ድልን የሚያቀዳጅ የመላእክት ተራዳኢነትን መሆኑን በዚሁ በታኀሳስ ፲፱ ቀን የምናከብረው የ ታኀሣሥ ገብርኤልበዓል ያስታውሰናል፡ ያስተምረናልም።

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

የቅ/ገብርኤል ጽላት በሌቦች ላይ ፈረደ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 29, 2011

 

በየዘመናቱ ሁሉ የተለያዩ ተአምራትን አይተናል ዛሬም በመታይት ላይ የሚገኙ በቀላሉ የሚገመቱ አይደሉም።

እግዚአብሔርም አምላክ ወደዚህ ዓለም ሲያመጣንና በዚህ ዓለም ሲያኖረን መልካም ሥራ እየሠራን እንኖር ዘንድ ሕግ ሠርቶልናል በዚሁ ሕግ መሠረት ቃሉን አክብረን ከተገኘን ደስ የሚያሰኝ ተአምር እናያለን። ይህም የሚያቋርጥ ችግር ሊሆን ይችላል።

የእግዚአብሔር ቃል ካልተከበረ በሰውና በሰው መካከል ንትርክ መቅሠፍት የሚያሳቅቅ በጎርፍ በምድር መንቀጥቀጥ የሚታየው አደጋ ሁሉ የጎላ ይሆናል ቃሉን አክብረን የምንመራ ስንሆን ደግሞ የምንመለከተው ሁሉ የሚያስደስትና የማያቋርጥ የእግዚአብሔርን በረከት በደስታ መሳተፍ ይሆናል።

በእግዚአብሔር ሕግ እየተመራን ያልደከምንበትን የሰው ንብረት ይልቁንም የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆኑ በምርምር የማይደረስባቸውን ብንሰርቅ በሕይወታችን ላይ አደጋ ያስከትላል ለትውልድም እንቅፋቱ ይተላለፋል።

በከፋ ሀ/ስብከት በጊሚራ ወረዳ የጉራ ፈርዳ ቅ/ገብርኤልን ጽላት የሠረቀው ግለሰብ ግንባሩ ከጉልበቱ ጋር ተጣብቋል ከዚህም ቀንደኛ ሌባ ተባባሪ የነበሩ ሰዎች ማለቃቸው ታውቋል። የቅ/ገብርኤል ፅላት ይህንን ተአምር የፈፀመው በ1989 /ም በኅዳር ወር እንደነበር የከፋ ሀ/ስብከት አስታውቆ ነበር።

የጉራ ፈርዳ ቅ/ገብርኤል ፅላት በተአምር ሠሪነቱ በሀ/ስብከቱ ውስጥ በጣም የታወቀና ለመናፍቃንም ሁልጊዜ አስደንጋጭ የሆነ ፅላት ነው።

የታኅሣሥ ገብርኤል

ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዊነት” ከሚለው የንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ፡ ኹለተኛ መጽሐፍ የተወሰደ።

ከታላቅ አክብሮትና ምስጋና ጋር።

በዚሁ በታኅሣሥ ወር፡ በ፲፱ነኛው ቀን የሚውለው የ ”ታኅሣሥ ገብርኤል” በዓል የሚከበርበት ምክንያት እንዲህ ነው፦

እግዚአብሔር በሙሴ መሪነት የእሥራኤልን ሕዝብ፡ በግብፅ አገር ይገኝበት ከነበረው የባርነት አገዛዝ ነጻ አውጥቶ ቤተ መቅደሳቸውንና ከተማቸውን በኢየሩሳሌም አድርገው በምድረ ከነዓን እንዲኖሩ አበቃቸው። እነርሱ ግን፡ ባካባቢያቸው ያሉትን አሕዛብ እየተከተሉ፡ አምልኮ ባዕድን በመፈጸም፡ አምላካቸውን እግዚአብሔርን አሳዘኑት። በነቢያቱ ቢመክራቸውና ቢገሥፃቸውም በዚያ ኃጢአታቸው እየጨመሩበት ከመኼድ በቀር፡ ከበደላቸው ተጸጸተው ሊመለሱ ጨርሶ የማይቻል ኾነ።

በዚህ መልክ በፈጣሪያቸውና ከርሱ ጋር በተጋቡት ቃል ኪዳናቸው ላይ በሥውርና በገሃድ ያካኺዱት የነበረው ክህደት፡ ዓመፅና አመንዛሪነት በመጨረሻ ጽዋው ስለሞላ እግዚአብሔር ለዚህ ድርጊታቸው ምስክር የሆነችው ታቦተ ጽዮን ከእሥራኤላዊው ንጉሥ ከሰሎሞንና ከኢትዮጵያዊቷ ንግሥት ከማከዳ በተወለደው በቀዳማዊ ምኒልክ አማካይነት በቅድሚያ ወደ ኢትዮጵያ እንድትሄድ አደረገ። ከዚያ በኋላም ያወረሳቸውን አገርና ከተማ ወርሮ ይበዛብዝ ዘንድ አረማዊውን ንጉሥ ናቡከደነፆርን ታላቅ የሠይፍ ኃይልን አስታጥቆ ወደ ኢየሩሳሌም ላከ፡ እርሱም በዚያ የቅጣት ተልዕኮውን እንዲፈጽም፡ ኃጢአተኛውንም የእሥራኤል ትውልድ ፈጅቶ የተረፉትን በምርኮ ወደምድሩ ወደባቢሎን እንዲወስዳቸው በስደትም እንዲዳርጋቸው አሠለጠነው።

ለዚያ ስደት ከተደረጉት እሥራኤላውያን ማካከል በሃይማኖታቸው የጸኑና በምግባራቸው የተጠናከሩ አካሄዳቸው ከነቢዩ ዳንኤል ጋር የሆነ፡ አናንያ፥ አዛርያና ሚሳኤል የተባሉ መንፈሳውያን ወጣቶች ነበሩ። እነዚህ “ሠለስቱ ደቂቅ” የተባሉት ሦስት ልጆች በእውቀታቸውና በብልህነታቸው ተመርጠው የንጉሡ ሹማምንት ሆነው ያገለግሉ ነበር።

የኋላ ኋላ ግን፡ የአገሩን አማልክት እንዲያመልኩ ንጉሡ ላቆመውም ጣዖት እንዲሰግዱ ያን ባያደርጉም በአዋጅና ባደባባይ እየነደደ ባለ አስፈሪ የእሳት ነበልባል ውስጥ የሚጣሉ መሆናቸውን የሚግልጽ የፈተና ጥያቄ ከንጉሡ ቀረበላቸው።

እነርሱም ለገንዘብና ለሹመት ጓጕተው የንጉሡን ቍጣም ፈርተው አምላካቸውን የማይክዱ ሃይማኖታቸውንም የማይለውጡ መሆናቸውን በመግለጽ “ንጉሥ ሆይ! የምናመልከው አምላካችን ከእጅህም ሆነ ከዚህ ከሚነድደው የእሳት ነበልባል ሊያድነን ይችላል፡ ባያድነንም እንኳ አማልክትህን እንድናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ጣዖት እንዳንሰግድለት እወቅ!” ሲሉ፡ በድፍረትና በቆራጥነት መልስ ሰጡት።

በዚህ ጊዜ ፍርዱ እንዲፈጸምባቸው ከንጉሡ ታዝዞ ሦስቱም ገድለኞች በሚነድደው እሳት ውስጥ ተጣሉ። ወደእሳቱ ሊጥሏቸው የወሰዷቸው ኃያላንም በነበልባሉ ብርቱ ወላፈን እየተቃጠሉ ሞቱ።

ወደ እሳቱ ውስጥ ታሥረው የተጣሉት እኒህ መንፈሳውያን አርበኞች ግን የእግዚአብሔር መልአክ እሳቱን አቀዝቅዞላቸው በነበልባሉ መካከል ወዲያ ወዲህ ሲመላለሱ ከመታየት በቀር በአካላቸው ቀርቶ በልብሳቸው ላይ እንኳ አንዳችም ጉዳት ሳይደርስባቸው ከተፈረደባቸው የቃጠሎ ሞት ድነው በደህና ሊወጡ ችለዋል። ይህንም “የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ አማካሪዎቹንም “ሦስት ሰዎችን አሥረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረም?…እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ስዎችን አያለሁ ምንም አላቈስላቸውም የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡ብሎ መለሰ።” የሚለው የመጽሐፍ ቃል ያረጋግጣል።

የአራተኛው መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል፡” የተባለው ለቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል መሆኑን ከትውፊታችን አግኝተነዋል።

በሃይማኖት ሳይወላውሉ፡ በምግባር ተጠናክረው እስከመጨረሻው ማለትም የሞት ጽዋን ለመቀበል ተዘጋጅቶና ቆርጦ እስከመቅረብ ድረስ፡ በጀመሩት ገድል ጸንቶ መገኘት የሚያስከትለው ውጤትና የሚያስገኘው ፍሬ በነፍስ ብቻ ሳይሆን የሥጋ ሞትን ጭምር በማስቀረት የምሕረት ሕይወትን በክፋት ኃይላትም ላይ ድልን የሚያቀዳጅ የመላዕክት ተራዳኢነትን መሆኑን በዚሁ በታኅሣሥ ፲፱ ቀን የምናከብረው የ ”ታኅሣሥ ገብርኤል” በዓል ያስታውሰናል፡ ያስተምረናልም።

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: