Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Orthodox Tewahedo Church’

በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤ እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 21, 2021

❖ በአክሱም ጽዮን ላይ እየተካሄደ ያለው የእነ ግራኝ ጂሃዳዊ ጥቃት ይህንን ነው የሚያሳያን፤

“ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ፥ ቀስታቸውንም ገተሩ ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፤ ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥ ቀስታቸውም ይሰበር። ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል። የኃጥአን ክንድ ትሰበራለችና፤ እግዚአብሔር ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል። የንጹሓንን መንገድ እግዚአብሔር ያውቃል፥ ርስታቸውም ለዘላለም ነው፤

በክፉ ዘመንም አያፍሩም በራብ ዘመንም ይጠግባሉ። ኅጥአን ግን ይጠፋሉ፥ የእግዚአብሔር ጠላቶች በከበሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠፋሉ።”

❖❖❖እኔስ ስለ ጽዮን ዝም አልልም! እናንተስ?❖❖❖

[መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፮፥፵]

፩ በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፤

፪ እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ይረግፋሉና።

፫ በእግዚአብሔር ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።

፬ በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።

፭ መንገድህን ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።

፮ ጽድቅህን እንደ ብርሃን። ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣል።

፯ ለእግዚአብሔር ተገዛ ተስፋም አድርገው። መንገድም በቀናችለትና ጥመትን በሚያደርግ ሰው አትቅና።

፰ ከቁጣ ራቅ መዓትንም ተው፤ እንዳትበድል አትቅና።

፱ ክፉ አድራጊዎች ይጠፋሉና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ የሚያደርጉ ግን እነርሱ ምድርን ይወርሳሉ።

፲ ገና ጥቂት፥ ኃጢአተኛም አይኖርም፤ ትፈልገዋለህ ቦታውንም አታገኝም።

፲፩ ገሮች ግን ምድርን ይወርሳሉ፥ በብዙም ሰላም ደስ ይላቸዋል።

፲፪ ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለካከተዋል፥ ጥርሱንም በእርሱ ላይ ያንገጫግጫል።

፲፫ እግዚአብሔር ይሥቅበታል፥ ቀኑ እንደሚደርስ አይቶአልና።

፲፬ ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ፥ ቀስታቸውንም ገተሩ ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፤

፲፭ ሰይፋቸው ወደ ልባቸው ይግባ፥ ቀስታቸውም ይሰበር።

፲፮ ለጻድቅ ያለው ጥቂት ከብዙ ከኃጢአተኞች ሀብት ይበልጣል።

፲፯ የኃጥአን ክንድ ትሰበራለችና፤ እግዚአብሔር ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።

፲፰ የንጹሓንን መንገድ እግዚአብሔር ያውቃል፥ ርስታቸውም ለዘላለም ነው፤

፲፱ በክፉ ዘመንም አያፍሩም በራብ ዘመንም ይጠግባሉ።

፳ ኅጥአን ግን ይጠፋሉ፥ የእግዚአብሔር ጠላቶች በከበሩና ከፍ ከፍ ባሉ ጊዜ እንደ ጢስ ይጠፋሉ።

፳፩ ኃጢአተኛ ይበደራል አይከፍልምም፤ ጻድቅ ግን ይራራል ይሰጣልም።

፳፪ እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፤ የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ።

፳፫ የሰው አካሄድ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይጸናል፥ መንገዱንም ይወድዳል።

፳፬ ቢወድቅም ለድንጋፄ አይጣልም፥ እግዚአብሔር እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።

፳፭ ጐለመስሁ አረጀሁም፤ ጻድቅ ሲጣል፥ ዘሩም እህል ሲለምን አላየሁም።

፳፮ ሁልጊዜ ይራራል ያበድርማል፥ ዘሩም በበረከት ይኖራል።

፳፯ ከክፉ ሽሽ፥ መልካምንም አድርግ፤ ለዘላለምም ትኖራለህ።

፳፰ እግዚአብሔር ፍርዱን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፤ ለዘላለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፤ የኅጥኣን ዘር ግን ይጠፋል።

፳፱ ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ፥ በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ።

፴ የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል፥ አንደበቱም ፍርድን ይናገራል።

፴፩ የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው፥ በእርምጃውም አይሰናከልም።

፴፪ ኃጢአተኛ ጻድቁን ይመለከተዋል፥ ሊገድለውም ይወድዳል።

፴፫ እግዚአብሔር ግን በእጁ አይተወውም፥ በተፋረደውም ጊዜ አያሸንፈውም።

፴፬ እግዚአብሔርን ደጅ ጥና፥ መንገዱንም ጠብቅ፥ ምድርንም ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ኃጢአተኞችም ሲጠፉ ታያለህ።

፴፭ ኃጥአን ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።

፴፮ ብመለስ ግን አጣሁት፤ ፈለግሁት ቦታውንም አላገኘሁም።

፴፯ ቅንነትን ጠብቅ፥ ጽድቅንም እይ፤ ለሰላም ሰው ቅሬታ አለውና።

፴፰ በደለኞች በአንድነት ይጠፋሉ። የኃጢአተኞች ቅሬታ ይጠፋል።

፴፱ የጻድቃን መድኃኒታቸው ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው፤ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።

፵ እግዚአብሔር ይረዳቸዋል፥ ያድናቸዋልም፥ ከኃጢአተኞችም እጅ ያወጣቸዋል፥ ያድናቸዋል፥ በእርሱ ታምነዋልና።

_____________________________

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

Timkat 2012: An Ethiopian Orthodox Celebration Of The Epiphany

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on January 19, 2012


The Feast of Timkat is the most important Christian holiday in Ethiopia. Timkat (baptism in Amharic), is the Ethiopian Orthodox celebration of the Epiphany. It celebrates the baptism of Jesus in the Jordan River by John the Baptist.

 

Continue reading…

Orthodox Christians celebrate the feast of Epiphany by jumping into freezing water

 

MELKAM TIMKET!

 ________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: