Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • March 2023
    M T W T F S S
     12345
    6789101112
    13141516171819
    20212223242526
    2728293031  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Mount Entoto’

Ethiopia: Unexpected Wonders in the Rock Churches of Lalibela and Addis Ababa

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on April 1, 2013

The last of my assumptions about Ethiopia were pleasantly swept away

Priest-in-Ashetan-Maryam-chapel-Lalibela-1790149A gold-robed deacon stood in front of a makeshift altar at the shadowy heart of the nave, clutching a staff as he led the mournful chanting.

Surrounding him was a cluster of white-shawled priests, some holding bibles and candles, others ornate crosses and icons. Around them were throngs of pilgrims, also robed in white, lost in a reverie of chanting and praying.

All I could do was sit transfixed in a darkened corner, my back against the stone wall of the ancient church carved out of the mountainside.

Not only was I in one of the most astonishing cultural sites in the world, but also in one of the most sacred places in Christendom during Easter.

It was as if I was watching proceedings from centuries past.

The Orthodox Christian pilgrims had flocked here to Lalibela from all corners of Ethiopia to take part in ceremonies like these.

The second-oldest Christian country in the world is still deeply pious and Easter is a serious business.

Followers eat a vegan diet for the 55 days leading up to the Orthodox Easter Sunday (May 5 this year), then everyone spends Easter eve at the church praying until 3am when it is announced that Christ has risen.

Continue reading…

__

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

የእንጦጦ ተአምራት – Entoto Miracles

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 24, 2012

የድንግል ማርያም ልዩ ልዩ ድንቅ ሥራዎች እና ገቢረ ተአምራት

በእንጦጦ ደብረፀሐይ ጠበል

በሀገራችን ኢትዮጵያ የቀደሙ አባቶች በፋቀደ እግዚአብሔር እየተመሩ ብዚ ገዳማትንና አብያተ ክርስቲያናትን ሲያሠሩ መኖራቸውን የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

በእግዚአብሔር ፈቃድ ከተሠሩት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ በአፄ ዳዊት ዘመነ መንግሥት የታነፀችው ጥንታዊቷና ታሪካዊቷ የእንጦጦ ርእሰ አድባራት መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ናት።

አፄ ዳዊት በ፩ ሺህ ፫፻፺፭ (1395) .. ነግሠው በዘመነ መንግሥታቸው ግማደ መስቀሉን ወደ ሀገራችን እንዲመጣ ጥረት አድርገዋል። የእመቤታችን ድንግል ማርያም ፅላት ከቡልጋ በማምጣት የእንጦጦን ከተማ መሥርተው በመጀመሪያ ጊዜ በእመቤታችን ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን እንዲተከል አድርገዋል።

ከአፄ ዳዊት በኋላ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመነ መንግሥት ገደማ መስቀሉን ካሳረፉበት ቦታዎች አንዱ በእንጦጦ ማርያም ቤተ ክርስቲያን እንደሆነ ታሪክ ጸሐፊዎች ዘግበዋል በዚሁ ቦታ ለ፫ ወራት ያህል ገደማ መስቀሉ ከተቀመጠ በኋላ የእግዚአብሔር ፈቃድ ባለመሆኑ ወደ መናገሻ ከመናገሻ ወደ ግሸን እንደተወሰደ ይነገራል።

በ፩ ሺህ ፭፻፳፩ (1521).. በተነሣው ክርስቲያንንና አብያተ ክርስቲያናትን የማጥፋት የግራኝ መሐመድ ወረራ በሀገራችን ካጠፏቸው ገዳማትና አብያተ ክርስቲያናት አንዷ አፄ ዳዊት ያሠሯት የእንጦጦ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ናት።

አፄ ምኒልክ ለመጀመሪያ ጊዜ የመናገሻ ከተማቸውን የቆረቆሩት በእንጦጦ ስለነበር ግራኝ ሌላ ስም ሰጥቷት የነበረውን የአባቶቻቸውን ከተማ የቀድሞውን ስሟን መልሰው እንጦጦ ብለው ጠሯት፡ በስደት የነበረችውን የእመቤታችን ፅላት ወደ መናገሻ ከተማቸው እንጦጦ ሰኔ ፲፱ ቀን ፩ ሺህ ፰፻፯፫ (1873).. ይዘዋት ገቡ ለእመቤታችን ቅድስት ማርያም ዕለት ወዲያውኑ መቃኛ ቤት ሠሩ በዚያ ዘመን ያሠሯት መቃኛ በአሁኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ቅጽር ግቢ በሸክላ ጉልላት አጌጣ ትገኛለች።

የአዲሱ ቤተ ክርስቲያን ሥራ ሲጀመር በዘመናቸው የነበሩት ግብፃዊው ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ በሥርዓተ ክህነት ሆነው እያጠኑ ንጉሠ ነገሥቱ አፄ ምኒልክ እና ንግሥተ እቴጌ ጣይቱ ብጡል በሥርዓተ መንግሥት ቆመው በጳጳሱ መሪነት ካህናቱ ዳዊት ውዳሴ ማርያም ወንጌል እየደገሙ በየማዘኑ አራት መቶ እግዚአታ አድርሰው ጳጳሱ አራት ድንጊያዎችን ባርከው በአራት ማዕዘን መሠረት ጣሉ ንጉሥ ምኒልክም ዘጠኝ አናፂዎች ከጎንደር አስመጥተው ሥራውን ዘወትር እየተከታተሉ አሠሩ።

ይህ በንጉሡና በንግሥቷ ከፍተኛ ክትትል የተሠራው ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶ እንዳለቀ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብዙ ተአምራት እንደተደረገ በየጊዜው ይገለፃል።

ባህታዊ ገ/መድህን እንደሚሉት እሳቸው በተለያዩ ገዳማትና በበረሃ ሲኖሩ ለሁለት ጊዜ ያህል አዲስ አበባ መጥተው ተመለሱ ከነበሩበት በረሃ ቦታ በ፲፮ መዓዘን እመቤታችን ድንግል ማርያም አሳየቻቸው የእመቤታችንን ሥራ እያደንቁ ሲጠባበቁ ወደ እንጦጦ መንበረ ፀሐይ እንዲሔዱ ፈቃዷ ስለሆነ ድኩላ እየመራቸው ከፀበሉ ቦታ ደረሱ፡ ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ ከጽ/ቤቱ ጋር ተነጋግረው ሥራ ጀመሩ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቸርነት ስለአልተለያቸው አሁን እንደሚትየው ብዙ ሕመምተኞች በእግዚአብሔር ፈቃድ በድንግል ማርያም አማላጅነትና ልመና ጤንነታቸውን እያገኙ ነው።

ከመስከረም ፩ ሺህ ፱፻፺፪ (1992).ም ወዲህ ከተለያዩ በሽታዎች የዳኑት የሚከተሉት ናቸው፦

የበሽታው ዓይነት የተፈወሱት ሰዎች

1

ከኤድስ በሽታ የዳኑ

2022

2

ከሽባነት

750

3

ከዐይነ ሥውርነት

350

4

ከአስም በሽታ

5003

5

ከስኳር በሽታ

3642

6

ከደም ብዛት

6874

7

ከነቀርሳ / ካንሰር

2561

8

ከሚጥል በሽታ

5734

9

ከታይፎይድና ከታይፈስ

2397

10

ከአጋንንት ቁራኝነትና ከስኳር ከዓይነ ጥላ

25000

11

ከአልማዝ ባለጭራ

889

12

ከኩላሊት

450

13

የሐሞት ጠጠር የወጣላቸው

26

14

አውሬ/አይጥ/ከሆዳቸው የወጣ/ከወባ

15

ከውጭ አገር መጥተው በጠበሏ የተፈወሱ

1

ከአረብ አገር

180

2

ከካናዳ

110

3

ከእንግሊዝ

68

4

ከኢጣሊያ

15

5

ከጀርመን

32

6

ከጃማይካ መጥተው ክርስትና የተነሱ

152

7

ከእስልምና ወደ ክርስትና እምነት የተመለሱ

710

የበሽታው ዓይነት የተፈወሱት ሰዎች

1

ከልምሻነት

380

2

ከሚጥል በሽታ

76

3

ከደም ብዛት

232

4

ከአስም

64

5

ከጨጓራ

55

6

ከደም ብዛት

233

7

ከአእምሮ ጭንቀት

182

8

ከትምባሆ ማጨስ

2543

ምንጭ፡ እንጦጦ ማርያም ቤ/ክርስቲያን 2004 .

________________________________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , | 1 Comment »

 
%d bloggers like this: