Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Moon’

Russian Space Agency Boss Says That ‘No Proof’ US Ever Landed on The Moon

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on May 9, 2023

🎈 የሩስያ የጠፈር ምርምር ተቋም /ኤጀንሲ ሃላፊ ድሚትሪ ራጎዚን፤ “ዩ.ኤስ አሜሪካ ጨረቃ ላይ እንዳረፈች ምንም አይነት ማረጋገጫ የለም! የዩኤስ አፖሎ 11 ተልዕኮ የውሸት ነበር እና አሜሪካዊያን ጠፈርተኞች ጨረቃ ላይ አላረፉም!” ብለዋል።

🤔 የማወቅ ጉጉት፤ “በ 60ዎቹ ዓመታት የአሜሪካ ጠፈርተኞች/ ናሳ የጌምቦይ መጫወቻ ሃይል ካለው ኮምፒዩተር ጋር ወደ ጨረቃ ለመውጣት በቅተው ነበር። በ2023 ዓ.ም ግን አሁንም ወደ ጨረቃ ለመመለስ አልቻሉም፤ ለምን ይሆን? ቴክኖሎጂውን አጥተውታልን?”

🤔 Curiosity: “In the 60s NASA went on the moon with a computer which had the power of a gameboy. In 2023 still not returned to the moon Why? They lost the technology?”

🎈 Russia’s Roscosmos space agency’s former boss Dmitry Rogozin, believes that the US Apollo 11 mission was faked and that American astronauts never landed on the Moon. He further questions why, all of a sudden, did the US stop sending manned missions to the Moon.

Russian space agency boss says that ‘no proof’ US ever landed on the Moon

Russia’s Roscosmos space agency’s former boss Dmitry Rogozin, believes that the US Apollo 11 mission was faked and that American astronauts never landed on the Moon. He further questions why, all of a sudden, did the US stop sending manned missions to the Moon.

Dmitry Rogozin, the former head of Russia’s Roscosmos space agency, has ruffled some feathers among global astronomy circles. Rogozin has voiced his scepticism on the narrative of whether the US Apollo 11 mission ever landed on the Moon in 1969, claiming that he has yet to see sufficient proof.

In a post on his Telegram channel on Sunday, Rogozin said he began his personal quest for the truth “about ten years ago” when he was still working in the Russian government, and that he became sceptical about whether the Americans had actually set foot on the Moon when he saw how exhausted Soviet cosmonauts looked upon returning from their flights, compared to how seemingly unaffected the Apollo 11 crew appeared.

Rogozin stated that at the time, he addressed requests for evidence to Roscosmos. All he got in return was a book with Soviet Cosmonaut Aleksey Leonov’s story of how he met the American astronauts and learned they had travelled to the Moon.

When he was named head of Roscosmos in 2018, the former official said that he maintained his work. However, no proof was offered to Rogozin, according to him. Instead, he was chastised by numerous anonymous academics for damaging the “sacred cooperation with NASA,” as he claimed.

The former Roscosmos boss also claimed to have “received an angry phone call from a top-ranking official” accusing him of complicated foreign ties.

Rogozin finished by remarking that despite enormous technological advances since the late 1960s, the US was able to carry off the feat but is now unable to do so.

He also claims to have discovered that Washington has “its people in [the Russian] establishment.”

The Apollo 11 mission was the first manned journey to the Moon, with Neil Armstrong and Buzz Aldrin being the first people to walk on the lunar surface.

The unmanned Soviet Luna 2 programme, which paved the way for Moon exploration, came before the trip.

President Vladimir Putin committed in April to restart Russia’s lunar programme.

______________

Posted in Ethiopia | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

የጽዮንን ተራራ በድሮኖቻቸው የደፈሩት አህዛብ ኤሚራቶች እየፈሩና እየተጨነቁ ነው

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on February 9, 2021

ሁለት ጨረቃዎች(ፕላኔቶች) በዱባይ ሰማይ? ለኤሚራቶች ድሮን መልስ ከአክሱም ትግራይ?

[የሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ፳፩]

፳፩ የዚያን ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራራዎች ይሽሹ፥ በመካከልዋም ያሉ ከእርስዋ ፈቀቅ ይበሉ፥ በገጠር ያሉም ወደ እርስዋ አይግቡ፤

፳፪ የተጻፈው ሁሉ እንዲፈጸም ይህ የበቀል ጊዜ ነውና።

፳፫ በዚያን ወራት ለእርጕዞችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው፤ ታላቅ ችግር በምድር ላይ፥ በዚህም ሕዝብ ላይ ቍጣ ይሆናልና፤

፳፬ በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉም ይማረካሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።

፳፭ በፀሐይና በጨረቃም በከዋክብትም ምልክት ይሆናል፤ በምድር ላይም አሕዛብ ከባሕሩና ከሞገዱም ድምፅ የተነሣ እያመነቱ ይጨነቃሉ፤

፳፮ ሰዎችም ከፍርሃትና በዓለም የሚመጣበትን ከመጠበቅ የተነሣ ይደክማሉ፤ የሰማያት ኃይላት ይናወጣሉና።

፳፯ በዚያን ጊዜም የሰው ልጅ በኃይልና በብዙ ክብር በደመና ሲመጣ ያዩታል።

____________________________________

Posted in Curiosity, Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

7 Heavens

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on December 14, 2009

ሰባቱ ሰማያት ፡ የመጀመሪያው ርእዮተ ዓለማትና ከዋክብት

እግዚአብሔር ከመጀመሪያይቱ ቀን አስቀድሞ በኃይሉ ቅነ ሰማያትን በጥበቡ በዘረጋ ጊዜ የሰማያትን ጠፈር ቀለም በማስተዋል በቀባና በደመደመው ጊዜ በሰማያት ክልል ውስጥ ምንም ፍጥረት አልነበረም።

እግዚአብሔር ከአሥራ ሁለቱ ሰማያት መካከል በመረጣቸውና ብሩሃን ብሩካን ሁኑ ከአላቸው ከሰባቱ ሰማያት ይልቅ በከበረው ግርማው በሚያስፈራው በሰባተኛው ሻዳያ ሰማይ ክበብና ክልል ውስጥ ላይ፡

  1. በአቃጣይነትና በነበልባል የተከበበውንና የእሳት ዓለም የሆነውን ኮሬብን
  2. የረጋና ከባድ የሆነ የአፈር ዓለምን ላሌብዱላሌብን
  3. የጠራ ፈሳሽና በረዶ ያለውን የውኃ ዓለም ናጌብን
  4. ረቂቅ ተንሳፋፊ ቀላል የሆነውን የነፋስ ዓለምን አዜብን

ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጠራቸው። እነዚህን አራቱን ታላላቅ ዓለሞች በሻዳያ ሰማይ ክልል ውስጥ አኖራቸው።

በእንዚህም ክበብና በውስጣቸው የሚንቀሳቀስና የሚሳብ ወይም የሚበርና የሚንሳፈፍ ሕይወት የአለው ፍጥረት እንዳይኖር አትሞ አፅንቷቸዋል።

የእግዚአብሔር መልእክተኞች መላእክት መናፍስት እንኳ አያልፉም በአካባቢያቸውም አይደርሱም።

እግዚአብሔር ብሩሃን ብሩካን ሁን ባላቸው በሰባቱ ሰማያት ክልል ውስጥ የከበረ ስሙን ለማሳወቅ የጥበቡን ኃይል ለመግለፅ የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪና ባለቤት የምስጋና ጌታ መሆኑን ታምኖበት እንዲመሰገን ሲል በሰባቱ ሰማያት ምሳሌ፡

  1. ሦስት ፀሐዮችን
  2. አራት ጨረቃዎችን
  3. አንድ መቶ ዓለማትን
  4. አእላፋተማእለፍታት ከዋክብትን
  5. በሰው ልጆች አንድበት በመላእክትም አፍ ሊቆጠረ የማይቻል ልዩ ልዩ የሆነን ግዙፍና ረቂቅ ፍጥረት
  6. የማይንቀሳቀስን ማእድን
  7. የሚንቀሳቀስ አየራትን

በእግዚአብሔር ቃል ፈጠራቸው። በአፉ እስትንፋስም ሁሉም እንደየወገኑ ደማዊ ነፍስ የሌለው ግን ሕይወት የሚሆን እስትንፋስ እፍ አለባቸው። ተንቀሳቀሱም፡ ገደብ የአለው መኖሪያቸውንና ምግባቸውን የሚመርጡበት የሚይስቡበትም የጸጋ አእምሮ ሰጣቸው። በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠሩበት ቀን ልደታቸው ሆነ።

እግዚአብሔር በቃሉ የፈጠራቸው የሦስቱ ፀሐዮች ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡

  1. ኦርያ
  2. ያሪስያ
  3. ቶማስያ (እኛ በምንኖርበት ኢዮር ክልል ውስጥ)

እነዚህ ፀሐዮች እግዚአብሔር ለፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ብርሃንነት ከመሆናቸው ሌላ ሙቀታቸው ለአጥንት ኃይል ብርሃናቸው ለአእምሮ ግልጽነት በመሆን የተፈጥሮን ሕይወት ያድሳሉ። እያጠነከሩም እድገትን ይሰጣሉ።

ነገር ግን እኛ ከሦስቱ ፀሐዮች መካከል ቶማስያ የተባለውን ፀሐይ ብቻ እንጂ ኦርያንና ያሪስያን አናይም። ከኢዮር ሰማይ ክልል ውጭ ናቸው።

እንደነዚሁ የአራቱ ጨረቃዎሽ ስሞች የሚከተሉት ናቸው፡

  1. ኢራአያ
  2. ናስያ
  3. አብላያ
  4. አስንያ (እኛ በምንኖርበት ኢዮር ክልል ውስጥ የሚገኘውና በሰው ልጆች የሚታየውና የሚፈተነው)

አስንያ የሚባለው ጨረቃ ከቶማስያ ፀሐይ የሚያገኘውን የብርሃን ጨረር ለዚህች ምድር ያበራል።

ነገር ግን ቶማስያ ለዚህች ምድር በምታበራበት ጊዜ ብርሃኑ ይቀንሳል። የፀሐይን ክበብ በሚያውድበት ጊዜ የሰሌዳው ገጽ ይቀንሳል ምድርም እንዲሁ የምታገኘውን ብርሃን ትቀንሳለች።

እግዚአብሔር በቃሉ ለፈጠራቸው ለሰባቱ ሰማያት ብሩሃን ብሩካን ካላቸው በኍላ መቶ ዓለማትን እስከ ሰራዊቶቻቸው አደላቸው። ለዘለዓልምም በእነርሱ ክበብ ውስጥ እንዲኖሩ አደረግ። ለዓለማትና ለከዋክብትም የራሳቸው እጣ የሆነ ክበብን አዘጋጀላቸው።

መቶ ዓለማት በእግዚአብሔር ቃል ተፈጥረው ወደ የእድል እጣቸው ወደሆነው ሰማይ እስከሚገቡ በውስጣቸው የሚንቀሳቀስ ፍጥረት አልነበረም። አንዱ ዓለም ከሌላው ዓለም በስፋትና በወርድ በዲካም እንዲበላለጡ አድርጎ ስለፈጠራቸው የተለያዩ ነበሩ።

እንዲሁ አእላፋተማእለፍታት የሆኑ ከዋክብት አንዱ ኮከብ ከሌላው ኮከብ በብርሃን በክብር በስፋትና በወርድ በቁመት በገጽና በቅርፅ ልዩ ልዩ አድርጎ ፈጠራቸው። ዓለማትም ይሁን ከዋክብት አንዱ ከሌላው ጋር እንዳይቀላቀልና እንዳይወሃድ ሲል በመካከላቸው ልዩ ልዩ የሆነ የተፈጥሮ ባህርይ እንዲኖራቸው አደረገ።

እግዚአብሔር ከአምስቱ ሰማያት ይልቅ በሰባቱ ሰማያት ዘንድ ክብሩንና ኃይሉን ቸርነቱንና ጌትነቱን ስሙንም እንዲያውቁትና እንዲያመሰግኑት ሲል ለፍጥረቱ ሁሉ ገደብ የአለው ነጻ አእምሮ ሰጣቸው ራሱንም ገልጾላቸዋል።

እኛም እድል እጣችን ከሆነችው ከዚህች ምድር ዓለም ተፈጥረናልና ሰለአለንበትና ወደፊት ወደ እጣ ክፍላችን ሰማያዊ ዓለም እስከምንሄድ ድረስ ለእግዚአብሔር በሰባቱ ሰማያት ክልልና በመቶ ዓለሞች ክበብ ሰለአለው ክብርና ኃይል ቸርነቱም ምህረቱንም በኪሩብ መልአክ እንድንጽፍ የተነገረንን እንጽፋለን። ከእኛ ጋር ሕብረትና አንድነት ይኖራቸው ዘንድ ከቃላቸው ብዛት የተነሳም መለያየት እንዳይኖር ለልጆቻችን እናስተምራለን።

በእዮር ሰማይ ክልል ውስጥ የአሉት አሥራ ሁለት ዓለሞች

ቀጣይ ነው…

ይህን ጽሑፍ እዚህ አቀርብ ዘንድ ፈቃዳቸውን የሰጡኝን፡ መሪራስ አማን በላይን ከልብ አመሰግናለሁ።



Posted in Curiosity, Ethiopia | Tagged: , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: