Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Meha Mikael’

ጥንታዊው ቅዱስ ሚካኤል መኽዓ ገዳም፤ ትግራይ

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on June 19, 2021

ከመቖለ በስተሰሜን ‘ተካ ተስፋይ’ ከምትባለዋ ከተማ አጠገብ የሚገኘው ጥንታዊው ቅዱስ ሚካኤል መኽዓ ገዳም ገዳም

ድንቅ ድንቅ ነው፤ ገና ዛሬ ማዬቴ ነው። እንደው እራሴን ደግሜ ደጋግሜ የምጠይቀው እነዚህን ትሁታን ወንድሞች እና እኅቶች ለመጨፍጨፍ እና እንዲህ የመሳሰሉትን ድንቃ ድንቅ የክርስትና፣ የኢትዮጵያ፣ የአፍሪቃ እና የዓለም ቅርሶች ለማውደም ነው “ተዋሕዶ እና ኢትዮጵያውያን ነን” የሚሉት ወገኖች በትግራይ ላይ የዘመቱት? እንግዲህ ከ አስቀያሚው ባህሪያቸውና ከብልሹው ስነ ምግባራቸው በመነሳት አህዛብ እንጅ የክርስቶስ ሕዝብ ሊሆኑ አይችሉም።

ፈተና ላይ ነንና፤ የሉሲፈር ኮከብ ያረፈበትን ባንዲራ የምትሸከሙ ወንድሞች እና እኅቶች ለትግራይ ኢትዮጵያውያን አባቶቻችን የተሰጣቸውን እና ታላቁ አፄ ዮሐንስ ያጸደቁልንን የጽዮንን ቀለማት (መገለባበጥ አለባቸው)ተመልከቱ። ትግራይን በመጨፍጨፍ ላይ ያሉት የሰይጣን ጭፍሮች በእነዚህ ቀለማት ስለሚናደዱ ገዳማቱን እና ዓብያተ ክርስቲያናቱን የጥቃት ሰለባ አድርገዋቸዋል። ለእነ ዳግማዊ ግራኝ ዕቅዳቸው፣ ፍላጎታቸውና ጂሃዳዊ ግዴታቸው እንደሆነ ስለምናውቅ ብዙም አይገርመንም ፥ የህወሓት ኢ-አማንያንስ? ዛሬም ሰይጣናዊውን “ችግር – ምላሽ – መፍትሔ / “Problem – Reaction – Solution” ‘ጥበብ’ በመጠቀም በነፍስ ቁስለኛው በትግራይ ሕዝብ ላይ የእነ አቦይ ስብሐት ነጋን የአልባኒያ ህልም እውን ለማድረግና የሉሲፈርን ባንዲራ በየግዳማቱ ካልሰቀልን ይሉ ይሆን? ወይንስ የተምቤን ዙቁሊ ሚካኤል ልጅ የሆኑትን የኢትዮጵያ ቍ. ፩ ባለውለታ የራስ አሉላ አባ ነጋን ፈለግ ተከትለው የትግራይን ሕዝብ እየጠበቀች ያለቸው ጽዮን ማርያም እንደሆነች እና ለትግራይ ኢትዮጵያውያንም እየተዋጉላቸው ያሉት ቅዱስ ሚካኤል፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ አባ ዘ-ወንጌልና ቅዱሳኑ ሁሉ እንደሆኑ በይፋ ይመሰክራሉ? የእግዚአብሔርን ስም እስካሁን አንዴም ስታነሱ አልሰማንም ወደዳችሁም ጠላችሁም ይህን አስመልክቶ ዛሬ የምትገኙበትን ማንነትና ምንነት የማሳወቅ ግዴታ አለባችሁ።

መቼስ አውሬው በማንጠብቀው መንገድ መጥቶና የመንፈስ ማንነታችንና ምንነታችንን ሰርቆ በዲቃላዎቹ ጭፍሮቹ አማካኝነት ሙሉ በሙሉ ሊያጠፋን ወስኗል። በተለይ ያን አስቀያሚ ባለ አምስት ፈርጥ ኮከብ ባንዲራ በሚመለክት በዛሬው የቅዱስ ሚካኤል ዕለት የተሰማኝን በቀጣዩ እምለስበታለሁ። በጣም ቁልፍ የሆነ ጉዳይ ነው።

የግራኝ ኦሮሞዎች ከእስማኤላውያን እና ኤዶማውያን ጋር አብረው አማራውን ጨፈጨፉ፥ አማራው ከግራኝ ኦሮሞዎች ፣ እስማኤላውያኑ እና ኤዶማውያኑ ጋር አብሮ ተዋሕዶ ትግራዋይን እየጨፈጨፏቸው ነው። ቅዱስ ሚካኤል ዛሬ ከትግራዋያን ጋር ብቻ ነው። ኦሮማራዎች የአቤል ደም ይጮኻል፤ ወዮላችሁ!

ለአእናፊከ። ቅዱስ ሚካኤል ሆይ፤ የነፍስ ቁስለኞችን ለማዳን መድኃኒተ ፈውስን እፍ ለሚለው እስትንፋስህ ሰላም እላለሁ። ድል አድራጊው መልአክ ሆይ ፤ ያ የቀድሞ አመፀኛው አውሬ (ዲያብሎስ) የጥንት ተንኰሉን ሊተው አልቻለምና፤ የጦር መሣሪያህን ታጥቀህ መጥተህ ድምጥማጡን አጥፋው።

የሚገርም ነው፤ ይህን የ’መልክአ ሚካኤል’አንቀጽ በረንዳ ላይ ሆኜ በማነብበት ወቅት ዛሬም ሁለት እርግቦች በድጋሚ በረንዳው ላይ አረፉ። ለካሜራ ስንቀሳቀስ በርረው ሄዱ። ፀሎቴን ስጨረስ ከፊት ለፊት ቁራው ‘በብስጭት’ ሲጮኽ ሳቄ መጣ።

🎣 የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ጥበቃ ከሁላችን ጋር ይሁንልን!🎣

_____________________________________

Posted in Ethiopia, Faith, War & Crisis | Tagged: , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: