Addis Ethiopia Weblog

Ethiopia's World / የኢትዮጵያ ዓለም

  • June 2023
    M T W T F S S
     1234
    567891011
    12131415161718
    19202122232425
    2627282930  
  • Archives

  • Categories

  • Recent Posts

Posts Tagged ‘Koshe’

የእናቶች ዋይታና ጩኽት፥ “የወገን ያለህ!… መውደቂያ የለንም… ድረሱልን!„

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on March 13, 2017

የሉሲፈራውያኑ ግሎባሊስቶች መሣሪያ የሆኑት ዜና ማሰራጫዎቻችን ግን የቢዮንስና ሪሃና ወይም የሶሪያ ሕፃናት ሁኔታ ይበልጥ ያሳስባቸዋል።

በቆሼ በኩል ወደ አየር ጤና በታክሲ ሳልፍ፡ “ምን አየር ጤና፤ አየር በሽታ አይሉትም!„ ስል ፡ መንገደኞች ይስቁ ነበር። ግን የሚያስቅ ጉዳይ አልነበረም!

ባለፈው ጥር ፲፬ ዕለት፡ በ ዘነበወርቅ ሆስፒታል ዘመድ ከጠየቅኩ በኋላ ወደ አቡነ አረጋዊ እና ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አመራሁ። በቤተክርስቲያኗ ቆይታየም የተለያዩ አስገራሚ የሆኑ ነገሮችን ለመታዘብ በቅቼ ነበር። ካሜራዬን ይዤ በቤተክርስቲያኗ ግቢ ዘወርወር ስል፤ ከወደታች በኩል ቆሼ የሚባለው ቦታ ላይ ቆሻሻው ተከምሮና ተራራ ሠርቶ ይታይ ነበር። እኔም በኃሳቤ፡ “እንዴ ወደዚህች ቤተክርስቲያን ስመጣ ሁሌ የተነጠረ ቅቤ ይሸተኛል ስል የነበረው ለካስ ይህ ቆሻሻ ኖሯል” አልኩኝና፤ ወደ አንድ የቤተክርስቲያን አገልጋይ ወንድማችን ጠጋ አልኩ። በጣም አስተዋይ እና አዳማጭ ወንደም ነበሩ የገጠሙኝ። እስክ ሁለት ሰዓት ስለዚህ የቆሻሻ ሽታ እና የአካባቢው መበከል፤ ብሎም ዲያብሎስ እንደዚህ በመሳሰሉት መሰናክሎች ዓማካይነት ምዕመናኑን ከቤተክርስቲያን ለማራቅ እነደሚሞከር አወሳን። እሳቸውም “ምን ይደረግ፡ እኛማ ለምደነዋል!” ነበር ያሉኝ። እኔም፡ “በአፍሪቃ የመጀመሪያው ነው የተባለው ቆሻሻውን መልሶ ጥቅም ላይ ይውል ዘንድ የሚያገለግል ፋብሪካ መሠራቱ ባልከፋ፣ ግን ለሽታው መከላከያ፣ ምናልባት ረጃጅም ዛፎች ቢተከሉስ? ከፍተኛ አጥር ቢሰራስ?„ ስል፤ “ከቆሻሻው ጋር የሚኖሩ ብዙ ወገኖች አሉ…„ አሉኝ፡ እሳቸው።

አዎ! ከቆሻሻው በመልቀምና በመሸጥ የሚተዳደሩ፣ የህልውናቸው መሠረት በቆሼ ዙሪያ የጣሉ ስንት እናቶች፣ ስንቱ ህፃን ደፋ ቀና እያሉ ኑሯቸው ይገፉ የለ!

ያለ ምክኒያት አልነበረም ወደዚያ የሄድኩት፤ በጣም የሚገርም ነው፡ አቡነ አረጋዊ ስለ ቆሼ ሠፈር አሳዛኝ ሁኔታ አስቀድመው ጠቁመውኝ ይሆን?

እጅግ የሚያስደነግጥ፡ የሚያሳዝን ዜና ነው፤ በጣም ነው ያዘንኩት፤ ቸሩ እግዚአብሔር ነፍሳቸውን ንጹሕ ቦታ ላይ ያስቀምጥላቸው።

___

Posted in Ethiopia, Faith | Tagged: , , , , , , , | Leave a Comment »

 
%d bloggers like this: